የናዝሬት ጉምሩክ የህግ ማስከበር ኃላፊ አቶ ተመስገን ጉልላት ታሰሩ

May 14, 2013

(ዘ-ሐበሻ) የወያኔ ሥርዓት ሰሞኑን በህግ ቁጥጥር አውያቸዋለሁ ካላቸው ተጠርጣሪዎቸ ጋር ሲፈለጉ ነበር የተባሉት አቶ ተመስገን ጉልላት ከአዲስ አበባ ወደ ጋምቤላ በመሸሽ ሱዳን ለመግባት ሁኔታዎችን ሲያመቻቹ ሊያመልጡ ሲሉ ተያዙ ሲል የወያኔ ሚድያዎች ሲገልጹ ተጠርጣሪው በእጃቸው የተለያዩ ሰነዶችና 160 ሺህ ብር ይዘው ሊሰወሩ ሲሉ ተይዘዋል ብለዋል።
መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።የጋምቤላ ጉሙሩክ ስራ አስኪያጅ ለሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ 80 ሺህ ብር በመስጠት ወደ ሱዳን ለመግባት ጥረት አድርገዋል በማለት የዘገቡት የወያኔ ሚዲያዎች ወደ ሱዳን ለማስገባት ተባብሯቸዋል ያሏቸውንም፡ አቶ ጌታቸው አሰፋንም በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተዘግቧል።
በተጨማሪም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታስረዋል የተባሉት 24 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዛሬ በዋለው ችሎትም ተጠርጣሪዎቹን በሶስት የክስ መዝገብ በመከፋፈል ፍርድ ቤቱ የተመለከተ መሆኑን የዘገቡት መንግስታዊ ሚድያዎች በእነ መላኩ የክስ መዝገብ ውስጥ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች መካተታቸውን አስታውቀዋል። አንደኛው ተጠርጣሪ አቶ መላኩ ፈንታ ጠበቃ ደንበኛቸው በዋስ ለመለቀቅ ያስችሏቸዋል ያሏቸውን ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ በቃል ማቅርባቸውም ታውቋል።
የሁሉንም ሀሳብ ያደመጠው ፍርድ ቤቱም በጊዜ ቀጠሮ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ ለነገ ቀጠሮ ይዟል። በተመሳሳይ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር፣ በአስርሺዎች የሚቆጠር ዶላርና ዩሮ ቤታቸው ሲበረበር ተገኘ በተባሉት በነገብረዋህድ የክስ መዝገብ ውስጥ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችንና የአቃቢ ህግ መከራከሪያን ያደመጠ ሲሆን መደበኛ የስራ ሰዓት በመጠናቀቁ በጊዜ ቀጠሮው ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ ይዟል ሲሉ የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።
በእነመላኩ የክስ መዝገብ ውስጥ የሚገኙ 7 ተጠርጣሪዎች
1.መላኩ ፋንታ
2.እሸቱ ወልደሰማያት
3.መርክነህ አለማየሁ
4.አስመላሽ ወልደማርያም
5.ከተማ ከበደ
6.ስማቸው ከበደ
7.ዶክተር ፍቅሩ ማሩ
ከተከሰሱባቸው ወንጀሎች መካከል ቀረጥና ታክስ በማጭበርበር እንዲሁም አራጣ በማበደር የተከሰሱ ግለሰቦች ክስ ስልጣንን በመጠቀም እንዲቋረጥ በማድረግና በዚህም ያልተገባ ሀብትን መሰብሰብ የሚል ይገኝበታል ።

በእነገብረዋህድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 11 ተጠርጣሪዎች
1.ገብረዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ
2.በላቸዉ በየነ
3.ጥሩነህ በርታ
4.ተስፋዬ አበበ
5.ነጋ ገብረ እግዚአብሄር
6.ምህረተአብ ካሳ
7.ሙሌ ጋሻው
8.አሞኘ ታገለ
9.ኮለኔል ሃይማኖት ታፈሰ
10. ሀብቶም ገብረ መድህን
11. ወይዘሮ ንግስቲ ተስፋዬ

ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ የተከለከለ ሲሚንቶ እንዲገባ ማድረግ ፣ በኮንትሮባንድ የተሰማሩ ግለሰቦችን በማገዝ ፣ ከተጠርጣሪዎች መካከል የሁለቱን ክስ የሚደግፉ ሰነዶችን ማሸሽ የሚል ይገኝበታል ።
በሶስተኛው የናዝሬት ጉምሩክ ባልደረቦች በሆኑት በነ መሀመድ ኢሳ የክስ መዝገብ ውስጥ የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎች
1.መሃመድ ኢሳ
2.ሰመረ ንጉሴ
3.ዘሪሁን ዘውዴ
4.ማር እሸት ተስፋዬ
5.ሙሉቀን ተስፋዬ
6.ዳኜ ስንሻው

የተከሰሱባቸው ወንጀሎች ደግሞ በኮንትሮባንድ የተለያዩ እቃዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረግና ያልተገባ ሀብት መሰብሰብ የሚሉ ናቸው።

6 Comments

 1. ተጨማሪ መጠየቅ ያለባቸ ኢ/ያ የመዘበሩ ህወሓት አዜብከነባላ:ስዪም:ሸባው የአማራናየኢ/ያ ጠላት ስብሀት ነጋ:አስመላሽ ወ/ስላሴ:ጌታቸው አሰፋ:ቴድሮስ ሀጎስ :ቅዱሳን ነጋ:ፀጋየ በርሄ:ዶ/ር ቴድሮስ:ዶ/ርክንዳያገ/ህይወት:ዶ/ርደብረ ፅዮን ናቸው::

 2. ደህደን ሽፈራው ሽጉጤ:ሬድዋን ሁሴን:መኩሪያ ሀይሌ:ሲራጅ ፈጌሳ:ደሴ ዳልኬ:ዶ/ር ካሱ ኢላላ:ገ/መስቀል ጫላ:ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም:ናቸው::ብአደን:አድሱ:በረከት:ደመቀ:አባተ ስጦታው:ካሳ ተ/ብርሀን ናቸው::

 3. ኦህደድ:ግርማ ብሩ:አለማየሁ ተገኑ:አባዱላ ገመዳ:ወርቅነህ ገበየሁ:ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ:ሞቱማ በጣሳ:አለማየሁ: ኩማ ሜደቅሳ አቶምሳ:ሶፍያን አህመድ ናቸው::ብአደን ላይ ህላዊ ዮሴፍና ዮሴፍ ረታ ይጨመሩ::እንድሁም ፕ/ር አንድርያስ እሽቴ ሽመልስ ከማል ጀ/ል ሳሞራየኑስ:ሜ/ጀ አብርሀም:ወ/ማርያም:ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ:ሜ/ጄ ገዛኢ አበራ:ሜ/ጄ ሞላ ሀ/ማርያም ኮ/ል ፀጋየ ገ/ተንሳይ ሻንበል ጠና ቁርደ

 4. ኦህደድ:ግርማ ብሩ:አለማየሁ ተገኑ:አባዱላ ገመዳ:ወርቅነህ ገበየሁ:ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ:ሞቱማ መቃሳ:አለማየሁ: አቶምሳ:ኩማ ሜደቅሳ:ሶፍያን አህመድ ናቸው::ብአደን ላይ ህላዊ ዮሴፍና ዮሴፍ ረታ ይጨመሩ::እንድሁም ፕ/ር አንድርያስ እሽቴ ሽመልስ ከማል ጀ/ል ሳሞራየኑስ:ሜ/ጀ አብርሀም:ወ/ማርያም:ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ:ሜ/ጄ ገዛኢ አበራ:ሜ/ጄ ሞላ ሀ/ማርያም ኮ/ል ፀጋየ ገ/ተንሳይ ሻንበል ጠና ቁርደ

 5. Hello H-Habesha Editor
  I would like to tell you some comment.
  When you did not know exactly about oromo peoples’ name please ask some one before you published with clear wrong Names.
  Kumaa mideqsa or Kumaa Demqsa ?Motma Betasa or Motuma Meqassa?
  Please take this correction.
  Thank you

 6. ኩማ ደመቅሳ :ሞቱማ መቃሳ ተብሎ ይነበብ::ደግሞ የዘ_ሀበሻ ሳይሆን እኔ በተለያየ መንገድ ሲመዘብሩ የማቃቸው ናቸው::”ሊነጋ ሲል ይጨልማል”

Comments are closed.

Gedeon4
Previous Story

ኢትዮጵያ በፍጥነት ወደኋላ እየገሰገሰች ነው!

habtamu
Next Story

Hiber Radio: የስዬ አብርሃ ወንድም ዳግም በሙስና ታሰረ

Latest from Blog

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የውጪ ግንኙነት የቤተክርስቲያኒቱን የሺሕ ዘመናት ታሪክ እና እሤቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርባታል!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) (ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) እንደመንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ- ባሳለፍነው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለአንድ ቀን የተካሄደው፤ ‹‹የአፍሪካ  መንፈሳዊ ቀን/The African Spiritual

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |
Go toTop