ያልመከተ ተፈነከተ፤ ያልተደራጀ ተፈጀ። – ጌታቸው ኃይሌ

ጌታቸው ኃይሌ

አንዱን የዘመናችንን ትልቁን ብሔራዊ ችግር ለመፍታት ያስችል የመሰለኝን ሐሳብ ከጥቂት ቀናት በፊት “በኢትዮጵያ ሰላም የሚያመጣ የአማራ የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት ያስፈልጋል” በሚል ርእስ አንድ ጽሑፍ በ ethiomedia ለሕዝብ አቅርቤ ነበር። በጽሑፉ ጥቂት ሰዎች የተወያዩበትን ወዳጆች ልከውልኝ አነበብኩት። በስልክ ያወያዩኝም አሉ። ትችቶቹን ሁሉ ስላላየኋቸው ይሆናል እንጂ፥ ያየኋቸውን ሳጠናቸው፥ ከዶክተር ፀሐይ ብርሃነ መስቀል በቀር ፍሬ ነገሩ ላይ ያተኮረ ሐሳብ የሰጠ አላጋጠመኝም።

የተቺዎችን ቀልብ የማረከው “አማራ የሚባል ሕዝብ አለ ወይስ የለም?” የሚለው ነው። ይኸንን መተቸት ደስ ይላል መሰለኝ፥ ተተችቶ ባለቀ በስንት ዓመቱ፥ ትችቱ እንዲያገረሽበት ጽሑፌ ምክንያት ሆነ። እኔ ግን ጽሑፌን የደመደምኩት እንዲህ ብየ ነበር፤

ለዚህ ድርሰት አስፈላጊነቱ ስላልታየኝ፥ “አማራ ማነው?” ከሚል፥ መልሱ ብዙ ገጽ ከሚፈጅ ጥያቄ ውስጥ አልገባሁም። ሁሉም ራሱን ስለሚያውቅ፥ “አማራ ነኝ” የሚል ሁሉ በሙሉ አባልነት፥ በድርጅቱ የዕርቅና የሰላም ዓላማ የሚያምን፥ ግን “አማራ ነኝ” የማይል ኢትዮጵያዊ ደግሞ በደጋፊ አባልነት መመዝገብ ይችላል።

እንዲህ ያልኩት መተቸቱ ተስኖኝ አይደለም። እንዲያውም ካሁን በፊት ማስረጃ እየሰጠሁ በሰፊው እንደተቸሁት የሚያስታውስ አይጠፋም። አሁን እንደገና ያልተቸሁት፥ ታኝኮ የተዋጠን በማመስኳት፥ የኔንም የአንባቢውንም ጊዜ ላለማጥፋት መርጬ ነበር። “አማራ አለ” የሚሉም “አማራ የለም” የሚሉም፥ እንደየመነሻቸው ተቀባይነት ያለው ምክንያት አላቸው። በዘር ከሄድን የዘመን ብዛት ስላዳቀለን፥ ዛሬ አማራ የሚባል ዘር አለ ለማለት አይቻልም፤ የለም። በባህል ከሄድን ግን አለ። አማራ ከማለት አማርኛ ተናጋሪ ማለት የሚመረጠውም ስለዚህ ነው። ይህ የባህል ሕዝብ ለመኖሩ ማስረጃው ቀላል ነው፤

አንደኛ፥ “አማራ ነን” የሚሉ ሰዎች አሉ። “አማራ አይደላችሁም” ብንላቸው ግራ ይጋቡና፥ “ታዲያ ምን ልታደርጉን ነው፤ ዶርዜ፥ ወይስ እስላም?” ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንድት አጭር መልእክት ለአቶ አብይ አህመድ (እውነቱ ቢሆን)

ሁለተኛ፥ ብዙ ሰዎች “አማራ ናችሁ” ተብለው ተገድለዋል፥ ከሀገራቸው ተፈናቅለዋል፥ ንብረታቸው ተዘርፏል። “አማራ አይደላችሁም” የተባሉ ጎረቤቶቻቸው፥ ወይም በአውቶቡስ ላይ አብረዋቸው የተቀመጡ ተሳፋሪዎች ግን አማሮች አይዶሉም ተብለው ድነዋል።

ሦስተኛ፥ በየዘመኑ የሚደረገው የሕዝብ ቈጠራ ሕዝቡን በጎሳ ሲመድብ አማራውን የለህም ብሎ አልዘለለውም። የአማራው ቍጥር መቀነሱን ያወቅነው፥ በቈጠራው አማካይነት ነው። ቈጣሪዎቹ በዚህ መንገድ መሄዳቸው ተሳስተዋል እንዳንል፥ በማንም አገር የሚደረግ ነው። አሜሪካ ረዘም ያለ ጊዜ እየኖረ፥ ይኸንን ልምድ ያልደረሰበት ያለ አይመስለኝም።

አራተኛ፥ አንድ ቋንቋ ለሌለ ነገር ስም አያወጣም፤ “አማራ” የሚል ቃል ወይም መጠሪያ ስም በቋንቋችን ውስጥ ካለ፥ በዚያ ስም ተጠሪ ሕዝብ አለ ማለት ነው።

አምስተኛ፥ “ኢትዮጵያውያንን በዘር መከፋፈል ይሆናል” ተብሎ ቀረ እንጂ፥ የቀድሞ መታወቂያ ደብተር ላይ “ዘር” የሚል መሥመር ነበረበት፤ ያለምክንያት አልነበረም። ምንጮቹ “ቤተ አምሐራ” ይሏቸዋል።

ግን አንድ እውነታ አለ። አማራው (ወይም አማርኛ ተናጋሪው) ራሱን እንዳንድ የተለየ ሕዝብ ቈጥሮ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ራሱን አላገለለም። ማለት፥ አንድነቱ በኢትዮጵያዊነቱ ነው እንጂ በአማራነቱ ላይ አይደለም። በሀገር ጉዳይ ላይ ጎሳ ሳይለይ ከሁሉም ጋር አብሮ ይሠራል። እንዲቀጥልበት ማበረታታት የሁላችን ግዴታ ነው። ግን ጥቃትን ለመከላከል መጠራራትና ዘዴ መፍጠር እንኳን በሰዎች በእንስሳት ዘንድም ያለ ነገር ነው። እንድ ኢትዮጵያዊ፥ “አማራ ነህ” እየተባለ ሲጨፈጨፍና ማንም ሰው ሳይደርስለት ዝም ብሎ ይታይ ወይ? ሌላው ቢቀር “ነግ በኔ” አይደለም ወይ? የሚል ጥያቄ ተነሥቷል። ጥያቄው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? አማርኛ ተናጋሪው እንዳይደርስለት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ተለይቶ የአማራ ወገን መፍጠር ሆነበት። ምን ይሻላል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ስራ አጥነት -የመንግስት ትልቁ ፈተና (አሸናፊ በሪሁን)

ለዚህ መልስ ሳሰላስል ችግሩ በተለይ የአማራው ሕዝብ ሳይሆን የሀገሪቷ ሆኖ ታየኝ። አገሪቷ አማርኛ ተናጋሪውን በጎሳዎች የሚያስጠላ ጠላት (ጸላኤ ሠናያት የሚባለው ሰይጣን) ገብቶባታል። ስለዚህ የጥላቻውን ምንጭና ምንጩን መድፈኛ ዘዴ ወደመፈለግ ሄድኩት። ምንጩ ወያኔ ብዙዎቹን ጎሳዎች በአማራው ላይ በጠላትነት ማስነሣቱ፥ መፍትሔው ደግሞ፥ “በኢትዮጵያ ሰላም የሚያመጣ የአማራ የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት” መሆኑን ለሕዝብ አቀረብኩ። ከአንባቢዎቼ የጠበቅሁት፥ ሐሳቡ የማያዋጣ ከመሰላቸው፥ ምክንያት ሰጥቶ ውድቅ ማድረግ፤ የሚያዋጣ ከሆነ፥ ተከታትለነው ከዚህ ትልቅ ብሔራዊ በሽታ እንፈወስ የሚል ነበር። ሰው ግን የጽሑፌን ቁም ነገር ወደጎን ትቶ፥ የሚያውቀውን ለመናገርና ብሶቱን ለመተንፈሻ አጋጣሚ አደረገብኝ። (1) አማራ አለ፤ (2) አማራ የለም፤ (3) አማራ በዘር መዘጋጀት የለበትም ለማለት ብዕር መዘዛ መጣ። ግን ሦስቱም የጽሑፌ የኅዳግ ነጥቦች እንጂ አስኳሎች አይደሉም።

ዶክተር ፀሐይ ብርሃነ መስቀል ብቻ የዕርቅ ድርጅ የማቋቋሙን ሐሳብ ደግፋ፥ ድርጅቱ በአካባቢ (regional) ቢሆን ይሻላል የሚል አማራጭ አቅርባለች። ግን ሐሳቧ የችግሩን መንሥኤ ይስታል። የተከሰሰው በአንድ አካባቢ ያለ ሕዝብ ሳይሆን፥ አማራው ተለይቶ ነው።

ሌላ ወዳጄ፥ በድርጅቱ ውስጥ አማራ ያልሆኑ ቢገቡበትስ የሚል ሐሳብ አቀረበልኝ። ይኸም የችግሩን መንሥኤ ይስታል። የተከሰሰው አማራው ተለይቶ ነው። ሌሎች እንደ አማራው ተከስሰው እንደ አማራው አልተጨፈጨፉም። ጽሑፌ ያተኮረው ወያኔ በሚያጠቃው ላይ ሳይሆን፥ ወያኔ በሚያስጠቃው ላይ ነው።

ፕሮፌሰር ሀብተ ጊዮርጊስ በዘር መደራጀትን (ከሞተበት) አናስነሣው የሚል ተማፅኖ አቀረበ። ጽሑፌን ባይጠቅስም የተማፀነው የኔ ሐሳብ ተቀባይነት እንዳያገኝ መሆኑ ግልጽ ነው። ይህን ጽሑፍ ያረቀቅሁት የሱን ጽሑፍ ስላየሁ ነው። የምናካሂደው ውይይት ሀገር የሚጠቅም መፍትሔ ለማግኘት ስለሆነ፥ ስሜትን ገታ አድርገን ከተወያየን፥ ልንግባባ እንዲያውም ከአንዳች ስምምነት ላይ ልንደርስ እንችላለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአቶ ሙሼ ትንታኔ - በዘንድሮ ምርጫና በምርጫ ሥርዓቱ ዙሪያ

የፕሮፌሰር ሀብተ ጊዮርጊስ ተማፅኖ እንደገባኝ፥ በጎሳ ከመደራጀት በዲሞክራሲ ላይ የተመሠረቱ ሥራዎች እንሥራ የሚል ነው። የዕርቅ ድርጅት ማቋቋምና በዲሞክራሲ ላይ የተመሠረቱ ሥራዎችን መሥራት ሲስማሙ እንጂ ሲጋጩ አይታየኝም። ልብ አላልነውም ይሆናል እንጂ፥ በባህል መደራጀት ከሰው ልጅ ጋር አብሮ የተፈጠረ ነው። ለምሳሌ፥ ክርስቲያኖች በሃይማኖት ተደራጅተው ከፓርትያርክ (ከፖፕ) እስከ ዲያቆን የራሳቸው አስተዳዳሪዎችና አገልጋዮች አሏቸው። ከዚያም አልፎ፥ የዓለም-አቀፍ አብያተ ክርስቲያን ማኅበር አለ። ሙስሊሞችም ተመሳሳይ ድርጅት አላቸው። የአንድ ሰፈር ሰዎች እድር አላቸው። የነጋዴዎች ምክር ቤት አለ። በዓለም ላይ በሚደርስ ድንገተኛ አደጋ ለሚጎዱ ችግረኞች ፈጥነው የሚደርሱላቸው እንደ ቀይ መስቀል ያሉ የክርስቲያኖች የተራድኦ ድርጅቶች ናቸው። ዕርቅና ሰላም ለማምጣት አማሮችን ማደራጀት የሚኮነን ከሆነ፥ መጀመሪያ እነዚህ ድርጅቶች መኮነን፥ ቤተ ጸሎቶችም መዘጋት አለባቸው።

ዲሞክራሲ ያወጀልን ትልቁ ፍልስፍና ሰዎች ዘርንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ የፖለቲካ ፓርቲ እንዳያቋቁሙ በሕግ መከልከልን ነው። ጽሑፌን የደመደምኩትም፥ በአንድ ሀገር ውስጥ የሚቋቋም የፖለቲካ ፓርቲ መሠረት የሚያደርገው ሁሉን እኩል አብሮ በሚያሳድግ የኢኮኖሚ ፍልስፍና ላይ ነው፤ ሕዝብን በዘርና በባህል የሚከፋፍል ድርጅት ግን “በሕግ መከልከል፥ መኰነንም አለበት። ለመረዳዳት፥ ከዚያም አልፎ ሌሎችን ለመርዳት ከሆነ ግን፥ በሕግ መፈቀድ፥ መደገፍም አለበት” በማለት ነው። እባብ ያየ ልጥ ቢያይ በራየ፤ የጎሳ ድርጅትን ጉዳት ያየ የተራድኦና የዕርቅ ድርጅትን ቢያይ በራየ ሆኖ ነው እንጂ፥ ድርጅቱ ስሕተት ኖሮበት አይደለም። ያልመከተ ተፈነከተ፤ ያልተደራጀ ተፈጀ የምለው ኢትዮጵያን ነው።

 

13 Comments

  1. A real ethiopian and hero just to say he is professor getache hail.my respect to you is,as high as professor mesfin weldemariam,professor asrat weldeyes.these and other well respected ethiopians.i give them undevided attention.as a matter of fact i like their any thing they said about ethiopia.thank. you.

  2. Professor getachew haile,ebakiwotin ayiselichu bizu gize temarina asitemari mahal alemegibabat sinor,mefitihew kememihiru enji ketemari ayidelem,erso ledekemubet leloch waga basetu enkuan,kesir yalewin yene bite yerso,number one degafi alena!

  3. ጋሽ ነጋሶ ጊዳዳ(እንድያ ያልኮዎት እሳቸውን ስለሚመስሉኝ ነው ደሞም በ ስጋ ይዛመዳሉና)
    ያስታውሳሉ ወያነ ወደ ስልጣን የመጣ ሰሞን የጣፉትን መልክት? ልምን ተረሳዎት? እና በዛ መልክት የ ፖለቲካ ፕሮፖጋንዳዎን ሲደሰኩሩ በ አማራ ነት መደራጀት እንደማያስፈልግ ሲስብኩ ነበር! እረ እንደውም ያገሮዎትን(የ ሸዋ) ሰዎች አማራ እንዳልሆኑ እና በ አንድ ወቅት ሌላ ቁዋንቁዋ እንደሚናገር እና አማራ እንዳልሆኑም ተናግረዋል! ያ ትክክል ነው ሸዋ ብሎ አማራ ያው ሲጠመቁ አማራ የሆኑ አርገው እራሳቸውን በመቁጠራቸው አማራ የሆኑ ይመስላቸዋል! እንዳሉት እምነቱን(ይህ አሁን ያለው የክርስትና እምነት አማራነትን የካደ ወይም በ እጅጉኑ አንሸዋሮ ትቂት ነገሮችን ከ አማራነት የወረሰ የ ሮማውያን አህዛብ ድቅል ስራ እንደሆነ ይወቁ) እና ቁዋንቅዋውን ስለተናገሩ አማራ ናቸው አያስብላቸውም! እርሶውም አይደሉም እናም አይዘላብዱ!
    ሌላው በ እዛን ወቅት በ ጣፋችሁት ፕሮፖጋንዳ አማራ ካለ ያለውም ወሎ ውስጥ ነ ብለዋል. ያም ትክክል ነው! ይህም ጠሃፊ ከዝያው ነው እና አልጠፋንም እርሶና ይገነቡዋት የነበረችው የ ባቢሎኖዋ ኢትዮጵያ አፍርሰን የ እያንዳንዱ ነገድ ሃገር አድርገናታል! እንደዛም ሆና ታብባለች! እርሶውም ወደ ነገደዎ ወደ ኦሮሞ ወንድሞችዎ ይቀላቀሉ! የ አማራን ስም መያዝ, በ ሮማውያን አህዛብ ፍልስፍና በተዳቀለው እምነታቹ(አማራነት የሌለው) አማራ መሆን አይቻል! አማራ ዘር አለው ነገድ አለው! እርሶዎ ላያቁት ይችላል ወሎዮች ግን እናውቃለን እና ያን ቆሻሻ ስራችሁን ታቅፋቹ ከ አማራ ራስ ላይ ራሳችሁን እንደቲማቲም አንከባላቹ አግልሉ! በተረፈ አምላክ ስራዎት አውቆ ነው እንዲ በ ዊልቸር ላይ አስሮ ያስቀመጠዎት!
    በ አንድ ወቅት ሄኖክ የሽጥላ በ ገጠመው በቅሎ ግጥም ላይ የ ሸዋን ሰዎች የ ነገር ትብታብ ሲል ወርፎዋቸው ነበር የገባኝ እየዋለ ሲያድር, ታሪክን ስመረምር ነው እና ያ አሁን አብቅትዋል! የ ታሪኩ ባለቤት አሉ እና እርሶ ስለ አማራው ቅንጣት ያህል አያገባዎትም!

  4. ፕሮፌሰር፡

    እንደዚህ አይነት መርዝ ከሚረጩ ምን አለበት ለአገርና ለህዝብ አንድነት ሲሉ ዝም ብለው አርፈው ቢቀመጡ

  5. አድናቂዎት ነኝ ለችግሩ መፍትሕሄ እንደመፍለግ ክፉልምድ ሁኖብን ዳር ዳሩን መቆፍር ችግሩን በምንመንገድ ማክሽፍ ይቻላል ብሎ ከመወያየት ይልቅ ችግር ያመታውን አካል ብቻ በመተችት ግዝየ ማጥፍት አንድ ጥያቄ ላንሳ አማራ በድሎሃል ለተባለ ጎሳ እኔ አልበድልኩም ክበደልኩም ቅሬታ ካለ በገለልተኝአ ድርጅት በደሉን አጥንቶ ክበደልኩ እክሳልሁ ከተበደልኩ እካሳለሁ የሚል ተደራጅቶ ራሱን የሚከላክል የአማራ ድርጅት ያስፍልጋል የ ጎንድር አማራ የጎጃም አማራ የወሎ አማራ የሽዋ አማራ ሳይል ካልሆነ ባለቤት እንደለለው ከተማ ያም ያም ተነስቶ ለስልጥአን መያዥያ ዳርንጎት ነው የሚያደርገን ስለዚህ እንደራጅ ንጽሕናችን እናስመስክር ለክርክር ግዚየ የለም የአማራ አለመደራጀት ለወያነ ጉልበት ነው በመርህ ደረጃ መደረግ ያለበት አማራ ራስህን አድን ሌላውንም ታደግ እናመሰግናለን ፕሮፍሰር

  6. ዶርዜ (እስላም) መሆን አማራ መሆን ና አለመሆን ጋር ምን ያግናኘዋል ? የሰውን እምነት ማሳነስ ;ማነትንስ ማንቅዋሸሽ ለአማራ አንድነት ምን ይጠቅማል ?መዳፈር አይሁንብኝ እና ጌታቸው ሀይሌ ስለ ህዝብና ሀገር አንድነት ከመስበኩ በፊት ከአስተሳሰቡ ጋር መታረቅ ይገባዋል : ለአማራው ‘በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ’ የሆነበት እና ስቃዩን ያበዙበት የሻገተው አስተሳሰብና አቀንቃኞቹ ናቸው።

  7. ወተት መግፋት ቅቤን ያወጣል ፡ አፍንጫንም መጭመቅ ደምን ያወጣል ፡ እንዲሁም ቊጣን መጐተት ጠብን ያወጣል ። ምሳሌ30:32 ……ያልመከተ ተፈነከተ ፤ ያልተደራጀ ተፈጀ ፡ እሕሕ… አንዳትፈነከት እንዳትፈናቀል እንዳትታሰር እንዳትፈጅ በአማራነትሕ ተስተናገድ ለሌላ ጦስሕ እንዳይተርፍ አንተ ጎሳ አድምጥ እያሉ ነዉ ! ኢትዮጵያዊ ነኝ ሳትል ! ይህ የምርጫ ወቅት አስጊም ስለሆነ እስቲ ሰብሰብ ብላችሁ በመንደርና በቡድን አመለካከት ልናስታርቅሕ ቂም የያዙብህ ስላሉ እባካችሁ ለናንተ ጥቅም እያሉ እየተቆጩ ይማፀናሉ ወይ ጉድ ለዚህ ቢፈጁት አላልቅ ያለ ፍሬም እንዳያፈራ በመርፌም ሁሉን ማህፀን ለማድረቅ ያልተቻለዉን አሁን በምን እንጨብጠዉ አማራ የሚባል የለም ብንል ግንዱን ያዉቃል ! ደግሞ እኮ ስም አዉጡልኝ ብሉ ክልል መስተዳድር ወይ ፌዴራል አልሄደ ? እንደዉ ጉድ እኮ ነዉ ጆሮ አይሰማ የለ… አርፎ የተቀመጠን ህዝብ መነካካት… ማጠፊያዉ አጠረባቸዉ መሰል ? ወይ የትግሬ ወያኔዎች ያሳዝናል ? (አቦይ) ጌታቸዉ ኃይለ ሃገሪቱ ወዴት እየሄደች እንደሆነ ያዉቁ ይሆን ? አይመስለኝም ? በዕድሜ ያረጁ ጠቢባን አይደሉም ! ሽማግሌዎችም ፍርድን አያስተዉሉም ይላል ቃሉ ። ኢዮብ 32:9… ስለዚህ እ/ር ማስተዋልን ይስጥህ !!

  8. You and your elite are active moral pankruptcy; give a chance to the new generation; keep your prof/Dr. titls in your bedroom. You failed from Church to politice so keep quite. You are just another Minlike an Zenawi of divide and rule mentality.
    Lemalimo

  9. የተከበሩ ፕሮፌሰር አዛውንት ኢትዮጵያዊነትዎ፡ ምሁርነትዎ ፡ የምንቀበለውና የምናከብርዎት ለጋራ ኢትዮጵያ ልጆች ሲያስቡና ሲንገበገቡ እንጂ ለያይቶ የሚያፋጅ ጽሁፍ ደጋግመው ሲረጩ አይደለም። እንዲያው አንዴ እንኳ ስለ ኦሮሞ ልጆች በወያኔ ስለሚደርስባቸው ግፍና መከራ፤ ስለእስላም ወገኖቻችን የወቅቱ የሀይማኖት ነጻነት አፈና ችግር አብረው ካማርኛ ተናጋሪው ችግር ጋር አብረው የሌላውንም ኢትዮጰያዊ መከራ ጠቅለል አድርገው ቢጽፉ ይበጃል እንጂ አጻጻፍዎ ከፋፍሎ የማፋጀት መልእክት ይመስላል ። የተማራችሁት ባሳችሁሳ !

  10. ይሄማ የተቀደሰ ሀሳብ ኘሮፌሰር፡፡ ፍቅራችንና አብሮነት አንድነታችን የሚመልስ መሬት ላይ ሊዎርድ የሚችል የመፍትሄ ሀሳብ ያሰፈልጋ፡፡አያቶቻችን ተከፋፍለው ሳይሆን አንድ ሆነው ነው ከጠላት ወረራ ጠብቀው ባለም አቀፍ በለውብ ታሪክ ሀገር የስረከቡን፡፡ዛሬ አለም በሰለጠነበት በ21ኛው ክለዘመን አንዳንዶች ለግል መሣሪያቸው ሊያደርጉን እደጋሪ ፈረስ ሲጎትቱን መከተላችን የግሪኩን ፈላስፋ ያስታውሰኛል ፡፡” ሰው ከንስሳ የሚለየው በማሰቡ ነው የሚለው ሳይሆን፡ሰው ከሰው የሚለየው በማሰብ ነው” ይላል፡፡እኛም እባካችሁ በሰከነ እና በቀና አእምሮ ያለንበትን ሁኔታ እናጢነው እና ለኢትዮጵያችን በጋራ እንቁምላት፡፡እውነት መናገር ባንችል እንኳ የውሽት ምስክር መሆናችንን እናቁም እላለሁ( ፨፡፡

Comments are closed.

Share