በጐንደር ክፍለ ሀገር ከወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የአማራ ማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!!

በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ላይ ወራሪውና ደም ጠጭው የህወሃት ፀረ-ሕዝብ ቡድን ጀግኖችን እያሳደዱ መግደል ማሰደድና ሀብታቸውን መዝረፍ የጀመረው ከዛሬ 40 ዓመት በፊት ቢሆንም የሚፈፀምባቸውን ግፍ በልባቸው አምቀው በመያዝ ጊዜና የሕግ የበላይነት ሲሰፍን በሕግ እንፋረዳለን ብለው ዝምታን የመረጡ ቢሆንም ተስፋፊው የሕወሃት ቡድን ማንኛውንም ጉዳይ ለማስፈፀምም ሆነ ለመማር በትግርኛ ነው እናንተም ትግሬዎች ናችሁ ትግሬ አይደለንም የምትሉ አባይን ተሻግራችሁ ትሄዳላችሁ እንጅ አማራዎች ነን እያላችሁ በትግራይ ክልል መኖር አትችሉም በማለት አካባቢውን ያቀኑትን ተወላጆች አሳዶ ከአካባቢው እንዲጠፉ ማድረጉ ይታወቃል።በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ ሀብት ንብረታቸውን ተዘርፈው ተወልደው ያደጉበትን አጥቢያቸውን ለቀው ሄደው ተሰደው ከሚኖሩበት የጐረቤት አካባቢ ሰላዮችን በመላክና አፋኞችን አሠማርቶ የግድያ ወንጀል ላይ ተሰማርቷል።በዚህ ባሳለፍናቸው ሁለት ቀናት ውስጥም ሮጠው ያልጠገቡ የጐልማሳነት ዘመናቸውን ተደብቀው ለማሳለፍ ወደ አርማጭሆ ሄደው ከሚኖሩበት ገዳይ ኃይል በማሠማራት አካባቢው በተማረ የሰው ኃይልም እንዲደኸይ ለማድረግ ባለው እቅድ መሠረት ሁለት ቀምበጥ የወልቃይ ወጣቶችን ገድሏል።

እነሱም 1/ ዘውዱ ገብረእግዚአብሔር ዓለማየሁ እና 2/ ሙላው ከበደ ውብነህ ሲሆኑ በህወሃት አረመኔ የአጋዚ ጦር ግፍ ተፈጽሞባቸዋል።የተገደሉት ወንጀል ፈጽመው ወይም ጥፋተኛ የሚያደርጋቸው ክስ ቀርቦባቸው ሳይሆን በትግርኛ አንማርም፤ጉዳያችን ለማስፈፀም ማመልከቻ በትግርኛ አንጽፍም፤አማራዎች ነን፤ድንበራችን ተከዜ ነው፤እናንተ መጣችሁብን እንጅ እኛ አልመጣንባችሁም በማለታቸው ብቻ ነው ይህን የመሰለ ዘግናኝ ግፍ የተፈፀመባቸው።እነዚህ ሁለት ወጣቶች ከልጅነታቸው ጀምሮ በሳል አርቀው የሚያስተውሉና በትምህርታቸው ጎበዞች፤ሳቂተኛዎች ቁምነገረኛና ታማኞች ነበሩ።

**ዘውዱ ገብረእግዚአብሔር ዓለማየሁ፦ወልቃይት ቃብትያ ሻሃሸም ሚካኤል በሚባል ተወልዶ ያደገ እድሜው በ30ዎቹ ገደማ ሲሆን እስከ ስድስተኛ ክፍል በዚሁ ቦታ የተማረ ገና የአራተኛ ክፍል ተማሪ እያለ እንግሊዘኛን አቀላጥፎ የሚነገረው ዘውዱ እኔ አማራ ነኝ በትግርኛ አልማርም በማለት እናት አባቱን ጥሎ ወደ ጎንደር በመሄድ ፋሲለደስ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ከ7ተኛ እስከ 12ተኛ ከተከታተለ በኋላ በተከታታይ በነበረበት ህመም ምክንያት ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ግብርና ገባ።ተወልዶ ባደገበት መሬት የሚያርሰው አጥቶ በትግሬ ተወሮ እስከ ሱዳን ድረስ ሄዶ መሬት በመከራየት የሰሊጥና ጥጥ ማሽላ ያመርት ነበር።ማንነቴ ይመለስልኝ እኔ ትግሬ አይደለሁም አማራ ነኝ በማለቱ ነብሰ ገዳዩና ወራሪው ወያኔ ህወሃት ሊያስረው ሲሞክር ከእስራት አምልጦ ወደ ወገኖቹ አርማጭሆ ውስጥ ገብቶ ህወሃትን ሲፋለም የነበረ ጀግና ነበር።**እኛ ሞተን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ስቃይና መከራ እስራት ሞት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማብቃት አለበት በማለት እንደ ክርስቶስ ለወገኖቹ ውድ የሕይወት ዋጋ ከፍሎ አለፈ ቤዛ ሆነ**።

**ኢኮኖሚስቱ አደራ ተቀባዩ ፤ታማኙ የወገን አለኝታው ከኔ በፊት ለወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ያለው የትግል አጋሩ ሙላው ከበደ ውብነህ፦በዚሁ በቃብትያ የተወለደ ሲሆን እድሜው ገና በ30ዎቹ አካባቢ ሲሆን በ1998 ዓ/ም በባህርዳር ዩኒቨችሲቲ ፔዳጎጅ ካምፓስ በኢኮኖሚክስ የመጀመርያ ዲግሪውን ያገኘና ተወልዶ ባደገበት አካባቢ በሁመራ ከተማ ሲሰራ የነበረ አማራ ነኝ በማለቱ በወያኔ ከሥራ የተሰናበተ ሲሆን የአባቱን ፈለግ በመከተል ወደ እርሻና ንግድ ገባ።በመጨረሻ ግን ለምን አማራ ነን አላችሁ ተብለው ጓዶቹ እነ ኮ/ሎኔል ደመቀ ዘውዱ፤አታላይ ዛፌ፤ጌታቸው አደመ፤መብራቱ ጌታሁን፤አለነ ሻማ፤ነጋ ባንቲሁን፤አዲሱ ሰረበ፤ንግሥት ይርጋ፤ጎይቶም አማረ፤አሊጋዝ አየለ፤ባየው ካሴ፤ሞላ ኃይሉ፤ሰለሞን ግዛቴ;ሊላይ ብርሃኔ፤ሰጠኝ አረሮ፤መሀመድ ያሲን፤አዛውንቱ የ70 አመት ሽማግሌ መኮንን ደስታ፤ሰፊሁን አበበ፤ዳኘው አቸነፈ፤ተሻገር ወልደሚካኤል፤ዮሐንስ ጠጋ፤አባተ ነጋ፤ዘውዱ ነጋ፤ገብረመስቀል ማማይ፤ወረታው አዛናው እና እንዲሁም እጅግ በርካታ የጐንደርና አካባቢው፤የባህርዳርና ባህርዳር አካባቢ ወጣቶች ጐልማሳዎች ጭምር በወያኔ ማጐርያ በሲኦል እስር ቤት የሚገኙ ብዙ አማራዎች የመገኘታቸው ሁኔታ ሕሊናው ሊቀበለው ባለመቻሉ ቤት ንብረቱን ጥሎ በአጠቃላይ ከወያኔ የሚደርስበትን ማንኛውንም ጥቃት ለመከላከልና አማራነቱን ለማስከበር ዱር ቤቴ ብሎ የወጣ ጀግና ከዘውዱ ጋር በመሆን ከወያኔ(ህወሃት)ወታደሮች ጋር ተፋልመው ታሪክ ሠርተው አለፉ።

ተወልደው ባደጉባት ቧርቀው ባልጠገቡባት ወልቃይት ልዩ ቦታ “”ቃብታያ ወልቃይት በክብር ፤በነፃነት የማልኖርብሽ መንደር ከሆንሽ ሞቼ በክብር አጽሜ የሚያርፍብሽ የክብር መቃብሬ ትሆኛለሽ””በማለት በ10/04/2009 ዓ/ም ከቀኑ7.00 ገደማ የቀብር ስነስራታቸው ተፈጽሟል።እነዚህ ሁለት ወጣት ጀግኖች የጀመሩትና የሕይወት ዋጋ የከፈሉበት ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል።የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አማራ ማንነት ጥያቄ በቅርቡ ይመለሳል።የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ አማራ ነው፤የአማራ ማነነት በቅርቡ ይመለሳል፤ድንበራችን ተከዜ ነው!!

ታጋይ(ጀግና) ይሞታል ትግሉ ግን አይሞትም!!

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይበቃል ከአንግድህ .......የበላይ  ለመሆን
Share