Sport: ቲኪ ገላና የኦሊምፒክ ድሏን በሩሲያ ለመድገም ተቃርባለች

August 9, 2013

ከቦጋለ አበበ

በሁለት ዓመት አንዴ የሚካሄደው የዓለማችን ትልቁ የአትሌቲክስ የውድድር መድረክ (የአትሌቲክስ የዓለም ዋንጫ ) በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ ሊጀመር የሃያ አራት ሰዓታት እድሜ ይቀሩታል፡፡ ይህን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርካታ የስፖርት አፍቃሪዎች በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ፡፡
ውድድሩ ነገ ሲጀመር ማለዳ ላይ በጉጉት የሚጠበቀው የሴቶች ማራቶን ውድድር ይካሄዳል፡፡ በዚህ ውድድር ውጤት ያስመዘግባሉ ተብለው ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል የኦሊምፒክና የኢትዮጵያ የርቀቱ ባለ ክብረወሰን የሆነችው ቲኪ ገላና ግንባር ቀደሟ ነች፡፡
ባለፈው ለንደን ኦሊምፒክ ከወደቀችበት ተነስታ አስቸጋሪውን የማራቶን ውድድር በድንቅ የአጨራረስ ብቃት ማሸነፍ የቻለችው ቲኪ በዘንድሮው የዓለም ሻምፒዮናም የአሸናፊነት ግምት ያገኘች አትሌት መሆን ችላለች፡፡

ቲኪ ባለፈው ዓመት በርቀቱ 2፡18፡50 የሆነ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ የስፖርቱን አፍቃሪዎች ያስደነቀች አትሌት መሆኗ በነገው የዓለም ሻምፒዮና ትኩረት የሚሰጣት አትሌት እንድትሆን አስችሏታል፡፡ ቲኪ በዘንድሮው ዓመትም በርቀቱ 2፡36፡55 የሆነ ሰዓት ያስመዘገበች ጠንካራ አትሌት መሆኗ በውድድሩ የአሸናፊነት ግምት እንዲሰጣት አድርጓል፡፡
ቲኪ ገና በርቀቱ ብዙ ያልተጓዘች ወጣት አትሌት እንደመሆኗ መጠን በነገው የዓለም ሻምፒዮና ውድድሯ ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት ብዙ ታሪኮችን ልትፅፍ እንደምትችል የስፖርቱ ተንታኞች እየተናገሩ ይገኛል፡፡ የነገው ውድድር ጠንካራ ፉክክር የሚደረግበት እንደሚሆን ቢገመትም ቲኪ በአይበገሬነቷ በድል ትወጣዋለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በውድድሩ የቲኪ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ኬንያውያንና የሌሎች አገሮች አትሌቶች አይደሉም፡፡ በዚህ ውድድር ዓመት በተለያዩ ታዋቂና ጠንካራ የማራቶን ውድድሮችን አሸንፈው ከቲኪ ጎን ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችም ነገ በውድድሩ ይጠበቃሉ፡፡
አበሩ ከበደ በነገው ውድድር ከቲኪ ያላነሰ የአሸናፊነት ግምት የሚሰጣት አትሌት ነች፡፡ አበሩ ባለፈው ዓመት በርቀቱ ባስመዘገበችው 2፡20፡30 ሰዓት በዓለም ሻምፒዮና አገሯን ለመወከል ሁለተኛዋ ተመራጭ አትሌት ለመሆን በቅታለች፡፡
አበሩ በዓለም አቀፍ መድረኮች የቲኪን ያህል የገዘፈ ስም ባይኖራትም በዛሬው ውድድር የአገሯንና የራሷን ስም የምታስጠራበት እድል አግኝታለች፡፡ አበሩ ይህን እድል ተጠቅማ ባለታሪክ ከሆኑ የአገሮቿ አትሌቶች ተርታ ለመሰለፍ ከቲኪ ጋር ተፋጥጣለች፡፡
በሌላ በኩል በዚህ የውድድር ዓመት በማራቶን ድንቅ ብቃት በማሳየት የተለያዩ ታዋቂ ውድድሮችን ማሸነፍ የቻለችው ፈይሴ ታደሰ የኦሊምፒክ ባለ ድሏን ቲኪን ልትፈትን የምትችል አትሌት ነች፡፡ ፈይሴ በርቀቱ ባለፈው ዓመት 2፡23፡07 የሆነ ሰዓት በማስመዝገብ በርቀቱ አሉ ከሚባሉ አትሌቶች ተርታ መሰለፍ ችላለች፡፡
ፈይሴ በዘንድሮው ዓመት በርቀቱ ቀድሞ የነበራትን ሰዓት ከሁለት ደቂቃ በላይ ያሻሻለች አትሌት መሆኗም በነገው ውድድር እንድትጠበቅ አድርጓታል፡፡ ፈይሴ ሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ የመግባት አቅም እንዳላት በዓመት ውስጥ ያሳየችው ድንቅ አቋም ምስክር ነው፡፡
መሰረት ኃይሉ ኢትዮጵያን ወክላ ከአገሮቿና ከሌሎች አትሌቶች ጋር ጠንካራ ፉክክር ታደርጋለች ተብላ ግምት የተሰጣት አትሌት ነች፡፡ መሠረት በውድድሩ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ለቡድን ጓደኞቿ የምታደርገው አስተዋፅኦ ቀላል እንደማይሆን ይጠበቃል፡፡
በለንደን ኦሊምፒክ የአስር ሺ ሜትር ውጤታማ የቡድን ሥራ በመሥራት ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ እንድታሸንፍ ያደረገችው መሰለች መልካሙ በነገው ውድድርም ከጠንካራ ተፎካካሪነቷ ባሻገር የተለመደውን ውጤታማ የቡድን ሥራ ትሰራለች ተብላ ትጠበቃለች፡፡
መሰለች ከቡድን ሥራው ባሻገር ውጤት የማስመዝገብ አቅም ያላት አትሌትም ነች፡፡ ለዚህም ባለፈው ዓመት በማራቶን ያስመዘገበችው 2፡21፡01 የሆነ ፈጣን ሰዓት እንዲሁም በዘንድሮው ዓመት ያስመዘገበችው 2፡25፡46 ሰዓት ምስክር ነው፡፡
ኢትዮጵያ በዘንድሮው ሻምፒዮና በተለይም በማራቶን ባሰባሰበችው ቡድን ከምንጊዜውም በላይ ውጤታማ እንደምትሆን የተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙኃኖች እየዘገቡ ይገኛል፡፡ በማራቶን ስብስብ ውስጥ የተካተቱት አትሌቶች የኦሊምፒክና ሌሎች ታዋቂ የማራቶን ውድድሮች ማሸነፍ የቻሉ መሆናቸው በነገው ውድድር ምንም መፍጠር አይችሉም ብሎ ለመገመት ከባድ እንዲሆን አድርጓል፡፡

Latest from Blog

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

Go toTop