ኢትዮጵያ በፍጥነት ወደኋላ እየገሰገሰች ነው!

May 14, 2013

ጌዲዮን ከኖርዎይ

ጌዲዮን ከኖርዎይ

የኢትዮጵያ እድገት መቼም በጣም አስገራሚና አነጋጋሪ መሆን ከጀመረ ሰነባበተ፥፥ ውሸት ሲደጋገም ውነት ይሆናል አለች ቻይና! አቶ መለስ ዜናዊ እንደቀልድ የተናገሩት ነገር ስር ሰዶ አሁን አሁን በሳቸው አጠገብ ያለፉት ሁሉ አብረው አጮሁት፥፥ የሚገርመው ነገር ግን አውሮ ፓውያንም አብረው አጮሁት እንደውም ስራቸውን በርዳታ ስም እንደፈለጋቸው እንዲያሮጡ መልካም አጋጣሚን የፈጠረላቸው ይመስላል፥፥

ግንቦት 13,2013 ቀን በኦስሎ ከተማ ሊተራቱር ህውስ በተባለው አዳራሽ ውስጥ ይህንኑ የኢትዮጵያን እድገት ለማስተጋባት በኖርዌጂያን ዴቨሎፕመንት ፈንድ በተባለ ድርጅት አማካኝነት Ethiopia – the reality behind the media በሚል ርእስ በተጠራው ስብሰባ ላይ ኖርዌጂያን ፖለቲከኞችና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች በእንግድነት በተገኙበት የውይይት መድረክ ላይ በርካታ ወድ ኢትዮጵያውያን በኖርዎይ እንዲሁም ኖርዌጂያን በቦታው ላይ ተገኝተው ነበር፥፥

ተጋባዥ ከነበሩት እንግዶች መካከል፥

  • ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ሚኒስቴር ሃይኪ ሆልሞስ ከሶሻል ሌፍት ፓርቲ
  • ፒተር ጊትማርክ የኖርዌጂአን ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ የኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ዋና ቃልአቀባይ እና
  • ዶክተር ሚሊዮን በላይ ኢኮሎጂካል ለርኒንግ እና ኮሚዩኒቲ አክሽን ዳይሬክተር ከኢትዮጵያ ሲሆኑ ስብሰባውን የመሩት አቶ አንድሪው ክሮግሉንድ የኖርዌጂያን ደቨሎፕመንት ኤንፎርሜሽን ኤንድ ፖሊሲ ዋና ክፍል ሃላፊ ነበሩ፥፥

ውይይቱን በይበልጥ ያተኮረው በስልጣን ላይ ባሉት አቶ ሃይኪ ሆልሞስ የኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ሚኒስቴር እና በአቶ ፒተር ጊትማርክ የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ የኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ዋና  ቃል አቀባይ መካከል ቢሆንም ዶክተር ሚሊዮን በላይ ብዙ ለመናገር ከኢትዮጵያ መንግስት ብዙም ፍቃድ የተሰጣቸው አይመስልም ነበር፥፥

ይሁን እንጂ አቶ ሃይኪ ሆልሞስና በአቶ ፒተር ጊትማርክ መካከል የነበረው የልዩነት አቋም አቶ ሃይኪ ሆልሞስ ኢትዮጵያ ውስጥ እድገት አለ ስለሆነም የገንዘብ እርዳታ ማድረጋ እንቀጥላለን የሚል ሲሆን አቶ ፒተር ጊትማርክ በበኩላቸው አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ስለሚባለው እድገት ጥርጣሬ እንዳላቸውና እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ከግዜ ወደጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱ ኖርዎይ የምታደርገውን የገንዘብ እርዳታ እንድታቆም እንዲሁም እርዳታው አስፈላጊ ከሆነም በስልጣን ላይ ላለው መንግስት ሳይሆን ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚደርስበት መንገድ መፈለግ አለበት ሲሉ የሳቸው ፓርቲም በስልጣን ላይ ከወጣ ይህው እርዳታ እንደሚቌረጥና በማንኛውም ጊዜ ይህ ሁኔታ ሲሻሻል እርዳታው እንዴት እንደሚቀጥል የሚታይ ይሆናል ብለዋል፥፥

እንዲሁም ከተሳታፊዎች መካከልም ብዙ ጥያቄዎች ለዶክተር ሚሊዮንና ለአቶ ሃይኪ ሆልሞስ የተሰነዘረ ሲሆን የተሳታፊው አቋም የነበረው፥ የኖርዎይ መንግስት እየሰጠ ያለው የገንዘብ እርዳታ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግስት ህዝቦችን ለማፈን እያተጠቀመበት ነው፥ እርዳታው መረዳት ላለበት ህዝብ አልደረሰም፥ የሚሉና በርካታ የተቃውሞ መልክቶችን ያዘኡ ነበሩ፥፥

በመጨረሻም ምንም እንኳን ከተሰብሳቢው በርካታ የወቅታዊ የሃገራችን አንገብጋቢ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለውይይቱ ተጋባዥ እንግዶች የቤት ስራ የሚሆኑ በርካታ ጥያቄዎች በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል፥፥

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

1 Comment

  1. እነዚህ ነጫጭባወች የራሳቸውን አንባገነን አጥፍተው የኛን ያበረታታሉአይደል?የእኔን ጅል ግደልልኝ የሰው ጅል አኑርልኝ::አሉ እማማ ማንጠግቦሽ::”ሊነጋ ሲል ይጨልማል”

Comments are closed.

Previous Story

የወያኔ ፖሊስ አባል 12 ንጹሃን ዜጎችን ባህርዳር ላይ ረሸነ

Next Story

የናዝሬት ጉምሩክ የህግ ማስከበር ኃላፊ አቶ ተመስገን ጉልላት ታሰሩ

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop