July 20, 2023
1 min read

በድብቅ የተቀረጸው የም/ቤቱ ገመና”መከላከያ ወደ ክልላችን ማን ፈቅዶለት ነው የገባው?” “በታሪክ የምትጠየቁ መሆናችሁን እወቁ” ዮሐንስ ቧያሌው

https://youtu.be/Y36gGQvGZ3A

 

2 Comments

  1. በእርጋታ ላዳመጠው በምድሪቱ ያለውን የአንድ ጎሳ የበላይነትና የሌሎችን በተለይም የአማራን መገፋትና የእርስ በእርስ መቆራቆስ ጠንቅቆ ያስረዳል። አማራው አማራውን በመግደል የሚያተርፈው የኦነግና የወያኔን እሰይታ ብቻ ነው። ቅጥ ያጣ በስመ ብልጽግና ሰውን በየቀኑ መግደል ወንጀል እንጂ ጀግንነት አይደለም። ያ ተገዳይ ሰው የሚረዳው፤ የሚያስተዳድረው በስሩ ብዙ ድሆች እንዳሉ መረዳትም ያስፈልጋል። አሁን የፋኖን አርማ ይዘው በዚህም በዚያም የሚሯሯጡት ወገኖች ግድያ ትርፍ የለሽ እንደሆነ ሊያውቁ ይገባል። ጀግንነት ህዝባችን የሚያመሳቅሉትን፤ የሚያፈናቅሉትን፤ ለስብሰባ ጠርተው በመትረጌስ የሚረሽኑትን፤ ሰውን በዘሩና በሃይማኖቱ እየመረጡ የሚገሉትን መፋለም ነው። አውቃለሁ አማራ ሆነው ሰውን የሚያስገድሉ፤ የሚያሰቃዪ፤ በህዝብ ላይ የሚነግድ እንዳሉ። ይሁን እንጂ ሞት ብቻውን የአጥፊዎች መልስ ሊሆን አይችልም። ሊመከሩ፤ ሊዘከሩ፤ በቀጥታም ሆነ በእጅ አዙር ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው ማድረጉ የቅድሚያ ምርጫ ሊሆን ይችላል። እርስ በእርስ እየተገዳደሉና ህዝብ እያሸበሩ ለነጻነት ቁሜአለሁ ማለት ወያኔና ኦነግን መምሰል ነው። አይመችም። የአንድ የታጠቀ ሃይል ዋናው ሃብት ያስጠለለው ህዝብ ነው። ያን ህዝብ ለስቃይና ለመከራ እያጋለጡ አብላኝ አጠጣኝ እርዳኝ ማለት ጾምን አድሮ ውድቀትን ለማምጣት ብቻ ነው።
    አንድ ሰው እውነት ታሸንፋለች በማለት አንድ ስብሰባ ላይ በደም ፍላት ይናገራል። በእድሜ ጠና ያሉ ሰው ቆም አሉና ውሸት ነው እውነት አሸንፋ አታውቅም። አንተ ልጅ ነህ እኛ በዘመናችን እውነት ሙታ ቀብር ላይ ተገኝተናል። በማለት ቁም ነገርና ቧልት ቀላቅለው ቁጭ አሉ። እኔ በነገሩ አሰብኩበት። ልክ ናቸው። እውነት አሸንፋ አታውቅም። እውነት በውሸትና በሸፍጥ ተሸፍና ሰው ይሞኝባታል እንጂ። የዓለምን ያለፈ የፓለቲካ ስሪትና አሁን ያለውን እሰጣ ገባ ለተመለከተ እውነት የሚባል ነገር የለም። ረጅም ከዘራ ያላቸው ዓለምን እንደ ፈለጉ ያሽከረክሯታል። ሲሻቸው የሌላ ሃገርን ያፈርሳሉ፤ መንግስት ይገለብጣሉ ብቻ ድርጊታቸው ሁሉ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ አይነት በመሆኑ በእኛም ሃገር ላይ የሚታየውና የማይታየው ሽኩቻ ሁሉ የሚያሳየን ይህኑ ሃቅ ነው። ትላንት በነጻነት ስም እልፍ ሰው የገደሉ ዛሬ በም ዕራቡ ዓለም በዘረፉት ሃብት ተንደላቀው ይኖራሉ። የድሃ ልጆች ግን ምስጥ ከበላቸው ቆይቷል። እውቁ ደራሲ ጆርጅ ኦርዌል እንዳለው ” ነጻነት ባርነት፤ ባርነት ነጻነት” ሆኖብናል። ከሱዳን የተገነጠለችው ደ/ሱዳን ዛሬ ላይ ህግ የሌለባት አልፎ ተርፎም ኢትዮጵያ ድንበር እየገባች በጥባጭ ሆናለች። 30 ዓመት የተዋጉት ኤርትራዊያን በተገኘው ሁሉ እግሬ አውጭኝ በማለት ሃገራቸውን እየለቀቁ ተሰደው በዓለም ላይ ተበትነዋል። 27 አመት በወያኔ ገመናውን ያየው የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬ ላይ በኦነግ ፓለቲካ ይኸው እንሆ ምድሪቱ አይታ የማታውቀው ሰቆቃ በመቀበል ላይ ትገኛለች። ክወያኔም ሆነ ከኦነግ የመከራ ዶፍ ለማምለጥ እልፎች በዚህም በዚያም ሲሰደድ ቀሪዎቹ ደግሞ በመንገድ ላይ ቀርተዋል። ለዚህ ነው የሃገሬ ሰው ኢትዮጵያ ሃገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ያለው። እነ ጌታቸው ረዳ፤ እነ ጄ/ጻድቃን ያን ሁሉ የትግራይ ወጣት አስፈጅተው አሁን የሰላም አየር ሲተነፍሱ ማየት የእውነትን መቀበር እንጂ ፍትህን አያሳይም።
    ብልጽግና በፊትም አቶ ዪሃንስ ቧያለውን አይወድም አሁንም የመጥለፊያ ገመድ እንደሚያዘጋጅ ከአሁኑ መተንበይ አያቅትም። ፓለቲካው ከተጣረሰ ቆየ። እያሰፈራሩ፤ እያሰሩ፤ እየገደሉ፤ ዲሞክራሲ ብሎ ነገር የለም። ጠ/ሚሩ ራሱን ብቻ የሚያዳምጥ፤ በማር የቀባ መርዙን በሾለ ምላሱ የሚረጭ፤ የሰዎች መከራና ሃዘን የማይገባው፤ ዛሬ እዚህ ይህን ያህል ሰው ሞተ ሲባል ሌላስ የሚል ነው። ቃል ብቻውን ዳቦ አይሆንም። በምድር ላይ ያለው እውነት መንግስት እንዳለ ሳይሆን እንደፈረሰ ነው የሚያመላክተው። የሚገርመው ዛሬ ላይ የኦነግ ጭካኔ ያስመረራቸው ወያኔን ማመስገናቸው ነው። ለዚህ ይሆን ከማያውቁት መላክ የሚያውቁት ሰይጣን ይሻላል የሚሉት አበው። ግራም ነፈሰ ቀኝ የአማራው ፓለቲካ አማራውን በመግደልና በመዝረፍ የትም አይደርስም። ዲሲፕሊን የሌለው የታጠቀ ሃይል ለራስም ሆነ ለሃገር እርባታ የለውም። መግደል መገዳደል የኖርንበት ያለንበት መንገድ በመሆኑ ሌላ አማራጭ መንገድ መፈለግ እንጂ የዚህ የፓሊስ አዛዥ ተገደለ፤ እዚያ እከሌ ወደቀ መባሉ የሽንፈት መንገድ እንጂ የድል ጎዳና አይደለም። እርግጥ ነው ታጥቆ ሊገልህ የሚተኩስብህን ደረትክን ስጥ እያልኩ አይደለም። ግን የተናጠልና የደፈጣ ግድያ ዋጋቢስና ከፓለቲካ መስመር የወጣ ውንብድና ነው። ይህን የተመለከቱ ጅላ ጅሎች ዛሬ ደም እንመልሳለን በሚል የቂል ባህል እርስ በርስ እየተገዳደሉ ነው። ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው እንዲሉ በጊዜ ወደ ልቦናችን ተመልሰን ለተገፉ፤ ለተጨቆኑ፤ መከራን በየጊዜው ለሚቀበሉ፤ ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ መሆን እስካልቻልን ድረስ በዚህም በዚያም ሳቢያ አማራው በራሱ ላይ የሚያደርገው ግድያና አፈና ሁሉ መልሶ ራሱን ለጠላት አሳልፎ ይሰጠዋል እንጂ አይጠቅመውም። ወያኔና ኦነግ ያሰቡልህን ታውቃለህ? ቆይቶ ማየት ነው። በቃኝ!

  2. ANDM (ADP). Ke zinjero qonjo min yimerariTual? Gedu, Buayalew, mintise, manitise – all criminals that handed over the Amhara for slaughter with hands tied behind the back.

    TPLF’s creatures keep changing their colors like the chameleon. Amhara is now overcoming the tendency to believe his ears over his eyes. Now the time is for action to speak volumes. ye Kadre fughera zemen alfual. ye kadre qes inna shek zemenim alfual. Ahun yemishemeghillen irsas inna imbita bicha new. Hullum kelibu yemiyadamiTewun quanqua bemenagher bicha new megbabat yemichallew. Isu degmo rasin mekelakel new.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Abiy Ahmed 5 1 1
Previous Story

መፍጠንና መፍጠር፡ የብልጽግና ፓርቲ አዲስ ጸረ-አማራ ዘመቻ – በደሳለኝ ቢራራ

456666 1 1
Next Story

ከሰዶም የከፋ እንዲህ ዓይነት ዘመን!

Latest from Blog

blank

አርበኛ አስረስ ማረ እና ምርኮኞቹ | ስለ ፋኖ የብሔራዊ ባንክ ገዥው ያልተጠበቀ ንግግር |

#ሰበር_ዜና #AmharaFano ➢መሰከረም 29/01/2017 ዓ.ምብዙ ድሎችን አግኝተናል፣➢1️⃣115 ምርኮኛ ➢2️⃣70 እስረኞችን አስለቅቀናል➢3️⃣ 7 ብሬን➢4️⃣2 ድሽቃ➢5️⃣ 4 ስናይፐሮችን➢ለትግል የሚጠቅሙ የነፍስ ወከፍ ክላሾችንተተኳሾችን መኪኖችም ገቢ… pic.twitter.com/GbYaOAtFtr — ትዝብቱ🔔 (@Geteriew1) October 12, 2024 በፋኖ የተማረኩት ኮሎኔል
blank

ትግሉ ይጥራ – ከጥሩነህ ግርማ

የህልውና ትግሉን ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ለማሸጋገር የኦይዶሎጂ ብዥታን ማጥራትና በመሬት ላይ ያለውን ተንኮል መጋፈጥና ማፅዳት ያስፈልጋል የህልውና ትግሉ በአማራ ብሄርተኝነት ላይ ያጠነጠነ እንደመሆኑ የመኖር አለዚያም እንደ ህዝብ  የመጥፋት ትግል ነው: ሌላው ኢትዮዽያዊ ወገን
blank

የፋሽስቱ አብይ አህመድ አሊ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ላይ እየተካሄደ ስለሚገኘው ጦርነት ከመስከረም 13 እስከ 27/2017 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች ላይ የደረሰ የጉዳት !!!መረጃ:

ሸዋ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ኮሉ በተባለ አካባቢ ላይ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ከኦሆዴዱ ጥምር ጦር ጋር ቅንጅት በመፈጠር መስከረም 22 ቀን 2017ዒ.ም ከለሊቱ
Go toTop