June 18, 2013
1 min read

አስገደ ገ/ስላሴ ለህክምና አሜሪካ ገቡ

Asegd2
አቶ አሰገደ ገ/ሥላሴ
(ፎቶ – ኢትዮሚድያ)
አስገደ ገ/ስላሴ ለህክምና አሜሪካ ገቡ 1

የታቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል ሆነው በፖለቲካ አቋማቸው ብቻ ሁለቱ ልጆቻቸው ያላንዳች ጥፋት እስርቤት መወርወራቸውን አይተው በቅርቡ ለኢትዮጵያ ህዝብ “ይግባኝ” ያሉት አቶ አስገደ ገ/ስላሴ ታመው ለህክምና አሜሪካ ገብተዋል።
አቶ አስገደ በአሁኑ ጊዜ በጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል እየታከሙ ይገኛሉ። አሕፈሮም አስገደ የተባለው ልጃቸው ደግሞ መቀሌ በሚገኘው ቀዳማይ ወያኔ ፖሊስ ጣብያ ታስሮ ይገኛል። ወጣቱ አሕፈሮም “ዳኛው የሉም” እየተባለ የዋስ መብቱን አስጠብቆ ሊወጣ ባለመቻሉ እዛው ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰረ 54 ቀናትን ቆጥሯል።
በእስር ቤት ሲማቅቅ ቆይቶ ያላንዳች ክስ የተለቀቀው የማነ አስገደ ደግሞ እስርቤት ባደረበት ህመም 22 ቀን ሆስፒታል ከተኛ በኋላ በአሁኑ ጊዜ በቤቱ የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ይገኛል።
አቶ አስገደ ሆስፒታል መግባታቸውን ያወቁ ኢትዮጵያውያን ገሚሶቹ በአካል፣ ሌሎቹም በኢሜይልና በስልክ በጎ ምኞታቸውን እና የትግል አጋርነታቸውን ገልጸውላቸዋል።

 

3 Comments

  1. አቶ አስገደ ስለ ህወሓት ግፍ ብዙ ጽፈዋል። ልጃቸው ቶርቸር ተደርጓል ብለዋል። ስለ “ባዶ ስድስት” ነግረውናል። እነ መለስ ስለፈጸሙት ዝርፍያ፣ በመለስ ቀብር ምክንያት የዓለምን ሕዝብ እንዴት እንዳታለሉ፣ ወዘተ በሰፊው ነግረውናል። አሁን የሚያስፈልገው ይህንኑ ጉዳይ በዝርዝር ለቪኦኤ ራዲዮ እንግሊዝኛ ፕሮግራም፣ ለሂዩመን ራይትስ፣ ለአምነስቲ፣ ለኒውዮርክ ታይምስ ወዘተ ቃለ ምልልስ መስጠት ይኖርባቸዋል። ለሐበሾች ይህን ማስረዳት ምንም ፋይዳ የለውም። የምናውቀውን የምናየውን መልሶ ለኛ መንገር አስፈላጊ አይደለም። ሊያውቅ የሚገባው እንግሊዝኛ ተናጋሪው የዓለም ሕዝብ ነው። የመለስንና ይመራ የነበረውን መንግሥት አውሬነት ማስረዳት ነው። በሕዝብ ዘንድ የሚሰበሰበው እርዳታ እንደሚዘረፍ የዓይን ምስክር መስጠት ነው። ይህ ካልሆነ እስካሁን አስገደና አብርሃ የተባለው የሚጽፉት እንዲሁም ኢትዮሚድያ የሚያስተጋባው ሁሉ “ትግራይ አልተጠቀመም፣ እንደ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በደል ደርሶበታል” ለማሰኘት ብቻ ነው፤ ውሸት ነው።

  2. Why you waste your time to write such nonsense and hatred article idiot? Your kind of article was aired before weeks by your Moresh party lead by Tekle Yeshaw. Asgede and Abraha have done their shares as an Ethiopian. Ethiomedia is also an Ethiopian Website where many Ethiopians exercise their views and thoughts for years even though the owner of it is a Tigrean Ethiopian. Abraha Desta and Asgede are using the Amharic language to write their article to reach their message to Ethiopians. So, why they need to write in English where it’s a foreign language? It’s time to stand in unison, then, such a narrow minded and divisive thinking is not fruitful.

    • Michael, so why are you writing in English? I don’t know what Moresh party are you talking about? I am afraid you are mistaking me for somebody else. Can’t you even guess who I am from my name? All I am saying is this: Asgede, Abraha and Ethiomedia should let the world know the atrocities of Woyane by writing in English. In fact Asgede should give interviews to VOA, NYT and such while in Washington, DC. What is wrong with that? Ethiopians already know what Woyane is doing so there is little use in writing in Amharic. Let us stand as one to expose Woyane!

Comments are closed.

Previous Story

የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ እና ለስልጣን ጸብ ጫሪው ህውሃት! ግርማ ሞገስ

Next Story

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ደጋፊዎችን ልፋት፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አፈር ድሜ አስጋጠው

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop