August 14, 2013
7 mins read

የሥላሴዎች እርግማን (ሁለት)፤ አደህይቶ ማድከም (ከፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም)

ከታትፎና ለያይቶ በማዳከም ቤቱን አፍርሶና መሬቱን ነጥቆ፣ ከሥራው አፈናቅሎና ሥራ አሳጥቶ ያለርኅራኄ ማደህየት በፕሮግራም የተያዘና በውጭ ኃይሎች የሚደገፍ ሥራ ነው፡፡ ለጥቂት ዓመታት በአሜሪካ ቆይቶ የመጣ አንድ ጓደኛዬ ራሱን በሁለት እጆቹ ይዞ ‹‹አዲስ አበባ በመሬት መናወጥ ፈራርሳ በመጠገን ላይ ያለች ከተማ ትመስል የለም እንዴ!›› አለኝ፤የመሬት አይደለም አንጂ የመናወጥ ነገር በእርግጥ አለ፤ የመሬት መናወጥ ባይደርስባትም የአእምሮ መናወጥ የመታት ከተማ ነች አልሁት፤ ቅንጅት ነፍሱን ይማረውና በፖሊቲካው መድረክ ብልጭ ብሎ ድርግም ካለበት ዓመት ጀምሮ በአዲስ አበባ ታይቶ የማይታወቅ የማፍረስና የመገንባት ሥራ በአንድ ላይ ጎን ለጎን ሲካሄድ እያየን ነው፤ ከጥንስሱ ጀምሮ የማሰብ ችግር ውላጅ መሆኑ በግልጽ ይታያል፤ ብዙ አገሮች አዳዲስ ከተማዎችን ሠርተዋል፤ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ሕንድ፣ ናይጂርያ፣ ብራዚል አሉበት፤ የወያኔ/ኢሕአዴግ ግን የተለየ ነው፤ አዲስ ከተማ እየሠራ ሳይሆን የጥንቱን እያፈረሰ ነው፤ ደርግ ሲጀምር ከጥንቱ ሥርዓት ጋር በመጣላት ነበር፤ ወያኔ ሲጀምር ግን ከማን ወይም ከምን ጋር ተጣልቶ አንደሆነ በግልጽ ባይታይም በጥላቻ መወራጨቱ ይታይ ነበር፤ ጎልቶ የወጣውም የችግረኛ ጉጉትና ምኞት፣ ሽሚያና ዝርፊያ የወያኔ ዓላማ ከራሱ የማያልፍ መሆኑን ያመለክት ነበር፤ በውጤቱም የሆነለት ያባትህ ቤት ሲዘረፍ እንደሚባለው ሆኖ ከውጭ ባንክ ተርፎ፣ ከአገር ውስጥ ባንክ ተርፎ፣ በጆንያና በጉድጓድ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያስቀመጠ ተደላድሎ እየሳቀ ይዝናናል፤ ያልሆነለትም በየሜዳው ያለቅሳል፤ ከተማው በሙሉ በማፍረስና በመገንባት ይታመሳል፤ ይተራመሳል፤ ዋናው ዓላማ ሕዝቡን ማዳከም ነው፤አዳክሞም ማደህየት ነው፡፡–

. ይህ ሁሉ መንገድ የደሀውን ቤት ሁሉ እየመነጠረ ሲረዝምና ሲሰፋ፣

. የደሀ ቤቶች ተመንጥረው መንገዱ ከረዘመና ከሰፋ በኋላ ባለሥልጣኖች በድንገት ስለባቡር የሚያስታውሳቸው አማካሪ ሲያገኙ፤

. የድሆች ቤቶች እየተመነጠሩ የሰፋውን መንገድ እያፈረሱ ሲያጠቡት!

.ቤቶች ሲፈርሱና መንገዶች ሲረዝሙ፣ መንገዶች ሲሰፉና ሲጠቡ፣

. መንገዱ ለባቡሮች ሲቆፈርና ሲተራመስ፣

. መንገዱ በደሀዎቹ ቤቶች ፍርስራሽ ተጨናንቆ በደሀ እንባ ሲጨቀይ፣

. ለደሀዎች መኖሪያ ኮንዶሚንየም እየተባለ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሲገባና ሲወጣ፣

. የመንገዱና የባቡሩ ወጪ ከኮንዶሚኒየሙ ሥራ ጋር ተዳብሎ በቢልዮን የሚቆጠር ብር እየተተራመሰ ከመንግሥት ኪስ ሲፈስ፣

.‹‹የመንግሥት ሌቦች›› የሚፈስሰውን እየለቀሙና እየተወዳደሩ ‹‹በምድር ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራ›>ብለው ግንበ-ሰናኦርን ሲክቡ፣

.የሙስና ተከላካዮች ፈራ-ተባ እያሉ በእርሳስ ሲመዘግቡና ግንዱንና ስሩን ሳይነኩ በኢዮባዊ ትእግስትና በሰሎሞናዊ ፍርድ ቅጠሎቹን እየከረከሙ ሲያረግፉ፣

.ሙስና ስሩ እየጠነከረ ግንዱም እንደግንበ-ሰናኦር ወደሰማይ እያደገ ሲሄድና ቅጠሉም ወዲያው ሲለመልም፤

.ደሀነትም በጌትነት እየተጋጠ በሞትና በሕይወት መሀከል ሆኖ እያቃሰተ ሲያድግ፣

.ለደሀነት መቀነሻ የሚባለው ሁሉ ደሀነትን ለማባባስ ሲውል፣

የደላው ይደሰታል፤ የተጎዳው እንባውን በየመንገዱና በየቤተክርስቲያኑ፣ በየቤተ መስጊዱ ይረጫል፤ የሚታዘብ ያንጎራጉራል፤

በቁንጣን፣ በስካር ጥቂቶች ሲንሩ፣

ብዙዎቹ ደግሞ በረሀብ መንምነው በቁንጫ ሲያርሩ፣

የደሀ እንባ ሲጎርፍ መሬቱ ሲሸበር፣

ዝብርቅርቁ ወጣ፤ ሕይወት ትርጉም አጣ፤

መንገዱ ጠበበ፤ ትርምስምሱ በዛ፤

እሪታው፣ ኡኡታው ቀለጠ እንደዋዛ፤

መሬቱም፣ ዓየሩም በክፋት ጠነዛ፤

ጥላቻና ቂሙ በሰፊው ተነዛ፤

እምቢልታው ሲጣራ ነጋሪት ሲያገሳ፣

የአለው ሁሉ ሞቶ የሞተው ሲነሣ፣

ምጽዓት መድረሱ ነው፤ ሊስተካከል ነው ፍርድ፤

በግና ፍየሉ ሊለዩ በገሀድ!

አፍርሶ መገንባት ዘለቄታ ያለው እድገትና መሻሻል ያስከትላል ብለው የሚያምኑ ከኋላቸውም ከፊታቸውም የሚያዩት ሁሉ ያከሸፋቸውና የከሸፉ ናቸው፤ ወደኋላ እንዳያዩ ታሪክ የላቸውም፤ ወደፊት እንዳያዩ ራእይ የላቸውም፤ የሥላሴዎች እርግማን!

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop