Sport: የባርሴሎናው ቴክኒሻን ኢኔሽታ ውለታውን እየመለሰ ነው

በውጤታማው የካታላኑ ክለብ በባርሴሎናና በስፔን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ቴክንሽያንነቱ ይታወቃል የ29 ዓመቱ አንድሬስ ኢኔሽታ።
በአውሮፓውያኑ 1996 በአስራ ሁለት ዓመቱ ይስፔኑን ኃያል ባርሴሎናን ከመቀላቀሉ በፊት በአገሪቱ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ቢ በመወዳደር ላይ ለሚገኘው አልባሴቴ በተሰኘው እግር ኳስ ነው ከእግር ኳስ ስፖርት ጋር የተዋወቀው።
ተጫዋቹ ታዲያ የቀድሞ ክለቡ ወደ አራተኛው ዲቪዚዮን ከመውረድ በመታደግ ውለታ መላሽነቱን አስመስክሯል።
ለተጫዋቾቹ ደመወዝና ላለበት የተለያዩ ዕዳዎች የሚከፍለው ገንዘብ በማጣቱ ምክንያት ካለበው ዲቪዚዮን ወደ ታችኛው ዲቪዚዮን የመውረድ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦበት የነበረውን የልጅነት ክለቡን አልባሴቴን ሁለት መቶ ሺ ፓውንድ በመስጠት አለሁልህ ማለቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ተጫዋቹ የክለቡ ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት ሲሆን ከሁለት ዓመታት በፊት በተመሳሳይ አራት መቶ ሺ ፓውንድ ድጋፍ ማድረጉን ዘገባዎቹ አስታውሰዋል።
በፊፋ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር የአውሮፓና የዓለም ዋንጫ ያነሳው የ29 ዓመቱ ኢኔሽታ በአልባሴቴ እግር ኳስ ክለብ ሁለት ዓመት ቆይቷል።
በተያያዘ ዜና የባርሴሎና የከተማ ተቀናቃኝ የሆነው የስፓኞል እግር ኳስ ክለብ ፐሬዚዳንት ዮአን ኮሌት ባርሴሎና ታዳጊ ተጫዋቾቻችንን ከአካዳሚያቸው አላግባብ ከመውሰድ ሊቆጠብ ይገባዋል ማለታቸውን ዴይሊሜል ዘግቧል።
የእስፓኞል የወጣቶች አካዳሚ አባላት የሆኑ አምስት ተጫዋቾች በቅርቡ አላግባብ በሆነ መንገድ ባርሴሎናን መቀላቀላቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አርቲስት ታማኝ በየነን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦች እና የቀድሞ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ግንባር ዘመቱ
Share