(ዘ-ሐበሻ) “አለው ነገር” በሚለው ዘፈኑ ከመንግስት ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት የነበረው የባህል ድምፃዊው ፋሲል ደመወዝ አሜሪካ ገብቷል። ድምፃዊው ይሁኔ በላይ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚያሳትመው ባውዛ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ “አሜሪካን ሃገር 6 ጊዜ ለመምጣት ሞክሬ ባይሳካልኝም እንደ [ቅዱስ] ያሬድ በሰባተኛው ተሳካልኝ” ብሏል። ፋሲል ከባውዛ ጋር በቪድዮ ባደረገው ቃለ ምልልስ አስቂኝ ገጠመኞቹንም አካፍሏል – የዘ-ሐበሻ ተከታዮችም እንድትካፈሉት አቅርበነዋል።