የአብይ ድብቅ ስብሰባ | አሜሪካ ዱቄቱ ተሽጧል! | አሜሪካ ስለአማራና ኦሮሚያ ተናገረች | የደመቀ፣ይልቃል፣ ዐቢይና ጌታቸው ዝግ ስብሰባ | ጎንደር፣ ራያ አላማጣና ወልቃይት

https://youtu.be/_S-LBbf-OoM

 

https://zehabesha.com/the-u-s-government-is-suspending-food-aid-to-ethiopia-due-to-widespread-theft/

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  Ze Habesha LLC

2 Comments

  1. አሜሪካ እጇን ባስገባችባቸው ሃገሮች ሁሉ በዚህም በዚያም በእርዳታና በድጎማ መልክ የሚሰጡ ዘይት፤ ጥሬ እህልና የተፈጨ ድቄት እንዲሁም አልሚ ምግቦች እንደ ብስኩት የመሳሰሉት መሰረቅ የሚጀምሩት ገና የአሜሪካን ወደብ ሳይለቁ ነው። ራስን መጽዋች አስመስሎ ለማሳየት የሚደረገው እኔን እዪ የሚጀምረውም ያኔ ነው። በመሰረቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የእርዳታ እህል አይሰረቅም የሚሉ ከውሸት ፈሳሽ የተጋቱት ብቻ ናቸው። በዚህም በዚያም ለተራበው ህዝብ የሚላከው ይሰረቃል፤ ይለወጣል፤ ይሸጣል። ይህን ጉዳይ ለማጣራት ዳቦ ቤት፤ ገቢያና ሌሎችም መካዝኖችን ተዘዋውሮ መመልከት ይቻላል።
    አንዴ ወያኔ ነዳጅ ሰረቀብኝ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይህን ያህል ሺህ ህዝብ የሚመግብ የእርዳታ እህል በትግራይ ከመጋዘን ተሰረቀ ያኔም ይሉናል አሁንም ያላዝናሉ። የአሜሪካ መንግስት ከወያኔ ጋር ከመንገድ የወጣ ፍቅር ውስጥ የገባው ወያኔ በዘመኑ ሁሉ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈጻሚ ተጋላቢ ፈረስና ተላላኪ በመሆኑ እንጂ አሜሪካ ለትግራይ ህዝብ ቅንጣት ያህል አይገዳቸውም። ዛሬ በምስራቅ አፍሪቃ እግር ማሳረፊያ ያጡት እነዚህ ሃገር አፍራሾች ዛሬም በጥቁር ደም ለመነገድ አንዴ አዲስ አበባ ሌላ ጊዜ መቀሌ መመላለሳቸው የሰላሙን ስምምነት ለማስተግበር ሳይሆን የወያኔ እስትንፋስ ለመለካት ነው። ሲጀመር ወያኔ 3 ጊዜ ወረራ እንዲያደርግ የገፉት እርዳታ በቀጥታም ሆነ በሰውር የሰጡት አሜሪካኖች ናቸው። አሁን የአስመራው መንግስት ከቻይናና ከራሽያ ጋር ባደረገው ስምምነት የደነገጡት አሜሪካኖች ጊዜ እየሸሻቸው ይመስላል። በላቲን አሜሪካ፤ በአረብ ሃገራት፤ በአፍሪቃ አልፎ ተርፎም በእስያ የነበራቸው ተጽኖና ተሰሚነት እየመነመነ ሂዷል።
    የአሜሪካን የአሁን ክስ የተለየ የሚያደርገው ተዘረፈ የተባለው የእርዳታ አቅርቦት በወታደሩ ነው መባሉ ነው። ይህ ስም ያጠለሻል። ይህ የሃገርን የቀረች ትንሽዬ ብትሆንም ኩራት ያጨልማል። ይህ Human Rights Watch ካወጣው ሪፓርት ጋር ይያያዛል። የውሸት ክምር። ጉዳዪ ሆን ተብሎ የሚደረግ የአሜሪካ የሴራ ፓለቲካ አንድ ስሌት ነው። ለዓለም ኢትዮጵያ ወታደሮቿን እንኳን መመገብ አትችልም እኛ ከምንልከው እየሰረቁ ነው የሚመገቡት ለማለት ነው። ደጋግሜ እንዳልኩት የዶ/ር አብይ መንግስት በአሜሪካኖች ፊት ተንበርክኮ በጉልበቱ ቢሄድ እንኳን አሜሪካንን ደስ ማሰኘት አይችልም። አሜሪካኖች የሚሰሩት ሃገር ለማፍረስና ለወያኔ ሙሉ ጥብቅና ለመቆም ነውና። እንዴት ሰው ይዘነጋል ዋሽንግተን ላይ እኮ ጊዜአዊ መንግስት አቋቁመው ነበር። ታክሲ ነጂዎችንና ወስላታ የወያኔ ደም አፍሳሾችን ስብስበው። የኤርትራው መሪ እንዳሉት “የኢትዮጵያና የኤርትራ ሰላም መሆን አሜሪካኖችን አላስደሰተም” ልክ ናቸው። ስንተራመስ፤ ስንገዳደል፤ ስንሰደድ ያኔ ይኸው እኛ ደርሰን ከመከራ አዳናቸው በማለት ለነጩ ዓለምና ለቀሪው ፍጡር የምድር አምላክ መስለው ለመታየት ይቀላቸዋል።
    ዛሬ በአማራ ክልል ትጥቅ ማስፈታት፤ የልዪ ሃይሉ መፍረስ፤ ገዳማትና ደብሮች መመዝበር፤ የአምልኮ ቦታዎች መፈራረስ፤ የወያኔ ትጥቅ ፈታ እየተባለ በሌላ ቦታ ትንኮሳ መጀመር ሁሉ ሚስጢሩ ወያኔን ለማጎልበትና ከቀድሞ ስፍራቸው ለመመለስ የሚደረግ የጠለቀ ሴራ ነው። ግን የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞችና ጠ/ሚሩ ዛሬ ላይ ጠላቴ ነው ብለው የፈረጅት ወታደሩን በተኙበት ያረድትን የትግራይ ድርቡሾች ሳይሆን ከወታደሩ ጎን አብሮ በመፋለም ደምና አጥንቱን የከሰከሰውን የአማራ ህብረተሰብ ነው። ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ እንደሚሉት ጠ/ሚሩ በጊዜ ነቅተው ማን ምን መሆኑን ለይተው ነገሮችን ካላስተካከሉ አወዳደቃቸው እንደ ዚያድ ባሬ፤ እንደ ጋዳፊ እንደሚሆን ሊረድ ይገባል።
    በመጨረሻም ዋሽንግተን ፓስት እንዲህ ብሎ፤ ቡልምበርግ ይህን ጽፎ ያ የቴሌቪሽን ጣቢያ ይህን አቅርቦ መባሉ ሁሉ ውስልትና ነው። በዲሞክራሲ ስም አሜሪካ ህዝቧን አደንዝዛ፤ ውሸትን ያላመደቻቸው ለብዙዎቹ ለሥጋቸው የሚመቸውን ከዚህም ከዚያም እየሸመቱ በማቅረብ ነው። ሆድ የሞላ ሰው እምብዛም አያጉረመርምና! የሚዲያ አውታሮችም የሚያናፍሱት ሰበር ዜና ብለው የሚያቀርቡት ከእውነት የራቀ ሰውን በስሜት እንዲንገዳገድ የሚያደርግ ለመሆኑ ዛሬ ያሉትን ቆይተው ሲከልሱት ይታያሉ። ስለሆነም ነጻ ሚዲያ፤ ነጻ ህዝብ ወዘተ መባሉ ሁሉ እፈረት ማጣት ነው። ነጻነት ያለ ገደብ ወደ አናርኪነት ተለውጦ ይኸው እንሆ ዛሬ በምድሪቷ እልፍ ችግር አለ። በምድር ላይ ከአሜሪካ በስተቀር 32 ቲሪሊየን እዳ የተዘፈቀ ሃገር የለም። ግን ይነጋል ብለው ስለሚያስቡ ብዙ አይጨነቁበትም። የእኛስ ሃገር መቼ ነው መገዳደላችን፤ ለነጭና ለዓረብ ተላላኪ መሆናችን ቀርቶ ህዝባችንና ሃገራችን አስከብረን ያማረ ኑሮ የምንኖረው? ያ ቀን ለህዝባችን ይመጣ ይሆን? በቃኝ!

  2. ህወአት ልጃቸው በእርዳታ የመጣውን እህል ሲሸጠው አልነበረም እንዴ? ምነው ዛሬ ከስህተት በላይ ስህተት ሆነ ምነው እንሱን የዛን ጊዜ እንደዚህ አላብጠለጠሉዋቸውም? ጉዳዩ የእህሉ ሳይሆን ይህን ግራ የገባውን መንግስት ማዋከብ ነው። አብይ የተባለ ሰው እስከ መቼ ተዋርዶ ይዘልቀዋል? ምነው እንደ አፈወርቂ ኮስተር ብሎ መኖር አቃተው መልከስክ መልከስከስ መልከስከስ የት ሊደርስ ነው ግን? ትላንት ነብሱን ያዳነው ፋኖ ጠላትህ ነው ሲል ኤርትራ መንግስት ልንረሳው የማይገባ ውለታ ዉሉልናል ብሎ ዛሬ ደግሞ ኮሽ ሲል የሚደነግጥ መንግስት አይደለም አርፋችሁ ቁጭ በሉ ብሎ ከህወአት ጋር አብሮ ሊወጋ መዘጋጀት ይሄ ሰውዬ ምን ቢያደርጉት ይሻለዋል? ዳንኤል ክብረት ሲሳይ መንግስቴ እና ሌሎች ጥላችሁ ውጡ አገኘሁ ተሻገር፤ደመቀ መኮንን፤ይልቃል ከፍያለው፤ጥሩነህ ምናምን ግን የሰራችሁት ስራ አባይ ወንዝ ሊያጠራው ስለማይችል ቀጥሉበት የእጅችሁን እስክታገኙ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share