እስቲ እረጋ ብለን ደግሞ እንነጋገር… “ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ” (ከአቤ ቶክቻው)

እስቲ እረጋ ብለን ደግሞ እንነጋገር… ”ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ”

ወንድማችን

ጃዋር መሀመድ እኔን ጨምሮ በርካቶች የሚያደንቁት ወጣት ነው፡፡ ሀሳቦቹ አንጀት ላይ ጠብ የሚሉ ገዢ ሀሳቦች ናቸው፡፡ የሚገዙት ታድያ እንደ ገዢው ፓርቲ አስገድደው አይደለም፡፡ ጃዋር ወደው ፈቅደው የሚገዙላቸው

ሀሳቦች ባለቤት ነው፡፡ እኔ ከጃዋር ሀሳቦች ጋር በቅጡ የተዋወቅሁት የቱኒዚያ አብዮት የተቀሰቀሰ ሰሞን ነበር፡፡ ስለ ቱኒዚያ እና ግብፅ አብዮቶች መንስኤ፤ አስፈላጊነታቸው እና ውጤታማነታቸው ጃዋር ከፃፈው በተሸለ ገብቶኝ እና ተመችቶኝ ያነበብኩት መኖሩን እንጃ…

ከዛም በኋላ ጃዋር የሚሰጣቸውን ትንታኔዎች ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ እሰማለሁ፡፡ ሰምቼም እስማማለሁ፡፡ ምን መስማማት ብቻ፤ የሆነ ቀን ጃዋር ምርጫ
ቢወዳደር ይምራኝ ብዬ የምመርጠው ሁሉ እስኪሆን ድረስ አክባሪው ሆኛለሁ…!

ከእለታት በአንዱ ቀን እኛ “በፌስ ቡክ አስተዳደር የኢህአዴግ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት” የምንለው ዳንኤል በርሄ በአሁኑ ሰዓት በአልጀዚራ የሚተላለፈውን እባክችሁ ቅዱልኝ ብሎ ተማፅኖ ሲያሰማ “እኔ እንደ እናንተ አይደለሁም” በሚል “ሙድ” ልቀዳለት ወደ አልጀዚራ ጎራ አልኩ… የማከብረው ጃዋር በአልጀዚራ ስቱዲዮ ጉብ ብሏል፡፡ እውነቱን ለመናገር ጃዋርን ባየሁት ጊዜ ኖራ… ብዬ አባቴ የሚያከብረው ሰው ሲመጣ እንደሚያደርገው በአክብሮት ከመቀመጫዬ ተነስቻለሁ…

እንግዲህ ይሄኔ ነው፡፡ ኦቦ ጃዋር እስከዛሬ ሲናገር ይስማሙኝ ከነበሩት በተቃራኒው የማይስማማኝን ነገር ሲናገር የሰማሁት፡፡ የተረገመቺቱ የአልጀዚራ ጋዜጠኛ አንድ የተረገመ ጥያቄ ጠየቀችው… ኦሮሞ ፈርስት ወይስ ኢትዮጵያ ፈርስት… አለችው… እርሱም ኦሮሞ ፈርስት አለ፡፡ ጃዋር ይሄንን የማለት መብት አለው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በግድ የተጫነብኝ ነው ሲልም ተናገረ፡፡ ይሄንንም የማለት መብት አለው፡፡ እኔ ደግሞ መብቴን በመጠቀም፤ አንድ ውሳኔ ላይ ደረስኩ… ጃዋር ምርጫ ቢወዳደር አልመርጠውም፡፡ እንኳንም ቀድሞ ተወዳድሮ ጉድ አላደረገኝ አልኩ… (አልጀዚራንም እረገምኩ እንድንከፋፈል አድርጎናልና፤ ዳንኤል በርሄንም ረገምኩ አልጀዚራን እንድመለከት አድርጎኛልና፤ ጃዋርንም አሽሟጠጥኩ ሀሳቡ አልረባልኝምና!)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕዝብን በኃይልና አጀንዳ በማስቀየር ለመምራት  መሞክር ትርፉ ኪሳራ ነው!! (ተዘራ አሰጉ)

ጃዋርን ያሰብኩት ለክልሉ አስተዳዳሪነት ሳይሆን ለሀገሪቷ መሪነት ነበር፡፡ ታድያ ለቤተዘመዶቹ ቅድሚያውን የሚሰጥ መሪ አማራሪ እንጂ ምኑን መሪ ሆነው… ለመሆኑስ የብሄርተኝነት ጥጉ የት ድረስ ነው…. ስልም… ሽሮሜዳ ደረስኩ… እናም የመጣው ምጣ ብዬ አሽሟጠጥኩ!

ይለይልህ ብለው የጃዋርን ሌላ ንግግር ሰዎች ካለበት ፈልፍለው አሳዩኝ… ይሄኛው ደግሞ የባሰበት ነው፡፡ ጃዋር ባደገበት አካባቢ ዘጠና ዘጠኝ በመቶው ሙስሊም ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ሙስሊም ያልሆነ ኦሮሞ ቀና ቢል “በሜንጫ ነው አንገቱን የምንለው” አለን፡፡ ልብ አድርጉልኝ ጃዋር “ኦሮሞ ፈርስት” ብሎ አላቆመም ደግሞ “ሙስሊም ኦሮሞ ፈርስት” አለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እኔ እና ሌላው ዋቄፈታ ኦሮሞ ጃዋርን ይምራን ብለን መርጠነው ቢሆን ኖሮ እጣ ፈንታችን ቀና ስንል ሜንጫ ነበር ማለት ነው፡፡

አንድ ጊዜ ቤተሰባዊ ዝምድናውን ያስቀደመ ሰው ማብቂያ አይኖረውም፡፡ የምለው ለዚህ ነው፡፡ በደሉ የሁላችንም ነውና በደል የሌለባት ሀገር እንድትኖረን ሁላችን በአንድ ላይ ብንተባበር የተሸለ ነው የምለውም ለዚህ ነው…! “ሁላችንም ነፃ ካልወጣን አንዳችንም ነጻ አይደለንም” የሚለው የኦባንግ ሜቶ ንግግር የሚማርከኝ ለዚህ ነው፡፡

በኦነግ ትግል ምስረታ ወቅት ከመስራቾች አንዱ የነበሩት ሀጂ ሁሴን ሱራ፤ ትግላችንን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲሆን፤ “ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ” (የተጨቆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች) እንበለው እና በጋራ በደልን እንታገል ሲሉ ቀደምት የኦሮሞ ታጋዮችን ለማሳመን አጥብቀው ሲከራከሩ እንደነበር ስለኦነግ ሚጢጢ እውቀት ያለው ሁሉ የሚያስታውሰው ነው፡፡ እናም ይህ ሀሳብ በኦሮሞ ዘንድ አዲስ ሀሳብ አይደለም፡፡

በአሁኑ ጊዜ ያሉ ኦሮሞ ታጋዮች የቀድሞ ንጉሳ ንጉሶችን በመኮነን በኦሮሞ ህዝብ ላይ የደረሰውን በደል ሲዘረዝሩ ይሰማሉ፡፡ እውነቱን ለመናገር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የአማራም የኦሮሞም የጉራጌም የትግሬም ገበሬ ደልቶት የሚያውቅበት ጊዜ አላነበብኩም፡፡ ከንጉሳውን ቤተዘመዶች ውጪ አብዛኛው ህዝብ ጭቁን ነበር፡፡ ለዚህም ነበር በእነ ሃጂ ሁሴን ሱራ ዘንድ “ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ” የሚለው ሃሳብ የተወለደው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ወይንስ ሁንም ፍጅት እና ኮሮጆ ግልበጣ? - መንግስቱ ሙሴ/ዳላስ

በአፄዎቹ ዘመን የተበደለው እና የተጨቆነው ኦሮሞው ብቻ እንኳ ቢሆን፤ እንደ ጃዋር የመሰሉት ምሁራን ያለፈውን ታሪክ ለታሪክ ፀሀፊዎች ትተው እነርሱ በሽሙጡም ሳይደነግጡ በሙገሳውም ሳኩራሩ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ የሚበጀውን የመቻቻል መንገድ በመቀየስ ታሪክ ቢሰሩ መታደል ነበር፡፡

ዛሬ በወዳጃችን ጃዋር ድረ ገፅ ላይ “በዲያስፖራ ያለውን የወቅቱን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በማስመልከት በአውሮፓ የኦሮሞ ወጣቶችና የሴቶች ማህበራት የጋራ መግለጫ” የሚል ፅሁፍ ተመለከትኩ፡፡

በተለይ ደግሞ ይቺ አንቀፅ ቀልቤን ሳበችው፡፡

“እኛ በአውሮፓ የኦሮሞ ወጣቶችና የሴቶች ማህበራት በአሁኑ ወቅት በአልጀዚራ ላይ ቅድሚያ ኦሮሞ ነኝ በማለቱ ብቻ በፖለቲካ ምሁሩ ጀዋር ላይ የተከፈተውን የሀሰት ዘመቻ ማውገዝ ብቻ ሳይሆን ለመከላከልም በመገደዳችን ይህ አይነቱ አጼያዊ ዘመቻ እስኪያቆም ድረስ ከቅርብ ጊዜ በፊት ከሰላም ወዳድ የአንድነት ሀይሎች ጋር የጀመርነውን የቅርርብ ዲያሎጎችና የሀሳብ ልውውጦች በይበልጥ ልንገመግምው ወስነናል። ”

እኔ ጃዋርን ብሆን ኖሮ ይህንን ፅሁፍ በራሴ ድረ ገፅ ላይ አላትምም ነበር፡፡ ምክንያቱም ጃዋር የዚህ ማህበር አባል አይደለም እርሱ የሚኖረው አሜሪካ ነው፤ መግለጫው ደግሞ “በአውሮፓ የኦሮሞ ወጣቶችና የሴቶች ማህበራት“ ያወጡት ነው፡፡ የአደባባይ ሰው ሲሆኑ ትችትም ሙገሳም እንደሚመጣ የታወቀ ነው፡፡ ለሚሰነዘርብን ትችት በሙሉ ዘመዶቻችን መግለጫ እንዲያወጡልን ከመጋበዝ ራሳችን ነጥብ በነጥብ ለመመለስ መሞከር የተሸለ ነው፡፡

ማህበሩም ቢሆን ጃዋር ላይ የሚሰነዘር ትችት ኦሮሞ ላይ የተሰነዘረ አድርጎ በማየት “…ከሰላም ወዳድ የአንድነት ሀይሎች ጋር የጀመርነውን የቅርርብ ዲያሎጎችና የሀሳብ ልውውጦች በይበልጥ ልንገመግምው ወስነናል።” የሚል ትልቅ ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው መግለጫ ማውጣቱ አስገራሚ ነው፡፡ ትልቅ ሀገራዊ ራዕይን አንድ ሰው ተነካ ብሎ እንደውም አንጫወትም ብሎ ለማቋረት መዳዳት ለማን እንደሚጠቅም ፈጣሪ ይወቅ…!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጭራቅ አሕመድ ሆይ እርምህን አውጣ፣ የመዋጋት አለመዋጋት ምርጫ ያንተ ሳይሆን ያማራ ሕዝብ ሁኗል

ጃዋር ወደፊትም ቢሆን ጥሩ ሲሰራ መመስገኑ መጥፎ ሲሰራ መተቸቱ የማይቀር ነው፡፡ ለትችቱ ምለሽ ለሙገሳውም ምስጋና መስጠት ያለበት ጃዋር እንጂ ዘመዶቹ አይደለንም፡፡

በአሁኑ ወቅት ትልቁ አሳሳቢ ችግር “ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ” (የተጨቆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች) አለመተባበራቸው ነው፡፡ እኔ ብቻ ነኝ የተበደልኩት ብሎ የራስን ችግር ብቻ አግዝፎ ማየት እና ማሳየት የትም አያደርስም፡፡ (ብዬ አስባለሁ… ማሰብ መብቴ ነው! (በሌላ ቅንፍ ደግነቱ ይሄንን ችግር ሀገር ውስጥ ብብዛት አላየሁትም…))

ጎበዝ ለማንኛውም “በስጫው”ን ትተን እስቲ ረጋ ብለን እንነጋገር…!

“በስጫ”… ማለት የአራዳ ብሄረሰብ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም ብስጭት ማለት ነው፡፡

23 Comments

  1. Abe,

    Don’t lie. Your lies do not solve the Ethiopian problem. We have advised you to stay away from politics. You have lost your identity and you cannot make judgements.

  2. Abe,

    I understand that you are in South Africa. Why don’t you tell your “Ethiopian” buddies about the resolution of the Oromo community in South Africa. I know you are not part of that community, but you have heard it all.

  3. Ay Abe….tebarek abo. You wrote us a very sweet article. I appreciate it! Many will come soon to admire you. We will be benefited when we start thinking like you!! Mother stomac is ranager endetebalew…Ethiopia yantem ye Jawarm enat nat. But he deny that and said Ethiopia is imposed on me by force.

  4. If u are a real oromo as u seem to write,the current rage and insult following jewar’s utterance of ‘i am oromo first’is also about u and all of us who are oromos whatever our age,sex,place,level of knowledge,etc.Ato Abe,it is better to serve ur people than amhara chauvinists who can reject u when u affirm ur identity like they did to juhar.I am currently in oromia,but after seeing that vid on youtube i see the fear of amhara’s towards oromo nationalism and how antagonistic they are at u when u are talking the plight of oromos.Even if i have many amhara friends i cannot trust amhara them anymore(ye ebab lij mechem ebab newu aydel?silezi Abe enem honku lelawu oromo temeleseh wede beteh betmeta shengay sayihon ewunetegna fikir yesayihal.There’s nothing good &hard than speaking the truth.ke oromo hizb gon komeh ende juhar demshin asema.May Allah help u. Oromia shall be free!

  5. selam tokichaw,

    For one willing for democracy and peace, Ones question for self rule has to be respected. Abe, please listed to most oromo hearts. Not those only in Addis but all over the country. Their dream is self autonomy and living in peace with others. You can hear this from what they speak, what most of the musicians sing, even those Ethiopianists like Tsegaye G.Medihin have dreams which he expresses in his poems. Bro. Peace to all. I wish majority dreams to get fulfilled. All nations are brothers. this doesnt mean they have to ignore their assets and identity…

  6. አቤ እስኪ ታዘብካቸው እነዚህን የኦሮሞ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ ሰዎች በጣም እሚገርመው ትግሬዎች መለሰ ዚናዊን እንደ ልዩ ፍጥረት ሱፕር ማን ያዩታል ለአስከሪኑም እንደ ጣወት ሲሰግዱ ተመልክተናል ትግሪዎቹ ይህን ቢሉም ቢያደርጉም ሰውየው በጣም አጭበርባሪ እና ወደድንም ጠላንም የሃገር መሪ ስለነበር ነው እንበል እና ምክኒያታዊ ናቸው እንበል።

    ከላይ አንተ የጠቀስካቸው የኦሮሞ ፖለቲከኞች ነን ባዮች ግን ለጀወህር ብለው ቤህራዊ አጀንዳን በግለሰብ እንቀይራለን የሚሉ ናቸው ። ጀውህር ማነው ምንስ ነው ያደረገው በትክክል እኔ እስከማውቀው ድረስ ካረቦችና ከግብጾች ጋር በመመሳጥር የኢትዮጵያን አንድነት ከሚፈታተኑት አንዱ የወያኔ ጀሌ ነው ። ሊላው ደግሞ አረቦች መሰረታዊ እና ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች መሆናቸው የታወቀ ነው። ይሄ ግለሰብ በጀዚራ እየቀረበ እራሱን አግዝፎ በማሳየት የነገው ሊንጮ ለታ ለመሆን እየጣረ ነው ። በእውነት ታዲያ ለዚህ ሲባል ነው ሃሳባችን እንቀይራለን የሚባለው?

  7. @Selam,

    God bless you, because you loved peace, respect and equality. We want matured Ethiopian like you. But I am worried as it seems it is yet too far to get such principle of human being as selfishness of Ethiopians is so extreme. Any way let us wait and see the consequences. But it will not be affordable.

  8. ሞላ ፣ኢሰሰት ላይ ዋዘና ቁም ነገር እያቀረበ እያየክ ደቡብ አፍሪካ ትላለክ ፊዞ

  9. Abe,
    If you think deep, you are the outcome of the oppression by Habeshas. It is your right to speak for them. No one can stop you from that. But, don’t put yourself in such kind of sensitive matters. The day they turn you their back, it’ll be disastrous for you. Such a thing is not new for Oromo’s. Habashas are using personalities like you for their hidden agenda. They will throw you away like a sugarcane when they achieve their goal.

  10. አቤ ተብዬዉ…. እኔን የሚገርመኝ ነገር ቢኖር የአንተ በኦሮሞነትህ ማፈር ነዉ…
    በነገራችን ላይ ጀዋር የእንደ አንተ አይነቱን መራጭ ይሁን በመሰሎችህ መመረጥም መሞገስም የሚፈልግ ሰዉ አይደለም ። ሲጀምር አበሻዊ ጭንቅላት ያላቸዉ አንተንና ጀሌዎችህን የልቦናችሁን ዓይን አሳዉረዉ በልጓም እንደሚመራ ፈረስ ወደፈለጉበት መንዳት የለመዱትን እነሱ ጀዋር እንደሚፈልጉት ማለትም እንዳንተ ስላልተመቻቸዉ አንተና መሰሎችህ እንደለመደባችዉ የፈለጋችዉን ማለት ብትችሉም በጀዋር ላይ ቅንጣት ታክል ምትጨምሩለትና ምትቀንሱለት ክብርም ሆነ ሹመት እንደለለ እንድታዉቁሉን እንፈልጋለን። በእርግጥም እናንተ እንኳን ለጀዋር ኦሮሚያነቱን በአለም ላሳወቀዉ ይቅርና… እስር ቤት ላለዉ ለኦሮሞ እስረኛም ስሙን ከማጥፋት እፍረት የማይሰማችዉ ዘጎች እንደ ሆናችሁ አለቃቃችሁ በአንድ ወቅት ገልጸዉልን ነበር….ብራኑ ነጋ.
    አንዳንዴ ላልፈርድብህም እገደዳለዉ ኦሮሞ ብዙ ጉድፈቻ ስለነበሩት ከእነሱም እንደ አንዱ ልትሆን ስለምትችል ብዙም እንድልህ ባልደፈርም ግን ያንተም ጽዋ እስኪሞላ እንጠብቅ፣፣ ወደድክም ጠላህም እኔ አበሻ ያልሆንኩ ንጹ ኦሮሞ ነኝ፤።
    ጀዋር ሁሌም የምንወደዉ ብርቅዬ ጀግናችን ነዉ። ለእናንተ ደግሞ የልቦናችሁ ትርታ ማጥፍያ ወይም ማዉደምያ ቁልፍ መሰለኝ

    • confusing analogy, what is the difference between habesha and oromo, does habesha a tribe like oromo? what does pure Oromo means ?

  11. እሰቲ ረጋ በሉ ሁላቸሁም ፣ስለሀገር የሚታሰበው በኢረፍት ቀን ብቻ አደለም ፣ ሁሌም ነው።አቤ ደግሞ ሁሌም ስለሃገሩ የሚያስብ ነው።ጀዋርም የቀን ጀግና ጥሎት ወይም የ ኢትዮጲያ አምላክ ፈርዶበት አፉን በጉሊስ መትቶት ነው፤፡ እንጂ እንዲህ አይነት ሰው አይመስልም ነበር ።አሁን ግን ሆነ።ያ አላህ ያ እረቢ አትበለን እምቢ”ብሎአል የሃገሬ ሰው።ወዳጄ ጀዋርም ለበደልህ ይቅርታ ጠይቅና ከመንደር ይልቅ ትልቋን ኢትዮጲያ አስበህ ወደልቦናህ ተመለስ።እንወድሃለን።(ሃሳባ ኩኒ ከነማ ከ አካ ኬቲ ከዱበቱ ሚቲ፤ (በኦሮምኛ) ለሁሉም ግን ማለት መሆን አደለምና ተረጋጉ።ከመድሃኒአለም ከመጣ ማንም የኢጁን ማግኘቱ አይቀርም።ጀዋር ስለተናገረ ኢትዮጲያ ምንም አትሆንም።ጀዋር ከሰራ ግን ከሌላው ጋር ተዳምሮ ለለውጥ ምክንያት ይሆናል።አንተም ጀዋር ብትሆን እኔም ጀዋር ብሆን የሆነ ጎዶሎ አናጣም።ሰው ነንና። ለሁሉም ከሁሉም በፊት ሁለቴ ማሳብ ደግ ነው ።የ አደባባይ ሰው ሲሆኑ ጣጣው በዙ ነውና ።ሽቅብ እንደቡና ውሃ መፍላቱ እሳቱ ሲበዛ ቶሎ ለማለቅ ነውና ።ወዳጄ ጀዋር ጠንቀቅ ማለቱ እንደመለስ ዜናዊ በድምፅ ከመሞት ይሰውርሃል።

  12. ere tewu selerasachu becha atasebu yetawekachuhal gen sentu oromo ke tegre*amhara*debubew ga tegabto endeminor. ewnetu lengerachu yetgnawem hezb berasu chekuagna aydelem amhara berasu weynem tegrie hezbu chekuagn adelem yetegrie ena ye amhara mengist enji teraw hezbe gen balseraw yeferjal yerasu eyarerebet becha segeletlen hulun enayalen eskezaw……..

  13. why don’t some oromo politicians speak about the oromo leaders of Ethiopia like Hailesilassie, Mengistu Haile mariam, Aba Jifar and others? Atse Minilik was half oromo and half Amhara so why don’t they speak it up about it instead of complaining about past things? the reason is beause it is not benefitable for their poitical agenda because it does not go with their secret agenda

  14. firew@ እንደ ኦሮሞነት የሚያኮራ ምን ነገር አለ ። የሚያሳፍረዉ በዚ በ21ኞው ክፍለ ዘመን ያውም በሰለጠነው አለም ቁጭ ብለቹ የዘሬ ሶሰት መቶና አራት መቶ አመት አመራ አሮሞን ገሎ ነበር ጉራጌ ትግሬን ገሎ ነበር እያለቹ በ ኦሮሞ ስም የመታወሩት የሳፍራል

  15. Abe Tokkichaw is a typical house Negro (he is slave of Amhara). When his master gets sick, a house Negro cries louder than the patient himself. That is Abe Tokkichaw.

  16. Abe you are telling the truth free from any prejudice. Many Oromos with clear conscious and accountability like you most often coming forward to condemn half century old futile and distractive objectives of OLF . Ignore the above nasty remarks generated from brutal monsters. By the way if they accuse MInilik and Mengistu for committing genocide exclusively on Oromo community that is their own problem nothing to do with Amhara because both of the premiers were Oromos. Rather we have had endured so many grievances and unspeakable ordeals that monster OLF inflicted on us.

Comments are closed.

Share