December 14, 2023
3 mins read

ሚናወቻቸውን የተለዋወጡት አቡነ ኤርምያስና አቶ ታየ ደንድአ

7778ioii7878

7778ioii7878 የሐይማኖት አባት ሚና ግፈኞችን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ፍርድ ጠፋ፣ ግፍ ተንሰራፋ፣ ፍትሕ ጎደለ፣ ሕዝብ ተበደለ እያለ በመጮህ ለእውነትና ለእውነት ብቻ በመቆም እመሸበት ማደር ነው።  የፖለቲከኛ ሚና ደግሞ አማላይ ንግግር በመናገር ሕዝብን አደንዝዞ ተወዳጅነት ማትረፍና የግልን ወይም የቡድንን ጥቅም ማሳካት ነው።

የሐይማኖት አባት የሚባሉት አቡነ ኤርምያስ ደግሞ የአማራን ሕዝብ በንቦቴ (drone) እየነቦተ ያለርህራሄ ከሚጨፈጭፍ የጭራቅ አሕመድ አረመኔ ወታደር ጎን ተኩራርተው ተቀመጠው በቅርቡ ላሊበላ ላይ ያደረጉት ንግግር በግልጽ የሚመሰክርባቸው የሐይማኖት አባትነት ሳይሆን የፖለቲከኛነት ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ ፖለቲከኛ የሚባሉት አቶ ታየ ደንድአ ከፖለቲከኛ መንገድ ሙሉ በሙሉ አፈንግጠው፣ ግላዊ ጥቅም ባፍንጫየ ይውጣ ብለው፣ አምባገነኑን ጭራቅ አሕመድን ፊት ለፊት ተጋፍጠው፣ ውሸት በልቶ ውሸት የሚያራ ቀጣፊ ብቻ ሳይሆን፣ በሰው ደም የሚጫወት አረመኔ መሆኑን በግልጽ ተናግረው፣ ለእስር ተዳርገው በተመስገን ጡሩነህ ገራፊወች እየተገረፉ ይገኛሉ።  በጭራቅ የመጣ ሥጋ አልበላም ይቅርብኝ ብለው ሥቃይ መብላት ጀምረዋል

ስለዚህም አቡነ ኤርምያስ ሆይ፣ ተግባርወ ሁሉ የመንፈሳዊ አባት ሳይሆን የፖለቲካኛ መሆኑ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ስለሆነና በሐይማኖት ካባ የፖለቲካ ደባ ለመፈጸም ከማይችሉበት ደረጃ ስለደረሱ፣ ፖለቲካውን በግልጽ ይያዙት።  ሳይመሽ ገሸሽ ብለው ብልጽግናን ይቀላቅሉና፣ ጭራቅ አሕመድ ባቶ ታየ ደንድአ ምትክ የሰላሚ ሚኒስቴር እንዲያደርግወት እግሩ ላይ ወድቀው ይማፀኑት።  አቡን እየተባሉ የነ አቡነ ጴጥሮስን ስም አያጉድፉ

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

images
Previous Story

ከትም አግሳ አንበሳ!

bayisa wak woya `
Next Story

የሽግግር መንግሥት፣ ምንነት፣ አስፈላጊነት እና ለስኬቱ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች  (ለወይይት መነሻ)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop