ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሌባ ተባባሪነት ለመደባቸው

June 23, 2013

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ዘ-ሐበሻ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀትጉሃን አስታጥቄ አባተ አቅመ ደካማ ለሆኑ አባት አርበኞች የፈቀዱላቸውን 25 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለግል ጥቅም አውለዋል፣ ከሚያከራዩዋቸው ሕንፃዎች ከሚያገኙት ገቢ ላይ የአከራይ ተከራይ ግብር አለመክፈል፣ ያላግባብ ወጪ ማድረግና በመሳሰሉት ተጠርጥረው መከሰሳቸውን መዘገቧ ይታወሳል። ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ታትሞ የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ “ፕሬዚዳንት ግርማ የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ክስ እንዲቋረጥ ጥሪ ማቅረባቸውን” ያትታል። ዜናውን ለተመለከተ ከዘራፊው የወያኔ ስርዓት ጋር በመተባበር “አበባ የመትከልና አበባ የመቁረጥ ስልጣን” ብቻ ተሰጥቷቸው ቁጭ ያሉት ፕሬዚዳንቱ እኚህን በርከት ያሉ አርበኞች አባቶችን ያስለቀሱትን ሊቀትጉሃንን ክሳቸው ተቋርጦ ይፈቱ ሲሉ በድፍረት መጠየቃቸው የሌባ ተባባሪነቱ ለመደባቸው፤ ወይም ከሌባ ጋር መተባበር ሱስ ሆነባቸው እንዴ? ያስብላል። የሪፖርተር ዜና እንደሚከተለው ነው። አንብቡትና ትዝብታችሁን ጣሉበት።

በከባድ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት፣ ዋና ጸሐፊና የአስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ፣ የተከሰሱበት ክስ እንዲቋረጥላቸው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ለፍትሕ ሚኒስቴር የጻፉት ደብዳቤ ውድቅ መደረጉን ምንጮች ለሪፖርተር አረጋገጡ፡፡

የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ለፕሬዚዳንት ግርማ በጻፉላቸው የመማፀኛ ደብዳቤ አማካይነት፣ ክሳቸው እንዲቋረጥላቸው ወይም በይቅርታ እንዲታለፉ ፕሬዚዳንቱ ደብዳቤውን የጻፉት በፍትሕ ሚኒስቴር የሕግና አስተዳደር ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ለአቶ ብርሃኑ ፀጋዬ መሆኑን ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡

በከባድ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ወንጀል ችሎት ክስ የቀረበባቸው የኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ፣ ዋና ጸሐፊው ፲ አለቃ ሰጥአርጌ አያሌውና የአስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ አቶ በቀለ ሻረው መሆናቸው ይታወሳል፡፡

ፕሬዚዳንት ግርማ ተጠርጣሪዎቹ በአገራቸው የጀግንነት ታሪክ ከፍተኛ ቦታ እንዳላቸው፣ ለአገር ልማትም በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ መሆናቸውንና ዕድሜያቸውም የገፋ መሆኑን በመግለጽ፣ መንግሥት ይቅርታ አድርጐላቸው ክሳቸው እንዲቋረጥ በደብዳቤ መጠየቃቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ግንቦት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በቁጥር መ/818/2005 የጻፉትን ደብዳቤ የተመለከቱት የፍትሕ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ጥያቄው ተገቢ አለመሆኑን፣ ግለሰቦቹም የተጠረጠሩበትን የወንጀል ድርጊት ፍርድ ቤት ቀርበው በሚደረግ የግራ ቀኝ ክርክርና የሕግ ሒደት ብቻ የሚታይ መሆኑን በመግለጽ፣ ጥያቄውን ውድቅ እንዳደረጉት ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

እነ ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ የተጠረጠሩበት ወንጀል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት አቶ አርከበ ዕቁባይ፣ አቅመ ደካማ ለሆኑ አባት አርበኞች የፈቀዱላቸውን 25 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለግል ጥቅም አውለዋል፣ ከሚያከራዩዋቸው ሕንፃዎች ከሚያገኙት ገቢ ላይ የአከራይ ተከራይ ግብር አለመክፈል፣ ያላግባብ ወጪ ማድረግና በመሳሰሉት ተጠርጥረው መከሰሳቸውን፣ ዋና ጸሐፊውና የአስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊው እያንዳንዳቸው በ25 ሺሕ ብር ዋስ መለቀቃቸውንና ፕሬዚዳንቱ ባለመቅረባቸው ታስረው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ መሰጠቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ (ሪፖርተር)

Latest from Blog

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

Go toTop