የአንድ ለ አምስት ጠርናፊዎች ጭምር አለመምረጣቸው ኢህአዴግን አስደንግጦታል

April 24, 2013

ፍኖተ ነፃነት 

ኢህአዴግ  የሚያዚያ 13 ቀን 2005ዓ.ም. የተደረገውን የአዲስ አበባና የደቡብ ክልል ወረዳዎች ምክር ቤት ምርጫ 1 ለ 5 ጥርነፋ ኃላፊነት የተሰጣቸው ግለሰቦች ግዴታቸውን አልተወጡም በሚል በግምገማ እያስጨነቃቸው መሆኑ ተሰማ፡፡ ቀደም ሲል ሚያዚያ 6 ቀን የተደረገውን የአዲስ አበባ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና  የአካባቢ ምርጫ ከዚህ በፊት ኢህአዴግ የልማት ሰራዊት ሲል ከህዝብ ግብር በሚገኝ ገንዘብ ደመወዝ እየከፈለ ለኢህአዴግ ፖለቲካ ቅስቀሳ እንደሚሰሩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ቢያቀርቡም የ2005ዓ.ም. ምርጫ ላይ ግን ኢህአዴግ እራሱ ማስተባበል ያልቻለውን የምርጫ ሰራዊት በማለት 1 ለ 5 ጥርነፋ ስራ በይፋ አሰርቷቸዋል፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ ከጠርናፊዎቹ የጠበቀውን ውጤት እንዳላገኘ ተጠቁሟል፡፡ በዚህም ምክንያት በተለይ በአዲስ አበባ ሳምንቱን ሙሉ እስከ ሚያዚያ 13 ቀን 2005ዓ.ም. ምርጫው እስኪጠናቀቅ የየወረዳ ኃላፊዎችና የጥርነፋ ኃላፊነት የተሰጣቸው የኢህአዴግ አባላት በየቤቱ እያንኳኩ ቃል የገቡላቸውን “ሄዳችሁ ምረጡ” የሚል ትዕዛዝ እየሰጡ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ጠርናፊዎቹም “የገባችሁትን ቃል አላከበራችሁም” በሚል በተለይ በአዲስ አበባና ደቡብ ክልል  ለሚያዚያ 13ቱ ምርጫ በየቤቱ እየዞሩ እንዲቀሰቅሱና የያዙትን ካርድ ይዘው ሄደው ድምፅ እንዲሰጡ በተሰጣቸው  ትዕዛዝ  መሰረት አልተገበራችሁም በሚል አሁንም ሄዳችሁ በአግባቡ አልቀሰቀሳችሁም፣ ቀደም ሲል ቃል ያስገባችሁትም ቢሆን የውሸት ነው ስለዚህ ተልኳችሁትን አልፈፀማችሁም ሲል ቁጣውን ያወረደባቸው መሆኑንና ወደፊትም እርምጃ ሊወስድባቸው ማሰቡንም የፍኖተ ነፃነት ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡ ይህንንም ሁኔታ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ባልደረባ በተግባር የተመለከተ ሲሆን በተለይ የየወረዳው ሰራተኞች በየቤቱ እያንኳኩ በማስከፈት ወረቀትና እስክሪብቶ ይዘው የትኛው ምርጫ ጣቢያ ነው ካርድ የወሰዳችሁት? ከቤታችሁ ስንት ሰው ካርድ ወስዷል? ከመካከላችሁ ሄዶ ድምፅ ያልሰጠ አለ እያሉ ይናገሩ እንደነበር ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በአዲስ አበባ አንዳንድ ወረዳዎች ጠርናፊዎችም ጭምር ድምፅ ለመስጠት አለመሄዳቸው ይበልጥ እንዳበሳጫቸው ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡ ከዚህና ከውጤቱ ጋር በተያያዘ ያነጋገርናቸው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ጸሐፊ አቶ ወንድሙ ጎላ በበኩላቸው ምርጫው በሰላም ከመጠናቀቁ በስተቀር የተለየ ነገር የለም፤ ውጤቱን በሚመለከት ውደ ፊት ተጣርቶ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

1 Comment

  1. የአንድ ለአምሰት ጠርናፊዎች የተባሉት ወያኔን አለመምረጣቸው አይደንቀኝም። ይልቅስ እኔን የሚደንቀኝ ኢህአዴግን ወክለው ለመወዳደር ፈቀደኞች የሆኑ ሰዎች መኖራቸው ነው።

Comments are closed.

Teklemichael Abebe
Previous Story

“ሕፃን ካቦካው – ልጅ ያቦካው ይሻላል” (ለተክለሚካኤል አበበ አስተያየት የተሰጠ ድጋፍ)

Next Story

በቤንች ማጂ በተነሳ ግጭት ሶስት ተማሪዎች ቆሰሉ

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop