#image_title

እጁ በንጹሀን ደም የተጨማለቀው አብይ አህመድና የአማራው የህልውና ተጋድሎ

#image_title

እውነቱ ቢሆን

አብይ አህመድ የአገር መሪ በሆነባት ኢትዮጵያ ዜጎች በዘራቸው እየተለዩ ሲታረዱ፣ ደም እንደጎርፍ ሲፈስስ፣ አስክሬኖች በዶዘር ተቆፍረው በጅምላ ሲቀበሩ፣ በተለያዩ የኦሮሞያ ግዛቶች ውስጥ ታራጆቹ እንዳይቀበሩ ክልከላ ተደርጎ አስክሬኖቻቸው በጅብ እንዲበሉ ሲደረግ፣ ሰው ታርዶ የስልክ እንጨት ላይ ሲንጠለጠል፣ በተለያዩ ድብቅና ግልጽ አደረጃጀቶችን በማሳለጥና ራሱ አብይ አህመድ ሆን ብሎና አቅዶ የተለያዩ የዳቦ ስሞችን በመስጠት ያደራጃቸውና ያሰማራቸው መንጋ የኦሮሞ አራጆቹ ካረዷቸው አማራወች አስክሬኖች ጋር ሰልፊ ፎቶ ሲነሱ፣ እርጉዝ የአማራ ሴትን አንገቷን በካራ አርደውና ሽሉን ከሆዷ ቀድደው አውጥተው በእቅፏ ሲያደርጉላት፣ ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም የሚል የህጻናት ዋይታ ሲቀልጥ…..ወዘተ “እኔ የሰፈር አብዮት ጠባቂ አይደለሁም” እያለ ያፌዘው አብይ አህመድ “እጁ በንጹሀን  ደም የተጨመላለቀ ነው” የሚለው ቃል ብቻውን የሰውየውን የእንሰሳነት ባህርይና የአውሬነት ደረጃ ሊገልጸው አይችልም፡፡

የታረዱትን አስክረኖች በቴሌቪዥን ፊት ቀርቦ በዘር ሲቆጥር ቅንጣት ስቅጥጥ ያላለው አብይ አህመድ በጭካኔውና አረመኔነቱ በታሪክ ከሚታውቁት  ጨካኝና ገዳይ መሪወች ይበልጣል፡፡ አብይ በጭካኔው በጨፍጫፊነቱ፣ በዘረኝነቱ በአለም ላይ ወደርየለሽ ነው፡፡ የትም አገር እንደ አረመኔውና “ልሙጡ’’አብይ አህመድ በፈጣሪ አምሳል በተፈጠረ የሰው ልጅ ላይ የእርሱን አይነት አረመኔነትና ጭካኔ የፈጸመ ማንም መሪ የለም፡፡

በአገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ሽህ አመታት የአገርነት ታሪክ ውስጥ በአንጻራዊነትም ለአንድ መቶ አመት ያህል በመሳፍንት አገዛዝ ስር ወድቆ ከቆየው ታሪኳ አውጥተው አገሪቱን አንድ አድርገው ካቆሟት ከታላቁ ንጉስ ከዳግማዊ አጼ ቴወድሮስ ከነገሱበት ከ1847 ጀምሮ ያሉትን መሪወች የጭካኔ ደረጃወችን በጣም በአጭሩ እንቃኘው፡፡

አንዳንዶቹ በህዝብ ላይ በአንጻራዊነት ጨካኝ የነበሩ ሲሆን በአገሪቱ ነጻ አገርነት ላይ ግን ድርድር የማያውቁና የህይወት መስዋትነት እስከመክፈል የደረሱ አገር ወዳዶች መሪወች ነበሩ፡፡ አጼ ቴወድሮስና አጼ ዮሀንስ ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ ናቸው፡፤ ለአገራቸው ክብር ሲሉ ንጉሶች ሆነው ራሳቸውን ሰውተዋል፡፡ የአድዋውን ጀግና አጼ ምኒሊክን ከሩህሩህነታቸው የተነሳ ህዝቡ “እምየ ምኒሊክ” ነበር የሚላቸው፡፡እምዬ ምኒሊክ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ መስራች ታላቅ ንጉስ ነበሩ፡፡ ቀዳማዊ አጼ ሀይለስላሴም ቢሆኑ በነበረው የፊውዳል ስርአትም ውስጥ ሆነውም ቢሆን  በጥበብ አገሪቱን ከነበረችበት የብዙ መቶ አመታት ኋላ ቀርነት አንስተው የያኔዋን ፊዉዳላዊት ኢትዮጵያን በሚችሉት የስልጣኔ ደረጃ ወደፊት አስፈንጥረዋታል፡፡

በጥቅሉ የነበሩትን መንግስታት ስንቃኝ ሁሉም በሚባል ደረጃ ጥፋት፣ ውድመት፣ የተዛባ የአገዛዝ ስርአት አልነበረባቸውም ማለት አይቻልም፡፤ ውስጣቸው ብዙ ስህተቶችና ህጸጾች ነበሩባቸው፡፤ ረሀብም፣ ጦርነትም፣ የብሄር ጭቆናወችም ነበሩ፡፡ይህም ዳሰሳ በጣም የቅርቦቹንም ማለትም የደርግንና የመለስ ዜናዊንና አሁን ያለውንም የአብይ አህመድን  አገዛዝ ያጠቃልላል፡፡ ገር ግን አንዳቸውም አገዛዞች በተናጠልም ቢሆን ወይንም ሁሉም ተደምረው የአሁኑን የእብይ አህመድን የኦሮሙማ አገዛን አይነት የገማና የገለማ እልቂት፣ ስቃይ፣ ስደት፣ ሞትና ዋይታ የበዛበት፤ ወጥቶ ለመግባት አለመቻልና ተስፋቢስ ህይወት በህዝቡ ላይ አምጥተው አያውቁም፡፡

በቅርቡ የነበሩትን የመጨረሻወቹን ሁለት አገዛዞች ማለትም የመለስ ዜናዊንና የአብይ አህመድን አገዛዞች ለማወዳደር ለብቻቸው ለይተን በወፍ በረር እንቃኛቸው፡፡ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ መርዘኛና አገሪቱን በዘር የከፋፈለ ኢትዮጵያን ያለወደብ ያስቀረ መጥፎ አገዛዝ ነበር፡፡ አሁን ያለው የአብይ አህመድ ኦሮሙማ አገዛዝ ደግሞ የመለስን አገዛዝ ያስንቃል፡፡ የአብይ አህመድ ኦሮሙማ ስብስብ ከራሱ ከበጥራቃው አብይ አህመድ ጀምሮ እስከታች ድረስ በእንብላው፣ በእንግደለው፣ በእናጥፋው መንጋ የታጨቀ ስብስብ ነው፡፡ መሪውስ ማን ነውና ስለመንጋው እናወራለን??? አንድ ናቸው፡፡ በዚህ ላይ በባዶው መቀደድን ጨምሩበት፡፡ የደንቆሮወች ጩሀት በሉት ወይንም የጅቦች ጋጋታ የፈለጋችሁትን ስም ስጡት፡፡ ብቻ ሰው ሰው አይሸትም፡፡ የኦሮሙማውን መንጋ አባላት የሞተ ከብት እንደሚቀራመቱ የዱር እንሰሳት በሏቸው፡፡

ከፈጣሪ አምላኩ ቀጥሎ “”በችግር ጊዜ  መንግስት ያድነኛል ፤መንግስት ይደርስልኛል”” ብሎ በሙሉ ልቡ የምያምነው ደጉ፣ገራሙና አስተዋዩ የኢትዮጵያ ህዝብ  በሽህ አመታት ታሪኩ ውስጥ እንደ አብይ አህመድ አይነቱን አረመኔ የሆነ፣ ጸረ ህዝብ የሆነ፣ ዘረኛ የሆነ በህዝብ የተጠላ፣ የተወገዘና አገርንም ህዝብንም ያወደመ፣ ያዋረደ አገዛዝ አይቶ አያውቅም፡፡ የትም አገር ለአንድ መንግስት በህዝብ ተቀባይ የመሆን ቁልፉ ምስጢር በህዝብ መታመንና ቅንነት ናቸው፡፤ ወያኔም ኦሮሙማም ይህ ባህርይ የላቸውም፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን ታግሎ ካስወገደ በኋላ አሁን ላይ ወያኔን ማረኝ የሚያሰኘውን ፍጹም አረመኔ የሆነውንና ከወያኔ በባሰ ደረጃ የሚጠላውን ኦሮሙማን ለማሽቀንጠር አምርሮ እየታገለ ነው፡፤

ከማእከላዊ የመንግስትነት ስልጣን በህዝብ አመጽ የተባረረው ወያኔ በአሁኑ ሰአት ሲምልበት በነበረው የትግራይ ህዝብም ዘንድ የተጠላና የተተፋ ሆኗል፡፡ ወያኔ ታላቋ ትግራይ በሚል ካርታ ሰርቶ ህዝቡን በማይሆንና በማይጨበጥ ፕሮፓጋንዳ ሞልቶ፣ በአማራና በአፋር ህዝብ ላይ አዝምቶ፣ ያደረሰው እልቂት፣ መከራና ውድመት ተነግሮ አያልቅም፡፡ጊዜው ደረሰና የትግራይ ህዝብ ወያኔ ስላመጣበት መከራና እልቂት አሁን በይፋ ሀቁን እየተናገረ ነው፡፡ በስሙ እየተነገደበትና በስሙ ወንጀል እየተሰራበት ያለውም የኦሮሞ ህዝብ እንዲሁ ጊዜው ሲደርስ ሀቁን ይመሰክራል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ተው ስማ ወገኔ!ተው ስማ ተው አድምጥ!

በመስመር ደረጃ ኦሮሙማ ወያኔ የሄደባቸውን የስህተት ጎዳናወች ስማቸውን እየቀባባ የመደመር፣ የለውጥ፣ የብልጽግና መንገዶች ይላቸዋል፡፡ በመሪነት ደረጃም የኦሮሙማው መሪ አብይ አህመድ ከወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ ጋር አይወዳደርም፡፡ በአጭሩ አብይ የበለጠ ደደብ ነው፡፤ ወደርየለሽ ዉሸታም ነው፡፤ እውቀትና መርህ የለሽ ነው፡፤ ከመለስ ይበልጥ አረመኔም ነው፡፡ ሁለቱን አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ከተፈለገ ሁለቱም የኢትዮጵያን የረዥም ጊዜ ታሪክ አሳንሰው ከማየታቸው ባለፈ ሁለቱም ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ መሆናቸው ነው፡፡

መርዛሙ መለስ አገሪቱን ወደ አልባ አደረጋት፡፡ አንድ ወቅት መለስ ዜናዊ ስለወደብ አስፈላጊነት ተጠይቆ ቃል በቃ ያለውን ላስታውሳችሁ፡፡ አሰብን ሲፈልጉ “ፍየል ያርቡበት” ነው በራሱ አንደበት የተናገረው፡፡ የመለስ  የታሪክ  ጠባሳ በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡ በአገሪቱ ውስጥ የማይነቀል የዘረኝነትን መርዝን ተክሎና የዘራው መርዝም የብክለት ፍሬ ሲያፈራ አይቶ ሄዷል፡፡

መለስ መናጢ ቢሆንም፣ መርዘኛ ቢሆንም፣ ዘረኛ ቢሆንም እርሱ ጠቅላይ ሚንስትር በነበረበት ወቅት በአገሪቱ ውስጥ በአራቱም ማእዘን ከጫፍ እስከጫፍ የትም ቦታ የህዝብ እልቂት በኦሮሙማ ደረጃ ሊፈጸም ቀርቶ ትንሽ  የጸጥታ ችግር በተፈጠረበት ቦታና ጊዜ ከመቅጽበት ምን አይነት ፈጣን የጸጥታ እርምጃ ይወሰድ እንደነበረና ህዝቡም በሰላም ወጥቶ ለመግባቱ በአንጻራዊነት የተሻለና አስተማማኝ የሆነ የጸጥታ ሁኔታ እንደነበረ ሁላችንም አንክደውም፡፡

አብይ አህመድ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የስንት ሽህወች ሰላማዊ ዜጎች እርዶች እንደተካሄዱ፣ ምን ያህል የህዝብ እልቂት እንደተፈጸመ ታሪክ ይቁጠረው፡፡ አሁን ድረስ እየተካሄዱ ያሉት የንጹሀን መታረድ፣ መሰደድና በጦርነት ማለቅ የህዝቡ የማያባራ የየእለት የስጋትና የሰቀቀን ኑሮና በችጋር መጠበስ  ለሰውየው ችሎታ ማነስም በሉት ክፋት እንደዚሁም ወደርየለሽ ጭካኔና አረመኔነት በቂና ህያው ማሳያወች ናቸው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፡፡ አብይ አህመድ እጅግ በሚያሳፍር ሁኔታ ይበጠረቃል;፡ ይቀደዳል፡፡ይዋሻል፡፡ ይህም ብቻም አይደለም፡፡ አብይ ሌላም ውርደት አለበት፡፡ በሚያሳፍርና ለእኛ ኢትዮጵያዊያንም በሚያሸማቅቅ ሁኔታ ማለትም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው በሚባለው በአብይ አህመድ አንገት ውስጥ ገብቶ ሲቦጠቡጠውማየት፣ ፎቶግራፉ አለምን ያነጋገረው የአረብ ኢምሬቱን ንጉስ የሙሀመድ ቢን ዛይድና የአብይ አህመድ ፎቶ ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን  እጅግ አሳፋሪና እጅግ አዋራጅ መልእክትን የያዘ ድርጊት ነው፡፡ አብይ አልፎ ተርፎም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ የወዳጁን የኢምሬቱን ንጉስ እናት ወ/ሮ ፋጢማን  ‘እባክሽ የልጅሽ የቢን ዛይድ ወንድም እንዲሆን እኔንም ልጅሽ አድርጊኝ’ ብሎ ራሱን በጉድፈቻነት የሰጠ ሰው ነው፡፡ ነውረኛውና በብዙ መድረኮች ኢትዮጵያን ያዋረደው አብይ አህመድ፤ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ሲል የአገሪቱን ደህንነትና ሉአላዊ አገርነት ለውጭ አገራት አጋልጧል፡፡ በተለዬ መንገድም ህዝብን ለመጨፍጨፊያ ድሮኖችንና ለንግስናው የሚሆን ቤተመንግስት መስሪያ ዶላሮችን ለምታስታቅፈው ለአረብ ኢምሬት በይፋ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡

እንደ ፖለቲካ ድርጅት ወያኔም ኦሮሙማም ሁለቱም ኢትዮጵያ እንደ አገር እንድትቀጥል አይፈልጉም ስንል በምክንያት ነው፡፤ ሁለቱም የሚመኙት ኢትዮጵያ ፈራርሳ በፍርስራሿ ላይ የየራሳቸውን አገሮች መመስረትን ነው፡፡ ወያኔ ታላቋ ትግራይን፡፡ እነርሱ አባይ ትግራይ ይሏታል፡፤ የታላቋ ትግራይን ካርታ ሰርተው በልጆች ትምህርት መማሪያ መጻህፍትም ላይ ጭምር ካርታውን አሳትመውት ነበር፡፡ የታላቋ ትግራይ ካርታ ሳይ እንደሰፈረውም ካርታው በምስራቅ በኩል እስከ ቀይ ባህር ደርሶ፣ አሰብ ወደብን አጠቃልሎ ይዞ ጂቡቲ ድረስ የተዘረጋ ነው፡፡ በአማራ በኩልም እስከውልድያ ድረስና አፋርንም የዋጠና የደፈጠጠ ካርታ ነበር፡፡ካርታው በወልቃይት በኩል አልፎ በቅማንት ላይ ተረማምዶ ለብዙ ህዝቦችና አገሮች የእድገትና የህይወት መሰረት የሆነውን የአባይ ወንዝን ፍሰት ለሀይል ምንጭነት ከስሩ ለመቆጣጠር ያቀደ ካርታ ነበር፡፡ አሁንስ የታላቋ ትግራይ የቅዠት ፕሮጀክት ምን ደረጃ ላይ ይገኝ ይሆን?? መልሱን ከወያኔ ሳይሆን ከትግራይ ህዝብ መጠበቁ ይሻላል፡፡

ኦሮሙማም የራሱ የታላቋ ኦሮምያ ኢምፓየር ካርታ አለው፡፤ ካርታውን አሁንም ልክፍተኞቹ የኦሮሞ ብሄረተኞች በሙሉ ያቀነቅኑታል፡፡ይመኙታል፡፤ ይጎመዡበታል፡፡ይናጡበታል፡፡ አሁንም ድረስ ካርታው በይፋ አለ፡፡ ካርታው ደቡብ ወሎን አጠቃሎ እስክ ራያ ድረስ የተዘረጋ ነው፡፡ በደቡብ በኩልም ሁሉንም ሰልቅጦ ውጦ እስከ ሱዳን ድንበር ድረስ የተዘረጋ ነው፡፡ ሶማሊያና አፋርንም እንድሁ በግማሽ እስከመሀል ድረስ ከርክሞ ትንንሽ አድርጓቸዋል፡

አብይ አህመድ አማራን መከፋፈል፣ ፋኖን ለማዳከም ሽማግሌወችንና የሀይማኖት አባቶችን ጨምሮ ሽምግልናንና ስለላን አጣምረው እንዲሰሩለት ወደ ፋኖ መላክ፣ ሚሊሽያና አድማ በታኝ የመሳሰሉ ሆዳም አማራወችንና የብአደን ምልምሎችን በከፍተኛ አበልና ደመወዝ  መግዛት፣ በውስጥም በውጭም ያሉ ሆዳም አማራወችን በጥቅማ ጥቅሞች እያማለሉ አሽከርና አገልጋዩ እንድሆኑ ማድረግ የወቅቱ ዋና አላማው አድርጎ እየሰራበት ነው፡፡በፋኖ ቅጽበታዊና ፈጣን የደፈጣ ምቶች ሽባ የተደረገው የኦሮሙማ አገዛዝና መንጋው የኦሮሞ ወራሪ ሰራዊት በአሁኑ ሰአት የሚይዘው የሚጨብጠው አጥቷል፡፡ 80 ከመቶ የክልሉን ከተሞችና ወረዳወችን ፋኖ ተቆጣጥሯቸዋል፡፡ አብይ ብአደንን በጣት በሚቆጠሩ ከተሞች ውስጥ  በአሻንጉሊት መንግስትነት ለመጠቀም እየተፈንራገጠ ነው፡፤ የአብይ አህመድ ሁሉምይነት ድንብርብሩ የወጣ አካሄድ ለፋኖ በጣም ግልጽ ነው፡፡ አብይ  አገውን፣ ቤንሻንጉልን፣ መተከልን፣ ቅማንትን ..ወዘተ አማክሎ ይዞ አማራን ውስጡን ለመሰነጣጠቅና የአባይ ውሀ ግድብን ለመቆጣጠር ብሎም ግድቡን በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ሊገነባት ወዳሚያልማት ወደ ኦሮምያ ኢምፓየር ለመጠቅለል እየሰራ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  39ኛ የካቲት ለማክበር ሽርጉድ እና የተሟጠጠው የትግራይ ህዝብ ስሜት

እንጭጩ አብይ አህመድ አላወቀም እንጅ አማራ አንድ ነው፡፤ ትርፍ አንጀቶቹ አሽከሮቹ እነ ተመስገን ጥሩነህና ቡድኑ “አማራን እንከፋፍለዋለን፣ እናዳክመዋለን፣ እጁንም እንዲሰጥ እናደርገዋለን” እያሉ ይበጠርቁለታል እንጅ አማራ እሳክሁን አልተከፋፈለም፡፤ ወደፊትም አይከፋፈልም፡፡ እጁንም አይሰጥም፡፡ ኦሮሙማ አላወቀም እንጅ  56 ሚሊዮኑ የአማራ ህዝብ እንዳለ ሁሉም ፋኖ ነው፡፤

ለእንድ አማራ ለሆነ ሰው ፋኖነት፣አማራነትና ነፍጠኛነት ምንጊዜም በውስጡ የሚኖሩ ካልሞተ በስተቀር የማይለዩት የራሱ የሆኑ የማንነቱ መገለጫወች ናቸው፡፡  

አውሬው አብይ አህመድና የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊትን ዩኒፎርም የለበሰው ከላይ እሰከታች ያለው የኦሮሙማው ወራሪ መንጋ እያወቀ የማያውቅ ይመስላል እንጅ ፋኖ የማይበገር መሆኑን በተግባር አሳይቶታል፡፡ ፋኖ አነጣጣሮ የማይስት መሆኑን፣ ኢላማውን  ነጥሎ የመምታት ብቃቱን፣ የሚያደቅቅ ክንዱንና ለጠላቶቹ አይበገሬነቱን ለኦሮሙማ በተግባር አሳይቶታል፡፡ ፋኖ የሚዋጋው በአብዛኛው ከኦሮሙማ መንጋ በተማረኩ ትጥቆችና  የዉጊያ መሳሪያወች ነው፡፡ አብይ  እያፈሰ የሚልከው የኦሮሙማ መንጋ ጦርና የብአዴን ሆዳም አድማ በታኝና ሚሊሽያ ሀይል የምድር ላይ ዉጊያ ስላላዋጣው አሁን ላይ ወደ ድሮን መጠቀምና በድሮንም ጠቅላላ ሲቪሉን ህዝብ ወደመጨፍጨፍ ስራ ገብቷል፡፡ አብይ አህመድ ፋኖን በድሮን አያገኘውም፡፡ ይህም ማለት ድሮኑ የአማራን ሲቪል ህዝብ ይጎዳል ፤ይህም በዉጤቱ ይበልጥ ህዝቡን ወደትግል እንዲገባ ያደርገዋል እንጅ የአብይ አህመድ ፋኖን ነጥሎ በድሮን የመምታት እቅዱ ዉጤት አያመጣለትም፡፡

በጥቅሉ ስናየውም ፋኖን ድሮን፣ ታንክና መድፍ አያንበረክከውም፡፡ ፋኖ የሚጓዘው በስሌት ነው፡፤ ስለዚህ አማራን ማዳከም፣ ማድቀቅ፣ ማሽነፍና ርስቶቹንና የአማራ የሆኑ መሬቶቹን መንጠቅ ለኦሮሙማ ህልም ሆኖበት ይቀራል እንጅ በተግባር ሊተረጉመው አይችልም፡፡ ድርጊቱ ግፋ ቢል ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ መግባት ነው የሚወስደው፡፤ ያ ደግሞ ለአማራው ለውጥ አያመጣም፡፡ አማራው አሁን ያለዉኮ በህልዉና ጦርነት ውስጥ ነው፡፡ታዲያ ምን ቀረኝ ብሎ ፈርቶ ነው አማራው እጁን ለኦሮሙማ መንጋ የሚሰጠው?? ኦሮሙማ ይህንን ማሰቡ የጅልነት መገለጫው ከመሆን አይዘልም፡፡ነውም፡፡

የአባይ ውሀ ባለቤቱ አማራ ነው፡፤ እልፍ ሲልም እንደ አገር ባለቤቱ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ፍሰቱ የሚነሳውም ከአማራው ደጅ ነው፡፡ ውሀው መነሻው ከአማራ መሬት ነው፡፡ ፍሰቱ የሚያልፈውና ግድቡም የተሰራው የአማራ ርስት በሆነው  መሬት ላይ ነው፡፡ ወያኔም ኦሮሙማወችም ይህንኑ ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ ግን ይህንኑ ሀቅ ሊውጡት ሲሉ አይዋጣላቸውም፡፡ ሲያንቃቸው ዉሀ የሚያቀብላቸው አሽከርዮው ብአደን ስለነበረ እስካሁን ድረስ አላነቃቸውም፡፡ አሁን ግን ብአደን የለም፡፡ በክልሉ ውስጥ ብአደን መቶ በመቶ ሽባ ሆኗል፡፡ተስፋም የለውም፡፡ የህዝብ ልጅ የሆነው የፋኖ ሀይል ነው በክልሉ ውስጥ አሁን ያለው፡፡  “እምቢኝ አትግደሉኝ” ያለ የተቆጣ የአማራ ህዝብ ነው ያለው ፡፤ ለህልውናው እየተጋደለ ያለ ባለ ደማቅ ታሪክ ህዝብ፡፡

መተክል ለአማራው ልክ እንደ አዲስ አበባ፣ ልክ እንደ ወልቃይት ልክ እንደ ራያ ሀብቱ፣ ርስቱ፣ ንብረቱ፣ ህይወቱና እስትንፋሱ ናቸው፡፡ ለአማራው ርስቶቹ አይበላለጡበትም፡፡ እኩል ናቸው፡፤ እስትንፋስ እንዴት ይበላለጣል???

የአማራ  ጠላቶች የፈለጉትን የፖለቲካ  ድሪቶ ይደርቱ እንጅ ድሪቷቸው ለ56 ሚሊዮኑ አማራ ምኑም አይደለም፡፤ ለጊዜው ነው፡፤ ኦሮሙማ ከወያኔ ጋር ቢጣመር ባይጣመር ፤ቢዶልት ባይዶልት ሊያመጣው የሚችለው የድርጊት ለውጥ የለም፡፡ ህዝቡ በደሉን ግፉን እልቂቱን ለማስቆም ቆርጦ ተነስቷል፡፡ በታንክ በመድፍ፣ በድሮን አማራን መድብደብ በጋራም ሆነ በተናጠል አማራው ላይ ወረራ መፈጸም ለጊዜው ትግሉን ሊጎዳ፣ ህዝብ ሊገድል፣ ኢኮኖሚውን ሊያደቅቅ  ይችላል፡፤ ኢኮኖሚን ካነሳን ዘንድ አማራን ማስራብን በሚመለከት አንዲት ትኩስ መረጃም ላጋራችሁ፡፡ አማራን ለማስራብ አማራውም ሲርበው ፋኖን  እንዳይደግፍ ለማድረግ ከአማራ ከአማራ ክልል ማንኛውንም እህል በተባለው ዋጋ እየገዙ ወደ ኦሮሚያ ክልል ለማጓጓዝ ኦሮሙማ ቢሊዮኖች ብሮችን መድቦ በዚህ ሳምንት ብቻ ከ600 በላይ ባለተሳቢ መክኖች ወደ አማራ ክልል እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ አይ ኦሮሙማ!! ፋኖ ይህንን ካወቀ ዉሎ አድሯል፡፡ የአማራ ህዝብን ማስራብ፣ አማራው መድሀኒትና ነዳጅን ጨምሮ  ሌሎች ሸቀጣ ሸቀጦችም እንዳይደርሰው ማድረግ ….ወዘተ መሰል የአውሬው አብይ አህመድ ጸረ አማራ እቅዶችና ሴራወች ለአማራው ምስጢር አይደሉም፡፡ ይህ ሁሉ ድሪቶና ሴራ የአማራውን የህልውና ተጋድሎን አያስቆመውም፡፤ አማራው የህልውና ትግል ውስጥ ነው ያለው፡፡አንድ መሰረታዊ ሀቅ አለ፡፡ ይህም ሀቅ እብሪት ጥጋብና የመሳሪያ ጋጋት የተገፋን ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ማሸነፍ አለመቻሉ ነው፡፡ ኦሮሙማ ይህ ቢገባውም ባይገባውም እስከሚላላጥ ድረስ  ይንፈራገጣል እንጅ የአማራን የህልውና ተጋድሎ ሊያሸንፈው አይችልም፡፡ ድሮን መድፍ ታንክ በአፍጋኒስታንም በቬትናምም በየመንም የህዝቦችን የነጻነት ተጋድሎ ሊያንበረክክ አልቻለም፡፤ በአማራም በኩል ያለው እውነታ ይሄው ነው፡፡ህዝብን በመሳሪያ ሀይል ማንበርከክ ያለመቻል እውነታ በታሪክ ተፈትሾ የተረጋገጠ አለምአቀፋዊ ሀቅ ነው፡፡

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ልክ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደምታደርገው በብዙ ታዳጊ አገሮች ውስጥ ያሉ መንግስታትን እየደገፈችና ለጥቅሟ በውስጥ ጉዳዮቻቸው ዘው ብላ እየገባች ብዙ ቅሌቶችን ደጋግማ ተከናንባለች፡፡ ምሳሌ  በየመን የውስጥ ጉዳይ ገብታና መንግስቱን ደግፋ ሁቲወች ላይ ከ25ሽህ ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት አድርሳ መጨረሻ ላይ በኪሳራ ወጥታለች፡፡ በታዳጊ አገሮች ህዝቦች ላይ ጡንቻ የሚፈታተሹት ሳኡዲ አረብያና አረብ ኢምሬቶች የተቻላቸውን ውድመት በየመን ህዝብ ላይ ካደረሱ በኋላ ሁለቱም በኪሳራ ከየመን ወጥተዋል፡፡ አሁን በየመን ውስጥ በአረብ ኢምሬቶች ድሮን ስላልተንበረከከው ስለሁቲወች አመጽ ወቅታዊ ሁኔታ አሜሪካ መፍትሄ ብላ ያቀረበችላቸውን ሀሳብ ራሳችሁ መርምራችሁ ድረሱበት፡፡ ይህ የሚያሳየን በራስ ጠንክሮ እስከመጨረሻው ድረስ አትግደሉኝ!! አልሞትም!! ብሎ ለነጻነት መታገል ዉጤት እንደሚያመጣ ነው፡፡

አብይ አህመድ በየእለቱ በአማራው ላይ  የድሮን ጥቃት እያካሄደእንደሆነ ሁሉም ያወቀው ሀቅ ነው፡፡ ታዲያ አማራው ላይ ስለሚዘንበው የድሮን ጥቃት ለአማራ ህዝብ ማን ይዘግብለት?? አለም ጸጥ ብሏል፡፡ በእስራኤልና ሃማስ መካከል እሰከዛሬዋ ቀን ድረስ ብቻ 24024 ፍልስጥኤሞች መገደላቸውን  መላው አለም እየተቀባበለ ዜናውን ዘግቦታል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በወለጋ በአንድት ወረዳ ብቻ ለታረደው 24024 በላይ የአማራ ህዝብ ግን ማን ይዘግብለት? በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ  24024 አማራወች ማይካድራ ውስጥ በመታወቂያ እየተለዩ በወያኔ ታርደዋልኮ፡፡ታዲያ ይህንን ማን ዘገበለት?? ይህ ነው በራስ ጠንክሮ ያልቆመ ማንነት ማንም የማይፈልገው የሚሆነው፡፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ወያኔ ያካሄደውን ጭፍጨፋ ኢሕአፓ ያወግዛል

አሁን ላይ አማራው ይህንን እውነታ በሚገባ ተረድቶታል፡፡ ራሱ ለራሱ ጠንክሮ ካልቆመና ጠንክሮ በመቆምም ጠላቶቹን ራሱ ታግሎ ካላሸነፋቸው በስተቀር እንደ ኩርዶች ጠላቶቹ ያሰድዱታል እንጅ፤ እንደ ኩርዶችጠላቶቹ  አገር የለሽ ያደርጉታል እንጅ ብሎም ከምድረ ገጽ ይጠፋታል እንጅ ማንም አይደርስለትም፡፤ ማንምም አያድነውም፡፡ ስለሆነም አማራው ይህንኑ በሚገባ አውቆ ከመሰደድ ለመዳን፣ አገር የለስ ከመሆንለመዳን፣ ከማለቅ ለመዳን ከአሁኑ ተጋድሎው ይበልጥ አምርሮኛ ጠንክሮ መታገል አለበት፡፡ለዚሁ ስኬትና ዉጤትን በውስጥ በአማራ ሆዳሞችም ላይ ጠንካራና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ አለበት፡፤ትግሉ እዚህ ደረጃ ከደረሰ በኋላ የነጻነት ተጋድሎውን በሚያደናቅፍ ማንም ሀይል ላይ  በተለይም በሆዳም አማራወች ላይ ምህረት የሚባል ነገር መታሰብ የለበትም፡፤ ማስወገድ ብቻ!!! ሰሞኑን ፋኖ በያለበት በአብይ አህመድ ተላላኪ አማራወች  ላይ የጀመረው ምህረት የለሽ እርምጃ ይበል፣ ይቀጥል፤ ተጠናክሮ ይስፋፋ የሚያሰኝ ነው፡፡ከዚህ በኋላ ለሆዳም አማራወች ሌላ የማስተማሪያ መንገድ የለም፡፡

አሁን ላይ በአንዳንድ የአማራ ከተሞች በከባድ መሳሪያወችና በአብይ አህመድ ኮማንዶወች ታጅበው ውር ውር የሚሉት የብአደን ሹመኞች በፋኖ እየተለቀሙ  በመሆናቸው ወደ አዲስ አበባ ሲፈረጥጡ ይስተዋላል፡፡ ፋኖ በአዲስ አበባም ውስጥ የማይከታተላቸውና ፋኖ አዲስ አበባንም በቁጥጥሩ ስር የማያደርግ መስሏቸው ከሆነ ተሳስተዋል፡፡

የፋኖ የሚታገለው ከአብይ አህመድ ኦሮሙማ ጋር ስለስልጣን መጋራት፣ ክልሉን ስለማስተዳደር፣ ስለህገ መንግስት ቅየራ፣ ስለአገራዊ ምክክርና ድርድር፣ ወዘተ… ስለመሳሰሉ ዝባዝንኬወች አይደለም፡፡ ፋኖ መጀመሪያ በአስተማማኝ ክልሉንና የአማራ ርስቶችን በሙሉ ከወራሪወች ነጻ ማድረግ ቀዳሚው አላማው ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የስርአት ለውጥን ማምጣትም ቋሚና የማይናወጥ “መዳረሻ” ብሎ በጽናት የቆመለት ኣላማው ነው፡፡

የአማራ ህዝብ ለኢትዮጵያ ነጻ እገርነት ያደረጋቸው ዘመን አይሽሬ የአርበኝነት ስራወቹን፣ ረዥም የተጋድሎና የድል አድራጊነት ደማቅ ታሪኮቹን ጠላቶቹ ጭምር በይፋ ይመሰክራሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ አማራውን በድሮን እያስጨፈጨፈ ያለው ምርኮኛው አምሳ አለቃ በርሀኑ ጁላም ይህንኑ በራሱ ቃል አረጋግጧል፡፡ታሪክን አለማወቅ ካልሆነ በስተቀር ትግሉ  የፈለገውን ጊዜ ይውሰድ እንጅ፣ የፈለገውን መስዋእትነትም ይጠይቅ እንጅ መጨረሻ ላይ  ድሉ የተገፋው የአማራ ህዝብ ነው፡፡ ያኔ እጃቸው በንጹሀን ደም የተጨማለቀው አብይ አህመድና ተከታዮቹ ቀናቸው ይጨልማል፡፡ ህዝቡም ትግሉን በማሸነፉ ከዘረኛው የኦሮሙማ የጭቆና አገዛዝ ነጻ ይወጣል፡፡

ሚስቱ እፊቱ የተደፈረችበት ባል፣ አስክሬናቸው እንዳይቀበር ተድርጎ በአውሬ የተበሉ ሟቾች ዘመዶች፣ ልጇ ፊቷ የተደፈረችባት እናት፣ ልጇንና ራሷን እናትዮዋን አንድ ቤት ውስጥ  በሰልፍ እየተፈራረቁ የደፈሯቸው እናትና ልጅ፣ ከት/ቤት ስትመለስ ጧት የወጣችበት ቤት ፈርሶ ያገኘችውና መግቢያ ያጣችው የታዳጊ ተማሪ ልጅ ሰቀቀን፣ ቤቶቻቸው ፈርሶባቸው እንዳይከራዩም ማከራየት ተከልኮሎ  ቤተሰቡ ተበታትኖ ልጆቻቸው በጅብ የተብሉባቸው ወላጆች…. ወዘተ ስንቱን አንስቶ ስንቱን መተው ይቻላል??

ከት/ቤት ስትመለስ ቢቷን ያጣችውታዳጊና አከራይ አጥቶ የተበታተነው ቤተሰብ ልጅ በጅብ የተበላው በአዲስ አበባ ዙሪያ በነበሩ ከተሞች ውስጥ ነው፡፤ በእነዚህ የአዲስ አበባ ዙሪያ በነበሩ ከተሞች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 120 ሽህ ቤተስቦች ማለትም በአማካይ 500 ሽህ ዜጎች በአብዛኛው አማራወች ሲሆኑ ቤቶቻቸውም በኦሮሙማ ግብረ ሀይል ነው የፈረሰባቸው፡፤ ኦሮሙማ እንዚያኑ የፈረሱ መንደሮች በኦሮምያ ክልል ውስጥ አካቶና ስሙንም ሽገር ከተማ ብሎ ነው አንድን ሰው በከንቲባነት የመደበላቸው፡፡እዚህ ላይ እጅጉን የሚገርም አንድ ጉዳይ አለ፡፡ ኦሮሙማወች የአዲስ አባባ መስተዳድር አካል ስር የነበሩ የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞችን፣ ሰፈሮችን ፣ወረዳወችን ያለአግባብን ያለ ከልካይ ወስደው በኦሮምያ ስር አድርገናታል ለሚሏት ሸገር ከተማ በኦሮምያ መንግስት ከንቲባ ተደርጎ የተሾመው ግለሰብ የአዲስ አበባ የከተማ የምክር ቤት አባልም ነው፡፡የተረኞቹ ኦሮሙማወች ጥጋባቸው፣ እብሪታቸውና ማንአለብኝነታቸው የቱን ያህል መረን እንደለቀቀ አስተዉሉ፡፡ ይህም ነውረኛ ሰው ነው የተባረሩትን ሰወች አሁን ህጋዊ ድሀ አድርገናቸውል ብሎ የተሳለቀው፡፡

እያለቀለት ያለው አብይ አህመድ ያለው አማራጭ አንድ ብቻ ነው፡፤ ስልጣኑን ለህዝብ ማስረከብ፡፡በአገሪቱ ውስጥ ሁሉንም የሚያስማማ የስርአት ለውጥ ብቻ ነው መፍትሄው፡፡ ከዚህ ውጭ ምንም የመዳኛ መንገድ የለም፡፡

አብይ አህመድ ለሁሉም የአውሬነት ስራወቹ ሰማይ ቤት ፈጣሪ አምላክ የሚያደርገውን አናውቅምና ስለዚያ ምንም ማለት አንችልም፡፤ በምድር ላይ ግን በህይወት እጁ ከተያዘ  የአገሪቱ የህግ አፈጻጸም እንዳለ ሆኖ ግን በቅድሚያ ግፍ የተሰራባቸው ዜጎች አስተያየቶች እንዲሰጡ ቢደረግና አስተያየቶቹንም ራሱ አብይ እንዲሰማቸው ቢደረግ ጥሩ ይሆናል፡፡ እጁ በንጹሀን ደም የተጨመላለቀው እንሰሳው አብይ አህመድ ያኔም ቢሆን ከመጸጸት ይልቅ ማድረግና መሆን ቢችል ድጋሜ የንጹሀንን ደም አፍስሶ ወደ ስልጣኑ ለመመለስ ነው የሚመኘው፡፡ ለዚህም ነው እጁ በንጹሀን ደም የተጨመላለቀው አብይ አህመድ መቼም ይሁን የትም  ስበእናው የተሞላው በእንሰሳዊ ባህርይ እንጅ በሰዋዊ ባህርይ አይደለም የሚባለው፡፡

6 Comments

 1. በዚህች መጣጥፍ አብይ አህመድ አልተረፈም፡፡
  አውሬዉ፣ እቡዩና አረመኔው አህመድ በእውን የማይተርፈው ግን በእውን ከስሩ ተመንግሎ ሲጣል ብቻ ነው፡፡ እንደኔ እንደኔ ፋኖ ክልሉን ከኦሮሙማ እያጸዳ መገስገሱ እንዳለ ሆኖና ይህም ሳይዛነፍ እንደተቃደው ቀጥሎ በአፋጣኝና በአቋራጭ አብይን ከስሩ ነቃቅሎ በቶሎ ለማስወገድ አቋራጩ በቋፍ ያለው የአዲስ አበቤ መነሳት ትግሉን እጅግ በጣም ያፋጥነዋል፡፡
  የአዲስ አበባ ህዝብኮ ከማንም በላይ ዘረኝነት የተሰራበት፣ ከማንም በላይ የፖለቲካ ንቃት ያለውና ከማንም በላይ ኦሮሙማን የሚጠላ ለአመጽና ለእርምጃ ዝግጁ የሆነ ህዝብ ነው፡፡
  የአገሪቱ የፖለተካ ቁማሮች፣ ዱለታወች፣ ጥንስሶች በሚፈልቁባት አዲስ አበባ ውስጥ መሬት አርድ የሆነ፣ ድብልቅልቅ ያለ የህዝብ አመጽ እንድፈጠር ማድረግ ብዙ ጠቀሜታ አለውና ቢሰራበት፡፡
  አዲስ አበባ ውስጥ አንዴ የህዝብ አመጽ ከተነሳ ያችኑ ቀን አብይ አህመድ ያልቅለታል፡፡

 2. ኦሮሙማ የሚወገደው በአብይ አህመድ አህመድ መወገድ ጋር ነው፡፤ አብይ ንጹህ ኦሮሞ ሳይሆን ከንጹህ ኦሮሞወች በላይ ኦሮሞ ነኝ የሚል ለኦሮሞወችም ያልቆመ ቅድ ሰውስለሆነ ነው፡፤ አብይ በኦሮሞ ስም ብቻ እየነገደ የሚግፎገላው ንፍፊታም የሆኑ መቶ ሽህ ቀርቶ አስር ሽህ የማይሞሉ ሆዳምና አጋሰስ ኦሮሞወችን ምርኩዝ አድርጎ እንጅ ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ ወክሎ፣ ጠቅሞ ወይንም ለህዝቡ አዝኖ አይደለም፡፡፡፤ በጥቅሉ አብይ ፍናፍንት ነው፡፡

 3. በዚህ በአለንበት የተሳከረ ፓለቲካ ውስጥ መካሪና አስታራቂን ገሸሽ በማድረግ ሁሉን በጦርነት ለመፍታት አለም ሁሉ ሃተፍተፍ እያለ ነው። የእኛይቱም ከፍርስራሽ የተረፈች ሃገር ከየት ወዴት እየሄደች እንደሆነ በእውን የሚያመላክተን አንድም ሃይል የለም። ግን ያለፈ ታሪካችን መንዝረን ስንመለከት ከክፋት ወደ ክፋት፤ ከጭካኔ ወደ እንስሳነት የተቀየረ ባህሪ ተላብሰን ያለምንም በደል በገደልናቸው አስከሬን ፊት ፎቶ ተነስተን የምንለጥፍ የሙት ቁሞች ሆነናል። ለዚህ ነው እድሜ ለሻቢያ፤ ለወያኔና ለኦሮሞ ፓለቲከኞች ሃገሪቱ ልትወጣ የማትችልበት ማጥ ውስጥ ገብታለች የምንለው። ችግሩ የረጅም ጊዜ የመከራ ዶፍ ስብስብ ውጤት ነው። አሁን በሄደና በመጣው ጠበንጃ አንጋች ግፍ የተፈጸመበትና እየተፈጸመበት ያለው አማራ ነፍጥ አንስቶ እዚህም ቤት እሳት አለ ማለቱ የህልውና ጉዳይ እንጂ ደልቶት አይደለም። ችግሩ አማራ አማራውን እየገደለና እያስገደለ፤ መንገዶች እየፈረሱና እየተዘጉ፤ የህክምና ጣቢያዎች እየፈራረሱ፤ የመማሪያ ስፍራዎች ተዘግተው ሰው ወደኋሊት እየሄደ እንዴት ባለ ስሌት ነው ለአማራ ህዝብ ቀን የሚወጣለት? ትላንት ወያኔ በሶስት ጊዜ ወረራው ያለ የሌለውን ቅራቅንቦ ተሸክሞ መቀሌ የወሰደበት ይህ የአማራ ህዝብ አሁን በፋኖና በአብይ ሰራዊት መካከል በሚደረገው ስርግብ ዳግመኛ እየሞተ፤ እየተራበና እየተሰደደ ነው። ይህ የሚያስፎክር ሳይሆን አንገት የሚያስደፋ ነው።
  ኢትዮጵያ ለሚያስቡላት የማትሆን፤ የሞቱላትን ረስታ የገደሏትን የምታቅፍ ለመሆኗ ዘመን ተሻጋሪ ታሪካችን ያሳየናል። አሁን የአብይ መንግስት ተለወጠ አልተለወጠ በሃበሳ ለሚጠበሰው የሃገሪቱ ህዝብ ምንም ለውጥ አያመጣም። እንዲያውም ግፍትሪያው በሃይልና በጠበንጃ ከሆነ የሃገሪቱ ህልውና የከፋ ደረጃ ላይ እንደሚደርስ አሁን በመሬት ላይ የሚታዪት እውነታዎች አስረግጠው ያሳያሉ። ጠ/ሚሩ በምርጫ ነው ስልጣን የያዝኩት ይለናል። ከሆነ መልካም። ግን መውረድ ካለበትም በወጣበት መንገድ ቢሆን ለሃገሪቱ እንጥፍጣፊ ተስፋም ቢሆን የመኖርና ቀጣይነት እድል ይፈጥራል ባይ ነኝ። ግባችን አራት ኪሎ ነው መባሉን ሳነብና ስሰማ ልብማ የሚለውን ተረት ትዝ አሰኘኝ። ምድሪቱ የቀማኞች፤ የታጣቂዎች የዘረኞች በሆነችበት በዚህ ያስረሽ ምቺው ፓለቲካ አራት ኪሎ ተደረሰ እንጦጦ ለህዝባችን ለውጥ አያመጣም። መርፌን በመርፌ መለወጥ ለማረሻነት አያገለግልምና። ታዲያ ነገር ሁሉ እንዲህ ጨለማ ከሆነ እንዴት ባለ መልኩ መታገልና ግፍን ማስወገድ ይቻላል? የፋኖ ተፋላሚዎች አቅፎ የያዛቸውን ህበረተሰብ በዚህም በዚያም በመንግስት ሃይሎች እያስገደሉና ራሳቸውም ከዚህ ነህ/ሽ ከዚያ እያሉ በመግደል የሚያተርፉት ከላይ እንዳልኩት የህዝቡን ጉስቁልና ማባባስ ነው። የጠራ የፓለቲካ አቋም በመያዝ በድህነቱ መንግስት በየጊዜው እየታፈኑ ዘብጥያ የወረድት እንዲፈቱ፤ የአማራ ህዝብ ራሱ በራሱ የመረጠው እንዲያስተዳድረው፤ የመጣ የሄደው ዳግም ጉዳት እንዳያደርስበት አሳሪ የሆነ ብልሃት ፈልጎ ጦርነትን በሰላም መቋጨቱ ለአማራ ህዝብም ሆነ ለመላ ሃገሪቱ አስፈላጊ ነው። በታሪክ በጦርነት ለዚያውም ብሄር ተኮር በሆነ ፍትጊያ ነጻ እናወጣዋለን የሚሉትን ህዝብ ለባርነት ሲዳርጉት እንጂ ነጻነትን ሲያጎናጽፉት አላየንም። ለዚህ ዋና ምሳሌዎቹ ሻቢያና ወያኔ ናቸው። የኦሮሞው ፓለቲካ አራማጆችም ትላንትናም ሆነ ዛሬ አውሬ ሆነው የራሴ ነው የሚሉትን ወገን ሁሉ እየበሉ ሌላውን መጤ ናችሁ በማለት የፈጸሙትንና በመፈጸም ላይ ያሉትን ጉዳይ አይንና ጀሮ ላለው ሰው ግልጽ ነው። እኔ የማይገባኝ ይህች የሃበሻ ምድር መቼ ነው የልጆቿን ደም ከመጋት በቃኝ የምትለው? ኦ ኢትዮጵያ በተሰኘው መጽሃፉ ላይ አሳምነው ገ/ወልድ ደመቀ የሲስተር ዞማለምና የሻምበል ወላሌን ታሪክ ላነበበና እንዲሁም Ethiopia: The country that cut off its head : A diary of the revolution by Blair Thomson ሌሎችንም ሃገር በቀል ግጥሞች፤ ቅኔዎች፤ ተረትና ምሳሌዎችን በቅንነት ላገላበጠና ለተመለከተ ምድሪቱ የሚያስቡላትንና የሚያሳስቧትን የማትለይ መሆኗ ቁልጭ ብሎ ይታየዋል። ድሮ ድሮ ሰው ሰው እያለ ነጋ ድራስ ተሰማ እሸቴ ብዙ ግፍ ከተቀበሉ በህዋላ በቅኔ እንዲህ ብለው ነበር።
  ለምን ሰውን ሁሉ ታሰቅቃላችሁ
  ነጣ የወጡትን ይገዙ እያላችሁ።
  የድግግም የባርነት ፓለቲካ ! ችግራችን ውስብስብ ነው። አመላችን እልፍ ነው። ህይወታችን የየቅል ነው። ቀናችን ነሲባዊ ነው። ሁሌ መኳተን፤ ሁሌ መባዘን፤ ኪስን ባዶ አድርጎ አለኝ ብሎ መኩራራት። እኔ በልቼ ካደርኩ ዓለም ሁሉ ጠግቧል ብሎ ማመን ይህ ሊፈተሽ የሚገባው ጉራማይሌ ባህሪያችን ዘርና ቋንቋን ተቃምሶ የህዝባችን ኑሮ ሬት አድርጎታል። ያኔም ጦርነት አሁንም ጦርነት ወደፊትም ጦርነት። አይ ፓለቲካ እልፈት የለሽ ግርግር። እውቁ ገጣሚ ዪናስ አድማሱ ከዘመናት በፊት ጉራማይሌ ከሚለው የግጥም መድበሉ አንድ ስንኝ ልዋስና ይብቃኝ።
  ቀኑ ሲመሽ ነጋ ጠባ
  ምርጫው ሁሉ በየፈርጅ ካልቀረበ ካልተጠና
  ህልውና ምን ሊፀና!

 4. ኦቦ/ጃሌ/ ተስፋ:-
  በዝባዝንኬ የታወቅህ የአብይ አህመድ ተከፋይ ፀሀፊ ተብዬ ነህ:: እንደ አለቃህ አብይ አህመድ ብዙ ቀባጠርክ:: ለችግሩ መፍቻ የሚሆን ቅንጣት መፍትሄ ግን አልጠቀስክም:: ለአማራው ህልውና ተጋድሎ መፍትሄው ይህ ነው አላልክም:: ዝባዝንኬ ብቻ ነው የምትለው በሙሉ::
  አዝማሚያህ ፋኖ ትግል ያቁም ልትል ይመስላል::
  ሞኝህን በሻሻ ሂድና ብላ::
  ፋኖ ግልፅና ቀጥ ያለ የማያወላውል አቋሙን
  አሳውቆ ከፋሽሽቱ አብይ አህመድ ወራሪ የኦሮሞ መንጋ ጋር እየተፋለመ ያለ ህዝባው ሀይል ነው::
  የአማራን እንደ ዘር ከመጥፋት ለማዳን; ክልሉን ከወራሪው ኦሮሙማና ከሙቱ የአብይ እሽከሮች ነፃ ለማድረግ; ነፃነቱን በክንዱ ለማረጋገጥ; በሀይል የተወስዱ ርስቶቹን ለማስመለስ
  በእገር ደረጃም የስርአት ለውጥን እውን ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ የሁሉም የአማራ ህዝብ ድጋፍ ያለው ሀይል ነው::

  አንተ ይህንን ሀይል ነው በንቀትም በጥላቻም ዋጋ የለሽ እያልከው ያለሀው:: ፋኖ ዋጋ ቢስ ስለመሆኑ ርሀኑ ጁላን ጠይቀህ ተረዳ::

  • ጅልን ሃይ ቢሉት አይደነብርም። እንዳንተ ያሉትን ወስላቶችና ቆርፋዳ እይታ ያላቸውን ተሻግረን ነው ለዛሬ የበቃነው። ሶፋህ ላይ ተቀምጠህ ሰውን እሳት ትማግዳለህ። ፋኖ በለው ምንም በምድሪቱ በጠበንጃ አፈሙዝ የሚገኝ ሰላም ሰላም ሳይሆን እልቂትና መከራን የሚያባብስ ነው። የአብይ ደጋፊ ገለመሌ ማለቱ ለመፈረጅ እንዲመችህ እንጂ እኔ የማንም የፓለቲካ ሽርክነት ኑሮኝ አያውቅም፤ እንዲኖረኝም አልፈልግም። አይ የሥርዓት ለውጥ ታሾፋለህ እንዴ? ስንት ጊዜ ይለወጥ፤ ስንት ጊዜ ይበረዝ ትርፍ የለሽ የአስረሽ ሚችው ፓለቲካ! ግባና ዋኝበት። እኔን ለቀቅ!

 5. ኦቦ/ጆሌ /ተስፋ፦
  የአብይ አህመድ ተከፋይ ወይንም አቃጣሪ ወይንም የኦሮሙማ ተስፈንጣሪ ወይንም ልሙጥ ኦሮሙማ ካልሆንክ አማራው ለተጋረተበት የህልውና ችግር መፍትሄ ብለህ የምታቀርበውን ሀሳብ ለምን ይፋ አታደርገውም፡፡ ቆርፋዳና ወስላታ ተሻግረህ ለዛሬ መብቃትህን ተናግረሀል፡፡
  አንተኮ አሁን ላይ፣ ራሱ ዛሬ፣ በዚህች የህዝብ በሆነችው የዘሀበሻ ድረ ገጽ ላይ ቆርፍደሀል; ወስልተሀል፡፤ እንደዚሁም ሆነህ ነው ከያኔው ጀምረህ ዛሬ ላይ የደረስከው ፡፡
  እስኪ አቋምህን አሳውቅ???
  በአስተያየትህ አብይንም በትንሹ ነካ ነካ አድርገህ ፤የአማራ ህዝብ ብቸኛ አለኝታ ሀይል የሆነውንም ፋኖን ኮንነህና ረግመህ አውግዘህም ጭምር እንዲሁ በደፈናው”” ..ብልሀት ፈልጎ በሰላም መቋጨት..።”‘ ብለህ ያልከው “”ያ ብልሀት”” የአማራ ህዝብ ዝም ብሎ በአብይ አህመድና በአሽከሮቹ ሆዳም ብአደኖች እየተገዛ ይለቅ የሚል ነው የአንተ ብልሀት???
  ይህንን ማለትህ ካልሆነ ብልሀቱን መፍትሄውን… አመላክት እስኪ የአብይ አህመድ ወልጋዳ ደጋፊ ካልሆንክ???
  ንክር!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ወይስ አማራ ገዳይ መንጋ (አገመ)

Next Story

ፍኖ ባለውለታችን ነው / የትግራይ እና የአማራ ህዝብ አንድ ነው/ ከዳንግላ ማረሚያ ቤት በፋኖ ነፃ ከወጡ የትግራይ መኮነኖች ጋር የተደረገ ቆይታ

Latest from ነፃ አስተያየቶች

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት

የፋኖ አደረጃጀቶች አንጻራዊ ወሳኝነትና የእስክንድር ነጋ ወሳኝ ሚና

ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ የተነሳው  በእስክንድር ነጋ ላይ ግልጽ ጦርነት እከፍታለሁ ብሎ በመዛት ስለነበር፣ ያ ማራ ሕዝብ ደግሞ ጭራቅ አሕመድን  ጨርቅ በማድረግ ቅኔያዊ ፍትሕ  (poetic justice) ሊሰጠው የሚገባው  በእስክንድር ነጋ መሪነት ነው።    ________________________________________ ያማራ ፋኖ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የቤታማራና የሸዋ

Share