አንድነት በአዳማ የጠራው ሰልፍ በሰላም ተጠናቀቀ

(ዘ-ሐበሻ) የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል በጎንደር፣ ደሴ፣ ባህር ዳር፣ ጂንካ፣ ወላይታ ፣ባሌ ሮቢ፣ ፍቼና አርባ ምንጭ ተካሂዶ የነበረው የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊ
ሰልፍ ዛሬ ደግሞ በአዳማ ከተማ ተደርጎ በሰላም መጠናቀቁን የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ከስፍራው ዘገበ። እንደ ጋዜጠኛው ዘገባ በዛሬው የአዳማ ሰላማዊ ሰልፍ መንግስት ፌደራል ፖሊሶችን በማሰማራት፣ የሰልፉን መንገድ በማስቀየርና በኢቲቪ በኩል ድራማ ለማሠራት ቢሞርክም እንዳልተሳካለትና ከምንም በላይ ሰልፉ በሰላም ተጠናቆ ሕዝቡ ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማበት ነው።

በአዳማ ከተማ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የአንድነት የምዕራብ ቀጠና ሃላፊ አቶ አስናቀ ሸንገማ በኦሮምኛ ቋንቋ፣ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስዮም መንገሻ እንዲሁም ዶክተር ሃይሉ አርአያ ንግግር ማድረጋቸውን የገለጸው ጋዜጠኛው ስልፈኛው በመፍክሩ መንግስትን የተለያዩ ጥያቄዎችን ጠየቋል፡
ከነዚህም መካከል፦
– ውሸት ሰልችቶናል
– የኢቴቪ የሃሰት ዶክመንተሪ ፊልም ከአሸባሪነት አይለይም
– ድህነት በፕሮፓጋንዳ ብዛት አይጠፋም
– ሰብዓዊ ልማት ለሁሉም
– ስራ ማግኘት የዜግነት መብት ነው
– አምባገነኖች ባሉበት የአንዷለም ቤት እስር ቤት ነው
– ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ እንጂ አሸባሪ አይደለችም
– ድሌ ዛሬ ነው! ድሌ ዛሬ ነው ድሌ ድሌ ድሌ
የሚሉ መፍክሮችን እነዚሁ ከፍርሃት የተላቀቁ ኢትዮጵያውያን አሰምተዋል።

አንድነትየሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል ላለፉት 3 ወራት በመላው ኢትዮጵያ በመዘዋወር ሕዝቡን በሰላማዊ ሰልፍ በማደራጀትና ፊርማ በማሰባሰብ ሲያደርገው የቆየውን ሰላማዊ ትግል በመቀጠል የፊታችን እሁድ ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በመስቀል አደባባይ ት ዕይንተ ሕዝብ መጥራቱን ዘ-ሐበሻ ከቀናት በፊት መዘገቧ ይታወሳል።

 

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሕወሓት አፈና ቢፈተንም ዓረና መድረክ በማይጨው ሕዝባዊ ስብሰባ አደረገ

4 Comments

  1. Peace fully ended ?why you guys do not tell us how many people do come out.i do not think they are that muchas esat radio is trying to exaggerate because there is no grass root work done by this party’s like andent and semayawe party.they are fake oppositions which weyane is controlling behind.

  2. well done UDJ and tanks EPRDF….we have democrat govt , u can talk u can demonstrat , u can wright…(unless u r terrorest .or extremist)_,
    no keye shebir no neche shibr….toxic diaspora peace full demonstration is allowed in ETHIOPIA. even single person.has a wright to oppose the govt.
    long live EPRDF.

  3. More than 15,000 peoples was participated in NAZERATE. UDJ is not fake opposition Nesanetu. you are fake person with fake personality. you are YEWEYANE ASHEKERE b/c you are trying to destroy oppositions.

Comments are closed.

Share