July 18, 2024
16 mins read

ሰማያት ጠ/ሚ አብይ ላይ አጉረመረሙ

abiy the Killerነገሩ እንዲህ ነው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ ሐምሌ 6፣ 2016 ዓ.ም. ጠ/ሚ አብይ በእናትዋ ጎንደር ጣና ሃይቅ ዙሪያ ጎርጎራ ላይ ብቅ ብለው ነበር፡፡ ከዚያ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ደግሞ ከጂማ እስከ ወለጋ ደቡብ ኢትዮጵያን ጨምር ከሰማይ የተሰማ ከባድ ፍንዳታ ተከሰተ፡፡ ይህንንም ተከትሎ በየአካባቢው ያለ ሰው ሁሉ ተሸበረ፣ ፈራ፣ ተጨነቀ፡፡

በኋላ የፍንዳታው ምስጢር ከሰማይ የወረዱ ድንጋይ ሽርፍራፊ ሜትሮይትስ ናቸው የሚል ለጥናት መነሻ የሚሆን ፍንጭ ተሰጠ፡፡ ታዲያ ጠቅላዩ ህዝቡ ምን ይላል ብለው ጠየቁ መሰል ሰዎች አንድ ነገር ሹክ ሳይሏቸው አልቀረም፡፡

መቼም እንደየ ባህሉና ወጉ ህዝቡ እንዲህ ላሉ ሰማያዊ ክስተቶችን ታላቅ ትርጉም ይሰጣቸዋል፡፡ አንድ ሙኢሊም የጂማ ሼክ ናቸው አሉ በኦሮሚኛ “ሳሚን ናመ ከና ኢራቲ ጉንጉማ” አሉ፡፡ ሰማያት ምንነው እዚህ ሰው ላይ አጉረመረሙ እንደማለት ነው፡፡ ይኽ ሰው የተባለው ደግሞ ጠ/ሚ አብይ ነው፡፡ ጠቅላዩም የህዝቡን መሸበር ሰሙ፡፡ ኦርቶዶክሱ ደግሞ ይህ ምልክት የመንግስት ለውጥን ያሳያል በማለት ድርሳነ ኡራኤል ላይ ከተጠቀሱት ሰማያዊ ምልክቶች ጋር ማዛመድ ጀምሯል አሏቸው፡፡ ጠቅላዩም ተሸበሩ፡፡ አንዳንዶቹ እንደውም ደብረዘይት ዙቃላ ተራራ ላይ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመብረቅ ቆሪጥን በመብረቅ ፈንክተው ካባረሩበት ተአምር ጋር አያይዘው የሐምሌ አቦ በዓልን ተንተርሰው የአቡዬ ቁጣ ነው ያሉም ነበሩ አሉ፡፡

ነገሩ በዋናነት ጠ/ሚ አብይ በተወለዱበት አካባቢ ስፍራ ቢከሰት እንዲህ ያለ ትርጉም ተሰጠው፡፡ ክስተቱን ተከትሎ ጠ/ሚ ሚኒስተሩ አንስት ሜጀር ዋን (ዋናዎቹን) ነብይቶች በአስቸኴይ አሰባሰቡ፡፡ ያ ዲ/ን(?)ም ነበረበት አሉ፡፡ የሴቶቹ ጸሎት በብርሃን ፍጥነት መልስ አገኘ መሰል፣ ጠቅላዩ የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ12፣28-29 ላይ ያለውን ጥቅስ እንዲያነቡ የጌታን ድምጽ እንደሰሙ ነገሯቸው፡፡ መልሱ ሁለት ሰዓት ባልሞላ ግዜ ደረሳቸው፡፡

እሳቸውም ያን የወንጌል ክፍል አንብበው እፎይ አሉ፡፡ ጥቅሱ የሚያትተው በክርስቶስና እግዜአብሔር አብ መካከል ስላለ ምልልስ ነው፡፡ እንዲህም ይነበባል፣ “አባት ሆይ፣ ስምህን አክብረው፡፡ ስለዚህም አከበርሁት፡፡ ደግሞም አከብረዋለሁ የሚል ድምጽ ከሰማይ መጣ፡፡ በዚያ ቆመው የነበሩትም ሕዝብ በሰሙ ግዜ፣ ይህ የነጎድጓድ ድምጽ ነው አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ መልአክ ተናገረው አሉ፡፡”

ይህን ወንጌል ስናነበው ክርስቶስ ሊፈጽመው ያለውን ስራና ተልእኮ፣ ሰዎች ግን ሰለ እሱ ተልእኮ መረዳት እንዳለቻሉ፣ ይህ ድምጽም የመጣው ለሰዎቹ ለምስክርነት ከአብ ዝንድ እንደሆነ የሚገልጽ ነው፡፡ እንግዲህ የጂማው ክስተት በአጭሩ ከእግዚአብሔር ለጠ/ሚ አብይ የወረደ የክብር ድምጽ ነው የሚል አንደምታ ተላብሶ ተተረጎመ፡፡

ጠ/ሚ አብይ ይህችን መገለጥ ይዘው በበነጋታው ጎረጎራ ላይ ለምርቃት ተገኘኝተው ንግግር አደረጉ፡፡ በዚህ ንግግራቸው ላይ እንደ ሌላው ግዜ እኔ እንዲ አደረጋለሁ፣ እኔ እንዲ አለሰራም አላሉም እኛ የሚለውን ቃል መርጠዋል፡፡ ምክነያቱም የጎርጎራ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ፍስሃ አሰፋ በምርቃቱ ላይ አብይ የዚህን ኢኮ ሪሶርት ሃሳብ በማቅረብ፣ በመከታተልና አቅጣጫ በመስጠት ዋነኛው መሆናቸውንና ከአስራ ሰባት ግዜ በላይ በአካል ተገኝተው አመራራር እንደሰጡበት ተናግረውላቸዋልና፡፡

ጠ/ሚሩ በንግራቸው መጨረሻ እንዲህ አሉ “…በመጨረሻም የሰኬታችን ምስጢር…የፈጣሪ አብሮነት ነው፡፡ ፈጣሪ እየደገፈን ብቻ ሳይሆን ከሰማይ ወርዶ ከእኛ ጋር እየሰራ ነው፡፡…እሱ ከእኛ ጋር እካለ ድረስ እንሰራለን፣እንጨርሳለን፡፡ እርሱ ሲጨርስ እኛም ለመጨረስ ዝግጁዎች ነን፡፡ ከዚያ በፊት ያሉ ከንቱ ሙከራዎች ግን ስራ ከማደናቀፍ አልፈው ውጤት ሰለማያመጡ የኢትዬጵያ ህዝብ ማወቅ …አለበት…፡፡” እኔ ደግሞ ለተዛማጅ ጥቅስነት ይሄን ጨመርኩላችሁ፣ “ኢየሱስ ግን፣አባቴ እስከ ዛሬ ይሰራል እኔም ደግሞ እሰራለሁ ብሎ መለሰላቸው” ዮሐ ም. 5 ቁ17

የጠ/ሚ ንግግር ስሰማ የጋዜጠኛና ገጣሚ አስረስ አሰፋው ወስን ኃ/ ስላሴ ግጥም ነው ትዝ ያለኝ፡፡

እግዜር የምንለው ከሰማይ ላይ ወረዶ

ቤት አይሰራልንም ግድግዳ ገድግዶ፣

አላወቅንም እንጂ ሰውም እግዚአብሔር ነው

ይችላል መከራን ደስታ ሊያደርገው፡፡

ጠ/ሚ አብይ እግዜር ከሰማይ ወርዶ ከእሳቸው ጋር እየሰራ መሆኑን ነግረውናል፣ ነገር ግን የስራ ድርሻውን አልገለጹልንም፡፡ አሽዋ አቡኪ ይሁን መሐንዲስ? መቼም የእግዜሩ ቤተ መቅደስ የሆነውን ሰው እንደጉድ በሚሊዮን እየፈረሰ(እየገደሉ) ባሉበት ሃገር፣ ለዚህም ዋንኛው ምክነያቱ የብልጽግና ፖለቲካ መሆኑ እየታወቀ፣ ሪሶርትና ሎጅ በመስራት የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ ማለት ምን የሚሉት መንፈሳዊ ሽሙጥ ነው? የሚገርመው ነገር ደግሞ እዛው ንግግራቸው ላይ ሴንጋፖርን መሪዋን ግዜ ሰጥተው ሲተነትኑባቸው መታየቱ ነው፡፡

እውነት ነው ሴንጋፖር ውብና ድንቅ ከተማ ነች፡፡ ነገር ግን በአለም ላይ እንደሷ የተዋቡ አያሌ ከተሞች አሉ፡፡ ሴንጋፖርን በሰላሳ አንድ አመት የጠ/ሚርነት ዘመናቸው (1959ዓ.ም. – 1990ዓ.ም.) ቀየሯት የሚባሉት ሊ ኩአን የው በእግዜር መኖር የማያምኑ አግኖስቲክ ነበሩ፡፡ የማያውቁት እግዛብሔር ከሰማይ ወርዶ ከጎናቸው ሳይቆም ነው ውብ ከተማ የሰሩት፡፡ ከ80% ሲንጋፖረዋያን ደግሞ ክርሰቲያኖች አይደሉም፡፡ ሴንጋፖርን ለመሆን ጠ/ሚ አብይ ሽር ጉድ እያሉም አይደል? ታዲያ እግዜር ከሰማይ ወርዶ ከጎናችን ቆማል ጨዋታን ምን አመጣው?

እዚህ ላይ ጠቅላዩ ግዜና ቦታ እንደሚምታታበቸው ለማወቅ ብዙ መጣር አይጠበቅብንም፡፡ ግልጽ ነዋ! የትናንቱን ለዛሬ፣ የነገውን ለትናንትና አርገው ቢናገሩም፣ ሆዳቸው በልቶ የማይጠረቃው የቅርብ ተከታዮቻቸው “ለእናት ሃገር ሲሉ ዞር አለባቸው…” ይሉ እንደሆን እንጂ ምንም አይሉም፡፡

አፍሪካ ውስጥ ቀኝ ገዢዎች የሰሯቸው ቆንጆ ከተሞች አሉ፡፡ ታዲያ እግዜር ከአፓርታይድ ጋር ቆሞ ሰራቸው እንበል እንዴ? ለምንድንስ ነው ጠ/ሚ አብይ እግዜር ስራውን ሲጨርስ እናበቃለን የሚሉት? እዚህ ጋር ነው እንግዲህ ፓርላማ የሚገባው በምርጫ ሳይሆን በስዩመ እግዚአብሔርነት ብቻ መሆኑን የሚነግሩን፡፡ አይ ሴኩላሪስም የት ነሽ ያለሽው? አወይ! “ሐይማኖት የግል ነው ሃገር የጋራ ነው!” ያሉ ነገስታት እንዳለነበሩን ሁሉ፡፡

የእሳቸው እግዜር እንደሆነ በኦርቶዶክሱም፣ በሞስሊሙም ሆነ በፐሮቴስታንቱ ዘንድ የሚታወቅ አይደለም፡፡ ለዚህ መስረጃ ወለዬው አለ ሲሉ የሰማሁትን ላጋራችሁ፡፡ ባለፈው የአረፋ በዓል ቀን ጠ.ሚ አብይ እንደለመዱት ከቁራን ጠቅሰው ፖለቲካቸውን ሰሩ፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት፣ “ነብዩ ኢብራሂም በልጃቸው በእስማኤል እንደተፈተኑት እኔም እየተፈተንኩ ነው…”

ይሄንን የሰማ ወለዬ እንዲህ አለ አሉ፡፡ “አቦ! ይህ ሰው የማይተወንሳ? ነበዩ ኢብራሂም በልጃቸው ኢሰማኤል ተፈተነ የሚለው ቅዱስ ቁራን ነው፡፡ የክርስቲያኖቹ መጠፍ ደግሞ ነብዩ ኢብራሂም በልጃቸው ይሰሃቅ ተፈተነ ነው የሚለው፡፡ ምነው ይህ ሰው በማያምንበት ተሸርጦ ቀልብያችንን ለያነሆልል ፈለገሳ? የዚህ ሰው መጨረሻ በቂያማ ቀን ስርፋው ወየት ይሆን? አላህ ሌላ የተለየ ስርፋ ሳያበጅለትም አይቀር…” ወለዬው ነቅቷል፡፡

በየአመት ባእሉ ላይና በየፖለቲካው ስፍራ ምን ያለሆኑት አለ? የትኛውስ ቅዱስ ተረፋቸው? እየሱስ፣ ሙሴ፣አብረሃም፣ ሰይድና እንቶኔ፣ ደመራው፣ አረፋው…፡፡ ሁሉንም የፖለቲካ ምጣዳቸው ማሟሻ ጥፍጥሬ አድርገዋቸዋል፡፡ እንድ ግዜ ጠ/ሚ አብይ በስብሰባ ላይ፣ እግዜር የለም ብሎ የመጣውን ኮሚኒስት ስርዓት ትተው፣ እግዜር አለ ብለን የመጣንውን እኛን 666 ይሉናል አሉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን 666 እኮ እግዜር የለም ብሎ የሚነሳ አይደለም፡፡ እንደውንም መጀመሪያ ክርስቲያን መስሎ ነው የሚወጣው “ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፣ የበግ ቀንዶች የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት” ዮሐ ራእይ 13፣ 11- 18 እንግዲህ የበግ ቀንድ የሚለው ትርጉም ክርስቲያን የሚመስሉ መሪዎች ማለት ነው፡፡ ያው ክርስቶስ የአለሙን ሃጢያት የሚያሰተሰርይ የእግዚአብሔር በግ ተብሏልና፡፡ የጠ/ሚሩን ንግግር በሰከነ መንፈስ ለሚያሰተውለው ጥንግርግሩ የወጣ ነው፡፡

እንግዲህ የበሻሻው ጠ/ሚ አብይ የጂማው ሼክ ላነሳው ጥያቄና ለህዝቡ ግርታ እግዜር ከሰማይ ወርዶ ከጠገባቸው እንዳለ፣ አብሯቸው እንደሚሰራና እግዜር ስራውን ሳይጨርስ ማንም ምን እንደማያደርጋቸው በመናገር መልስ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም ደጋፊዎቻቸውን ለማረጋጋት ሞክረዋል፡፡ ያ የመሃበራዊ ጉዳይ አማካሪያቸው ዲ/ኑ(?) ግን የፕሮቴስታንት ነብያቱን ትርጉም ከመደገፍ በቀር የደረሰበትን አልነገራቸውም፡፡

ለጠቅላዩ ጥያቄ መልስ ፍለጋ መጽሐፍትን ሲያገላብጥ የዲቦራ ታሪክ ላይ ደረሰ አሉ፣ ወፎቹ ሹክ እንዳሉን፡፡ ታሪኩም እንዲህ ነው፡፡ ያን ግዜ እስራኤላውያን ከከነአናውያኑ ጋር ይዋጉ ነበር፡፡ የእስራኤላውያኑ ጦር መሪ ባራክ ከነቢይቱ ዲቦራ ጋር ለሰልፍ ወጣ የኢያቢስም ሠራዊት አለቃ ሲሣራ በዚያ ነበር፡፡

ጦርነቱ ሲጋጋል ሲሣራ በሴት እጅ ተገደለ፣ አሟሟቱም የከፋ ሆነ፡፡ የእግዚአብሔር እጅ በሲሶራ ላይ ከሰማይ እንዴት እንደተገለጸ ዲቦራ እንዲህ ስትል ቅኔውን ተቀኘች፣ “ክዋክብት ከሰማይ ተዋጉ፣ በአካኼዳቸውም ከሲሳራ ጋር ተዋጉ፡፡ ከድሮ ጀምሮ የታወቀ ያ የቂሾን ወንዝ፣ የቂሾን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው…” መጽሐፈ መሳፍንት ም5፣ 20-21 ሲሶራን ደግሞ በጆሮ ግንዱ የድንኳን ካሰማ ቀርቅራ የገደለችው ሴት ነች፡፡ ታዲያ ይኼንን ምን ብሎ ለጠቅላዩ ይንገራቸው? ኋላ ሊቀ ነቢይቱ ይህንን ብትሰማ “ዝንዬ ቢሮ ውስጥ ዘንዶ ተጋድሟል…ለእሷ እንዳትነግራት…” ባለችበት አፏ ያ ያፈረሰ ዲያቆን ላይ ፈጥነህ ውጣበት ብትልስ? ወቼ ጉድ! እንግዲህ ነገረ ጂማ ወበሻሻን እንዲህ አድርገን በእነሱ አይን አየናት፡፡

 

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮ ቫንኩቨር፣ ካናዳ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

Go toTop