የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ “የኦሮሞና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ መፅሃፍ፡-

  • በቨርጂኒያ- መዓዛ ሬስቶራንት Dec 03/2016
  • በዋሽንግተን ዲሲ-ላሊበላ ሪስቶራንት Dec 04/2016
  • በሜሪላንድ- አዲስ አበባ ሬስቶራንት Dec 05/2016

በርካታ ኢትዮጵያዊያን ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት ተመረቀ።

  • መጽሐፉን ሰላምንና ፍቅርን፣ የሚሰብክ የህዝቦች አብሮነትና ብሎም አንድነት እንዲመጣ  የሚረዳን ነው።
  • መጽሃፉ ባለፉት 25 ዓመታት አማራና ኦሮሞን ለማራራቅ ሲጥሩ የነበሩ ፀረ አንድነት ኃይሎችን አንገት ያስደፋ ነው።
  • ህዝብ ለህዝብም አስታራቂ መጸሀፍ ነው
ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ

ልብ ወለድ የሆኑ፣ ያልነበሩ የሌሉ የፈጠራና የሀሰት ታሪኮችን የሚያከሽፍ የሚያፈርስ፣የሚደመስስ በተጨባጭ ማረጋገጫና የማስረጃ ምንጭ የተደገፈና የተመሰረተ ብቁ እጅግ ታላቅ መጽሃፍ ነው በማለት በርካቶች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ፕ/ር ፍቅሬ የኦሮሞና የአማራን የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ እውነተኛ ትክክለኛ የዘር ምንጭ ምን እንደሆነ ከ5ሺ አመታት በላይ ወደ ኋላ ተጉዘው ማስረጃ አስደግፈው ምንጭ ጠቅሰው እሰከ አሁን ድረስ የምናውቀውን የኢትዮጵያ ታሪክ ከስር መሰረቱ የሚሽር፣ በአዲስ ታሪክ የሚተካ አዲስ የኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በዝርዝርና በጠራ አቀራረብ የሚገልጽ ድንቅ መጽሃፍ አቅርበዋል።

ኑሮአቸው በአሜሪካ የሆነው ተዋቂ የስነፅሁፍ ምሁር ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በሊንከን ዩኒቨርስቲ በሂዩማኒቲስ የትምህርት ዘርፍ የሚያስተምሩና ከዚህ ቀደም “ Heaven to Eden”  እና “The Hidden and untold history of the Jewish people and Ethiopians”  የሚሉ መጽሃፍ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሳተሙ ሲሆን ሁለቱም በኢንተርኔት “አማዞን” በተባለ የመጸሃፍ ሽያጭ ድረገጽ  ላይ ከተፈላጊ መጸሃፍት ተርታ ተሰልፈዋል። በሙያቸው ፀሃፊ ተውኔትና የሥነ ጽሁፍ ምሁር ሲሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ይታወቃሉ።

አንጋፋው ምሁር ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም በቅርቡ ለንባብ ባበቁት “አዳፍኔ” በተሰኘ መጽሃፋቸው ላይ “የኦሮሞን ታሪክ ሙሉ አድርጎ ሊጽፍ የሚችለው ፕ/ሮ ፍቅሬ ቶሎሳ ብቻ ነው” ሲሉ ለብቃታቸው ምስክርነትና ዕውቅና መስጠታቸው ይታወቃል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሐረር ከተማ ባሉ ነጋዴዎች ላይ እየተደረገ ያለው ጫና ተጠናክሮ ቀጥሏል

ፕ/ሮ ፍቅሬ ቶሎሳ በርካታ ቲያትሮችን ለመድረክ ያበቁ ሲሆን ከነዚህም መካከል “ጓደኛሞቹ” “ፍቅር በአሜሪካ” “መቃብር ቆፋሪው” ሌሎቹም ይገኙባቸዋል። በቅርብም “ላሟ” ይተሰኘ ባለሁለት ገቢር ቲያትር ጽፈው ማጠናቀቃቸውም ታውቋል።

ካሳተሟቸው የአማርኛ መጽሃፍት ውስጥ “ወለላ” የተሰኘ የልብ ወለድ መጽሃፍ እና “ይቺ ናት ሀገሬ” የተሰኘ የግጥም መጽሃፋቸው ይገኙበታል። በ2000ሺ ዓ.ም(እ.ኤ.አ 2008) “ multicolored flowers”  (የተቅለመለሙ አበቦች) የተሰኘው ፊልማቸው ለህዝብ እይታ ማብቃታቸው ይታወሳል።

በዲሲና በቨርጅኒያ የሚገኘው ናፍቆት ኢትዮጵያ የተባለው  መጽሄትና አሳታሚ ድርጅት መጸሃፉን አሳትሞ፣ መጽሃፉ በአሁኑ ጊዜ በሽሚያና በወረፋ እየተሸጠ ያለ ከመሆኑም በላይ በዚሁ ሳምንት በድጋሜ እንደገና ለህትመት እየተዘጋጀ መሆኑና በተጓዳኝ በእንግሊዘኛ እንደሚታተም የናፍቆት መጽሄት ዋና አዘጋጅ አቶ ግርማ ዘገዬ ገልጾልናል።

ናፍቆት ኢትዮጵያ መጽሄት አሳታሚ ድርጅት የታሪክና የሌሎችንም ማህበራዊና ፖለቲካዊ መጽሃፍት ለምሳሌ ያህል የታላቁን የሙዚቃ ሰው የአቶ ተስፋዬ ለማን “የኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ” የተባለ መጽሃፍ እና “ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር” የሚለውን የጀኔራል ውበቱ ፀጋዬ መጽሃፍ ከማሳተም በተጨማሪ የአርትየት ስራ እና የግራፊክስ ስራዎችን፣ የታይፒንግ ስራዎችን የሚሰራ ድርጅት ከመሆኑም ባሻገር  የማርክ የታክስ አገልግሎት ይህንን በመደገፍ ግንባር ቀደም ተባባሪ በመሆን ሙሉ ድጋፍ ያደርጋል።

መጽሃፉ ባለፉት ወራቶች በኢትዮጵያ ውስጥ “ነባዳን የሚዲያ ማማከር ኃ/የተ/የግል ማህበር” በተባለ አሳታሚ ድርጅት ታትሞ በአገሪቱ ውስጥ በአመቱ ከታተሙ መጸሃፍት በከፍተኛ ሁኔታ በመሸጥ ላይ የነበረ ከመሆኑ በላይ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያም ሆነ በሌሎች ርዕስ ጉዳዮች ላይ ከታተሙት መጻህፍት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብዛት ክብር ወሰን ማስመዝገቡ ታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ያላዩት አገር ሲናፍቅ፥ የአዲስ መንግሥት ምኞት (ጌታቸው ኃይሌ)

ፕ/ር ፍቅሬ ከበርካታ ህዝብ በቀረበላቸው ጥያቄ መሰረት መጽሃፉ በቅርቡ በአፋን ኦሮሞ(ኦሮምኛ) በላቲን ፊደልና እንደዚሁም በአፋን  ኦሮሞ በኢትዮጵክ ኦሮሞኝ ፊደል( በዘልማድ ግዕዝ ተብሎ በሚጠራው) ተተርጉሞ ለማሳተም ጥረት እየተደረገ ተጀምሮ እንዳለና በቅርቡ እውን እንደሚሆን ገልጸዋል።

በቀጣይ ሂደትና ጊዜያት በተቻለ መጠን ኢትዮጵያዊያን በሚገኙበት ሁሉም የአሜሪካን ስቴቶችና ከተሞች እንዲሁም በአውሮፓና አፍሪካ ባጠቃላይ በመላው አለም መጸሃፉን ለማደረስ ጥረታቸውን እያካሄዱ ነው። በመላው አሜሪካ የምገኙ ኮሚኒቲዎችና ስብሰቦች ጥሪ በቅደም ተከተል ወረፋ ተራ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።

ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በሌሎች ስራዎቻቸውና በተለይም በዚህ መጽሃፍ አበርክቶሻቸው በኢትዮጵያና በውጭም ባሉት ጭምር “ሐቀኛ የኦሮሞ ልጅ የኢትዮጵያ ልጅ” “ የመከራ ቀን ደራሽ” “ የመከራ ቀን ልጅ” “ የታሪክ ና የፍቅር አባት” “የኢትዮጵያ መድን” “የህዝብ ዕርቅ አባት” አስታራቂ” “የኢትዮጵያ ቤዛ” “ነብይ” ተብለዋል። (ተሰኝተዋል”

“ነብይ በአገሩ አይከበርም” የሚለው ተረት ፈርሶ ለአገር ቁም ነገር ያበረከቱ ግለሰቦችንና ስራዎቻቸውን ማክበር ማመስገን ማወደስ መተባበር ማገዝ መረዳት በዚህ አዲስ መጻሃፍ መነሻ አዲስ ባህላችንና ልማዳችን እንዲሆን በአንድንቆት ተብሏል፣ ተዘክሯል፣ ተነግሯል።

አብርሃም ቀጄላ(ከዋሽንግተን ዲሲ)

 

 

 

 

 

 

6 Comments

  1. ebs ላይ ፕሮፌሰሩን አንድ አለቅላቂ ልቡም እንደዐየኑ በጥቅም የታወረ ሀሰት ነው የተፃፈው እያለ ራሱንም እንደታሪሪክ ተመራማሪ ለማድረግ ሲሞክር አይቼ ታዘብኩት ውሻ በበላበት ይጮሀል፡፡

  2. Fake narrations !
    There is no proof for the authenticity of the refereed documents. He is a professor who worked in Germany and now working in US. He knows all the procedures for publishing research works. He should have genuinely followed that. He wrote the book and is spreading it thinking he can buy the acceptance of ordinary readers. Why he doesnt reply to Prof. Getachew and other scholars

    Its unfortunate, We Ethiopians blew with the wind. We have to ask and invistage for the truth.

  3. Kush, Sem ena nilotik mehonachin qere malet new? Keselemon zer mehonu qerre beqe minilik I ena II haregu ferese. Somalemma minu qerre tetale enji.Enasuun degmo belela melk maqreb yichal yihon? Mehuru biasibubet lela amarach aytefam.Ye ethiopia ena yemoqdisho somaliwoch yeteleyu zer new yalechew yih ye adababay mistir new. Yene mikir beteleyeyu gize yeteleyaye tarik le ethiopiachin tetsfewal, negeroch endyimtatu engidhih keylubet feligen ethiopiawi ermija mewsed yasfligal.

    Prof. FIKRE TOLESA bezih lela AMARAC ye Ethiopia tarik bemefelasefachew kehulum ye zare taqaraniwoch “erasachew yetarik sew honew” endiweralachew wayim endiwerabachew honewal. Mikiniyatum, bezih sile ethiopia tarik fitit qulich wust belenibet zemen yih “AMARACH TARIK” mesematu rasu Tarik newuna!!

  4. you are right blind in his heart is more blind he afraid of not to lose his EBS TV STATION FOR THAT HE DRINKING AND EATING THE BLOOD AND FLESH OF ALL ETHIOPIAN SPECIALLY THE OROMO&AMHARA YOUTH

Comments are closed.

Share