“ሕፃን ካቦካው – ልጅ ያቦካው ይሻላል” (ለተክለሚካኤል አበበ አስተያየት የተሰጠ ድጋፍ)

ይህ ፅሑፍ የኢሳት ባልደረባ ተ/ሚካኤል አበበ “የኢሳት 3ኛ ዓመት ክብረ በአል የሙስሊሞች ብቻ ነው እንዴ?( https://zehabesha.info/archives/1923) ’’ በሚል ርዕስ ላቀረበው ፅሑፍ አቶ  ቶፊቅ ጀማል ከቼክ ሪፖብሊክ(ፕሪግ) መልስ እንዲሆን ብለው “ልጅ ያቦካው (https://zehabesha.info/archives/2039) ” በሚል ርዕስ “  ለሰጡት  ባለ 12 ነጥብ (የቃላት ጨወታ) የተሰጠ ምላሽ ነው፡፡

 1.  ውድ አቶ  ቶፊቅ ጀማል “የአብዬን ወደ እምዬ ልክክ” እንዲሉ በኢሳት 3ኛ ዓመት ክብረ በአል ዝግጅት ላይ በሙስሊም  ( እዚህ ላይ አወልያን መሰረት አድርጎ የተነሳውን የሙስሊም እንቅስቃሴ የማትደግፉ ወይም አካሄዱን የማትቀበሉ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች እንድትረዱኝ አደራ የምለው በዚህ ፅሑፍ “የሙስሊም ተወካዮች” እያልኩ የምጠቅሰው አወልያን መሰረት አድርጎ የተነሳውን የሙስሊም እንቅስቃሴ ደግፋው “በዲያስፖራ” የሚንቀሳቀሰውን ቡድን መሆኑን እንድትረዱኝ አደራ እላለሁ ) ተወካዮች ብቻና ብቻ እንዲሞላ መደረጉ ተገቢ አይደለም ከዚህ ይልቅ የሁሉም ሃይማኖት ተወካዮች ጥሪ ሊደረግላቸው ይገባል የሚል ግልፅ የሆነ የእርምት መልዕክት ያለውን ፅሑፍ የኢሳት ባልደረባ የሆነው ተ/ሚካኤል አበበን ቁምነገር አዘል ምክር “ልጅ ያቦካው” ነው ብለህ ለመተቸት በመድፈረህ “ልጅ” ማን እንደሆነ ምላሽ እንድሰጥህ ግድ ሆኖብኛል፡፡

አንተ ግን ያደረገውንና የተናገረውን  ፈጥኖ እንደሚረሳ ሕፃን በዚህ ፅሑፍ አልተበሳጨሁም ወይም አያበሳጭም ብለህ ከፃፍክ ከጥቂት መስመሮች በኋላ ቀለሙ እንኳን ሳይደርቅ ወዲያው “ኧረ በጣም ያበሳጫል” ብለህ መፃፍህንና ተ/ ሚካኤል አበበ የጻፈዉን  ጽሑፍ አንብበህ ሳትጨርስ ለትችት መንደርደርህን የተመለከትን ማለትም የኢሳት ባልደረባ ተ/ሚካኤል አበበ የፃፈውን ባለ 15 (አስራ አምስት) ነጥብ ፅሑፍ ባለ 12 (አስራ ሁለት) ነጥብ የአቋም መግለጫ ብለህ ከጅምሩ ስትቀባጥር የታዘብን አንባብያን የአንተን ፅሑፍ “ልጅ ያቦካው” ነው ወይስ “ሕፃን ያቦካው” ነው የምንለው?

ተ/ሚካኤል አበበ የተጠቀመበት የአነጋገር ስልት ገና ከጅምሩ ሊገባህ እንዳልቻለ ስለ ማበሳጨት እና ስለ ማስጨብጨብ  የሰጠኸው ትንታኔ ያሳብቅብሃል እንዲያው በከንቱ ያለአቅምህ ተወጣጠርክ እንጂ::  አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን በሚተቸው ፥ በሚገስፀውና ስህተቱን በሚያርመው የማይደሰት ከሆነ መስተካከልና መታረም ባለመፍቀዱ “ያበሳጨዋል”። እንዲሁም ምክር አዘል መልዕክቶችን አንብበው ከስህተታቸው ለመታረም : ለችግራቸው መፍትሄ ሰጪ ይሆናል ብለው ለሚያምኑና ለሚያነቡ ደግሞ “አስጨብጫቢ” ይሆናል ማለት እንጂ “ማበሳጨት” ማለት ፊትህ እስኪቀላ መኮሳተርን ወይም “ማስጨብጨብ” ማለት ደግሞ እጅህ እስኪቃጠል በመዳፍህ አጋና መምታትን የሚመለከት አለመሆኑን ለመረዳት ከፈለክ ለማቡካት የሚጣደፉትን የህፃን እጆችህን ሰብሰብ ብታደርጋችው መልካም ነው’።

 1. የኢሳት ባልደረባ ተ/ሚካኤል አበበ ከዜና አንባቢነት ጀምሮ በኢሳት በሚተላለፉ የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ ግዜውን ፥ እውቀቱንና ጉልበቱን ያፈሰሰ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከመሆኑም በላይ በተለያዩ የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ላይ በበርካታ የሰሜን አሜሪካ ክፍለ ሃገራት ( states) በመገኘት የታወቀ ሆኖ ሳለ መሰረታዊውን የፅሑፉን መልዕክት በተ/ሚካኤል መጋበዝና ባለመጋበዝ ዙሪያ ለማቡካት መከጀልህ አንተን የመሳሰሉ ህፃናቶችን ልትቀልድባቸው አልመህ ካልሆነ በስተቀር ኢሳት የኢትዮጵያውያን ሁሉ እንደ መሆኑ መጠን የሃይማኖት ተወካዮች መጋበዛቸው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የሁሉንም ኃይማኖት ተወካዮች ማካተት አለበት የሚለውን ጭብጥ ሊያጠፋው አይችልም።

አቶ  ቶፊቅ ጀማል ስታቦካ የረሳኸውን ነገር ላስታውስህ የኢሳት ባልደረባ ተ/ሚካኤል አበበ ጳጳስ ነኝ ፥ ቄስ ወይም ፓስተር ነኝ ወይም የሃይማኖት ተወካይ ነኝ አላለም ነገር ግን የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ ካስፈለገ ኢሳት የኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንደመሆኑ መጠን ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ የሚያካትት መሆን ስለሚገባው የሁሉንም ሃይማኖት ተወካዮች መጋበዝ  ነበረባቸው በማለት ምክር አዘል እርምት መስጠቱ በየትኛውም የአፈታት ወይም የአተረጓጎም ስልት(ተፍሲር) ተ/ሚካኤል አበበ እኔ ጳጳስ በመሆኔ የሃይማኖት ተወካይ ነኝና ጋብዙኝ ማለትህ ነው ሊያስብለው የሚያስችል ጭብጥ የለውም።

 1. በ3ኛው ነጥብህ ላይ ኢሳት ለዲያስፖራ የሙስሊም ተወካዮች ሽፋን የሰጣቸው የኢትዮጵያዊያን የመብት ትግል ሲያቀጣጥሉት በመገኘታችው ነው ብለሃል  ነገር ግን የሙስሊም ተወካዮች ትግሉን ለማቀጣጠል መነሳታችው የሚለካው ከሃይማኖት ጎራ ወጣ ብሎ ለዜግነት ክብር በመቆም በሁሉም  ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ለሚደርሰው የመብት ጥሰትና ጭቆና በጋራ መቆም ሲችሉ እንጂ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ዜጎች ለምሳሌ ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፥ አንዷለም አራጌ ፥ ጋዜጠኛና መምህር ወ/ት ርዮት አለሙ ፥ አቶ በቀለ ጎረባና ለሌሎችም የህሊና እስረኞች መቆምና መታገል ካልቻሉና ልባቸው ካልተነካ እንዲሁም በየሄዱበት ቦታ በዋነኛነት የሚያነሱት የሙስሊም እስረኞችን ጉዳይ ብቻ ከሆነ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን መብትና ነፃነት የሚታገለው ኢሳት ተጠቃሚ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው? ይልቅስ ኢሳት የአንድ ሃይማኖት ተወካዮችን ብቻና ብቻ በዓመታዊ ክብር ባዓሉ ላይ ለመጋበዝ መወሰኑ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ ኢሳት የኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሳይሆን አወልያን መሰረት አድርጎ ለሚንቀሳቀሰው የሙስሊም ተወካዮች ብቻ የሚሰራ የፕሮፖጋንዳ ማሽን ያስመስለዋል እንጂ።
  1. አቶ ቶፊቅ ጀማል በአራተኛው ነጥብ ላይ ምጡቅ ሃሳብ ልታመነጭ የምትንደረደር በሚመስል መልኩ “ያልተረዳኸው ወይም ልትረዳው ያልፈለከው ወይም ያልሞከርከው ጉዳይ ያለ የመስለኛል” ብለህ ከጀመርክ በኋላ የሙስሊሙ ችግር የሃይማኖት እንጂ የፖለቲካ አይደለም የሚንቀሳቀሰውም ይህንኑ የሀይማኖት  ችግር  ለመፍታት ብቻ ነው” ብለሃል።አስተሳሰብህ የሕፃን ቡኮ ሆኖብህ ነው እንጂ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ በጥራት የሚገባህ ሰው ብትሆን ኖሮ በዚህ ነጥብ ላይ ያነሳኸው የተ/ሚካኤልን  ስጋት የሚያጠናክር ነው።

ሙስሊሙ የሚመለከተው የሙስሊሙን ሃይማኖታዊ ጉዳይ ብቻ እንጂ የመላው ኢትዮጵያውያ ህዝብ ያለበት የኢኮኖሚ ፥ የፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስ አይመለከተውም የምትል ከሆነ አንተና አንተን መሰል አስተሳሰብ ያላቸው ግለሰቦች ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በዜግነት አጀንዳ ዙሪያ ወደ ላይ ከፍ ለማድረግ በተቋቋመው በኢሳት ዙሪያ ሳይሆን መሰብሰብ የሚገባቸው በሃይማኖት ጣራ ስር ወይም በመስጊድና በመስጊድ ብቻ ነው።

አንተ ሊገባህ ያልቻለው ኢሳት  የኢትዮጵያውያን ሁሉ የዜግነት አጀንዳ የሚስተናገድበት ሚድያ እንጂ ከሙስሊሙ ጥያቄ ውጪ የሌላው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ችግር አይመለከተንም ለሚሉና እንዲሁም በኢሳት ዓመታዊ ክብር በዓል ላይ መጋበዝ ያለባቸው  የሙስሊሙ ተወካዮች ብቻ ናቸው ብለው ለሚያስቡ  ወገንተኛ አስተሳሰብ ላላቸው የጠባቦች ንብረት አይደለም።

 1. እዚህ ላይስ እኔም መልስ መስጠት የለብኝም ብዬ አሰብኩና  “ለዚህ መልስ መስጠት ያለብኝ አይመስለኝም”  ካልክ በኋላ  ወዲያው ከቼክ ሪፖብሊክ የአማርኛ ሰዋሰው እርማት ለማድረግ መከጀልህን አይቼ “መልስ በመስጠትና ባለ በመስጠት” መካከል ያለው ልዩነት የማይገባህ ህፃን መሆንህ ትዝ ስላለኝ አንድ ሁለት ነገር ልጠቁምህ ወሰንኩ።

ኢሳት በዜግነት ክብር እንጂ እንዳንተ በሃይማኖት ብቻ የማያስቡ ውድ  ኢትዮጵያዊያን የተሰባሰቡበት በመሆኑ ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ላይ የሚጋበዙ እንግዶችም ይህንኑ የሚያንፀባርቁ ሊሆን  ይገባል ስለዚህም  የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ ካስፈለገ ሁሉም ቤተ እምነቶች በመወከል በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ እየተፈጠረ ያለውን ስጋት እና ጥርጣሬ ያገናዘበ ቢሆን እንደዜጋ በኢትዮጵያዊነታቸው

: ዜግነትን መሰረት አድርጎ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ለመታገል ለቆመው እንደ ኢሳት ዓይነት ተቋም ጠንቅ መሆኑን መቀበል ፥ መረዳትና መገንዘብ አቅቶህ ብትዘባርቅ ሃይማኖታዊ ብቻ እንጂ ብሔራዊ አጀንዳ የለንም ከምትለው  ከአንተ እና ከመሰሎችህ ሌላ ምን ይጠበቃል።

 1. በ6ተኛ ነጥብ ላይ ያነሳኸውን ሃሳብ “የራስዋ አሮባት የሰው ታማስላለች” የሚለውን ቁም ነገር አዘል ምሳሌ እንዴት እንዳስታወስከኝ እንደሚከተለው ላመላክትህ:: በዚህ ነጥብ ጅማሬ ላይ “መንግስትና ሃይማኖት አይለያዩ ማለታችን ነው..” የሚለውን አረፍተ ነገር ጠቅሰህ የአማርኛ ቋንቋ አጠቃቀም ላይ ትችት ለመስጠት በማሰብ ያልገባህ በመምሰል የህፃን ነገር ሆኖብህ ነውረኛና ነገረኛ ለመሆን ሞክረሃል ነገር ግን በዚሁ  አረፍተ ነገር ላይ በዚህ ነጥብ አንተው ራስህ “በእርግጥም ምን ለማለት እንዳወብህ አልገባኝም” ስትል ምን ማለት ፈልገህ ነበር? “እንዳወብህ” የሚል አዲስ የአማርኛ ቃል አንተ ፈጥረህ ነው? ወይስ ከመኖሪያ ሃገርህ ከቼክ ሪፖብሊክ ቃላት ተውሰህ ነው? አየኸው የራስዋ አሮባት የሰው ታማስላለች ይሉሃል እንዲህ ነው።

እንዲያው ለነገሩ ነው  እንጂ ከአረፍተ ነገሩ አሰካክና ከአውደ ንባቡ አንፃር ለማለት የፈለከውን ለመረዳት በጣም ቀላል ነው የሚጠይቀው ቅንነት ብቻ ነው አንተ ለማለት የፈለኩት ሌላ ነው ካላልከኝ በስተቀር መጠቀም የፈለግከው ቃል በታይፕ ግድፈት  “ሰ” በ “ወ” ቢቀየርብህም  “እንዳሰብህ” ለማለት ፈልገህ እንደሆነ ይታየኛል  ከዚህ የምረዳው  የተ/ሚካኤልን ጽሑፍ በቅንነት ለማንበብ አለመሞከርህንና በዚህም ምክንያት ለአላስፈላጊ ትችትና ጥላቻ መዳረግህን ብቻ ነው።

ተ/ሚካኤል በ7ተኛው ነጥብ ላይ የገለፀውን ሃሳብ አንተ ለጥላቻ መልዕክትህ እንደቆረጥከው ወይም ለመጠምዘዝ እንደሞከረከው ሳይሆን አውደ ንባቡ በግልፅ እንደሚያስረዳው መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ መሆናቸውን ነው:: በተ/ሚካኤል ፅሑፍ በ6ተኛው ነጥብ መጀመሪያ ላይ “… ሀይማኖትና መንግስት የተለያዩ ናቸው፤ መንግስት Secular ይሁን፤ የሚለውን መሰረታዊ የፖለቲካ መርህ አምነንበት…” ነው ይላል:: በተጨማሪም በ 7ኛው ነጥቡ ላይ “ አሁንም መንግስትና ሀይማኖት ይለያዩ፤ መንግስት በሙስሊሞች ጉዳይ ጣልቃ አይግባ ስንል ያ ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን የሞቱለት መርህ ይከበር ማለታችን ነው ”ይላል:: እነዚህን አረፍተ ነገሮች ያነበበ ቅን ሰው

 

ከላይ “አይለያዩ ” የሚለው ቃል “አ” በታይፕ ግድፈት የገባች እንጂ በግንዛቤ ችግር የገባች አለመሆንዋ እየታወቀ ይህን ያህል በጥላቻ የተሞላህና በእድሜ ብቻ የገፋህ በአስተሳሰብህ ጨቅላ ህፃን ያስመሰለህን ጉዳይ ቆም ብለህ እንድታስብበት እጠይቅሃለሁ።

 

 1. ለነገር ከመቸኮልህ ብዛት ናላህ ስለዞረ  የተ/ሚካኤል 6ተኛ እና 7ተኛ ነጥብ ከአንተ 6ተኛ እና 7ተኛ ነጥብ ጋር የተለያዩ ቢሆኑም “ህፃን ያቦካው” እንዲሉ አገለባብጠከኸዋል ስለዚህም ነጥቦቹን እየተከታተሉ ለሚያነቡ አንባቢያን አደናጋሪ እንዳይሆን በበኩረ ፅሑፉ ቅደም ተከተል ሳይሆን መልስ የምሰጠው ላንተ በመሆኑ አንተ የፃፍክበትን ቅደም ተከተል መርጫለሁ።  የኢሳት ባልደረባ ተ/ሚካኤል አበበ የኢሳት ዓመታዊ ክብረ በዓል የሁሉም ኢትዮጵያውያን በመሆኑ የሁሉም ሀይማኖት ተወካዮች ሊጋበዙ ይገባል የሚል ምክር በማቅረቡ “የልጅ ራዕይ ነው” ብለህ ከተሳለቅክበትና ለማጣጣል ከሞከርክ ፣ በበዓሉ ላይ መጋበዝ ያለባቸው የሙስሊም ሀይማኖት ተወካዮች ብቻና ብቻ መሆን አለበት ብለህ ሽንጥህን ገትረህ የምትሟገተውን ያንተን ህልም “የሕፃን ቅዥት ነው” ከማለት የተሻለ ምን ማለት ይቻላል?

 

 1. በዚህ ነጥብ ላይ የሚገርመው ይሄን ሁሉ ትችት ስትደረድር ከቆየህ በኋላ በእርግጠኝነት ባልገባህ ጉዳይ ስትፅፍ መቆየትህን  “…በእርግጥ አልገባኝም …“በማለት ማመንህ ነው። በእርግጠኝነት ባልገባህ ጉዳይ ላይ ስትቸከችክ መቆየትህ ዘባራቂ መሆንህን አረጋገጠልኝ። በእርግጥም ሊገባህ ያልቻለውን ነገር እኔ ልንገርህ አንተ ያልገባህ ኢሳት የኢትይጵያዊያን ሁሉ መሆኑና በዓመታዊ ክብረ በዓሉ ላይ መጋበዝ ያለባቸው የአንድ እንቅስቃሴ ተወካዮች ብቻ መሆን እንደማይችል ነው። በዓመታዊ ክብረ በዓሉ ላይ የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ ካስፈለገ  ሁሉም የሃይማኖት ተወካዮች ቢጋበዙ ኢትዮጵያዊነትን ከማንፀባረቅ በስተቀር ሌላ ምን ችግር ይኖረዋል?

 

አንተ ግን አንዳንድ የአክራሪ ኢስላም አቀንቃኞች እንደሚናገሩት ኢትዮጵያዊነትን በሚያንፀባርቁ ጉዳዮች ላይ ቀስ በቀስ መታየትና መገኝት ያለባቸው የሙስሊም ተወካዮች ብቻና ብቻ መሆን አለባቸው በሚል በሸሪያ ፍልስፍና የተጠመቁ ሰዎችን አስተሳሰብ ለማራመድ የምትከጅል ሕፃን በመሆንህ ነው።

ተ/ሚካኤል በተደጋጋሚ ለማስረዳት የሞከረው ኢሳት ኢትዮጵያዊ ዜጎችን ሁሉ በሚያካትት መልኩ ሊሆን ስለሚገባ የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የሁሉም ሃይማኖት ተወካዮች ቢገኙም ባይገኙም መጋበዝ ተገቢ ሆኖ ሳለ የአንድ ሃይማኖት ተወካዮችን ብቻ ነጥሎ መጋበዝ አደጋ ከመፍጠር በስተቀር ጠቃሚ ሊሆን አይችልም:: በተለይ ደግሞ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ በጥርጣሬ የሚመለከቱ ኢትዮጵያዉያን እንዳሉ በተረዳንበት ግዜና ወቅት::

9.  በዚህ ነጥብ ላይ ያነሳኸው ነጥብ በአጭሩ “የእርጎ ዝምብ” መሆንህን ከማሳየት በስተቀር ሌላ ምንም ቁም ነገር የለውም በ5ተኛው ነጥብህ ላይ የአማርኛ ሰዋሰው ሊቅ ለሞሆን ሲቃጣህ አንብቤ ሲገርመኝ አሁን ደግሞ የታማኝ በየነ በኢትዮጵያዊነቱ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የቆመበትን አላማ በመጠምዘዝ አሳፋሪ አፈቀላጤ ለመሆን ሞከርህ ከዚህም በላይ ኢሳት የኢትዮጵያውያን ሁሉ ዓይን ፥ ጆሮና አንደበት እንጂ እንደ አንተና እንደ  መሰሎችህ በኢሳት ክብረ በዓል ላይ መጋበዝ ያለባቸው የአወልያ እንቅስቃሴ ተወካዮች ብቻና ብቻ ናቸው ብለው ሽንጣቸውን ገትረው ለሚሟገቱ ሕፃናቶች መፈንጫ አይደለም።

የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የሙስሊሙን ተወካዮች ብቻ ነጥሎ መጋበዝ ታላቅ አደጋ አለው በተለይ ደግሞ አወልያን መሰረት አድርጎ የተነሳውን የሙስሊም እንቅስቃሴ በጥርጣሬ የሚመለከቱ እና  የማይደግፉ ሙስሊሞችንም ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ በሚታወቅበት በዚህ ወቅት ጥንቃቄ ማድረጉ ተገቢ መሆኑን መጠቆሙ ሊገባህ ያልቻለበት ምክንያት አንድም ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ እንደ ዜጋ ለመቀበል ችግር ያለብህ ከመሆኑም በላይ ሙስሊም ላልሆነው ኢትዮጵያዊ ክብር የሌለህ መሆኑን ነው።

10. የኢሳት ባልደረባ ተ/ሚካኤል በፅሑፉ 11ኛ ነጥብ ላይ “የሀይማኖት መሪዎች ከጋበዝን ደግሞ ቢመጡም ባይመጡም የኦርቶዶክሱንም የፕሮቴስታንቱንም፤የይሁዲውንም፤ የካቶሊኩንም ነው እንጂ፤ በምን መስፈርት ነው የሙስሊሞቹን ብቻ የምንጋብዘው? ይሄአደገኛና መታረም ያለበት አካሄድ ነው። “  እንዲሁም በ12ተኛ ነጥብ ላይ ኢትዮጵያ “ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች ያሉባት ሃገር “ መሆኗን በግልፅ ጠቅሷል። ይህም ኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች የሚኖሩባት አገር መሆኗን የሚያስረዳ ሆኖ ሳለ ነገር ግን አንተ ከአውደ ንባቡ ውጪ የሆነ መደምደምያ ይዘህ ለዚህ ትችት መነሳትህ ቀደም ሲል ደጋግመህ እንዳረጋገጥክልኝ የኢትዮጵያዊነት ፅንሰ ሃሳብ ያልገባህ መሆንህን ነው።

ለነገሩ “የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል” እንዲሉ አንተ እስከ 12ተኛው ነጥብ ብቻ በማየት የፅሑፉን መዳረሻ ሳትረዳ በመዘባረቅህ ይቅርታ መጠየቅ ይገባሃል። ምክንያቱም የተ/ሚካኤል ፅሑፉ ሙሉው አንተ እንዳልከው ባለ 12  (ኣስራ ሁለት) ነጥብ ብቻ ሳይሆን 15 (ኣስራምስት) ናቸውና :: ለምሳሌ ስለ ብሔር ብሔረሰቦች ስብጥር ለመግለጽ ቢያስፈልገን ከ80 በላይ የሆኑትን የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች  በንግግሩም ሆነ በፅሑፉ ላይ ሁሉንም ካልጠቀሰ በስተቀር በአንተ የ “ህፃን” አስተሳሰብ መሰረታዊ የጠባብነት ማስረጃ ሆኖ ከተወሰደ እስከ ዛሬ ድረስ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የብሔር ብሔረሰቦችን የሚመለከት ንግግር ሲያደርጉ ወይም ሲፅፉ ለናሙና ያህል የተወሰኑትን ጠቅሰው በማለፋቸው በአንተ የጠባብነት መስፈርት መሰረት ሁሉንም ባለ መዘርዘራቸውና የተወሰኑትን ጠቅሰው ሌሎቹን ግን “የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች” በማለታችው በአንተ የ”ሕፃን” መስፈርት መሰረት በጠባብነት ጎራ ተፈርጀው ላልበሰለ ትችትህ ተጋልጠዋል ማለት ነው።

አንተ በመግቢያህ ላይ ማንንም አልወክልም ብትልም የተፅዎ ስምህ አልያም የብዕር ስምህ “ቶፊቅ ጀማል” እንደሚያሳብቅብህ ሙስሊም ልትሆን ትችላለህ ነገር ግን ኢትዮጵያ የጀግና ሙስሊሞችም አገር ናት ብለን ለምናምን እንደኔ ላሉ እንደዜጋ በኢትዮጵያዊያነት ለምናምን ወገኖች አንተና አንተ ያለህበት ማህበረሰብ ምናልባትም እንዳንተ የሚያስቡ ከሆነ የኢትዮጵያ ግማሽ አካል ተበላሽቷል ፥ ታሟል፡ በድን ሆኗል ፥ አልያም ከርፍቷልና የወገን ያለህ ብዬ ጩኸቴን አሰማለሁ።

11.    በ11ኛው ነጥብ “ኢሳት በህዝብ ድጋፍ የሚተዳደር ነፃ ሚድያ ይመስለኛል” ብለሃል እዚህ ላይ “ይመስለኛል” ስትል መቼ ይሆን “ነው” ብለህ የምታምነው? በዜግነት የሚያምኑ ኢትዮጵያዊያን የሚሰባሰቡበት መሆኑ ቀርቶ ኢሳት ሙሉ በሙሉ በሙስሊሙ ተወካዮች ብቻና ብቻ ሲሞላ ነው? ሌላው ደግሞ ኢሳት “በህዝብ ድጋፍ የሚተዳደር ነው” ብለሃል እንግዲያውስ ኢሳት በህዝብ ድጋፍ የሚተዳደር ከሆነ በኢሳት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ የሚገኘው ሁሉም ህዝብ ማለትም በሙስሊሙ እንቅስቃሴ ላይ ጥርጣሬ ያለውም ጭምር ማለት እንጂ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ማለት የሙስሊም ተወካዮች ማለት ብቻ ሊሆን አይችልም።

ወይስ አንዳንድ ቅዠታሞች እንደሚደሰኩሩት ከአቡጃ አዋጅ (Abuja declaration of 1989 http://en.wikipedia.org/wiki/Abuja_Declaration) ወዲህ ኢትዮጵያ ኢስላማዊ አገር ሆናለችና መወከል ያለባት በሙስሊም ብቻ ነው ብለው ከሚያስቡት ቡድን በመሆንህ ምክንያት እንጂ በኢትዮጵያዊያን ስብሰባ ላይ መጋበዝ ያለባቸው የሁሉም ሃይማኖት ተወካዮች ናቸው የሚለው የተ/ሚካኤል አበበ ጥሪ ባልጎረበጠህ ነበር።

ስለዚህም ኢሳት ሕዝባዊነቱን ጠብቆ ረጅሙን ጉዞ መጓዝ እንዲችል የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ ሲያስፈልግ የሁሉንም የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ አለበት እንጂ የሙስሊም ተወካዮችን ብቻ  መጋበዙ የአወልያን እንቅስቃሴ በጥርጣሬ ለሚመለከቱ ኢትዮጵያዊያን ተጨማሪ ስጋትና አደጋ መፍጠር ስለሆነ የሁሉንም ሃይማኖት ተወካዮች መጋበዙ እውነታና ጥበብ መሆኑን የሕፃን አይምሮህ ከልክሎህ ካልሆነ በቀር በቀላሉ ሊገባህ የሚገባ ገዢ ሃሳብ ነበር።

12.   በአስራሁለተኛው ነጥብህ ላይ ከላይ ከፃፍካቸው 11 ነጥቦች በባሰ ሁኔታ የተሳከረ ሃሳብ አንፀባርቀሃል። በአጠቃላይ እርግጠኛ ባልሆንክባቸው ጉዳዮች ሁሉ እንደ እርጎ ዝንብ ዘለህ እየገባህ የምታስቸግር ዘባራቂ መሆንህን ዳግም ያሳየህበት ነጥብ ነው።

በ12ተኛው ነጥብህ ላይ “እንዳልሆኑ ቢናገሩስ?” “ከማሳወቃቸው በፊት ቢሆንስ?” “ተነሳሽነት አሳይተው ቢሆንስ?” በሚሉ ኀረጎች የተሞላ በመሆኑ ስለምትጽፍበት ጉዳይ በቂ ግንዛቤ የሌለህ ለዜግነት ክብር ያላቸውን ሰዎች ለኢትዮጵያዊነት መጎልበት የሚሰጡትን ሃሳብና እርማት የማጣጣልና የማብጠልጠል አባዜ ይዞህ በጽንፈኝነት ለአንድ ቡድን ከመቆም የመነጨ ደካማና መጥፎ ባህሪ በመሆኑ ለወደፊቱ ቆም ብለህ ራስህን እንድትገመግም አደራ እላለው።

ፅሁፌን ለማጠቃለል ሳስብ በጣም የሚገርሙ ከላይ ከፃፍካቸው በበለጠ ማንነትህን ያጋለጥክበት ሃሳብ በማጠቃለያ ፅሑፍህ ውስጥ በማግኘቴ ለማጠቃለያህም ማጠቃለያ መፃፍ አስፈላጊ ሆነ:: ነገር ግን የአማርኛ ሰዋሰው ሊቅ በመሆንህ በሮማኖች ቁጥር (Roman number)  መጠቀም ትቼ ትንሽ ደስ ይልህ እንደሆን ብዬ የነጥቦቹን ተራ ቁጥር በአማርኛ ፊደላት እንደሚከተለው ገልጫቼዋለው:-

ሀ.  ተ/ሚካኤል በግልፅና በተደጋጋሚ ኢትዮጵያዊነትን አጉልቶ በማሳየት የፃፈውን ፅሑፍ አንኳር ሃሳቡን አውርደህ አውርደህ የቃላት ጨዋታ ለማድረግ ስትሞክር “የአማርኛ ክፍተት ይታይብሃል” ብለሃል ጉዳዩ ግን የአማርኛ ክፍተት ጉዳይ ሳይሆን ኢትዮጵያዊያን በዜግነታቸው ተሰብሰበው በሃገራቸው ላይ ለሚከሰቱ ችግሮች የጋራ መፍትሔ እንዲፈልጉ የማድረግ ጉዳይ ሆኖ ሳለ አንተ ግን ጭብጡ ላይ ከማተኮር ይልቅ የአማርኛ ቋንቋ ውድድር ልታስመስለው መሞከርህ እጅግ በጣም ያሳዝናል :: ነገር ግን እግረ መንገድህን  “የኢሳት ባልደረቦችን የአማርኛ ክፍተት ለመሙላት” የአማርኛን ቋንቋ ለማስተማር ሃሳቡ ካለህ ለኢሳት አስተዳደር ማመልከቻ ብታስገባ የተሻለ ነው።

ለ.     አቶ  ቶፊቅ ጀማል በኢሳት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያንን በሚያካትት መልኩ መዘጋጀት አለበት ብሎ ተ/ሚካኤል አበበ መፃፉ ኢሳትን ማጠልሸት ነው ብለሃል::  ለመሆኑ በኢሳት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ  የሁሉም ሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዙ ጣቃሚ ነው መባሉ በየትኛው አተረጓጎም (ተፍሲር) ነው ኢሳትን ማጠልሸት የሚሆነው?

የማጠልሸት ጉዳይ ከተነሳ ግን በግልፅ እንዲገባህ የሚያስፈልገው  ነገሩ “የእምዬን ወደ አብዬ ልክክ”መሆኑን ነው ። አንተንና አንተን የሚመስል ሃሳብ ያላቸው አንዳንድ በሙስሊሙ ስም የሚነግዱ ቅዠታሞች ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ኢስላማዊ በመሆንዋ ልትወከል የሚገባው በሙስሊሞች ብቻ ና ብቻ መሆን አለበት እያሉ በተለያዩ ሚዲያዎች እንደሚደሰኩሩት ( http://www.selamta.net/Downloads/Letter_to_International.pdf )  አንተም የነዚህን የቀን ህልመኞች ፈለግ ተከትለህ በቂ ግንዛቤ ሳይኖርህ ይህንን ተራ ቱልቱላ ተሸክመህ ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ በዜግነት የሚያሰባስበንን ኢሳትን ለማጠልሸት የተነሳኸው አንተ ሆነህ ሳለ የኢሳትን ገፅታ እንዳይበላሽ ምክርና እርምት የለገሰንን ሰው ጥፋተኛ ለማድረግ በመሞከርህ “የእምዬን ወደ አብዬ” ብዬ ከማለት በቀር ሌላ አማራጭ የለም። ነገር ግን በዚህ “የህፃን” አስተሳሰብህ በአንተም ፥ አንተን በሚመስሉህም በተጨማሪም እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖርህ ተፅኖ ባደረገብህም የማህበረሰብ ክፍል እጅግ በጣም አዝኛለሁ።

ሐ.   በመጨረሻም በአንተና የአንተን አስተሳሰብ ተከትለው በሚነጉዱ ሰዎች እኔንና እንደ እኔው ለኢትዮጵያዊ ዜግነት ክብር ላለን ሰዎች ተስፋ አስቆራጭ የሆነውን ማጠቅለያ ስትፅፍ እንዲህ ነበር ያልከው “ ሌላው ልትረዳው እምፈልገው ጉዳይ ቢኖር እንደው ግላዊንት ካልሆነ በስተቀር ምንን ምክንያት አድርገው ነው የሌላው የሃይማኖት አባቶች ሊሳተፉ የሚችሉት በብዙ ሺህ የታሰሩት ሙሰሊሞች፣ ከአመት በላይ ደምፃቸውን ያለማቋረጥ በሰላማዊ መልኩ እያሰሙ ያሉት ሙሰሊሞች፣ ከትምህርት ገበታቸው በጅምላም በችርቻሮም እየታፈኑ ያሉት ሙሰሊሞች፣ በምሽት እየተዋከቡ የሚገኙት ሙሰሊሞች ወንድሜ ቆም ብለህ ማሰብ ያሻሃል፡፡”

በዚህ አስተሳሰብህ አንተን ኢትዮጽያዊ ዜጋ ነህ ብሎ ለመቀበል አይቻልም ወይም ለኢትዮጽያዊያን በችግራቸው ወቅት ከጎናቸው ልትቆምላቸውና ልትደግፋቸው የሚገባህ በሀይማኖታቸው አይነት ሳይሆን በዜግነታቸው ብቻ መሆኑን የማታምን የዜግነት ክብር የሌለህ “ጨቅላ ህጻን” መሆንክን ክማረጋገጡም በላይ ለሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ችግሮች; በሃይማኖታቸው ሳይሆን በዜግነታችሀው ብቻ ለሙስሊሙ መብት ቀንና ሌሊት ሲጮሁ የከረሙትን የሃይማኖት መሪዎች : የፖለቲካ መሪዎች:  የሲቪክ ማህበራት : ታዋቂ ግለሰቦች:  የሰባዊ መብት ተሟጋቾች:  የሚዲያ ተቋማት : ጋዜጠኞችና እንደ ኢሳት አይነቱን የቴሌቪዥን ጣቢያ በግልጽ ያቃለልክበትን: ያላገጥክበትና ለኢትዮጵያዊያን ያለህን ንቀት  ያረጋገጥክበት የማንነትህ መገለጫ ነው::

v አቶ(ሼክ) ቶፊቅ ጀማል ለሙስሊሞች ችግር ሙስሊሙ ብቻ ከሆነ  መቆም ያለበት ለመሆኑ እነዚህ ሁሉ “ምንን ምክንያት አድርገው ” ነበር ለሙስሊሙ ጥያቄዎች ክሙስሊሙ ጋር አብረው በየ አደባባዩ ሲጮሁ የከረሙት?

v በዚህ ጽሁፍ ላይ በስም የጠቀስከው “አርቲስትና አክቲቪስት” ታማኝ በየነ ምንን ምክንያት አድርጎ ነበር በየ አደባባዩና በየ ሚድያው ድምጹን ሲያሰማ የነበረው?

v በኢትዮጵያዊነት ብቻ አንዳችን ለአንዳችን በመቆም የማታምን ከሆነ ታድያ እንደ አንተ አይነቱን “እጅ ነካሽ” አምነን ለዜግነት ክብር ያለውንና ኢሳትም ይህንኑ መስመር ይዞ እንዲቀጥል ሃሳቡን  ያካፈለንን የወንድማችንን የተ/ሚካኤል አበበን ምክር አዘልና የተቀደሰ ሃሳብ  አጣመህና አወላግደህ በማቅረብ ልታወናብደነን የሞከርከው?

v አንተንና ስምህ እንደሚያመለክተው ምናልባት ሙስሊም ከሆንክ የአንተ አይነት አስተሳሰብ ያላቸውን ሙስሊሞች ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆናችሁን እንዴት ለማመን ይቻላል?

v አንተንና አንተን የመሰሉ ሰዎች በሚኖሩባት ኢትዮጵያ አወሊያን መሰረት አድርጎ የተነሳውን የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ኢትዮጵያዊ ዜግነትን አጥፍተው በኢስላማዊ ዜግነት ለመተካት ነው የሚፈልጉት ብለው የሚጠራጠሩና ስጋት ያለባቸው ኢትዮጵያዊያን ቢኖሩ ጥፋታቸው ምንድነው?

v በኢትዮጵያ ውስጥ በሃይማኖታቸው ዙሪያ ችግር የገጠማቸው ሙስሊሞቸ ብቻ መሆናቸውን በዝርዝር አስቀምጠሃል ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ከሃገር ተሰደው የሚኖሩት በሃይማኖታቸው ሙስሊም ስለሆኑ ነው?

v አቶ(ሼክ)  ቶፊቅ ጀማል እነ እስክንድር ነጋ ፥ አንዷለም አራጌ ፥ ርዮት አለሙ ፥ አቶ በቀለ ጎረባና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በየ እስር ቤቱ የሚሰቃዪት  በሙሉ በሃይማኖታቸው  ምስሊሞች ናቸውን?

መካሪ ህሊና ወይም ለመካሪነት የደረሱ ሰዎች በዙሪያህ ካሉ በዚህ ሃላፊነት በጎደለው አባባልህ በሀይማኖት ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ከሙስሊሙ ጋር አብረው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ሲያሰሙ የነበሩትን ወገኖች ሁሉ የሚያሳዝን አፀያፊ ስራ ሰርተሁልና በአደባባይ ይቅርታ ልትጠይቅ ይገባሃል::

ኢትዮጵያዊያን በገጠማቸው ማናቸውንም ችግሮችና  የሰብዓዊ መብት ረገጣ ላይ አፋጣኝ መፍትሄ ሊያመጡ የሚችሉት በሃይማኖት ፥ በጎሳና በፖለቲካ ሪዮተ ዓለም ሳይሆን ከምንም በላይ በኢትዮጵያዊ ዜግነት ላይ መሰረት ሲያደረጉ ብቻ ነው።አንተ ግን ይሄ እውነታ እንዲገባህ ያልፈቀድህ በኢትዮጵያዊንት ላይ የምትቀልድ “ህፃን” ብቻ መስለኸኝ ነበር በዜግነት ክብር ላይ ያልህን ንቀት ካረጋገጥክልኝ በኋላ ግን “ሕፃን” ብቻ ሳትሆን “ከሕፃንም ሕፃን” እንጂ።

ኢሳት ለዜግነት ክብር ላላቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ የጋራ ሃብት በመሆኑ በኢሳት ክብረ በዓል ላይ የሙስሊም ተወካዮች ብቻ እና ብቻ የሚጋበዙበት መስጊድ አይደለም!!!

አስተዋይ: ታዛቢ

Asteway.tazabi@gmail.com

16 Comments

 1. There is no question that ESAT has been hijacked by extreme Amharas. The name has to change. Let every one know that ESAT cannot fool the diaspora any more. We have kep quiet for some time as ESAT was gradually dragging itself towards the mouth piece of Amhara extremists since we did not want to give an opening to the TPLF. But now, ESAT has gone over the board and it is time to say that it is the Amhara version of ETV as ETV is to the TPLF.

 2. Commentor Molla, April 24, 2013, I am sorry to read your comment, shame on you. We know that you are tplf supportor. If you don’t know ESAT is broadcasting the problem of all Ethiopians. It is for all Ethiopians

 3. Why not focus on the issue facing all Ethiopians instead of insulting a particular ethnic group. What is wrong if those who work at ESAT are Amharas? Brother Molla, you have a long way to grow. It’s sad that we have people who think like Molla.

 4. Knowingly or unknowingly Tekelemichael Abebe has been a controversial figure in recent times. His latest comment on the displaced Amhara people from Benishangul region has angered many people. He deliberately referred them as “Amharic Speaking People” instead of Amhara people to deny their suffering. Tekle knows that those people Woyane kicks out of Benishangul and other parts of Ethiopia are not just Amharic speaking people, but they are Amharas. Many non-Amhara people including himself speaks Amharic, but they are not been displaced. Ato Shegute and those TPLF cadres who are committing genocide against Amhara speak Amharic, but that doesn’t make them Amhara.

  • Alex,
   You are absolutely right Tekelemichael has been talking and writing anti Amhara propaganda. I have noticed that for quite sometime now. It is very sad.

  • what are you talking about? yes there is no amhara but amharic speaking people. We are ethiopians don’t try to bring your ethnich policy give it to your master woyane and his mental infrierity group. Again no one you will get call himself amhara. I am amharic speaker but no amhara, my family never raise me by my race for fact never told me i am amhara. I never call my self amhara too. So be it there is nooooo amhara but one ethiopia

 5. Molls use your name. Do not be ashamed of your name. Stop you shit that is of no use to Ethiopia. What you wrote reflects you level of thinking. Shallow. Get off the mud you slept in and walk non your feet. A brain is in the head and does thinking. Get it?

 6. ESAT & Tamagn you better be back to your senses I mean if you still have some left of course. Tofiq Jemal loooool learn how to be an Ethiopian guys like you need integration courses

 7. i closely follow what Esat is doing ,as genuine social media ,to advance the struggle of the Ethiopian people against the genocidal ,looters, majerat meche of woyane by way of feeding accurate information and facts on the magnitude of torture .killings .lootings evictions and other in human acts of crimes committed by graziani like rule of woyane .If ESAT would have not been in existence ,we could have not been able to witness the grand conspiracy manifested itself in what we call Ethnic cleansing of the Amharas . Had Esat would have not been operating in full swing , folks!!!! we had no any chance to get information on Afars drought situation and the number of people died due to deliberate act of negligence by woyane and its stooges. Now ESAt seem to have gained popularity among poor and under dogged Ethiopians and thus pledge to render any support knowing that it is the only instrument we have at hand to bring all Ethiopian democratic forces together to device ways and means to wipe the woyane thugs out and throw to dust bin of history. It would not be surprising if woyane and its sleeper agents disparage the service of ESAT and categorically denounce and brand it as the voice of the Extremist Amharas. In fact , what ESAT, so far has done is highly commendable .This was evidenced from the woyane’s accusation and its deep concern for ESaT to being the only and only media out let of the people. I hope it would continue until the Ethiopian people advance the anti woyane struggle to its logical conclusion of establishing DEMOCRATIC ETHIOPIA where all Ethiopians equally participate in the political,economic and social life of the nation. Death to woyane and crumb pickers

 8. Meles did a great job of balkanizing the country into ethnic factions and drawn power out of the tension. He did excellent job of killing the democratic process that he started really well. He hated the idea of galvanizing Ethiopians, as people, as Ethiopians, to come together and work for the country with vision. He fought and died entrenched in the narrow shell of ethnic identity. He was not great enough, selfless enough to embrace the idea of loving others, taking care of others, and carving Ethiopianness. He was very smart in being small and narrow. The mark of greatness is selflessness. Greatness is forgiving, and broad. He lacked those qualities, Meles started displacing Amhara out of Gambela and Benishangul for the safety of Tigrai elite investors but he told to those insane Amhara representatives that the displacement is for the purpose of the country security, because of deforestation

 9. I am not blaming molla or any other intruder in this regard. I am blaming Tekle and those who are quarreling each other for some gutter article which does make any impact on the people struggle for freedom. Tekle or those who are arguing each other may think that they are doing something good. But what they did is opening up some kind of crack for those woyan’s and their banda’s effort to splash cold water on the growing unity of all opposing forces. If the issue written by Tekle was really important, we have heard something/ response from ESAT or other concerned bodies. So I advise every one to ignore this trash talk and concentrate on the main agenda of saving Ethiopia from destruction. I also advise those who are writing these trashes back and forth to shut the hell up and focus on the main goal.

  • xanadu
   well said man , we all need to ignore such small bs and move foreward n save our country. most of all. pls i beg all z ppl to ignore all trash talker n tplf supporters who comments on a social media like this one just to provoke and get u mad with arguing with them, there is no point of that just express ur opinion and if u can, attend varies meetings and discussion panels in ur city and help to make a difference. tnx

 10. Hi all commenters

  It seems like you didn’t read the article because you are talking about ethnic issues or about importance of ESAT. but the article is all about saving ESAT from being hijacked by propagating only for the leader of “Alweliya” based movement because they are millions of Muslims and Christians who don’t support this movement back home.

  Read the articles carefully before you comment on it. Victory to all Ethiopians!!

  • REspect humanity
   do u know the meaning of ” respect humanity”, i bet u don’t. if u do, u will understand why we say our Muslim brothers question is a case of basic humanity. any one can belive in anything, that’s their individual and collective rights, regardless if they are supported by saudi or somalia. as long as they r n’t against to others religon, they have the right to follow what ever they belive in with out goverment interference. i know u support ESAT and u want to save it from such invasion , but the fact is ESAT is a voice for all ethiopians whom their rights r violated & the issues of the muslims are one of that. tnx

 11. On the link between “Mengist vs. Haimanot” … It’s time for fellow Ethiopians to question the hithereto unquestionable “make believe” tact – Art that (as a meta theory) fathers the making of politics. By virtue of being an aspect of Art, politics is ‘a making’… thanks to the ‘white (paper) mythology’. That proximate tact -‘WRITING’- performs the drama and owes it a metaphysical present. Meles, Endrias, Paul (late Pat.) etc used this manupilative trick … to format the-long-survived country and her people. In the guise of goodness, “haimanot and mengist” are at the forefront of the template… which applies to sujects, but the makers. Untill we install our wills, best to nourish our transactions by retrieving one of the Oldest but fresh (like morning news) humane-ware – founting out of our most cherished ‘qin-libwona’. ‘kemayawqut mel’ak …’ indil bihilu.

 12. This is reply to Molla..
  Why you just don’t come out and tell us ur real name is Hagos..It is people like u
  who live in different world with different face. You might be active member of Woynes. Have a stand. I dont think u have any knowlege of what ESAT is contibuting for all ethiopians. Get a life

Comments are closed.

Ya twld
Previous Story

በደም የተከበረ የዓለም ሠራተኞች ቀን፤ ሜይ ዴይ

Next Story

የአንድ ለ አምስት ጠርናፊዎች ጭምር አለመምረጣቸው ኢህአዴግን አስደንግጦታል

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop