August 5, 2023
25 mins read

ከኦሮሙማው የፋሽስት መንግሥት ጋር ድርድር አይሞከር፤ ለፋሽስቶች ድርድር ጠላቶቻቸውን አዘናግቶ ማጥፊያ መሳሪያ ነውና!!

ክፍል አንድ፡

በዶ/ር አሰፋ ነጋሽ – በሆላንድ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ

E-mail -→Debesso@gmail.com – አምስተርዳም (ሆላንድ) ሃምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም.

 

“ብሄረተኛነት እንደ እስስት በአካባቢው ያለውን ቀለም ይወስዳል”

“Chameleon-like nationalism takes its color from its context1”

ይህንን ከላይ የገለጽኩትን አክራሪ ብሄረተኞች ሁልጊዜ እንደ እስስት ቀለማቸውን እየቀያየሩ ጠላቶቻቸውን በማታለል ባህሪ እንዳላቸው የገለጸው አንቶኒ እስሚዝ የሚባለውና ስለብሄረተኛነትና ብሄረተኞች በጻፋቸው በርካታ መጽሃፍቶቹ የሚታወቀው እንግሊዛዊ የአንትሮፓሎጂ ፕሮፌሰር ነው። ይህ ሰው አብዛኛውን ህይወቱን ስለብሄረትኛነት ጥናት በማድረግ በርካታ መጽሃፎችን ከጻፉት ጥቂት በዓለም ውስጥ እውቅ የተባሉ ሰዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ሰው ነው። “ስንኖር ኢትዮጵያዊ፤ ስንሞትም ኢትዮጵያዊ” እያለ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በተደጋጋሚ ያታለለው ዓቢይ አህመድም ሆነ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ” ነው በማለት ዓባይን ተሻግሮ የብአዴንን ካድሬዎች ቀልብ የሳበው፤ በመቀጠልም የኢትዮጵያን ህዝብ ይሁንታ ያገኘው ለማ መገርሳ ድርጊቶች የዚህ ከላይ የጠቀስኩትን የአክራሪ ብሄረተኞችን ከፍተኛ የሆነ የአስመሳይነትና የአጭበርባሪነት ባህርይዎች የሚመሰክሩ ናቸው።

ባለፉት 32 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስታዊ ሥርዓትነት የተቋቋመው ትግራዋይነትን (የትግራይን የበላይነት፤ የትግሬዎችን ልዩ ባለመብትነት፤ ልዩ የታሪክ፤ የባህል፤ የእውቀት፤ የጀግንነት፤ወዘተ ባለቤትነት ይሰብክ የነበረ የአፓርታይድ አገዛዝ)፤ ባለፉት 5 ዓመታት ትግራዋይነትን ተክቶ ሥልጣን የተቆናጠጠው ኦሮሙማ የተባለው አቻው (የኦሮሞን ነገድ ተወላጆች የበላይነት የሚሰብክ የአፓርታይድ ሥርዓት) ፋሽስታዊ የሆነ መንግስታዊ ሥርዓት ነው ብዬ ስሟገት ቆይቻለሁኝ። በዚህ ጽሁፌ የፋሽዝም መሰረት ስለሆነው የሶሻል ዳርዊኒስት አስተሳሰብና በዚህ አስተሳሰብ የሚመሩ ፋሽስቶች በምንም ዓይነት በድርድር እንደማያምኑ አሳያለሁኝ። እንዲያውም ለፋሽስቶች ድርድር ጠላቶቻቸውን አታለውና አጃጅለው የሚያጠፉበት ዓይነተኛ መሳሪያቸው እንደሆነ ለማሳየትና ለማመልከት እሞክራለሁኝ።

 

በሶሻል ዳርዊኒዝም አስተሳሰብ የተቃኘ የፋሽስቶች አይምሮ የሰዎችን ዓለም እንዴት ይረዳል?

በሶሻል ዳርዊኒዝም አስተሳሰብ ላይ መሰረቱን የጣለው ፋሽዝም ሁልጊዜ በህብረተሰብ ውስጥ ያለን ማህበራዊ ግኑኝነት አሸናፊና ተሸናፊ ወገኖች የሚፋለሙበት፤ ኃይለኛው ደካማውን አጥፍቶ በደካማው ሞትና ኪሳራ ህልውናውን የሚያረጋግጥበት የትግል ሜዳ ወይንም መድረክ አድርጎ ይመለከታል። በዚህም ምክንያት በፋሽስቶች እምነት ጠንካራው የሰው ዝርያ ደካማውን የሰው ዝርያ ህልውና በማጥፋት የራሱን ዝርያ ህይወት ማስቀጠል ኢ-ግብረገባዊ ወይም ኢ-ሞራላዊ የሆነ ነውር ድርጊት ሳይሆን ትክክለኛና ተገቢም ነው። የሶሻል ዳርዊንዝም አስተሳሰብ ተቀባይነት እያገኘ መምጣት በሰው አካላዊ ህይወት(physical life) እና በሰው ማህበራዊ ህይወት(social life) ውስጥ ያለውን ልዩነት የማይገነዘብ፤ የሰዎች የህይወት የማያቋርጥ ትግል የሚካሄድበትና ኃይለኛው ደካማውን አጥፍቶ የራሱን ህይወት በደካማው ኪሳራ የሚያስቀጥልበት ሂደት አድርጎ የሚያይ የፋሽስት አስተሳሰብ በመጀመሪያ በአውሮፓ ውስጥ ተስፋፋ። ይህ የሶሻል ዳርዊንዝም ፍልስፍና ጠንካራው የሰው ልጅ ዝርያ ደካማውን የሰው ልጅ ዝርያ ህልውና በማጥፋት የራሱን ምርጥ ዘር አድርጎ ህልውናን ያረጋግጥ በማለት ያስተምራል። ይህ የሶሻል ዳርዊንዝም ፍልስፍና በጀርመን የናዚን፤ በጣሊያን ደግሞ የፋሽስት የፓለቲካ ስርዓት ለመሰረቱት ለሂትለርና ለሙሶልኒ የፋሽስት ርእዮተዓለም መደላድል ሆነ። በሀገራችንም የሶሻል ዳርዊንዝም ፍልስፍና የወያኔ ትግሬዎች በትግራዋይነት ሥም በኢትዮጵያ ውስጥ ለመሰረቱትና ለ27 ዓመታት በሥልጣን ላይ ለቆዩበት የፋሽስት ሥርዓት መሰረት ሆነ። ትግራዋይነት የሚባለው የፋሽስት እምነት የትግራይን ተወላጆች ወርቅነት፤ የሌሎችን የኢትዮጵያ ነገዶች ጨርቅነትና ልፍስፍስነት ሰበከ፤ የትግራይን የበላይነት መሰበክ ብቻ ሳይሆን የአንድን በቁጥር አናሳ የሆነ ነገድ ተወላጆች ልዩ ባለመብትነት የሚያጸና፤ በነገድ ማንነት ላይ የተመሰረት የመድሎ ወይም የአፓርታይድ ሥርዓተ መንግስት ፈጠረ። ከአምስት ዓመት ወዲህ ደግሞ የወያኔ ትግሬዎችን ተክቶ ኦሮሙማ በሚል ሥም የኦሮሞን ነገድ ተወላጆች የበላይነት የሚሰብክና የሚተገብር ፋሽስታዊ አገዛዝ የመሰረተው የገዢው የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ በዚህ የሶሻል ዳርዊንዝም ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ የተቃኘ የፋሽስት ፍልስፍና ተከታይ ነው። በሥልጣን ላይ ያለውን የዓቢይን መንግስት እንቃወማለን የሚሉት የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ)፤ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስና ሌሎችም የኦሮሞ አክራሪ ብሄረተኛ ድርጅቶች ይህንኑ በሶሻል ዳርዊኒስት አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ፋሽስታዊ የአፓርታይድ ስርዓት ደጋፊዎች እንደሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። በሚያሳዝን ደረጃ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶችና ምሁራን ጭምር የወያኔን ትክክለኛ ተፈጥሮና ባህርይ ባለመረዳት አንዴ የአልባኒያ ኮሚኒስት እምነት ተከታይ፤ አንዴ ወያኔ ራሱን በሚጠራበት ሥም የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሥርዓት አራማጅ ሲሉት፤ አንዴ ደግሞ የልማታዊ መንግሥት ወዘተ ነው እያሉ ለዚህ ፋሽስታዊ ሥርዓት የተሳሳተ ትርጉምና ብያኔ ሲሰጡት ቆይተዋል። የዚህን ፋሽስታዊ ፍልስፍና የሚመራ ድርጅት ትክክለኛ ተፈጥሮና ባህርይ ለመረዳት ተቸግረን የቆየን ቢሆንም በተለይ ባለፉት አምስት ዓመታት የተፈጸሙት የጥፋት ድርጊቶች፤ ለሁለት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ የተደረገው ጦርነት፤ ብብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በአማራና በአፋር ህዝብ ላይ ማዕበላዊ በሚባል ደረጃ እንደ መንጋ ተንቀሳቅሰው በወረራ የፈጸሙት ዘግናኝ ድርጊት፤ በትግራይ ውስጥ ሀገር ሰላም ነው ብለው በተኙ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባሎች (አብዛኞቹ ሰለባዎች የአማራ ተወላጆች ነበሩ) ላይ በተራው የትግራይ ተወላጅ ጭምር የተፈጸሙት ዘግናኝ ጭፈጨፋዎች2 በትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ በ49 ዓመታት ውስጥ የበቀለውን የፋሽስት ሥርዓት ምንነት በግልጽ አሳይቷል።

 

– ለዝርዝሩ “የተካደው የሰሜን እዝ” የሚለውን በጋሻዬ ጤናው (ቻቻው) የተጻፈውን መጽሃፍ ፈልገው ያንብቡ።

የፋሽዝም አንዱ መገለጫ የሆነው የሶሻል ዳርዊንስት አስተሳሰብ ተስፋፊነትን፤ ወሰን-ገፊነትን፤ በሌላው ኪሳራ የራስን ወገን ጥቅም የማስከበርን ዓላማ፤ ሁሉን ነገር ለራስ ብቻ የማድረግን (የኦሮሞ ብሄረተኞችን ሁሉም ነገር የኦሮሞ ነው የሚለው የ”ኬኛ ፓለቲካ”፤ ስግብስብነትን፤ ሁሉን እኔ ብቻ ልቆጣጠር የሚልን አስተሳሰብ ያስፋፋል፤ ያስከትላል። የጀርመን ናዚዎች “ጀርመን ከሁሉ በላይ ነው” (Deutchland Uber Alles”) የሚለውን የፋሽስት አስተሳሰብ በመከተል የምርጡ የአርያን ዝርያ ነኝ ይል ለነበረው የጀርመን ህዝብ ማስፈሪያ የሆነ ምቹ የመኖሪያ ሥፍራ(Lebensraum፟) ስላስፈለጋቸው የፓላንድን፤ የቼኮዝሎቫኪያን ወዘተ ለም መሬቶች በኃይል ወደ ጀርመን የጠቀለሉበት ሁኔታ የዚህ በሶሻል ዳርዊንዝም ላይ የተመሰረተ ፋሽስታዊ የመስፋፋትና ሁሉን ነገር ለራስ የማድረግ ፓለቲካ ውጤት ነበር። የወያኔ ትግሬዎች ከታህሳስ 1972 ዓ. ም. ተከዜን ተሻግረውና በወታደራዊ ኃይል ወልቃይትን በመውረር ለምርጡ የትግራይ ህዝብ የጎንደር አማሮች ይዞታ የሆነውን የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ሁመራን መሬቶች በወረራና በኃይል በመያዝ፤ ነባሩን የአማራ ተወላጅ ዝርያ በጅምላ በማጥፋት፤ በማሰደድና ህልውናውን በማጥፋት ይህን ለም አካባቢ ለ”ወርቁ የትግራይ ህዝብ” (መለስ በየካቲት 11 ቀን 1984 ዓ. ም. የኢትዮጵያን ህዝብ “ወርቅና ጨርቅ3” ብሎ በመለየት በብዙ መቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎቹ መቀሌ ላይ ለትግራይ ተወላጆች ያደረገውን ንግግር አንርሳ!!!!!) ዝርያ ህይወትና ህልውና ማስቀጠያ አደረጉት። ይህንን የወያኔ ትግሬዎችን ፋሽስታዊና ሂትለራዊ የሆነ በሶሻል ዳርዊኒዝም አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ወረራና የዘር ማጥፋት ትክክል እንደሆነ መለስ ዜናዊ ያሳወቀው በሚከተለው ንግግሩ ነበር።

“ተፈጥሮ አፈርን የምትሰጠው ለተወለዱባት ሳይሆን በጉልበት ለሚይዟት ነው። መሬት የጉልበተኞች ናት። እኛ ወደዚህ (ወደ ወልቃይት፤ ጠገዴና ጠለምት) ስንመጣ ጨፌ እየተነሰነሰልን አይደለም፤ ደም አፍስሰን፤ አጥንት ከስክሰን፤ ህይወት ከፍለን ነው። እናም እንዲህ ማድረግ የሚችል ብቻ መሬትን ይወስዳታል፤ ይጠቀምባታል4” ። መለስ ዜናዊ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ትህነግ) የተባለው የፋሽስት ድርጅት መሪና ኋላም ለ21 ዓመታት የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረ ሰው ከተናገረው የተወሰደ።

ከላይ በጥቅስ ያሰፈርኩት መለስ ዜናዊ እንደዚህ ብሎ ሲናገር የሰሙ አንድ የወያኔ የጥቃት ሰለባ የሆኑ የዚህ በወረራ ትግሬዎች ይዘውት የነበረው አካባቢ ተወላጅ ስለ ወልቃይት፤ ጠገዴና ጠለምት ሰፊ ሳይንሳዊ ጥናት ያደረገው የጎንደር ዩኑቨርሲቲ የጥናትና የምርምር ቡድን ሁመራ ከተማ ላይ ከእኚህ ሰው ጋር በመጋቢት 30 ቀን 2013 ዓመተ ምህረት ቃለመጠይቅ ባደረገበት ጊዜ ከሰጡት የግል ምስክርነት የተወሰደ ነው። ለዝርዝሩ “ወረራና መዋቅራዊ ዘር ማጥፋት በወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት – የምርምር ውጤት” የሚለውን በጎንደር ዩኑቨርሲቲ በ2014 ዓ. ም. የታተመውን በመረጃና በአሃዝ የተደገፈ ግሩም የሆነ ጥናት ያካተተውን 380 ገጾች ያለው መጽሃፍ በማንበብ ማንኛውም ህሊና ያለው ኢትዮጵያዊ የወያኔ ትግሬዎች መንግሥት በወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት ህዝብ አማራ በመሆኑ ምክንያት ብቻ የፈጸመበትን ግፍ ያንብብ። የወያኔ ትግሬዎች የተከዜን ወንዝ በመሻገር እነዚህን የጎንደር አካል የሆኑ ለም አካባቢዎችን በመውረር የአማራን ወንዶች ህይወት በማጥፋት፤ የአማራን ሴቶች አስገድዶ በመድፈርና ልጅ በማስወለድ የአማራውን ታሪካዊ ይዞታ ለመንጠቅ የፈጸሙትን ሊረሳ የማይገባ ዘግናኝ ፋሽስታዊ የጅምላ የዘር ፍጅት ድርጊት፤ በአማራው ህዝብ ላይ ያካሄዱት የስነልቦና ጦርነት፤ ማፈናቀል፤ አማራውን ህዝብ የማሰደድና በማህበራዊ

– ለዝርዝሩ መለስ ዜናዊ በየካቲት 1984 ዓ. ም መቀሌ ላይ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ያደረገውን ንግግር ያዳምጡ።

– “ወረራና መዋቅራዊ ዘር ማጥፋት በወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት – የምርምር ውጤት” በጎንደር ዩኑቨርሲቲ

ነሃሴ 2014 ዓ.ም. ታትሞ የወጣ 380 ገጾች ያለው መጽሃፍ ውስጥ በገጽ 222 ላይ ከሰፈረው ጥቅስ የተወሰደ። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነው የጥናት ውጤት በኢትዮጵያ ውስጥ እንኳን በበቂ ሁኔታ ታትሞ ለአንባቢያን እንዲደርስ አልተደረገም። ይህንን ችግር ለመቅረፍ ለጎንደር ዩኑቨርሲቲ የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ አንደኛ ጥናቱ በስፋት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አንባቢ እጅ እንዲደርስ ብናደርግ፤ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ይህ እጅግ ጠቃሚ የሆነ የጥናት ውጤት ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲተረጎም የገንዘብ ድጋፍ ብናደርግ ይህንን የወያኔ ፋሽስታዊ መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ ያካሄደውን ወደ 38 ዓመት የዘለቀ (ከነሀሴ 1971-2019 ዓ. ም. ድረስ የቆየ) የዘር ማጽዳት ወንጀል (ethnic cleansing of Amaras in Welkait-Tegede en Telemet regions of Gondar)፤ እንደዚሁም እነዚህ የወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት ተወላጆች የደረሰባቸውን ከልክ ያለፈ ሰቆቃና ሥቃይ ለዓለም ህዝብ ለማሳወቅ እንችላለን ብዬ አምናለሁኝ። በዚህ በጎ ተግባርም ማንኛውም ለፍትህና ለእውነት የቆመ ኢትዮጵያዊ እንዲተባበር በዚህ አጋጣሚ እጠይቃለሁኝ።

ምህንድስና (social engineering) አማካይነት የአካባቢውን የህዝብ ስብጥር (demographic profile) ለመቀየር የሄዱበትን ርቀት አንባቢ ልብ እንዲል አሳስባለሁኝ። ይህ ከላይ የጠቀስኩት የመለስ ዜናዊ ንግግር ሂትለራዊ የሆነውንና በሶሻል ዳርዊናዊ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተውን ጠንካራው የሰው ነገድ የደካማውን ሌላ የሰው ነገድ ዝርያ በማጥፋት የራሱን ነገድ ህልውና ማስቀጠል አለበት የሚለውን አመለካከት የሚያንጸባርቅ ነው።

የወያኔ ትግሬዎች በኋላም ሥልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊት ወልቃይት ጠገዴን በኃይል ወረው የያዙበት፤ ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ደግሞ የራያን፤ የጋምቤላን ሰፊና ለም መሬቶች “ለወርቆቹ” የትግራይ ነገድ ተወላጆች ጥቅም ያዋሉበ መንገድ ከጀርመን ናዚዎች የመስፋፋትና ሌሎችን ህዝቦች ወሮ በማጥፋት መሬታቸውን ከተቆጣጠሩበት ሂደት ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው። የጀርመን ናዚዎች የጀርመን ተናጋሪዎች የሚኖሩበት ቦታ ሁሉ የጀርመን ይዞታ ሊሆን ይገባል ብለው በወረራ የሌሎችን ህዝቦች ህልውና በማጥፋት ያደረጉት መስፋፋት፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ወያኔ ፋሽስቶች የ1968ቱን የወያኔ ማኒፌስቶ ካወጡበት ጊዜ በኋላ ትግሬዎች የሰፈሩበትን ቦታ ሁሉ የትግሬ ይዞታ ነው ብለው እንደነ ሂትለር በመከለል በእብሪትና በማን አህሎኝነት ስሜት በወታደራዊ ኃይል በመስፋፋት በወልቃይት-ጠገዴ፤ በጠለምት እንደዚሁም ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ በራያ ህዝብ ላይ የፈጸሙት የዘር ማጽዳት ድርጊት የዚሁ የፋሽዝም መገለጫ የሆነ የሶሻል ዳርዊኒዝም አስተሳሰብ አካል ነው።

ባለፉት አምስት ዓመታት ደግሞ የወያኔ ትግሬዎችን ፋሽስታዊ መንግሥት የተኩት የኦሮሞ ፋሽስቶች በወለጋና በምዕራብ ሸዋ በአማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የፈጸሙት የዘር ማጥፋት (ethnic genocide) ወንጀል፤ አማራውን በጅምላ በመፍጅት፤ በማፈናቀል፤ በቤኒሻንጉልና መተከል፤ በሰሜን ሸዋ (በአጣዬ፤ በደራ፤ በሸዋ ሮቢት ወዘተ)፤ በምሥራቅ ሸዋ (በምንጃር ሸንኮራ፤ ወልንጭቲ፤ መርቲ፤ ወዘተ) በኦነግ ሸኔ ስም የሚያካሂዱት ፋሽስታዊ የመስፋፋት ሙከራዎች በዚህ የሶሻል ዳርዊንስት አስተሳሰብ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። እንደዚሁም የኦሮሞ ፋሽስቶች በደቡብ ኢትዮጵያ ባሉ ነገዶች ላይ (በጉራጌ፤ ሲዳማ፤ አማሮ፤ ጌዴኦ፤ ወዘተ)፤ በኦጋዴን የሶማሌ ክልልን ድንበር በመጣስ እያደረጉ ያለው መስፋፋት ከዚሁ ከፋሽስታዊ የመስፋፋትና ሁሉን የመጠቅለል አባዜ ጋር የተያያዘ ነው። አምስት የኦሮሞ አክራሪ ብሄረተኛ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላይ ወጥተው “አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት” ብለው ካለአንዳች ይሉኝታና እፍረት በጋራ የሰጡት መግለጫ ከዚህ የሶሻል ዳርዊናዊ አስተሳሰብ የሚሰርጽ ነው። የአዲስ አበባን ነባር የህዝብ ስብጥር ሥር-ነቀል በሆነ መንገድ ለመለወጥ ቀደም ሲል በለማ መገርሳ በኦሮሞዎች ስብሰባ ላይ የተነገረው እቅድና ኋላም ኦሮሞዎችን ከሀረርጌ አምጥቶ አዲስ አበባ ዙሪያ በስፋት የማስፈሩ ድርጊት የዚሁ አዲሱ የፋሽስቶች የማህበረሰባዊ ምህንድስና (social engineering project) አንድ አካል ነው።

 

ክፍል ሁለትና ክፍል ሶስት በተከታታይ ይቀርባሉ፤ ይጠብቁኝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop