የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሸን የንግድ ሥርዓቱ በሙስና የተዘፈቀ መሆኑን አረጋግጫለሁ አለ…(ትዕግስት ዘሪሁን)

ኢሕአዲግ

ይህን የሰማነው ኮሚሽኑ ዛሬ የአዲስ አበባ ነጋዴዎችንና የንግድ ሥርዓት አስፈፃሚ የሆኑ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ኃላፊዎችን ሲያወያይ ነው፡፡

ምክትል ኮሚሽነሩ አቶ ወዶ አጦ እንዳሉት የንግድ ፈቃድ ለማደስ የሚጠየቅ ጥቅማ ጥቅም አለ፣ በትላልቅ የመንግሥት ንብረትና አገልግሎት ግዢ ላይም በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ብር ይጭበረበራል፡፡

በተጨማሪም የዕለት ተዕለት ኑሮ ጋር የተገናኘ መሠረታዊ የንግድ ሥርዓት ችግር መኖሩንም ሰምተናል፡፡

በመሠረታዊ የሸቀጣ ሸቀጥና የፍጆታ እቃዎች አቅርቦትና ስርጭት ህዝቡን እያማረረ ነው ተብሏል፡፡ የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ የንግድ ዕቃዎችም በመመሳጠር ለወጪና ገቢ ንግድ ፈቃድ እንዲሚሰጥ ደርሼበታለሁ ብሏል ኮሚሽኑ፡፡

በንግድ ስርዓቱ ላይ ያሉ የተበላሹ አሰራሮችንም አይቻለሁ፤ ብቻዬን ለውጥ ማምጣት ስለማልችል የንግዱ ማህበረሰብም ችግሩን በማጋለጥና መፍትሄ እንዲመጣ በማድረግ ሊያግዘኝ ይገባል ሲል የንግዱን ማህበረሰብ እያወያየ ነው፡፡

እንደ አለም ባንክ ግምት ከሆነ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ የአለም አገሮች 80 ቢሊየን ዶላር በየአመቱ በሙስና መልኩ ይከፈላል፡፡

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ብርጌድየር ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ትላንት በጆንያ ስለተያዘው ሽጉጥ ተናገሩ

1 Comment

Comments are closed.

Share