ግብፅ የሰጠችንን የቤት ሥራ ለምን አንሰራም?

ከዘካሪያስ አሳዬ

**የአባይ ጉዳይ የሰሜት ጉዳይ አይደለም!!!**

ትልቅ ጉዳይ ነው።ግን ያለ ነፃነት ልማት ዋጋ የለውም!!!
የህዝቡ ጥያቄ በአሁን ሰዓት የነፃነት ፕሮጀክት ነው የሚፈልገው።
የውኃ ጥም የሚያረካው ውኃ ፍሪጅ ውስጥ ስለተቀመጠ አይደለም፡፡ ሱቅ ውስጥም ስለተደረደረ አይደለም፡፡ ምንጮች ውኃ ስላላቸው አይደለም፡፡ የውኃ ማስታወቂያዎች ስለተሰሙ፣ ስለተነበቡና ስለታዩ አይደለም፡፡ በተጨባጭ የተጠማው ሰው ማግኘትና መጠጣት ሲችል ነው፡፡
ገዥው ፖርቲ እውነታውን ለህዝብ ከመነሻው ጀምሮ ማሳወቅ አለበት።ግብፆች ስለአባይ ጉዳይ እኮ ተቃዋሚውቹንም ጠርተው ስለ አገራቸው እንዲመክሩ ተደርጓል ታዲያ የገዥው መንግስት ተቃዋሚውን ለማማከር አይደለም እንደ ባህዳን አገር ሰው መቁጠሩን ተያይዞታል ይህ አካሄድ ምንም አያስኬድም ዋጋ ያስከፍላል እንጂ።እነ በረከትም አገር ውስጥ ያሉትን ጋዜጠኞች ሰብስበው ስለ አባይ ጉዳይ ምንም መጥፎ ነገር እንዳይዘግቡ ማስፈራራት ተያይዘውታል።
አገራዊ ጉዳይ ብቻ እንዲያደርጉት እያሳሰቧቸው ነው።ከህዝብ ምንም ነገር ሊደበቅ አይችልም።ወያኔ/ኢህአዴግ የአባይን ጉዳይ ፕሮፓጋንዳ መንፊያ አድርገውታል።
የኢትዮጵያ መንግስት የአባይን ጉዳይ የፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረጉን እንዲያቆም ማድረግ ግድይላል።እውነቱ ግን ይህ ነው
ሁሉንም ነገር ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የቆረጠ ፓርቲ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ መጣሉ የማይቀር ነው።
የአባይ ከመገደቡ በፊት መፈፀም የሚገባው የዲፕሎማሲ ስራዎች አልተሰሩም፡፡
እውነታውን ይዘን መሄድ ካለብን “በአባይ ላይ ግድብ ከመሰራቱ በፊት ማለቅ የሚገባቸው የዲፕሎማሲ ስራዎችና ሌሎች ጉዳዮች በውል ታይተዋል ወይ የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነው፡፡ ከነዚህም ዋነኛው በቂ የዲፕሎማሲ ስራ ያለመሰራቱና ከአባይ ተጋሪ ሃገሮች ጋር በቂና አስተማማኝ ውይይት አድርጎ ስምምነት አለመድረስ በዚህ የተነሳ ሃገሪቱ የጦርነት ስጋት ቢገጥማት ለመቋቋም በቂ ዝግጅት ያለማድረግ ይገኙበታል፡፡”
የኢትዮጵያና የግብፅ መንግስት ከፀብ አጫሪ ድርጊትተቆጥበው በጠረጵዛ ዙሪያ ንግግሮች ላይ እንዲያተኩሩ መሆን አለበት።
ሁለቱም ሀገሮች የአባይን ጉዳይ ለውስጥ ፓለቲካ ማብረጃ ከማድረጋቸው እንዲቆጠቡና የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ ጉዳዩን ለፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረጉን ማቆም አለበት፡፡

እውነታው ግን ገዥው ፓርቲ በህዳሴው ግድብ ላይ ህዝቡን ባለቤት አላደረገም ፡፡

“ችግሩ የሚመነጨው ገዥው ፓርቲ በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመስራት መነሳቱ ሳይሆን የአባይን ጉዳይ የኢሕአዴግ ጉዳይ ማድረጉ።
የአባይን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ ራዕይ ማድረጉና ከእለት ጉርሱ ቀንሶ ቦንድ እየገዛ ያለውን ህዝብ የግድቡ ባለቤት ማድረግ አለመቻሉ ነው፡፡
ግድቡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግድብ ይሁን የኢሕአዴግ በዉል አልለዩትም፡፡
ኢትዮጵያዊነት በዘፈቀደ የመጣና በዘፈቀደ ሊደበዝዝ የሚችል አርእስተ-ጉዳይ አይደለም፡፡ አዲስና ቅኝ አገዛዝ ሰራሽም አይደለም፡፡ ለረጅም ዘመናት አብሮ በመኖር ከቁሳዊና ማህበራዊ ውህደት የመጣ ታሪካዊና ሕያው ህልውና ነው፡፡ ሉዓላዊነትም ነው፡፡ ትላንት የነበረ ዛሬም ያለ ለወደፊትም የሚኖር ነው።
እውነታው ግን የአባይን መገደብ የሚቃወም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የለም ።ኢትዮጵያዊ ሀገሩን ሲነኩበት አይወድም እውነታው እንዲ ነው። ነገር ግን አባይ የሚገደበው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጠቀም ከሆነ ፤ ህዝብ ይከበር ነው የምንለው ። ከአባይ በፊት፦
ነፃነት ይቅደም!
ዘረኝነት ይገደብ !
ህዝብን ማፈናቀል ይቁም !
ሰብኣዊነት ይቅደም !
በሃገራችን የአፓርታይድ ስርዐት ይወገድ !
የሃይማኖት ነጻነት ይከበር !
አባይን ለርካሽ ፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ ይቁም !
በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች ይፈቱ !
የሙስሊም ድምጽ ይሰማ !
ታሪካዊ ገዳማችን ዋልድባ ይከበር !
በህዝብ የተመረተ መንግስት ይምራን !
የህዝብ ድምጽ ይሰማ !
ነብሰ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ !
እና ሌሎችን ተያያዥነት ያላቸውን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ነው የተጠየቀው ።

ኢህአዴግ/ወያኔ አባይን ለኢትዮጲያ ህዝብ አጀንዳ መስጠቱ ነው ህዝቡ በጣም ነቅቷል!
የህዝቡ በአሁን ሰዓት የነፃነት ፕሮጀክት ነው የሚፈልገው።

ከሳምንታት በፊት የግብፅ ባለስልጣናት እና ፖለቲከኞች ኢትዮጵያ ላይ ሲያሴሩ የሚያሳይ ቪዲዮ እንደወጣ መቸም ብዙወቻችን አይተናል ወይም ሰምተናል:: ቪድዮዉን ሲያይ አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ ደሙ እንደፈላ በፌስ ቡክ እና በሌሎች መንገዶች ከሚሰጡ አስተያየቶች ለመታዘብ ችያለሁ፤ እኔም እራሴ በጣም ነው የተናደድኩት:: ነገር ግን አብዛኛዎቻችን በጉዳዩ ላይ ስሜታዊ ሁነን “ እስኪ ትምጣ እና እናሳያታለን” አልን እንጅ ግብፅ ብትመጣ የኛ ጠንካራ ጎን የቱ ላይ ነው? ደካማ ጎናችንስ? ጠንካራ ጎናችን እንዴት እንጠቀምበት ? ደካማ ጎናችንስ እንዴት እናሻሽለው የሚል ዉይይት እስካሁን አላየሁም፤ እንዲሁ ስሜታዊ ሽለላ አሰማን እንጅ::

ግብፆች ሀገራችን ለማዳከም እና በዓባይ ላይ ምንም ሥራ እንዳንሰራ በዋናነት ያስቀመጧቸው ስልቶች የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ የውስጥ ተቃዋሚወችን መርዳት ሲሆን ይህ ካልተሳካ ደግሞ ደግሞ ወታደራዊ ኃይል መጠቀም ነው:: ነገር ግን የአብዛኛዉን ሰው አስተያየት ስመለከት በግብፅ ኃይል እጠቀማለሁ ዛቻ መናደድ እንጅ ግብፆች ቁጥር አንድ ስልታችን ብለው ላስቀመጡት ኢትዮጵያዉያንን እርስ በእርስ ማዋጋት ምንም ትኩረት አልሰጡትም እንዲያዉም ይባስ ብሎ በካይሮ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች ያደረጉትን ሰልፍ ተከትሎ ሰልፈኞቹን ከመሳደብ በዘለለ ጉዳዩን ጠለቅ ብሎ የሚዳስስ አስተያየት እና ፅሁፍ አላስተዋልኩም ፤ ይህን ጉዳይ ሳስተዉል የግብፆች ወጥመድ ዉስጥ ሰተት ብለን እየገባን እንደሆነ ይሰማኛል:: ኦሮሞ ወንድሞቻችን ለምን ኢትዮጵያዊነታቸውን በአደባባይ ካዱ ? እነዚህን ኦሮሞ ወንድሞቻችን መሳደብ እና ማንቁአሸሽ ነው ወይስ ቀርቦ መማማር ኢትዮጵያዊነታቸዉን ከልባቸው እንዲቀበሉ የሚያደርጋቸው?

በመጀመሪያ ደረጃ በካይሮ የሚገኙ ኦሮሞዎች ያደረጉትን ሰልፍ ሲያይ የደነገጠ ካለ የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርበት ማወቁን እጠራጠራለሁ:: እኔ በበኩሌ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያላቸው ኦሮሞወች ጋር ባንድ ጣሪያ ስር የኖርኩበት ወቅት ስላለ የካይሮው ሰልፍ አላስደነገጠኝም :: አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበርኩበት ወቅት ያጋጠመኝን ላካፍላችሁ:: ወቅቱ የፈረንጆች አዲስ ዓመት 2007 መግብያ ጃኗሪ አንድ ነው የተወሰኑ የኦሮሞ ባህል ልብስ የለበሱ የኦሮሞ ተማሪዎች ተሰባሰቡ እና ርችት እየተኮሱ በጭፈራ የፈረንጆችን አዲስ ዓመት 2006 ማክበር ጀመሩ፤እንኳን የፈረንጆችን አዲስ ዓመት አይደለም የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ዩንቨርስቲዉ ዉስጥ በዚህ መልኩ ማክበር የተለመደ አይደለም :: ዝግጅታቸዉን ካጠናቀቁ በኋላ በዝግጅቱ ተካፋይ ከነበሩ አንድ ኦሮሞ ተወላጅ የዶርሜ ልጅ ጋር ስለሁኔታዉ ተጨዋወትን ፤ ለምን እንደዛ እንዳደረጉ ጠየቅኩት እሱም መለሰልኝ “እኛ ኦሮሞ እንጅ ኢትዮጵያዉያን አይደለንም” ስለዚህ መቁጠር የምንፈልገው በኢትዮጵያ ዘመን መቁጠሪያ ሳይሆን በአዉሮፓዉያን ዘመን መቁጠሪያ መሆኑን ለማሳየት ነው አለኝ:: ልብ በሉ ከዚህ ላይ ሁሉም ኦሮሞወች እንደዚህ ያስባሉ እያልኩ አይደለም፣ አብዛኛወቹ ኦሮሞዎችም በዛ ዝግጅት ላይ አልተሳተፉም ነገር ግን እንደዚህ የሚያስቡ ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ኦሮሞ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንዳሉ መካድ ግን እዉነታን ለመጋፈጥ መፍራት ነው ::

እነዚህ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ለምን የዚህ አይነት አቁአም እንደያዙ ስትጠይቃቸው የሚሰጧችሁ መልስ ባጭሩ ኢትዮጵያ ዉስጥ በእኩልነት እና በፍትህ መኖር ስላልቻልን ብለው ይመልሱልኛል:: ታዲያ እንደዚህ ሲሉን ብንሰድባቸው ችግሩ ይፈታል ወይ ? በእኔ አመለካከት ስድብ ችግሩን አይፈታዉም የተሻለ የሚሆነው እርስ በእርስ በሰለጠነ መልኩ መማማር ነዉ:: ኢትዮጵያ ዉስጥ የብሔር ጭቆና የሚደርስበት ኦሮሞ ብቻ አለመሆኑን መተማመን ፣ ትልቅ ሀገር ከትንሽ ሀገር የተሻለ ያለዉን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ሌሎች ጠቀሜታዎችን ማሳየት ፣ ሃገርን ወደ መገነጣጠል ቢኬድ ሊከተል የሚችለዉን ጦርነት እና ጥፋት መወያየት፣ መገንጠል በራሱ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ዋስትና አለመሆኑን ከተሞክሮ የኤርትራን ሁኔታ ማሳየት፣ ሀገር እና ሃገርን የሚመራዉ ቡድን የተለያዩ መሆናቸዉን መረዳዳት እና ሌሎች የትልቅ ሀገር ጠቀሜታዎችን ማስገንዘቡ የተሻለ ይሆናል:: በተጨማሪም ኦሮሞ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የሚያነሱትን ሃሳብ በሰለጠነ መንገድ በቅንነት በመረዳት የተሻለች ኢትዮጵያን እንዴት እንገንባ በሚለው ላይ መወያየቱ ጠቀሜታዉ ከፍተኛ እንደሆነ ይታየኛል::

በሌላ በኩል ህውሃት/ ኢህአዴግ ስልጣኑን ለማራዘም የሚጠቀምበት አንድ ስልት አለው ይኽዉም በሀገር አንድነት በሚያምኑት እና መገንጠል በሚፈልጉት ኢትዮጵያዉያን መካከል የኃይል ሚዛን እንዲኖር ማድረግ እና ሁልጊዜም ቅራኔ እንዲኖር ሌት ተቅን ተግቶ መስራት:: በሀገር አንድነት የሚያምኑት ጠንከር ብለው ለስልጣኑ አስጊ ሲሆኑ መገንጠል የሚፈልጉትን ለቀቅ በማድረግ እንዲጠናከሩ ይፈቅዳል (ለምሳሌ ከምርጫ 97 ማግስት ኢህአዴግ የወሰዳቸዉን እርምጃወች ልብ ይላችዋል)፤ መገንጠል የሚፈልገው ሲጠናከር እና ለህውሃት/ ኢህአዴግ ስልጣን አደጋ ሲጋርጥ በአንድነት የሚያምኑትን ጠንከር እንዲሉና ሚዛኑን እንዲጠብቁ በማድረግ ለራሱ ፖለቲካዊ ትርፍ ይጠቀምባቸዋል :: ስለዚህ የህወሓት እድሜን ከሚወስኑት ወሳኝ ነገሮች አንዱ እና ዋነኛዉ የነዚህ ሁለት ኃይሎች የመተባበር እና የመተማመን ሁኔታ ነው:: ነገር ግን በአሁኑ ስዓት ይህን የሀገራችን የፖለቲካ ደካማ ጎን የምታዉቀው ግብፅ ለራሷ ጥቅም ልትጠቀምበት እንደሆነ በአደባባይ ነግራናለች፤ እኛ ከግብፅ ቀድመን የቤት ሥራችን ካልሰራን እና ችግራችን ካልፈታን ትናንት ኤርትራን በማስገንጠል ሀገራችን ላይ እንዳደረሰችዉ ከባድ ኪሳራ ይህኛዉም ዉጥኗ ሊሳካላት ይችላል::

በነገራችን ላይ ሀገራችን ዉስጥ በመንግስት ላይ ቅራኔ ያለው ኦሮሞ ብቻ አይደለም ሌሎችም ብዙ ብዙ ጥያቄዎች አሉ:: ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን በመገንባት በእዉነተኛ ምርጫ በሕዝብ የተመረጠ መንግስት ስልጣን ላይ እንዲወጣ ከማድረግ አንስቶ የፕሬስ ነፃነትን ማክበር፣ የመንግስትን በሃይማኖት ጣልቃ መግባትን ማስቀረት፣ የብሔር ጭቆናን ማስወገድ እና እኩልነትን ማስፈን፣ ትክክለኛ ፌደራሊዝም እንዲተገበር ማድረግ ፣ አሸባሪ እና ሌላም ስም እየተሰጠ ያላግባብ የታሰሩትን ሰዎች መፍታት እና እርቅ እንዲኖር ማድረግ፣ ሙስናን መዋጋት እና ሌሎች ሀገሪቱ ዉስጥ ያሉትን ችግሮች መፍታት ካልተቻለ ከግብፅ ጋር ሳይሆን የምንዋጋዉ ግብፆች እንዳሴሩልን ልክ እንደከዚህ በፊቱ እርስ በእርስ እንዳይሆን እሰጋለሁ:: እነዚህ ችግሮች መፈታት ያለባቸው ግብፅ ትመጣለች ተብሎም ሳይሆን ለሀገራችን በዘለቄታዉ ከፍተኛ ችግር ስለሚፈጥር አሁንም እየጎዳን እንደሆነ ስናምን ነው::በእርግጥ እነዚህ ችግሮች ባንድ ሌሊት አይፈቱም ነገር ግን አሁን ባለዉ አኳዋን ጉዞአችን ወደዋላ ሁኗል ስለዚህ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት ወደፊት መራመድ መጀመር ይኖርብናል::

ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ሳንፈታ የዓባይ ግድብን ተሳክቶልን ብንጨርስ እንኩአን እርስ በእርስ ስንዋጋ እንደተከዜ ድልድይ ላለመፍረሱ ዋስትና የለንም፤ የጋዳፊዋን ሊቢያን ታሪክ እንዳንደግመውም ስጋት አለኝ:: ጋዳፊ የምዕራብ ዜና ማሰራጫዎች እንደሚነግሩን ሙሉ በሙሉ መጥፎ ሰው አልነበረም፤ ስልጣን ላይ እንደወጣ ባብዛኛዉ በምዕራብ ሃገራት የነዳጅ ካምፓኒዎች እጅ የነበረዉን የሀገሪቱን ነዳጅ በመዉረስ ከነዳጁ የሚገኘዉን ገንዘብ ለሕዝቡ ትምህርት፣ ጤና፣ ምግብ እና እንዲሁም ለሌሎች ጥቅማጥቅም እንዲሆን ከማድረጉም በላይ በነፍስ ወከፍ ጥሬ ገንዘብ ለዜጎች ያድል ነበር:: ሀገሪቱንም በመሰረተ ልማት እና በሌሎች ዘርፍች በከፍተኛ ደረጃ ለመለወጥ በቅቶ ነበር፤ ነገር ግን ጋዳፊ ዘረኛ እና አምባገነን ነበር:: የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ተቋማት በአብዛጋዉ ስርጥ የተባለ ቦታና ዙሪያ የሚኖሩ እሱ የሚወለድበት ‘የቃዳድፋ’ ጎሳ አባላት ነበር የተቆጣጠሩት፤ በዚህም ምክንያት በቤንጋዚ እና ሌሎች አካባቢ የሚኖሩ ሌሎች ሊብያዉያን ከፍተኛ ቅሬታ ነበራቸው:: ምንም እንኩአን እነዚህ ሊብያዉያን የምዕራቡን ዓለም የሚወዱት ባይሆኑም ጋዳፊን ለመጣል ግን ጠላቶቻችን ከሚሏቸዉ ምዕራባዉያን ጋር ተባብረዋል በመሀልም አርባ ዓመት ሙሉ ጋዳፊ ሲገነባዉ እና ሲያስገነባዉ የነበረው ነገር ሁሉ ወድሟል:: እኛም ከዚህ መማር ይገባናል::

እኛ ከተግባባንና ከተባበርን “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ነውና የማንመክተው ዉጫዊ ኃይል አይኖርም እርስ በእርስ መግባባት ካልቻልን ግን የሚያጠፋን ጠላታችን ሳይሆን የእርስ በእርስ ቅራኔአችን ይሆናል::

 

ከዘካሪያስ አሳዬ(edenasaye@yahoo.com)

 

7 Comments

 1. እነዚህሰዎች፡የሀገር፡አንድነትጉዳያቸዉሊሆንአይችልም፡ባህሪያቸዉም፡አይደለም፡የበታኝናአስበታኝ፡ዘቦች፡አባይደርግእንዳይሞክረዉምእራባዉያንናግብፆችየዛሬነፃወጭዎች፡የሀገራችንልማትነቀርሳነበሩ፡ዛሬደግሞአባይንለጥቂትናዘረኛ፡ስርአታቸዉገበናመሸፈኛሊያደርጉት፡ህዝቡንበመለያየትናበማግለልየሀገሪቱንአንድነትእንደመደራደሪያይዘዉታል፡”እኛከሌለንሀገሪቱ፡ትፈርሳለች”ይሉናል፡አባይከሚያስፈልገንበላይነፃነታችንንምአንደራደርበትም።

 2. Dear Zekarias, you raised defenses raised by Egypt itself! I don’t know some diasporas/e.g you and Abebe Gellaw/ are barking always “freedom before development”! It is immpossible (to you) to achieve both in one time!! Anyways try to be rational!!!

 3. ተስፍሽ!ራሳችሁን”ጥቂት”ግንብቸኛኢትዮ’ያዊ፡አደረጋችሁትሳእናንተ፡ለስልጣናችሁ፡ማቆያ፡የከፈታችሁትን፡ቀዳዳግብፆች፡ይጠቀሙበታል፡ክፍተትን፡ዝጉ፡ነዉ።የሀገርአንድነት፡የሚጠበቀዉሰብአዊናዲሞክራሲያዊመብቶች፡ሲከበሩ፡ነዉእንደአባትሻእቢያ”ባርነትወይምአባይ፡እያላችሁ፡ነዉይህ፡አካሄድ፡ለሀገሪቱምለዘረኛዉ፡ስርአታችሁ፡አይበጅምበአማርኛ”ነፃነትናልማትበአንድአይሳካም”ትሉናላችሁ፡ድንቋም፡ልማትወነፃነት፡ራስህምነፃ፡አይደለህ

 4. tesfayehu,
  Your so called ‘development’ is enriching people like your master and the ‘golden race’. What we got is contributing our hard earned money for your ‘development’ and corruption.

  We have seen here and there a development with out basic human right respect and fair wealth and power distribution will end up like seryia. have you seen what is happening in Brazil, Turky..? It is all about fairness!! It is like building your vila over sandy foundation.

  Fascist Italy have constructed much more roads and buildings in just 5 years!!!! Should we beg them to come back. We born FREE, we want to live FREE and die FREE. We are demanding our natural right.

  It is amazing to hear weyanes say ‘national’ We know what you did with Egypt and Shabia. negerugn bay

 5. This is my article except the first few paragraphs. U can check my status up date on face book @mastewal de almost a month before.What a robbery! I don’t think someone who fight for democracy should post someones work without his permission in their own name. If u had asked me, i have no reason to say no.

  Shame on u zehabesha!

 6. ወያኔዎች ናቹ በየዌብ ሳይቱ እየገባቹ ሰውን ሀሳብ የሚያስቱት ትክክለኛ ሀሳብ ነው ቅድሚያ ሰብኣዊነት ይቅደም

  ሞት ለወያኔ!!!!!!!!!

Comments are closed.

Previous Story

የአውሬ-አምባው ካድሬ ዳዊት ከበደ – (ከያሬድ አይቼህ)

Temam Ababulgu
Next Story

“የሙስሊሙን አቋም ወክለው የሚናገሩት የታሰሩት የእኔ ደንበኞች ናቸው” አቶ ተማም አባቡልጉ

Go toTop