July 5, 2023
11 mins read

“ጠላት ለማስደሰት ኢትዮጵያን ማስከፋት እና ትጥቅ ማስፈታት ለምን “

በታሪክ ጅረት ኢትዮጵያን እና ህዝቧን በመከራ ጊዜ ከፊት የተገኙ የቁርጥ ቀን ልጆች  በተለያየ ጊዜ በአድርባይነት እና በብልጣብልጥነት ልክፍት ባለባቸዉ መገለላቸዉ ድንገት ሳይሆን ልማድ ሆኖ ዉሎ አድሯል ፤ የፖለቲካ ባህል አካል ሆኗል ፡፡

በግፍ እና በዕብሪት ለዘመናት በራሱ አገር የተገለለ፣ የተገደለ እና በብዙ ነገር የተበደለ ህዝብ ራሱን ፣ህልዉናዉን እና አገር ከዕብሪተኛ እና ጎጠኛ ለመከላከል የከተተ  ህዝብ ባልሞት ባይ ተጋዳይነትራስን የማዳን ተፈጥሯዊ መብት ለማስጠበቅ  እጂ እና አግሩን ይዞ  ወደ ዕሳት ዕቶን የገባ ህዝብ ዓለማዉ ሞቶ ትዉልድ እና አገር ማስቀጠል ነበር ፡፡

ይህም ከሶስት ዓመታት ዕልክ አስጨራሽ ግብግብ ህላናን በሞት እና በአካል ጉዳት ገዝቶ ጠላትን አንበርክኮ እና ማርኮ የመሳሪያ ባለቤት ሆኗል ፡፡

ይህም በብርቱ መስዋዕትነት የተገኘ አገርን እና ትዉልድን የማስቀጠል ህልም ዕዉን የሖነዉ በዕዉነተኛ የአገር ፍቅር ዋጋ በከፈሉት የቁርጥ ቀን ደራሽ ኢትዮጵያን እና ልጆች ነዉ ፡፡ በዚህ ግንባር ቀደም የዕብሪት ጦርነት የጣወጀበት ፣ ወረራ እና መከራ የደረሰበት ፣ ምዝበራ እና ካራ የጠሳለበት የዓማራ ህዝብ አንዱ እና ዋነኛዉ ነዉ ፡፡ እኮ እንዴት የረጂም ዓመታት ግፍ እና መድሎ ሳይበቃ አገር እና ህዝብ ለማጥፋት አስከ ሲኦል  የተዛተበት ህዝብ አገሩን ፣ ራሱን እና ወገኑን ማዳኑ ሊያስሸልመዉ እና ሊያስመሰግነዉ ሲገባ ብረት አዉርድ ለዓመታት እንደሆነዉ ራስህን ለዕርድ እጂህን ነብር ይባላል ፡፡

ይህ ለኢትዮጵያም ሆነ ለቀጠናዉ እንዴት የህግ እና የሠላም ማረጋገጫ ዋስትና ሊሆን ይችላል ፡፡ በኢትዮጵያ ህዘብ ሀብት እና ንብረት ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ቁም ስቅል የሚነሱ አካላት ለዘመናት ያደረሱት በደል እና ግፍ ዛሬም በሚፈራረቅባት ኢትዮጵያ የክፉ ቀን ደራሽ ኅዝብ በላብ እና ደም እንዲሁም ክቡር ህይወቱን ቤዛ አድርጎ የያዘዉን (ያለዉን) ለዚያዉም ለአገር እና ለወገን መኩሪያ እና መታፈሪያ የሆነዉን እና የሚሆነዉን ህዝብ እና የህዝብ ልጂ “በጥቁር ጠብ መንጃ” ጠብ ያለሽ በዳቦ ማለት ኢትዮጵያዊነት ወይስ ሌላዊነት የሚለዉን ስጋት የሚያስተጋባ ነዉ፡፡

ደን ዉስት ጉንዳን አለ ብሎ ደኑን በዕሳት ተያይዞ ጥፋት መሆኑን መለየት እንዴት ያቅተናል ፡፡ አስከ መቸ ይሆን ኢትዮጵያ እና ዜጎቿ በመከራ ጊዜ  ቀድሞ ደራሽን  የክፉ ቀን ባለዉለታ እንደ ክፉ አድራጊ ማየት ፡፡

ሲመሽ  እና ሲጨልም  ጥግ የሚይዝ በንጋት ወጋገን  የንጋት አርበኛ ከእኛ በላይ የሚሉ በአገር ክህደት እና በሰሩት ወንጀል ተጠያቂ ሳይሆኑ የወንጀለኛ ዳኛ በመሆን  ጠያቂ እና አዋቂ የሚሆኑት አስከ መቸ ነዉ ፡፡   ዕዉነትን በሀሰት ፣ ብርታት በድክመት ፤ ጀግንነት በአድር ባይነት …እየተጨቆኑ የአገር ባለዉለታዎችን በማሳደድ እና በማዋረድ ህዝብ ለዚያዉም ተበዳይ እና አቤት ባይ ሆኖ እያለ ጮኸት የመቀማት ልማድ  እንዴት ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅም እና ስም ለማምጣት የሚያስችል ስምምነት ሊያስገኝ ይችላል ፡፡

የህዝብ እና የአገር ጉዳይ ከምንም ነገር በላይ መሆኑ እየታወቀ ከዚህ ዉጭ ስለመብት እና ነፃነት ( የመኖር ተፈጥሯዊ ህግ) የምንም ነገር ስጋት ቢሆን ከህዝብ ፍላጎት እና ከአገር አንድነት በላይ ሊሆን አይችልም ፡፡

የአንድ አገር ህዝብ ሠባዊ እና ተፈጥሯዊ መብት ከየትኛዉም  ሠዉ ሰራሽ ህግ እና ደንብ ፣ ተቋም፣ ፍላጎት፣ስምምነት…… በላይ መሆኑን ለመቀበል ፍላጎት ፣ብቃት እና ቁርጠኝነት አስከሌለ ድረስ ዘላቂ ብሄራዊ እና ህዝባዊ ጥቅም ፤ስም እና አንድነት ማለትም ሆነ ማሰብ  የማይተገበር እና የማይኖር የድንቁርና ምኞት ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያዉያን ለዚያዉም የዓማራ ማህበረሰብ ስለ ብሄራዊ አንድነት ፣ አብሮነት ፣ እና ወንድማማችነት በዚህ በ21ኛዉ ክ/ዘመን ቀርቶ ጥንት ለዓለም የነበረዉን ምሳሌነት ታሪካዊ ጠላቶች ከዘመናት በፊት የሚያዉቁት የሚመሰክሩት አለማቀፋዊ ዕዉነታ ነዉ ፡፡

የረጂም ዘመናት ታሪክ ትተን በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ነጻ አዉጭ ኃይሎች መካከከል ከሠላሳ ዓመታት በላይ ጦርነት አስቀድሞ ከመካሄዱ በኮንፌደሬሽን ሆነ በፌደሬሽን ኤርትራ ከእናት አገሯኢትዮጵያ እንድትቀጥል በጊዜዉ ከነበረዉ ስርዓተ መንግስት በላይ የሁለቱ አገር ህዝቦች በተለይም የዓማራ ህዝብ እና የደጋማዉ ኤርትራ ህዝብ ጥረት የሚረሳ አይደለም ፡፡

ከዚህም በላይ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትለይ እና ሁለቱ ህዝቦች  ሆድ እና ጀርባ እንዲሆኑ ይሰሩ ከነበሩት ባዕዳን አገሮች ይነገር የነበረዉ የዓማራ ገዥ ኃይል መላቀቅ እንጂ ኤርትራ የኢትዮጵያ ህዝቧም ኢትዮጵያዊ አልበረም የሚል አልነበረም ፡፡

ይህ ያነሳሁት ዛሬ የዓማራ ህዝብ ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያን ማለቱ በጠላትነት እንዲታይ ማድረጉን ከ12ኛዉ ክ/ዘመን ጀምሮ ያለ እና ዛሬም እንደትናንቱ ለህለዉናዉ ፤ለሉዓላዊነት እና ለአገር አንድነት ያለዉ አቋም በጥቁር መሳሪያ ትጥቅ ስም የሚወቀስ እና የሚከሰስ ሳይሆን በላቀ ሁኔታ የሚነግስ መሆን ነበረበት ፡፡

መታጠቅ እና መጠንቀቅ አገርን እና ህዝብን ከማንኛዉም ኣይነት ጥቃት መታደግ እንጂ ስጋት ሊሆን አይችልም ፡፡ ርግጥ ነዉ ስጋት መኖሩ በኢትዮጵያ እና በተለይም በኢትዮጵያዊነት ላይ ጥላቻ እና ቂም  ፀንሰዉ በሚጨነቁት የዉጭ እና የዉስጥ ፣የሩቅ እና የቅርብ የኢትዮጵያ ጠላቶች ወይም ስጋቶች ከስጋትም ብርቱ ዉጋት እንዳይሰማቸዉ ማድረግ ከቶዉንም አይቻልም ፡፡

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ለዓመታት የደረሰባቸዉ ዘርፈ ብዙ ድርብርብ በደል እና መስተጓጎል መርሳት ቀርቶ መተዉ ሠዉ ሆኖ ለሚኖር ሠባዊ ኢትዮጵያዊ የሚቻል አለመሆኑን ጠላት በዘራዉ እንክርዳድ ስለሚያዉቅ እና የዘራዉን መሰብሰብ አይቀሬ የተፈጥሮ ህግ መሆኑን ሲረዳ የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ እና የኢትዮጵያን ትጥቅ እና መጠንቀቅ ዕንቅልፍ መንሳቱ ሀቅ ነዉ ፡፡

መቸም ግማሽ ሠላም እንደሌለ ሁሉ ግማሽ ዕንቅልፍ ስለማይኖር ጠላት ይረበሻል ፤ ጠላት ሠላም ያጣል ብሎ “ጠላት ለማስደሰት ኢትዮጵያን ማስከፋት ፤ትጥቅ ማስፈታት” አገር እና ህዝብ ከማፋት ዉጭ ርባና ቢስ የጨለማ ሩጫ እና መጨረሱም ድካም ነዉ ፡፡

ሁላችንም ባለችን አገር በየትኛዉም የኑሮ ደረጃ ፣ ዉጣዉረድ ዉስጥ ብንሆንም ሁሉም በአገር ነዉ እና ስለ አገራችን የሚገደን ከሆነ በታሪክ በየትኛዉም ዓለም ህዝብ ለራሱ ፣ ለአገሩ እና ለማንነቱ ስጋት ሆኖ ስለማይተወቅ በማንኛዉም መመዘኛ ፣ ከየትኛዉም አካል ….ስሙኝ፣ ተከተሉኝ ፣ዕመኑኝ …ከማለት የድንቁርና አስተሳሰብ ወጥቶ ህዝባዊ እና ታሪካዊ ቅቡልነት ያለዉን የዕዉነት መንገድ መፈለግ እና መከተል ለትዉልድ እና ለአገር የሚፈይድ ተግባር እና ስም ከማስተላፍ ባሻገር  አበዉ “በማር ጠብታ አገር ተመታ” እንዲሉ ” በጥቁር ጠብመንጃ ”  ” ጥቁር የታሪከር ሙጃ”  እየተከልን ቂም እና ደም ለአገር እና ትዉልድ እንዳናወርስ ሳንዘገይ  ልናዉቅ ፣ልንጠነቀቅ እና ከስህተት ድግምግሞሽ  ልንጠበቅ ይገባል፡፡

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

 

Allen z Amber

 

 

  

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop