Hiber Radio: የስዬ አብርሃ ወንድም ዳግም በሙስና ታሰረ

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ!
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ግንቦት 4 ቀን 2005 ፕሮግራም
<<አቶ መለስ ግፈኛ መሪ ነበር።የዚህ ግፈኛ ልደቱ ሊከበርለት አይገባም ብለን ተቃውመናል።የአማራው፣የጋምቤላው፣የአፋሩ መፈናቀል የዚህ ሁሉ ቀውስ መነሻው መለስ ዜናዊ ነው።ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅም ሽማግሌነኝ ሲል ቆይቶ ከስርዓቱ ጋር ያለውን ወዳጅነት ልደቱን ኤምባሲ ሊያከብር ሲመጣ አግኝተነዋል። ይሄ ሰው ገለልተኛ ሽማግሌ አይደለም ።ወገንተኛ ነው ተቃውመነዋል. . .>> አቶ መስፍን (በዲሲ የአቶ መለስን ልደት ሊከበር አይገባም ያለውን ተቃውሞ ካስተባበረው ግብረ ሀይል አስተባባሪዎች አንዱ ለህብር ከሰጡት)
<<እኔ ትግሬ አይደለሁም ወልቃይት ሰሜን ጎንደር ነኝ።ወልቃይት ትግሬ የተባለው በወያኔ ዘመን በግድ ነው።ወያኔ ሲወገድ የወልቃይት ትግሬነት ያበቃል። እዚህ የመጣሁት መለስ ዜናዊ የተወለደበት ቀን የተረገመ ነው ሊዘከር አይገባም ብዬ ነው...>> ከሰልፈኞቹ አንዱ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<<ተስፋ አልቆርጥም !>> ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከቃሊቲ የጻፈው ደብዳቤን ተርጉመን ይዘናል
<<የግራዚያኒን ሐውልት መሰራት የሚደግፉት የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር በቅሌት ስልጣን ለቀዋል።አሁን አዲስ ስልጣን ላይ የወጡት ግራዚያኒን የሚቃወሙ ናቸው።መታሰቢያው በቆመበት አውራጃ የተሾሙት አዲስ ሰውም ግራዚያኒን ይቃወማሉ ይሄ ለእኛ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ሐውልቱ እንዲፈርስ ወይ ስሙ እንዲቀየር መታሰቢያ እንዳይኖረው የምናደርገው ተቃውሞ ሰሚ እያገኘ ነው።የአውሮፓ ሕብረት ለላክንለት ደብዳቤ ምላሽ ሰጥቶናል ...>>
አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የግራዚያኒ ሐውልት እንዲፈርስ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ የሚያስተባብረው ግብረ ሀይል ቦርድ ም/ሰብሳቢ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
ሌሎች ቃለ መጠይቆች አሉን
ዜናዎቻችን-
– የስዬ አብርሃ ወንድምን ጨምሮ ከሙስና ጋር በተያያዝ የተጠረጠሩ 16 ከፍትኛ ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች ታሰሩ
– አገሪቱ በእስር አመታታ ውስጥ ከ11 ቤሌዮን ዶላር በላይ አጥታለች
– ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በሙስና ተጠርጥረው ስለታሰሩት እንዳይጽፍ በደህንነቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጠው
– ለአጼ ሀይለስላሴ ሐውልት ሊቆም ይገባል ሲሉ ፕ/ር ግርማ ወ/ጊዮርጊስን ጨምሮ ታዋቂ ሰዎች የፈረሙበት ጥያቄ ለሀይለማሪያም ደሳለኝ ቀረበ
– ለአቶ መለስ ልደት ሊከበር አይገባም ያሉ ኢትዮጵያውያን ዋሽንግተን ኤምባሲ ፊት ለፊት ተቃውኦ አደረጉ
* ፕ/ር ኤፍሬም ይስሐቅ ልደቱን ለማክበር ከመጡ የስርዓቱ ደጋፊዎች መካከል ነበሩ
– አቶ ሃይልማሪያም ደሳልኝ የፍትህ ሜኔስትራችውን አባረሩ እርምጃው ከአማራ ተወላጆች የዘር ማጽዳት ዘመቻ ጋር ያያዙት ወገኖች አሉ
– በኢትዮ ኬኒያ ድንበር ላይ በተቀሰቀሰ የጎሳዎች ግጭት 8 ሰዎች ሞቱ
– በቬጋስ በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ የፍሪያስ አሽከርካሪዎች ለገቨርነሩ ድምጻቸውን ለማሰማት
ሌሎችም ዜናዎች አሉን

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን አሉ
Share