አቶ ገዱ በምክር ቤቱ ያደረጉት የተቃውሞ ንግግር

 

https://youtu.be/H2MCgkxB5hc

 

 


 

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢዜማ አራት ከፍተኛ አመራሮቹን አገደ

4 Comments

  1. Ato Gedu Feyatay Zeyeman mehonu melkam new.
    That said, given the treacherous and chameleon-like nature of EPRDF people, I understand those people who are suspicious that team Lemma (of which Gedu is a prominent member) maybe setting us up for a second round of speach-based confuse and convince campaign. Why else would they allow him to speak and then leak it to the public?

  2. “…ገዱ የብሔራዊ ደኅንነት የጠቅላዩ አማካሪ አልነበር እንዴ? በሚልዮን ለሚቆጠረው የዐማራ ዘር መጥፋት ዋነኛ ተጠያቂ ሰው አጀንዳዬ አይደለም። አይሆንምም። ጥፋ ከዚህ።”
    Zemedkun Bekele

    They never give up. These EPRDF thugs. They always manifest with the same old trick, partly because it works. Our naive people are obsessed with speeches. What a tragedy!

  3. “…የአቶ ገዱ ንግግር ዐማራን በኦሮሙማው ዐቢይ ከመታረድ አያድነውም። ዐማራው ራሱን ያዳምጥ። ለአሽቋላጭ፣ ለአሽቃባጭ ጆሮ አይስጥ። ጥፋ በለው። የት ነበር እስከዛሬ? ደግሞስ የትግሬው ህወሓት መስራች የአማረ አረጋዊው የሪፖርተር ጋዜጣ በብቸኝነት እንዴት የገዱን ብቻ ንግግር አሾልኮ አወጣው? ትግሬዎቹስ ከምኔው ተቀባበሉት።
    ገዱ አንዳርጋቸው ከዓመት በፊት ፋኖን ያዋረደ፣ ዘራፊ፣ መንገድ ዘጊ ብሎ የወረፈ፣ የዐቢይ አሕመድ የህዳር አህያ የነበረ ሰው አይደለም እንዴ? ”
    Excerpt from Zemedkun Bekele

  4. የምድሪቱን ችግር ከላይ በገድ ንግግር ዙሪያ ከተሰጡ ኮሜንቶች መረዳት ይቻላል። ትላንት እንዲህ ነበረ ዛሬ እንዲህ መሆን አይችልም፤ ዞሮ ተመልሶ ሊሸጠን ነው ይሉናል። ሰው ለዛሬ ነው የሚኖረው። የምትራመደው የረገጥከውን መሬት ብቻ ነው። ባልነጋ ሌሊት የምሳ ሰአት ነው ማለት ጅላንፎ መሆን ነው። ጊዜው የተሰባጠረ፤ መልካሙን ከክፉ መለየት የማይቻልበት ሁሉም ጋዜጠኛና ወሬ አድራሽ የሆነበት የስርግብ ዘመን ላይ እንገኛለን።
    የብልጽግናው መንግስት በጉልበት ሃገር እመራለሁ ማለቱ ስህተት ነው። ይህም ያም ተብሎ የመደመሩን ሂሳብ ላሰላው ከተደመረው የተቀነሰው ይበልጣል። አብሮ መኖር በዓለም ዙሪያ መሆኑ ቀርቶ ክልሌ፤ ልዪ ጥቅም ገለ መሌ እያሉ መፋለጥ የድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ መሆኑ እንሆ በየጊዜው በሃበሻይቱ ምድር ላይ የሚደርሰው የመከራ ዶፍ ምስክር ነው።
    አቶ ገድ የተናገረው እውን ነው። ትላንት በትግራይ ይደረግ እንደነበረው ዛሬም በወረፋ በአማራ ላይ በድሮን ሰላማዊ ሰውን መፍጀቱ የመንግስቱን አረመኔነት አጉልቶ ያሳያል። ልክ ነው ብልጽግና ከአማራ ህዝብ ጋር ዳግም ላይገናኝ ተፋቷል። አቶ ገድ እንዳሉት ነገሩን በሰላም እንደማብረድ በሃይል ለማንበርከክ መነሳት እብደት እንጂ ሰላማዊነት አይደለም። ግራም ነፈሰ ቀኝ ለአማራ ህዝብና ለመላ ሃገሪቱ ብልጽግና ያመጣው የመከራ ዶፍ እንጂ ሰላምን አይደለም። ሲጀመር የዘርና የቋንቋ ፓለቲካ የድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ ነው። በዚህ ዙሪያ የተገኑትን ትርፍ ያስገኘ ቢመስልም ትርፉ ጥቂት ጉዳቱ እልፍ የሆነ የአተካራ ፓለቲካ ለልጅ ልጅ እየተላለፈ ከመገዳደልና ሰዶ ከማሳደድ የተለየ ፍሬ አያፈራም።
    አሁን እንደምንሰማው በዚህም በዚያም መታሰር፤ መገደል፤ ከሥራ መባረር በአማራው ላይ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ይህን የተገፋ ወገን በምክክር ነገርን በማርገብ ሰላምን እንደማረጋጋት በድሮን መደብደብ ድርቡሽነት ነው። ምንም ይሁን ምንም የመረረውን ህዝብ በጉልበት ጸጥ ማድረግ አይቻልም። አቶ ገድም ሆነ ሌሎች በኦነግ እስር ቤቶች ከየመንገድ ተጎትተው፤ ከቤታቸው ታፍሰው በር የተቆለፈባቸው ሁሉ የጠየቁት አንድ ነገር ነው። የአማራ ህዝብ ስቃይ ይቁም። የሃበሻ ፓለቲከኞች እጣት እንደ ሌለው ጉንድሽ እጆች ናቸው። ቢያጨበጭቡ አያደምቁም። ለመኖር ትገላለህ፤ ታስራለህ፤ በእህትና በወንድምህ ሬሳ ላይ ትጨፍራለህ፤ ሰው መሆንህን ረስተህ የአውሬ ባህሪ ተላብሰህ በለው በላት ስትል ጀንበር ጠልቃ ትወጣለች።
    ዓለማችን በመውረግረግ ላይ ትገኛለች። የአንደኛው የዓለም ጦርነትን የጦርነት ሁሉ ማብቃ እያሉ ተጠዛጥዘው ሁለተኛው ከፍቶና ሰፍቶ የሃገራትን ድንበር ሲያጠብ፤ ሃገራትን ሲያጠፋና ሲያዳብል የበፊቱ ጦርነት ተረስቶ ወሬው ሁሉ ናዚ ጀርመኒና ሌሎች ሆነ። አሁን እንሆ በዪክሬንና በራሺያ ተቀጣጥሎ ዓመት የዘለለው ጦርነት ዓለም አቀፋዊ መልክ እየያዘ መምጣቱ ችግሩን ያሰፋዋል እንጂ አያጠበውም። የሃበሻዋ ምድርም በራሷ እሳት ለኩሳ አንዴ በሰሜን አንዴ በምስራቅ ሌላ ጊዜ በደቡብ ወዘተ የሰዎችን መከራ ማበራከቷ ራሷን ያጠፋታል እንጂ አይጠቅማትም። ጊዜ እያለ በትጥቅና በእስራት ነገሮችን ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ በሰላም ለመፍታት መሞከሩ ለአሁንና ለመጭውም ትውልድ ትምህርት ይሆናል። መገዳደል፤ መታሰር፤ መገረፍ፤ ይብቃ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share