ፍኖ ባለውለታችን ነው / የትግራይ እና የአማራ ህዝብ አንድ ነው/ ከዳንግላ ማረሚያ ቤት በፋኖ ነፃ ከወጡ የትግራይ መኮነኖች ጋር የተደረገ ቆይታ

December 28, 2023

 

4 Comments

  1. ወደ ትግሬ ስትመለስ ይህን ካልክ መልካም ነው ለማንኛውም ጊዜው ይፍረድ። አማራው ግን ሰብአዊነቱን ዲሲፕሊኑን ሰውነቱን አሳይቷል።

  2. ኢትዮጵያዊነትን ለማፍረስ ሕወሀት ከኦነግ ጋር በመቆም ኢትዮጵያን ለብዝበዛ እንድትመች 9 ክልሎች ፈጥሮና ተጠያቂነት የሌለበት፣ ፌደራነትም ሆነ ዲሞክራሲያዊነት ያልነካው የጭቆና አገዛዝ ሕገ መንግሥት አርቅቆና አጽድቆ፣ በስሙ በሚነገድበት በጀግናው የትግራይ ሕዝብ ስም በመጠቀም የሕወሀትን ሹማምንት ሥልጣንና ሰፊ ሀብት ለማስጠበቅ ብቻ የትግራይን ድሀ ወጣት ለጦርነት ማግዶ፣ ከዘመናት ታሪካዊ አጋርነቱ ሌላ ከትግራይም ሕዝብ ጋር አማራ በጋብቻ መተሳሰሩ ተረስቶ፣ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ አማራ በጠላት ዓይን ታይቶ ለእልቂት፣ መፈናቀልና መገደል ሕወሀት መሪ መሆኑ፣ ለዛሬው የኢትዮጵያ አንድነት፣ ሉዓላዊነትና ሰላም መናጋት አብቅቶንም፣ ፋኖ የቅርቡን ውድቀት ሳይሆን ታሪካዊውን የሕዝቦቻችንን የደምና አጥንት ትሥሥር በማገናዘብ ለሕወሀት እስረኞች በጎ ሥራ መሥራቱ ከጀግና አባቶቻችን የመጣ ውርስ ነው። የትግራይ ሕዝብ በስሙ የተነገደበት ውድቀት እንዳይደገም በአባ በዝብዝ ካሣ ልጅነቱና ኢትዮጵያዊነቱ መሠረት ከወንድሙ ከአማራ ሕዝብ ጋር ቆሞ በአንድነታችንም ሆነ በሃይማኖታችን ላይ እንደማይደራደርና አማራንና ትግሬን አጣልቶ በመከፋፈል ኢትዮጵያዊነትን ለማውደም የተሸረበውን ሴራ ለማክሸፍ ከፋኖ ጋር እንደሚተባበር በቅርቡ እንደሚያሳይን እምነታችን የፀና ነው።

  3. ነገሩ እንደተባለው ከሆነ ማለፊያ ነው። ሰው ሆኖ የሰው ልጅን ሲያከበር ማን ይከፋል? ግን በባዶ ስድስትና በሌሎች የወያኔ የድብቅና የይፋ እስርቤቶች ከምድር ስር ከአፍር ጋር ተደባልቀው ለዘመናት የታሰሩትን ማን ያስፈታቸው? እነዚህ አሁን በፋኖ ኦፕሬሽን ተፈቱ የሚባሉት ዳንሻ ላይ ምን ወንጀል ሰርተው ነበር? በእግጥ ከእስራት እስከ ሞት የዳረጋቸው የትግራይ ልጆች በመሆናቸው ብቻ ነው? የሃበሻ ምድር ትልቁ ችግሯ ግፈኞችን እያቀፈች የሞቱላትን መግደሏ ነው። ያኔም የሆነው ዛሬም የሚሆነው ያው ነው። በግፍ የተጨፈጨፉትን ዋይታና ደም እየረሳን፤ ለወገን ለሃገር አንድነት የተፋለሙትን አንዴ ዘብጥያ ሲወርድ እየዘነጋን መትመም ነው። በዚህ ሁሉ ግን የሚጎዳው ሃገሬ ወገኔ የሚለው ተላላ ገበሬና ተፋላሚ ነው።
    አሁን እንሆ በትግራይና በአማራ አካባቢዎች ድርቁ ከማየሉ የተነሳ ሰው ልክ እንዳለፈው ሁሉ በጠኔ እየሞተ ነው። አዲስ አበባ ላይ ተቀምጠው ባለጊዜዎቹ የሱፍ አበባ ፊልም ይመለከታሉ። አይ ውስልትና እኔ ከኖርኩ ሰርዶ አይብቀል። የደነዘዘ በያዘው ጥለፈው የሚንገዳገድ የፓለቲካ ስልት። ቀልደኛው እንዳለው ነው። ምነው ከሰሞኑ ጠ/ሚሩ ከቴሌቪዥን እይታ ጠፉ ቢሉት ” አይ ቀይ ባህርን በአፋር በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ቦይ እያስቆፈሩ ነው እንዳለው ነው” አሰልቺ ፓለቲካ። ሁሌ ጦር መዛዥነትና በሆነ ባልሆነው እሳት አቀጣጣይ ባህሪ። እስከ መቼ ነው በህዝብ ስም ቁማር ስንጫወት የምንኖረው? አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ችግር ከአቅሜ በላይ ነው ማለቱ ጥሩ ነው። ባይሆን እንኳን የዓለም ህብረተሰብ ለህዝባችን ይደርስ ይሆናል። ተገኘ የተባለው የበልግ የስንዴ ምርት ወደ ኬኒያ ተልኮ የለ። ምን ቀርቶን። ፍሬ የሌለው የማሳ ማሳያ ፓለቲካ! ወያኔ ሊያፍር፤ ሊያዝን፤ ሊያለቅስ ይገባዋል። ያ በደርግና በወያኔ እንዲሁም በሻብያ ፍትጊያ እንደ ቅጠል የረገፈው ወገናችን አሁን የልጅ ልጅ ሲራብ ከማየት የበለጠ ውርደት የለም። እነዚያ በወሎና በጎንደር የተራቡት ልጅ ልጆቻቸው ዳግመኛ ለስደትና ለጠኔ ሲጋለጡ ማየትና መስማት ያማል። ግን እኛ በልተን ካደርን ዓለም ሁሉ የጠገበ ለሚመስለን የፓለቲካ ጅሎች እርዳታም ተገኘ አልተገኘ ሁልጊዜ የምናሰላው የእኛን መኖርና ትርፋችን ነው። የዚህ ግን ማብቂያው መቼ ይሆን። አፍቃሪ ወያኔ የሆነው የቢቢሲ ድህረ ገጽ ትግራይ ውስጥ አንዲት ነገር ኮሽ ባለች ቁጥር በአፍሪቃ ገጽ ላይ ይህንም ያንም ይሸነቁራል። ስለ ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ ግን ይህችን ስሙ ብሎን አያውቅም። ተከፋይ የወሬ ወኪሎች። በዛሬው ገጽም በድጋሜ የትግራይን የረሃብ ሁኔታ ዘግቦታል። ሰሚ ካለ መልካም ነው። የሚላከው እርዳታ ለተጎዳው ህዝብ ከደረሰ እሰየው ነው። ግን ያ በጭራሽ አይሆንም። ስርቆት ከበረሃ ጀምረው የተላመድት የፓለቲካ ስልት ስለሆነ ህዝብን እያስራቡ የእርዳታ እህል መሸጣቸው አይቀሬ ነው።
    የአብይ መንግስት የፈረሰን ግድግዳ ቀለም እየቀባ ዓለም ሁሉ ሰላም ነው ቢለንም በምድሪቱ ላይ ያለው የመከራ ዶፍ አይኑን አፍጦ አዙሮ ተው ህዝብ እየዋሸህ ነው እያለው ነው። ለዚህ ደግሞ ተጠያቂው መንግስት ነኝ ባዪ ብቻ አይደለም። መንገድ የሚዘጋው፤ በብሄር ስም ሰክሮ የሚንገዳገደው፤ ቀረጥ አስከፍላለሁ ብሎ ህዝብ የሚያጉላላው፤ ከክልሌ ውጡልኝ በማለት ህዝብን የሚገድለውና የሚያፈናቅለው ጠባብ ብሄርተኛ፤ የእህል ክምር የሚያቃጥለው፤ ባህር ማዶ ተቀምጦ በለው በይው የሚለው ሁሉ በጥቅል ለምድሪቱ ክፋት ተጠያቂ ነው። ምድሪቱን ያኔም ዛሬም ያጨለምናት በጋራ ነው። የምናድናትም በጋራ እንጂ በተናጠል አይሆንም። ከጦርነት ሰላም ይሻላል ሲባሉ አካኪ ዘራፍ የሚሉን አንድም ቀን የባሩድ ሽታ፤ የሙታን ጠረን አፍንጫቸውን ያላፈናቸው ቀፈታም ፓለቲከኞች ናቸው። ጦርነት ሃገር አውዳሚ ነው። በጦርነት የሚፈጸሙ መንግስታዊ ግልበጣዎች መሰረትን ንደው ከዜሮ የሚያስጀምሩ ናቸው። ጦርነት ይብቃ። የታስሩት ይፈቱ። ሁሉም በሰላምና በድርድር ይፈጸም። ዓለም እየሳቀብን ነው። ሱዳን ምን ተረፋት? ተው በህዋላ እንዲህ ተካራችሁ ተካራችሁ ሃገር አልባ እንዳታረጉን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Abiy Ahmed 3 1 1
Previous Story

እጁ በንጹሀን ደም የተጨማለቀው አብይ አህመድና የአማራው የህልውና ተጋድሎ

187926
Next Story

ምዕራባውያን ሀገራት ተቃውሞ፥ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች አፈና፥ መሳሪያ ነጠቃ በአዲስ አበባ፥ ሹመት በሰላም ሚኒስቴር

Go toTop