“ድሃውን በማፈናቀል ላይ የሚገነባ ከተማ ‘ስማርት’ ሳይሆን የሰይጣን ከተማ ነው።” ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ [ኤኮኖሚስት]

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  አርበኞች ግንቦት 7 በአዲስ አበባ ዋና ዋና አደባባዮች ቅስቀሳ ሲያደርግ ውሏል

3 Comments

  1. ያለንበት ዘመን ሰው የደነዘዘበት ጊዜ ነው። እኖራለሁ እንጂ እሞታለሁ ባይ የለም። ችግሩ በራፉ ላይ ደርሶ የመከራው ወላፈን ራሱንና የቅርብ ዘመዶቹን እስካላሰ ድረስ ዓለሙ ሁሉ ለዚያ ሰው ሰላም ነው። ዛሬ ሌላውን እያስለቀሱ እነርሱ የሚስቁ እብዶች ባሉበት ሃገር ከክልሌ ውጡልኝ በማለት በተገኘው ነገር ሁሉ ሰውን መጨፍጨፍ የነጻነት ሰንደቅ ሳይሆን የመከራ ደወል ነው። የሚያስገርመው ትላንት ተጨቆንኩ የሚለው ዛሬ የከፋ ጨቋኝና ገዳይ ሲሆን ማየት ህሊና ላለው ቋሚ ያንገፈግፋል። የብሄር ነጻነት የእብዶች ጥርቅም የፈጠሩት የሃብት ማካበቻ ዘዴ ነው። ነጻ እናወጣሃለን የተባለው ህዝብ ዛሬም እንደታሰረ ነው። Shallow Graves በተሰኘ መጽሃፍ ላይ ስለ ባድሜው ውጊያ ጸሃፊው በአስመራና በአዲስ አበባ የታዘበውን ሲያሰፍር እንዲህ ይላል። ” በከንቱ የሰው ደም ፈሰሰ፤ ያተረፈውም አንድም ነገር የለም፤ የሞቱና የቆሰሉትም ተረስተዋል ይለናል። ሲጀመር የዘርና የክልል ፓለቲካ የውሻ ፓለቲካ ነው። የግድ ቋንቋዬን ተማሩልኝ እያሉ ሰውን ማጨናነቅ የበለጠ ሰው ቋንቋውን እንዲጠላው ያደርጋል እንጂ ኦሮሞነትን አጉልቶ አያሳይም። ታዲያ ጊዜ የሰጣቸው የኦሮሞ ታጣቂዎች ዛሬም ድሃን እያስለቀሱ ስልጡን ከተማ ገነባን ቢሉን አይደንቀንም። መስለጠን መሰይጠን የሆነበት ጊዜ ላይ እንገኛለና።
    ግን በዚሁ ሁሉ ስርግብና የውሸት ጋጋታ አንድ እውን ነገር አለ። ጊዜ ሁሉንም ያስድፋል። የማይገባው ድንጋይ ብቻ ነው። ዛሬ በአማራ ክልል ጠበንጃ በማንገት ከተከፋይ አማራዎችና ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር የሚፋለመው ፋኖ መጨረሻው ምን ይሆን? መገመት የሚችል ይኖር ይሆን? በጭራሽ። ይህ የመገዳደል ፓለቲካ እስካልቆመ ድረስ ዛሬም ወደፊትም ተስፋ እንሰጥሃለን የሚሉትን ህዝብ እያሰቃዪና እያስጨረሱ ከዘመን ዘመን ደካማና በበሽታና በረሃብ የተጠቃ ህዝብን ሞት ከማፋጠን ሌላ ብርሃን አያስገኝም። በትግራይ የረጅም ጊዜ የወያኔ ዘመን ያየነው ይህኑ ነው። ሰው ማስጨረስና ሃገር ማፍረስ። የትግራይ እናቶች ዛሬም ያነባሉ ድሮም አልቅሰዋል። ለውጥ የለሽ ፓለቲካ!
    እውቁ ደራሲ አቶ ከበደ ሚካኤል እንዲህ ብለውን ነበር “የትንቢት ቀጠሮ” በተሰኘው መጽሃፋቸው መግቢያ ላይ።
    እንዳይነጋ እንዳይመሽ ብልሃት ተገኝቶ
    ጊዜውን መከልከል እንዳይቻል ከቶ
    እንዲሁም ባለም ላይ አለ ብዙ ነገር
    በዚያም ቢሉት በዚህ መሆኑ የማይቀር።
    ደም አፍሳቾችና ድሃ አስለቃሽ መንጋ አንተም አንቺም በሰአቱ ማንቀላፋት አይቀርም። ሰውን በሰውነቱ መዝኖ፤ ብሄርን በብሄራዊነት ለውጦ፤ ቋንቋን እንደ መግባቢያ እንጂ እንደ ፓለቲካ መሳሪያ ሳይጠቀሙ በሰላም ኑሮ፤ ለሌላው አዝኖ ማለፍ ምንኛ ያስቀናል። ግን ይህ በሃበሻ ምድር ዛሬ ይገኛል? አይመስለኝም። በቃኝ!

  2. ተስፋ፦
    ታዲያ አማራ ዝም ብሎ ይገደል ነው የምትለው?? በአንተ ትንታኔ የአማራ ህዝብ ትግልም ስህተት ነው ብለሀል፡፡ ፋኖ የሚያደርገው የአልሞት ባይ የህልውና ተጋድሎ ዉጤት አያመጣም ብለሀል፡፡ እና አማራ ምን ያድርግ ነው የምትለው?? ዝም!!!
    አማራ ዘሩ እንዳያልቅ፣ ከምድረ ገጽ እንዳይጠፋ ዝም ብሎ ይገደልልህ??
    ግሳንግስና አገም ጠቀም ነው ጽሁፍህ!!!!
    አንተ በሁለት ቢለዋ ለመብላት የቆምክ አስመሳይ ትመስላለህ፡፡

    • እህቴ አበበች – በጭራሽ አማራ ዝም ብሎ ይጨፍጨፍ የሚል ሃሳብ ቀርቶ ህልምም የለኝም። የእኔ እይታ ሁሌ ለምን በጦርነት ነገርን ለመፍታት እንጥራለን። ጦርነት የፈታው የህዝባችን ችግር የለምና! የዛሬዎቹ አለቆቻችን የኦሮሞ ጽንፈኞች በህዝቡ ላይ በግልጽና በስውር የሚሰሩትን ግፍ ከመረጃ ጋር እከታተላለሁ። እኔ የምለው ለኦሮሞ ህዝብም ሆነ ለቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ መገዳደል ከመከራ ውጭ የሚያመነጨው ምንም ነገር የለም ባይ ነኝ። ይህ የግሌ አቋም እንጂ እኔን ምሰሉ እያልኩም አይደለም። ከሰጠሁት አስተያየት ያልተስማማሽን መተው ነጻነትሽ ነው። በተጻፉ መስመሮች መካከል የራስን ትርጉም አስገብቶ ሰውን መኮነን ግን መልካም አይመስለኝም። የአማራ ህዝብም ሆነ ሌላው ራሱን ከአጥቂዎች የመከላከል መብቱ ተፈጥሮአዊ እንጂ የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ ብቻ ያመነጨው እምቢተኝነት አይደለም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share