December 23, 2016
3 mins read

ጎንደር ከተማ ላይ ውጥረትና ፍተሻ አለ – ራሳቸውን ያደራጁ ታጋዮች በእስቴ ወረዳዎች ባደረጉት ውጊያ ድል ተቀዳጁ

አክቲቭስት ሙሉነህ ዮሐንስ እንደዘገበው:-

መተማ አካባቢ ከፍተኛ ተኩስ ነበር። ይህ ከባድ ጦርነት የነበረበትን ግጥሚያ ዝርዝር ሁኔታ እየተከታተልን ነው።

ጭንቅ ውስጥ የገባው ወያኔ በዛሬው እለት በየ200 ሜትር እርቀት ላይ ፍተሻ እያደረገ ነው። ከተማዋ በወያኔ ወታደር ተሞልታለች።

የጎንደርን ሕዝብ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ በአዲስ መልኩ የገንዘብ መቀጮ እየዳረጉት ነው። በዛሬው ቀን ወደ 150 የሚሆኑ ባጃጆችና ታክሲወች በየመንገዱ እያስቆሙ ምክንያት በሌለው ጉዳይ ከፍተኛ የቅጣት ገንዘብ እንዲከፍሉ እየተደረጉ ነው።

በተመሳሳይ መልኩ ሰብሰብ ብለው የተገኙ ወጣቶችን ገንዘብ ክፈሉ ካለዛ እናስራቹሃለን በማለት በእስርና በገንዘብ ክፍያ ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል። በሁሉም ወረዳወች ላይ ከፍተኛ ውጥረት ላይ የወደቀው ወያኔ የከተማውን ህዝብ እያሰቃየ ነው።

ኮሎኔል ደመቀን አንገረብ እስር ቤት ለብቻው ለይተው አስቀምጠውታል የሚል መረጃ አለ።

አርብ ታህሳስ 14 ቀን 2009 በራሳቸው ምንገድ ተደራጅተው ወያኔን የገጠሙ በተለይ በእስቴ ወረዳወች እየተንቀሳቀሱ እየተዋጉ የሚገኙ ወገኖች ድል ተቀናጅተዋል።በተለይ ደግሞ ስሙን መጥቀስ የማያስፈልግ ግንባር ላይ ከፍተኛ ጦርነት ነበር። አሁንም ውጊያው መቀጠሉና ህዝቡም እየተሰባሰበ መሆኑ ተነግሯል።

ወልደ ጊወርጊስ የተባለ የፀረሽምቅ መሪ እና ሳሙኤል የተባለ ተራ ወታደር በቅፅል ስሙ ሸሪፎ የተባለ ወታደር ቢራራ የተባለ ተራ ፓሊስ በዛሬው እለት ሲገደሉ ከወገን በኩል ለቤተሰቡ ደህንነት ሲባል ስሙን የማንጠቅሰው አንድ ጀግና ተሰውቷል።ከሰሞኑ በጠቅላላው ስማቸውን መግለፅ በማያስፈልገው የተለያዩ የደቡብ ጎንደር ግንባሮች ከ20 በላይ የወያኔ ወታደሮች ተገለዋል።
አቸ ምናየ የተባለ የእስቴ ወረዳ የደህንነት እና ሚኒሻ ዘርፍ ሀላፊ ማስጠንቀቂያ ተልኮለታል።

Go toTop