October 1, 2023
16 mins read

የብሄረተኝነትና የዘር ፖለቲካ አደገኛነት ማሳያ፣ እነ ዩክሬንን ማየት ይበቃል – ግርማ ካሳ

55678yhy

በኢትዮጵያዉያን መካከል ስለ ዩክሬን ብዙ አይነገረም፡፡ በዩክሬን ያለው ችግር ስር መሰረቱ ብሄረተኝነት ነው፡፡ የተወሰኑ በዩክሬን ያሉ ፖለቲከኞች በራሺያኖች ላይ ካላቸው ጥላቻ የተነሳ፣ በዩክሬን የሚኖሩ ግማሽ የሚሆኑ ራሺያዎችን መብት ለማክበር ባለመፈለጋቸውና፣ ከዩክሬን ጋር የሩሲያንንም ታሪካዉ ትስስር ለመበጠስ በመሞከራቸው ነው፡፡

በአገራችንም ተመሳስይ ሁኔታ ነው ያለው፡፡ አንድን ማህበረሰብ እንደ ጠላት አድርጎ የማየት፣ የጥላቻና የዘረኝነት ፖለቲካ፡፡

የቀድሞ ሶቬት ህብረት በውስጧ 15 ፌዴራል መስተዳደሮች ( እነርሱ ሪፑብሊክ የሚላቸው) ነበራት፤ ሩሲያ፣ ዩክሬን፣ ካዛክስታን፣ ቤላሩሲያ፣ ኤሰቶኒአ፣ ላትቢያ፣ ሊቱኤኒያ፣ አርሜኑያ፣ ጆርጂያ፣ አዘርባጃን፣ ኡስቤኪስታን፣ ታጂኪስታን፣ ቱርክሚኒስታን፣ ኪርጊኪስታን እና ሞልዶቫ፡፡ እነዚህ አገራት ሲፈጠሩ በዋናነት ህዝብ ውሳኔዎች ከ50 በመቶ በላይ በሚል ነበር፡፡ ያ ማለት ለምሳሌ 55% አገር እንሁን ሲሉ፣ 45% ሲቃወሙ ማለት ነው፡፡

ከሚካኤል ጎርባቾቭ በፊት በሶቬት ህብረት ጠንካራ መዓከላዊ መንግስት ስለነበረ፣ በሶቬት ህብረት ብዙ የርስ በርስ ችግሮች አልነበሩም፡፡ ከኮሚኒዝም ስርዓት ጋር በተገናኘ ፣ በሰብዓዊ መብት ዙሪያ ካሉ ችግርን በስተቀር፡፡

ጎርባቾቭ ሲመጣ ነገሮች መልካቸውን መቀየር ጀመሩ፡፡ ብዙም አልቆየም ሶቬት ህብረት ፈራረሰችና በምትኩ 15 አዳዲስ አገራት ተፈጠሩ፡፡ የተለያዩ አገሮች መመስረታቸው በወቅቱ ጥሩ ተድርጎ ቢታይም፣ አሁን አሁን ግን ከፍተኛ መዘዝ እያመጣ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በአዳዲስ አገራት መካከል የድንበር ውዝግቦችና በአዳዲስ አገራት የተቀሰቀሱ የማንነትና የአናሳ ማህበረሰባት መብት መጨፍለቅ ጉዳይ፣ ከ15 አዳዲስ አገራት በሰባቱ ደም መፋሰስን ያስከተ ቀውስ እንዲከሰት አድርጓል፡፡

ከጎርባቾች በፊት ዩክሬን የሚባል አገር ኖሮ አያውቅም፡፡ በአስረኛ ክፍለ ዘመን ሩስ በሚባሉ ኪየቭ ትቆረቆራለች፡፡ በኪየቭ ዙሪያ፣ የዲኒፕሮ ወንዝን ተከትሎ፣ የኪየቭ ሩስ ግዛት ( empire ) ተፈጠረ፡፡ ሞንጎሎች የኪየቭ ሩስ መንግስት ካፈረሱ በኋላ፣ ራሺያኖች በተለያዩ ቦታዎች የከተማ መስትገዳደሮች መመስረት ጀመሪ፡፡ ቮልጎራድ፣ ሞስኮ ወዘተ፡፡ ኪየቭ ደካማ ከተማ ሆና ቀረች፡፡ በሂደት የሞስኮ ገዢዎች ግዛታቸውን እያስፋፉ መዓከላዊ የሩሲያኖች ግዛት መሰረቱ፡፡ ኪየቭ ጨምሮ፡፡ በታላቁ ካትሪና ሁለተኛ ዘመን፣ የሩሲያ ግዛት አብዛኛው አሁን ዩክሬን ተብሎ የሚታወቀው አካባቢ ሁሉ የጠቀለለ ነበር፡፡ እንደ ኦዴሳ፣ ኬርሶን፣ ሜካኤልቭ ያሉ ትልቅል የዩክሬን ከተሞች ከባዳ የተቆረቆሩት በንግስት ካትሪና ነበር፡፡ እነዚህ ከተሞች የሩሲያኖች ከተማ የነበሩ ናቸው፡፡ ክሪሚያ፣ ዛፖሪቻ የተባሉ አካባቢዎች ደግሞ ኦታምን ቱኮችን በማሸነፍ የሩስያ ግዛት ሆኑ፡፡ የተወሰኑ ምእራባዊ ዩክሬን ግዛቶች የፖላንድ ግዛት ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ልቪቭ የሚባለው ትልቁ የኡክሬን ምእራባዊ ከተማ የሩሱያ ግዛት ስር ሆኖ አያውቅም፡፡ በሃያኛው ክፍለ ዘመን በቦልቺቪኮች ጊዜ ነው ወደ ሶቬት ህብረት የተካተተው፡፡

ያኔ ቦልቼቪኮች ለመጀመሪያ ጊዜ ዩክሬን በሚል ስም የሶቬይት ህብረት አንድ መስተዳደር ወይንም ሪፑብሊክ መሰረቱ፡፡ ይህ ሪፑብሊክ ራሱን የቻለ አገር ሲሆን፣ ታሪካዊ የራሺያዎችን ከተሞችና ቅርሶች ይዞ ነው አዲስ አገር የሆነው፡፡ አንድ ሶስተኛ ዩክሪኖችም ሩሲያኖች ሲሆን፣ ከ70% ደግሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ራሺይኛ ነበር፡፡

ይህ ሩሲያ ባሉ ዘንድ የተወደደ አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን የተለያዩ አገሮች ቢሆኑም፣ ቢያንስ በዩክሬንና በሩሲያ መካከል መቀራረብ ስለነበረ፣ በዩክሬን ያሉ ሩሲያኖችም መብታቸው ተከብሮ፣ እንደ በፊቱ ያለ ልዩነት ይኖሩ ስለነበረ ብዙ ችግር አልተፈጠረም ነበር፡፡

በኋላ ግን በምእራባዊያን ግፊትና ተጽኖ ጸረ ሩሲያ እንቅስቃሴ በተለይም በኪየቭና በምእራብ ዩክሬን ባሉ አካባቢዎች እየጨመረ መጣ፡፡ ራሺይኛ የመንግስት የስራ ቋንቋ ከመሆን ተሰረዘ፡፡ ትምህርት ቤቶች ፣ መንግስታዊ አገልገሎቶች በዩክሬንኛ ብቻ እንዲሆን ተደረገ፡፡ (ልክ በኦሮሞ ክልል እንዳለው) ኔቶ እንገባለን ተባለ፡፡ ሩሱያ እንደ ጠላት በዩክሬን ፖለቲከኞች መታየት ጀመረች፡፡ ያ በዩክሬን ባሉ ሩሲያኖች ዘንድ አልተወደደም፡፡ ትልቅ ቀውስ ተከሰተ፡፡ ከ8 አመት በላይ የርስ በርስት ጦርነት ውስጥ ተገባ፡፡ ምእራባዉያን እጆቻቸውን በማስረዘም የዩክሬን መንግስትን በትጥቅ በመደገፍ፣ ዶንባስ በሚባለው ቦታ ያሉ ሩሱያኖች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ጀመሩ፡፡ ያንንም ተከትሎ ቫልዲሚር ፑቲን፣ በፊትም ዩክሬን አገር መሆኗን ያበሳጨው ነበር፣ በዩክሬን ሩሲያኖችን ለመታደግ በሚል ሰራዊቱ ወደ ዩክሬን እንዲገባ አዘዘ፡፡

እስራኤክና ቱርክ ለማስማማት ሞከሩ፡፡ ተኩስ ለማቆም፣ ዩክሬን በዶንባስ የራስ ገዝ እንድትፈቅድ፣ ራሺያ ተናጋሪዎች መብታቸው እንዲከበር፣ ዩክሬን ኔቶ የሚለው እንደማታነሳ በመርህ ደረጃ ተስማሙ፡፡ ሆኖ አሁንም በምእራባዊኡያኑ ግፊት ዜሌንስኪ አልስማማም አለ፡፡ ያ ባለመሆኑ ጦርነት ቀጠለ፡፡ ምእራባዉያን ሩሲያን ለማዳከም በሚል ዩክሬንን የመስዋት በግ አደረጓት፡፡

ከሁለት አመት በፊት ዩክሬን 46 ሚሊዮን ህዝብ ነበራት፡፡ አሁን በጦርነቱ ምክንያት 26 ሚሊዮን የሚሆኑ ፣ ከግማሽ በላይ ዩክሬንን ለቀው ተሰደዋል፡፡ከዚህ በኋል ምን እንደሚሆን ገና አልታወቀም፡፡ እንግዲህ ፣ የዘር፣ የብሄረተኝነት መዘን ይሄ ነው፡፡

ሞልዶቫ ነሳ መንግስት ነን ብላ ስታወክ፣ በሞልዶቫ ፣ በኢንዱስትሩ ያደገውን አካባቢ በመያዝ፣ ከሞስኮ ስር መውጣት አንፈልግም በሚል ተቃውሞ ተነሳ፡፡ ትራንዚስቲያ በሚል ነጻ አገር ነን ብለው አወጁ፡፡ ፡ በአሁኑ ጊዜ ከሞልዳባ መንግስት ውጭ እራሳቸውን እያስተዳደሩ ያሉ ናቸው፡፡ የሩሱያ ወታደሮችም በዚያ ተሰማርተአል፡፡

በአርሜኒያና በአዘርባጃን መካከል በርካታ ጦርነቶች ተድርጎዋል፡፡ አዘርባጃኖች ሙስሊሞች ናቸው፡፡ አርሚኔያኖች ደግሞ ኦርቶዶስክ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ በአዘርባጃን መካከል ፣ አርሚኔያኖች የሚኖሩበት ናጎርኖ ካራባ የሚል ሰፊ ተራራማ ግዛት አለ፡፡ በዚህ ግዛት ዙሪያ ትልቅ ቀውስ አለ፡፡ ሩሲያ ገብታ ለማረጋጋት ሞክራ የነበረ ቢሆን፣ ሩሲያ አሁን በዩክሬን ተጠምዳለች በሚል፣ አዘርባጃኖች ወረራ የፈጸሙበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡በዚያ ብዙ ሰው አልቋል፡፡ ምነገር ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡

በጆርጂያ ከፍተኛ ጦርነቶች ተደርገው፣ አብካዚያና ደቡብ አሳቲያ የሚባሉ፣ በብዛት ሩሲያኖች የሚኖሩበት ሰፊ ግዛት፣ ከጆርጂያ መንግስት ስር ውጭ ሆነው ራሳቸውን እያስተዳደሩ ነው፡፡ ብዙ ጦርነቶች ተድርገዋል፡፡ ብዙ እልቂት ተከስቷል፡፡ በጆርጂያ ያለው ቀውስ እስከ አሁን እላብት አላገኘም፡፡

በኪርጊስታንና ታጂኪስታን መካከል ጦርነቶች የተደረጉ ሲሆን ፣ አሁን ችግራቸው አልተፈታም፡፡ በኪርጊስታን ውስጥ ታጂኮች የሚኖሩበት፣ የታጂኪስታን ግዛቶች አሉ፡፡ እንደገና ሁለቱም አገሮች የዉሃ ችግር ስላለባቸው፣ የዉሃ ምንጭ በሆነ አንድ ወንዝ ዙሪያም የይገባናል ጥያቄዎች አሏቸው፡፡ ከዚህም የተነሳ በሁለት አዳዲስ አገራት መካከል ። ከማንነት ጋር በተገናኘ ትቅ ቀውስና ችግር አለ፡፡

በላትቢያና በኤስቶኒአት አንድ አራተኛው ነዋሪ ሩሲያዊኡያን ናቸው፡፡ የራሺያ ቋንቋ ተናጋሪዎች፡፡ ሚካኤል ጎርባቾቭ ከለቀቀ በኋላ ፣ የሩሲያ መሪ የነበረው ቦሪስ የልሲን እጅግ በጣም ደካማና ሰካራም መሪ ስለነበረ፣ ሩሲያ በጣም የተዳከመችበት ጊዜ ነው የነበረው፡፡ ያኔ ኢሰቶኒያ፣ ላትቢያና ሊቱኤኒያ የኔቶ አባል ለመሆን ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ምእራባዊያንን ለጎርባቾቭና ለዬልሲን የገቡትን ቃል ክደው፣ እነዚህ አገሮች የኔቶ አባል እንዲሆኑ አደረጉ፡፡ የኔቶ ጥበቃ አለን በሚልም ሩሲያን መገዳደር ጀመሩ፡፡ የራሺይኛ ቋንቋን በማገድ፣ ከፍተኛ የሆነ በደልም ጭቆኖ በራሺያዎች ላይ መፈጸም ጀመሩ፡፡ በሊቱኤኒያ ራሺያዎች 3% ስለሆኑ ችግር ላይኖረው ይችላል፡፡ በላቲቢያን በኤስቶኒያ ኝ፣ አንድ አራተኛ ስለሆኑ፣ ለሩሲያም ጎሮቤት በመሆናቸው፣ ወደፊት ትልቅ ችግር መፍጠሩ አይቀርም፡፡

እንግዲህ ከ15 የቀድሞ ሶቬት ህብረት ሪፑብሊኮችና አዳዲስ አገራርት፣ ስምንቱ፣ ሩሲያ፣ ዩክሬን፣ ሞልዶቫ፣ ጂርጂያ፣ አርሜኒያ፣ አዘርባጃን፣ ታጂኪስታን፣ ኪርጊስታን ጦርነት ውስጥ ተዘፍቀዋል፡፡ በሁለቱ ኤስቶኒያና ላትቢያ ትልቅ ቀውስና መካረር አለ፡፡ ኔቶ ስላለ እንጂ ይፈነዳ ነበር፡፡ ሲደምሩ ከ15ቱ አስሩ ማለት ነው::

የቀሩት ቱርክሚኒስታን፣ ካዛክስታን፣ ኡስቤክስታን፣ ሊቱኤኑያን ቤላ ሩሲያ ናቸው፡፡ ሊቱኤኒያ 97% ሊቱኤኑያንስ ስለሆነ የማንነት ችግር አይኖርባቸውም፡፡ ከካዛኮች ውጭ ያሉት 30% ናቸው፡፡ በቤላሩሱያ ከቢላሩሱያኖኢች ውጭ፣። በኡስቤኪስታን ፣ ከኡዝቡእኮን ውጭ ያሉት 15% ናቸው፡፡ የቤላሩስና የኡዝቤክ መንግስትት የማይኖሪትን መብት አክብረው የሚስሩ በመሆናቸው ብዙ ችግር አልተፈጠረም፡፡ መንግስታቱ ሌላ መንገድ ካልተከተሉ በቀር፡፡ ካዛክስታንና ቱርክሜኒስታን ግን በተለይም ከራሺይኛ ተናጋሪዎች ጋር በተገናኘ ፣ እንደ ላትቢያና ኤስቶኒያ ችግር ያልከረከ ቢሆንም፣ ወደፊት ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡

ይህን ሳቀርብ፣ ኢትዮጵያዉያን ከሶቪየት ህብረት በመማበር ቆም ብለን እንድናስብ ነው፡፡ የማንነት፣ የዘር ፖለቲካ በመለያየት ብቻ የሚፈታ አይደለም፡፡ ተለያይተን ደም መፋሰሱ አይቀርም፡፡ ጎጠኝነትና ዘር እጅግ በጣም አደገኛ ነው፡፡ ለዚህ ነው የዘር ክልል መፍረስ አለበት፣ የጥላቻ ሕገ መንግስት መቀየር አልከበት የምለው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop