November 13, 2023
10 mins read

የበሰለ ፣ የተረጋጋ እና በእውቀት የታገዘ ውጫዊ እና ውስጣዊ ትግል ለዘላቂ እና አፋጣኝ ድል

397539170 338347498789979 7366106918386753928 n 1 1በአሁኑ ስዓት የአማራው ትግል በአገር ቤትም ሆነ በውጭ ሃገራት እየተጧጧፈ እና አመርቂ ውጤት እያስገኘ ነው።

መታወቅ ያለበት የትግሉ ፋና ወጊ ፣ ባለቤቱ ፣ የትግሉን መስመር ቀማሪ እና ምድር ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የሚያውቀው እና የሚመራው ሃገር ውስጥ ያለው ተፋላሚው ቡድን (ፋኖ) ነው።
ትግል ለድል ይበቃ ዘንድ ከአለም አቀፍ የትግል ልምድ አንፃር ሊታወቁ እና ግንዛቤ ሊወሰድባቸው የሚገቡ መርሆዎች አሉ ። እነዚህን መርሆዎች መሰረት እድርገን አሁን መሬት ላይ ካለው የአማራ ትግል ጋር እያነፃፀርን ስናየው የትግሉ አቅጣጫ እሰየው የሚያሰኝ ነው።
በዲያስፖራ የሚካኤደው ትግል በተመሳሳይ መልኩ አመርቂ ሲሆን ሊቀጠልባቸው የሚገቡ አካሄዶችን እያበረታታን ፣  ጥንቃቄ የሚያስፈልጉ ክንውኖች ካሉ መማማር የግድ የሚለን ይሆናል።
የመጀመሪያው አንድ ትግል ሲደረግ ዓላማ ያስፈልገዋል። ይህን መሰረት አድርገን አሁን መሬት ያለውን የአማራ ትግል ስናይ ቁልጭ ያለ ዓላማ ያለው ትግል እየተካሄደ መሆኑን እንገነዘባለን እሱም “ መነሻችን አማራን ነፃ ማውጣት መዳረሻችን ኢትዮጵያን ቀደምት ወደነበረችበት ማማ መመለስ” የሚል ነው። ስለዚህ በአማራ የትግል ዓላማ በኩል በሃገር ቤትም ሆነ በውጭ ሃገር ምንም አይነት ብዥታ የለም ለማለት ያስደፍራል።
በውጭ ሃገር ንዋሪ የሆነው አማራ ኢትዮጵያዊ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ይህን ዓላማ የጋራ የትግል ዳራ አድርጎ እየታገለ በመሆኑ ሁላችንም በሃሴት እድንሞላ አድርጎናል።
ዋናው ልናውቀው የሚገባ ጉዳይ ግን የምዕራቡ ዓለም መንግስታት የአፍሪካ ግጭት እንዲነሳ እጃቸው እረጅም እና ምክንያቶችም እነሱ ሲሆኑ ለአፋቸው እና ለይስሙላ የሚቀናቸው እና የሚሰጡት ሃሳብ ምንም ሆነ ምን ግጭቶቹ በሰላም እንዲፈቱ ማበራታት ነው።
ስለዚህ በተወልድንበት ምድር የሚከናወኑ ግድያዎችን ፣ የዘር ማጥፋት ድርጊቶችን እና ግጭቶችን ሞሳወቁ (Lobby)  እና የዲፕሎማሲ ስራዎችን ማከናዎኑ እንዳለ ሆኖ ይህን የተቀደሰ ዓላማ ስንፈፅም  ጥንቃቄ ልናደራግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ማወቅ የግድ ይለናል።
አማራ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተሰደው በሚኖሩበት ሃገር ፖሊሲ ላይ ተፅህኖ በማሳደር እና  ምልዕክቶቻቸው ወደ ተፈለገው እቅጣጫ ተጉዞ ወታደራዊ ድጋፍ ማግኘት ይቻላቸው ዘንድ እየተፈፀመ ይለው ግድያ ፣ የዘር ፍጅት እና ስደት ለአለም መንግስታት እና ለምዕራባውያን  ሊያቀርብ የሚገባው ፣ የሚያዋጣው እና የተሻለ የሚሆነው ትግሉን በምድር ላይ በሚያካሂዱት የአማራ ፋኖዎች እና ታጋዮች ከመነሻው ቢሆን የበለጠ አጥጋቢ እንደሚሆን ጥናቶች ያሳያሉ።
“If a diaspora wishes to influence the policy choices of its host government in support of military activities in the homeland, the only acceptable avenue of influence should be through lobbying within the normal domestic process.” Thierry Verdier.
ከዚህ ተነስተን ስናይ አማራው ኢትዮጵያዊ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊው ማንኛውንም የጦርነት ጉዳት ፣ ስደት እና የዘር ፍጅት ሲያስተላልፉ ሆነ የዲፕሎማሲ ስራ ሲሰራ መሬት ላይ ያለውን የትግል አካሄድ መሰረት አድርጎ መንቀሳቀስ አለበት።
ከዚህ ባሻገር ለውጭ መንግስታት እና ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች  የሚቀርቡ ጥያቄዎች ፣ መልዕክቶች እንዲሁም  የዲፕሎማሲ ስራዎች  ሲከናዎኑ  የተሳሳተ እና ከዓለም አቀፍ የሰባህዊ መብቶች መርሆዎች ጋር እንዳይጋጩ ትልቅ ጥንቃቄ ሊወሰድባቸው  የግድ ይላል።
ሌላው ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ “ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም “ እንዲሉ በሩዋንድ በኡቱ እና በቱቱሲ የተደረገውን የዘር ፍጅት( Genocide) የድርጊቱን ዳርዳርታና ጅማሮ ወደከፋ እልቂት እንደሚያመራ እያወቁ የተባበሩት መንግስታት ፣ የአውሮፓ ህብረት ፣ አሜሪካ ፣ እንግሊዝ እና በተለይ ቀኝ ገዥዋ ፈረንሳይ ጀሮ ዳባ በማለታቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ አልቋል።
ይህ ማለት የችግሩን ግዝፈት ከማሳወቅ እና ከዲፕሎማሲ ስራው ባሻገር ለነፃነት እና ለድል በሚደረገውን ርብርብ ላይ በይበልጥ ማተኮር  እና መረባረቡ የግድ የሚል ይሆናል።
“Once the civil war broke out in Rwandan 1990, increasingly there were warnings, supported by evidence, that large-scale civilian massacres might occur. Nevertheless, virtually no-one anticipated genocide on the scale that took place. Preparations to deal with the contingency of massive violence that targeted civilians were inadequate.” Howard Adelman.
ሌላው ጥገኛ ተጥይቆ በሚኖርበት በምዕራቡ ዓለም እንደ አሜሪካ ፣ እንግሊዝ እና አውሮፓ ባሉት ሃገሮች ጥገኞች ሰላማዊ ሁነው የትውልድ ሃገራቸውን ገንዘብ በመላክ ፣ ለመጡበት ሃገር አስፈላጊውን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ እንጂ በጦርነት ፣ በግጭት እና በፖለቲካው ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆንን አይገፋፉም። ስለዚህ አካሄዳችን የያዙትን አቋም በማይፃረር መልኩ እና ብልጠት በተሞላበት መልኩ እንዲሆን እንመክራለን።
“Diasporas can play multiple roles in both the host country and the homeland, and diaspora activities can varyingly contribute towards peace-building processes or perpetuate conflict back home.”  Mari Toivanen
ስለዚህ በሃገር ቤት በመንግስት ወይም በፖለቲካ ፓርቲዎች የሚደረግን እስር ፣ ግፍ እና የዘር ፍጅት ለማሳወቅ (lobby ) ወይም የዲፕሎማሲ ስራ ስንሰራ በጥንቃቄ ፣ በእውቀት የታገዘ ፣ የተባበሩት መንግስታትን ፣ የአውሮፖ ሕብረት ሕጎች (Conventions) ፣ ሳይጣረዙ ፣  ከዓላማችን የተቃረኑ እይታዎች እና ትርጉሞች እንዳይኖራቸው  ጥንቃቄ መውሰድ የግድ ይላል ።
አሜሪካኖች ፣ እንግሊዞች ፣ አውሮፓዊያን እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከምንቃወማቸው ቡድኖች ጋር ወገንተኝነት እንዳይፈጥሩ አካሄዳችን ታስቦበት እና በብልሃት ሊከናወን ያስፈልጋል።
በተለያዩ ድህረ ገፆች ፣ በይነ መረቦች እና የመገናኛ ብዙሃን የምንለቃቸው ምስሎች ፣ ቪዲዮዎች እና መልዕክቶች በጥንቃቄ እና የሚጣረዝ መልዕክቶችን እዳያስተላልፉ እንጠቀቅ።
በአጠቃላይ እኛ አማሮች የጦርነትን አካሄድ እና አፈፃፀም ከአያቶቻችን እና ከአባቶቻችን በወረስነው ትብህል ፣ ስልት እና ቀመር የምንከውነው ስለሆነ ጦርነቱን በድል እንፈፅመዋለን።
የሚናካሄደው ጦርነት የተፃራሪ ቡድን ተመልሶ እንዳያንሰራራ እና አከርካሪው እንዴት እንደሚንኮታኮት ከአምላክም / ከአላህ /ጋር ተማክረን ስለምናከናውነው እንደምናቸንፍ አንጠራጠርም ። በትዕግስት ፣ በፀሎት ፣ በአንድነት ቁመን መፋለሙን እና ተመካክረን በጋራ መጓዙን ህይዎት እና የደረሰብን ግፍ አስተምሮናልና ከእንግዲህ ላንሰበር እና አንገታችን ቀና አድርገን የሚያስጉዘንን የፍኖተ ካርታ ማተብ በአንገታችን አጥልቀን ያለማወላወል እንጓዛለን።
ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop