April 14, 2013
6 mins read

የሕዝብ ልጅ ምንግዜም የሕዝብ ነው!

ግዛው ስለሺ ጃኖ መፅሔት ቅፅ 1 ቁጥር 2 ላይ የሰማኒያ አመቱ አዛውንትና የአምስት አመቱ ፈረሳቸው ብሎ የፃፈውን ፅሁፍ ላነበበ ሰው በእርግጠኝነት ስለፀሐፊው የሚኖረው አመለካከት የተዛባ ነው የሚሆነው፡፡አቶ ግዛው ማመዛን የከበደው ሰው ለመመሆኑም መስካሪ አያሻም፡፡ በግል ፕሬስ ማሊያ የሕዝብ ልጆችን ላማጥላላት ታጥቆ የተነሳ ባንዳ መሆኑን ከፅሁፉ ጭብጥ መረዳት አያዳግትም፡፡
የሰማኒያ አመት አዛውንት የተባሉት ፕሮፌሰር መስፍን በአምስት አመት በተመሰላው ተመስገን ደሳለኝ መፅሔትና ጋዜጣ ላይ የሚያወጡት መጣጥፎች የአንባቢን ቀልብ የሚስቡና ጠማማውን ለማቅናት የሚታትር፤ ገዥውን የሚያስተምር መሆናቸውን የዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ በፅኑ ያምናል፡፡ እኚህ ምሁር በስተርጅና ፈርሆንን የሚቃወሙበት ምክንያት የስልጣን ጥማት ስላላቸው ነው ተብሎ የሚታመን እንኳን ቢሆን በፍትህ፤በአዲስ ታይምስ እንዲሁም የእሳት እራት በሆነችው ልህልና መፅሔት ላይ ቋሚ አምደኛ በመሆን የሚያወጧቸው ፅሁፎች የበሰሉ ትችቶችና ፍትህና ዲሞክራሲን ናፋቂዎች ለመሆናቸው ማንም ሊመሰክረው የሚችለው አቅ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ አቶ ግዛው ስለሺ ምንም እንኳን ስለፕሮፌሰሩ የኋላ ታሪክ ቢነግረንም ምሁሩ ላይ ያለውን የመረረ ጥላቻ ያሳብቁበታል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና በመላው አገሪቱ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ምሁራን ሊነግሩን ያልደፈሩትንና ከመሞት መሰንበት በሚል አገርኛ ብሂል አድር ባይነትን መርጠው አፋቸውን ለጉመው በተቀመጡበት ወቅታዊ የአገራችን ችግሮች ላይ እንዲሁም የታሪክ አመክንዮ ላይ እኚህ ምሁር የሠላ አስተያየቶችንና የተጣመመ የታሪክ አተያዮችን(ኢትዮጵያ የመቶ አመት ታሪክ ያላት አገር ነች እና የመሳሰሉትን) በማቅናትና እውነትን በመመስከር ለሚያበረክቱት አስተዋፅሆ ምስጋና መቸር ሲገባን የስልጣን ጥማተኛ አስመስሎ ማብጠልጠሉ ነገ ከአድር ባይነት ተላቀው በቀናነት ለመስራት ለሚነሱ ምሁራን ታላቅ እንቅፋት መሆኑ እሙን ነው፡፡
ሌላው የአቶ ግዛው የተመረዘ ብህር ያረፈው ወጣቱና አንጋፋው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ነው፡፡ መቼም አንድ አመዛዝናለው ከሚል ሰው ሊያውም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ደፍሮ የማብጠልጠል አቅም ይኖረዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ይህ ወጣት ለብዙዎቻችን ምሳሌ የሚሆን ታላቅ ብዕርተኛ ነው፡፡ስለመንግስት በግልፅ ልናውቃቸው ያልቻልናቸውን የተደበቁ ምስጢሮች ፈልፍሎ በማውጣት፤ወጣቱም የፍትህና የዲሞክራሲ ጥማቱን መቁረጥ የሚችልበትን መንገድ ከታሪክና ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር በማቀናጀት ተስፋችን እጃችን ላይ መሆኑን ደጋግሞ የሚነግረን የኢትዮጵያ ትንሳኤ አብሳሪ ውድ ልጃችን ነው፡፡ ተመስገን እንደሙያ አጋሮቹ ወደ አሜሪካና አውሮፓ አገራት በማምራት የግል ሕይወቱን ማበጀት አሊያም ቤቱን ዘግቶ መቀመጥና የፋሽን መፅሔት (ሁሉም የፋሽን መፅሔት ለማለት አይደለም) በማዘጋጀት ወጣቱን ራዕይ አልባ ማድረግ አቅቶት አይደለም ከእሳት ጋር ጨዋታ የጀመረው ይልቁንም ድሃውንና ፍትህ ናፋቂ የሆነውን የኢትዮጵያን ሕዝብ በቆራጥነት ለማገልገል በሚል መነሳቱን ከአሳዳጆቹ ሁኔታ እንኳን መረዳት አያዳግትም፡፡
ይህን የሕዝብ ልጅ ተላላኪ በማስመሰልና የሰዎች መጠቀሚያ እየሆነ እንደሆነ በመሳል አቶ ግዛው ሊጠቀም የሚችለው ነገር ምን ሊሆን እንደሚችል ፈፅሞ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ምናልባትም የፈርሆን እጆች እርዝመታቸው የግሉንም ፕሬስ ሳይዳስሰው እንዳልቀረ ጥርጣሬው ጎልቶብኛል፡፡ በግሉ ፕሬስ በመጠቀም የግሉን ፕሬስ ትጉሃን በተለመደ የማጥላላት ዘመቻው ከሕዝብ ላማቃረን እየሰራ ለመሆኑም ተቋሚ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት አድሮብኛል፡፡
ቸር ይግጠመን!

Latest from Blog

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

Go toTop