June 18, 2013
7 mins read

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ደጋፊዎችን ልፋት፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አፈር ድሜ አስጋጠው

ከግርማ ደገፋ ገዳ (ጋዜጠኛ)
ደስ ይበልህ ፌዴሬሽን!
ሁሌም ውርደት የማያጣው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ዘንድሮም እንደለመደው አሳፋሪ ቅሌት ለመላ ኢትዮጵያ የስፖርት አድናቂ አከናነበ! ይህ እጅግ አሳፋሪ ነው! ሁሉ ነገር ከአፍሪካ አንደኛ የማለት ነገር ይቀናናል። ይህስ ከአፍሪካ ስንተኛ ውርደትና ቅሌት ነው? ለአውሮፕላን፣ ለሆቴል፣ ለማሊያ፣ ለጫማ፣ ለመከላከያ እና ለመሳሰሉት ነገሮች በሙሉ የወጣው ወጭ አፈር ድሜ ጋጠ! ከሁሉም በላይ የደጋፊዎች በዋጋ የማይተመን ድጋፍና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ስፖርት የላቀ ደረጃ ላይ ደርሶ ለማየት የመጓጓቱን ሕልም፤ የትም ቀበሩት። የፊፋን ሕግ አሳምረው በማያውቁና የተጫዋቾቻቸውን ሪከርድ መመዝገብ በማይችሉ ስግስብግ ግለሰቦች የተሞላው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የሀገራችንን ስፖርት በቁሙ ቀበረው። በደስታ ብዛት መኪና ላይ ሲፎልሉ የነበሩ ወጣቶችን የጫነ መኪና ሲገለበጥ፣ ለሞቱ ዜጎችም አንዱ ምክንያት በእግር ኳሱ የተገኘው ድል ነበር። በስንት ድካም የተገኘው ነጥብ ለቦትስዋና የሚሰጥ ከሆነ፣ ለፌዴሬሽኑ ሰዎች ዳንኪራ ሆነ ማለት ነው፤ ለደጋፊዎች ግን ለቅሶ! እንግዲህ ስፖርት አፍቃሪ ምን ይሻልሃል? ከወደ ኋላ ሆኖ ወጥሮ የሚይዘው አስራት ባልቻ እና የሚያቀብላቸው ኳሶች በሙሉ ቁም ነገር ላይ የሚደርሱለት እድለኛው አዲስ ህንጻ፣ ያ ሁሉ ትግላቸውን፤ የፌዴረሽን ጅብ በላው!
ደስ ይበልህ ፌዴሬሽን!

በዚህ ዙሪያ የመንግስት ሚድያዎች ዘገባ የሚከተለው ነው፦
ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምንያህል ተሾመ ሁለት ቢጫ ካርድ አይቶ ሳለ ሰኔ 1/2005 ከቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ጋር በተደረገው ጨዋታ መሰለፉ ስህተት እንደሆነ አመነ፡፡

ፌዴሬሽኑ ብሄራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ከመጫወቱ በፊት ችግር ስለመፈጠሩ ፊፋ አሳውቆት እንደነበር ገልጿል፡፡

ሆኖም ይህ ችግር በቡድኑ ተጫዋቾችና በደጋፊዎች ላይ ያልተፈለገ የመንፈስ ጫና እንዳይፈጥር በመስጋት መረጃውን ይፋ ሳያደርግ ቆይቷል፡፡

ፌዴሬሽኑ በፈጠረው ችግር ዙሪያ ዛሬ ሰኔ 11/2005 ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ መሰረት ፊፋ ተጫዋቹ ሁለት ቢጫ ካርድ በማየቱ የተነሳ ከቦትስዋና ጋር በተካሄደው ጨዋታ እንዳይሰለፍ የሚገልፅ ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑ ልኳል፡፡ ይሁንና የፌዴሬሽኑ አመራሮችና አሰልጣኝ ይህን የፊፋ ውሳኔ በመዘንጋታቸው ተጨዋቹን አሰልፈውታል፡፡

የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለችግሩ ተጠያቂ ያላቸውን ግለሰቦች ዝርዝርም ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ መሰረት የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንትና የብሄራዊ ቡድኑ ቡድን መሪ አቶ ብርሀኑ ከበደ፣ ዋና አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው፣ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ፣ የቡድኑ ተጨዋች ምንያህል ተሾመ፣ የስራ አስፈፃሚ አባልናየቡድን መሪ የነበሩ አቶ አፈወርቅ አየለ እና የፌደሬሽን ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አሸናፊ እጅጉ በጥፋተኝነት ተፈርጀዋል፡፡

በፊፋ ህግ መሰረት ተገቢ ያልሆነ ተጨዋችን ማሰለፍ በጨዋታው የተገኘውን ነጥብ የሚያሳጣና ተጨማሪ የገንዘብ ቅጣትም የሚያስጥል ነው፡፡

በዚህመሰረትም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 3 ነጥብና 6 ሺህ ስዊስ ፍራንክ እንደሚቀጣ ፊፋ ያስታወቀ ሲሆን በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን እስከ ሰኔ 14/2005 ዓ/ም ምላሽ እንዲሰጥም በፃፈው ደብዳቤ አስታቋል፡፡

አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው በተፈጠረው ስህተት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው ጳጉሜ 2/2005 ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ጋር ለሚካሄደው ጨዋታ ከወዲሁ መዘጋጀት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ጨዋታ አሸንፈን ወደ መጨረሻው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ እንደምናልፍ እርግጠኛ ነኝ ብለዋል አሰልጣኙ፡፡ለዚህም የቡድኑ አባላት ዝግጁ መሆናቸውን አሰልጣኙ አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ሳህሉ ገብረወልድ በበክላቸው በአሰራር ክፍተት የተፈጠረው ችግር አሳዛኝና ሊከሰት የማይገባው ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፌደረሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጥፋተኞቹ ተገቢውን ቅጣት ማግኘት እንደሚገባቸው የተስማማ መሆኑን በመግለፅ በአጭር ጊዜ ውስጥ የቅጣት ውሳኔውን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ በተፈጠረው ችግር ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማው ገልፆ ለኢትዮጵያ ህዝቦችም ይቅርታ ጠይቋል፡፡

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop