መረጃው ትክክል ከሆነ፣ አዳዲስ ንቃተኅሊና አዳዲስ ድምዳሜዎችን፣ ጥያቄዎችን ያስነሳል።
1/ከሁሉ አስቀድሞ እግዚአብሔርን የሚያሳማው፣ ይኸ ሁሉ ውስብስብ የሃብታሞች ተንኮል፣ ይኸ ሁሉ በሰው ነፍስ ኳስ ጨዋታ፣
ምንናምኒት የማያውቀዉን፣ ባዶ እግሩን የሚሄደውን፣ ረሃብተኛ ገበሬ ዘመድ/ወገኔን፣ አሮጊት እናቱን፣ ሕጻናት ልጆቹን እስቲ ምን አድርገውት ነው የሚያስጨርሳቸው?
2/ አንድ ሐቅ…. አዋቂ ነን የሚሉት የአገርውስጥም ሆነ የአለም አቀፍ ኃያላን የፖለቲካ ልሂቃን፣ ምንም ሂደቶችን እንደፈለጉት ቢጠመዝዙ የ Social Dynamics ውጤቱ ምን እንደሚፈጥር፣ ወዴት እንደሚሄድ ማወቅ አይችሉም፤ መምራት አይችሉም። Pandoras Box. (ከሳይንቲስቱ፣ ከመሃንዲሱ የሚለያቸውም አንዱ ያ ነው)
-አማራው ከሞት አፋፍ ተነስቶ በፋኖ ንቅናቄ፣ በአጭር ጊዜ “Political Earthquake” ያመጣል ብሎ ያሰበ የለም።
-በተመሳሳይ ወያኔ በዚያ መልኩ ፈራርሶ፣ መሪዎቹ በየጥሻው ከተደበቁበት እንደ ሳዳም ሁሴን ተጎትተው በካቴና ይታሰራሉ ብሎ የተነበየም አልነበረም።
-(ተፈተው ተመልሰው ቤተመንግስት ይገባሉ ብሎ ያሰበም አልነበረም)
3/ኃያሉም የአሜሪካ መንግስት፣ ወሰን የሌለው የሰው ኃይልና ሃብት እያለው ከላይ የተጠቀሰውን መመለስ ካለመቻሉም በላይ፣ ውሳኔዎቹ (የዉጭ ጉዳይ) የሚዋዥቁና በማንም ሃብታም ባለስልጣን ሊጠመዘዙ መቻላቸው ይደንቃል። እኛ የዋሆች ይመስለን የነበረው ኃያላን የ20 – 30 አመት ስትራቴጅ ቀይሰው የሚንቀሳቀሱ ነበር።
ግን እውን ሃብታም ግለሰቦች የአሜሪካን የዉጭ ፖሊሲ ያስቀይራሉን? ይህ ከሆነ ከኢትዮጵያ የሙስና አሰራር ምን ይለያቸዋል??
(“We Have The Best Government Money Can Buy”, Mark Twain)
መደምደምያ፣ እንደዚህ ከሆነ እውነትም በ ሎቢ ቅጥረኞችና በሙስና ቢያንስ እውነት እንድታሸንፍ ማድረግ ይቻላል ማለት ነው!
4/ኃያላኑ አንዳንዴ ደግሞ ለራሳቸው የማያዉቁም ይመስላሉ። በአንድ በኩል የቀጠናው መፍረስ ሲያሳስባቸው በሌላ በኩል የወያኔን ዘውገኛ ስርአት እያወቁ “ስንቅ በማቀበል ” አዝለዉት ሲ የኖሩበት ምን ምክንያቱ ምንድነው? (ከኃይማኖት ግጭት የዘሩ ይሻላል ባይ ናቸው ብለውናል ዲያቆኑ ምሁር)
ወደመጨረሻው ግን እንደማያዋጣ እየገባቸው ፣ ኮኸን እየጮኸ ፣ ወይ ዉለታ ያውቃሉ ማለት ነው ወይም ባለስልጣኖቹን የያዛቸው አስገዳጅ ውል አለ ማለት ነው።
5/ ለመሆኑ ማነው ድኃ አገሮችን የሚመራው? ራሳቸው እንዳልሆኑ ይገባናል። Is It Money Or Poverty That Is The Root Of All Evil?
6/ ፍትሕን ወደፊት ለማምጣት ምን እናድርግ? ለሚለው ጥሩ መንደርደርያ መረጃ ይመስለኛል።
ግን በቅን ዓላማ ላይ ኅብረት እንደማጣት የከፋ የአዕምሮ ድኅነት የለም።
TT