ክፉዎችን የሚያስፈራዉ ዕዉነት ነዉ! 

June 8, 2023
Abiy Ahmed
#image_title

አበዉ ኢትዮጵያዉያን “የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ “፡፡

ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡

ዛሬ በአገራችን ስለ ዕዉነት ብለዉ ለራሳቸዉ ፣ስለ ህዝቦች እና አገር ነፃነት ፣ ፍትህ እና ህልዉና የሚተጉ አስተዋይ እና ልባሞች በጠላትነት የሚያቸዉ መኖሩ በአገራችን የፖለቲካ ልማድ ነባር እና ተጠባቂ  ነዉ ፡፡

ይህም በሀሰት እና ክህደት መኖሪያቸዉ ላደረጉት ምንግዴዎች አግሪቷ የግል ንብረት በማድረግ ሌላዉን ስለ ዕዉነት እና ፍትኃዊነት የሚቆሙትን  በጠላትነት መፈረጁ የቆየ የፖለቲካ ታሪክ አካል ነዉ ፡፡

በኢትዮጵያችን የዕዉነት እና የነፃነት ጎህ አስኪቀድ ስለ አገር እና ህዝብ ያሉ ሁሉ ለአገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ ካላቸዉ ነዲድ  ፍቅር እና ክብር  ሲሉ ከፍተኛ እና ትዉልድ የማይረሳዉ ዋጋ ከፍለዋል ፤ አልፈዋል ፡፡

ሆኖም አንዳንዶች ያለፉትም ሆነ በህይወት ያሉት  ፍትህ ፣ መብት እና ነፃነት ከቀማቸዉ  በምህረት እና በችሮታ እንዲመለስላቸዉ የሚጠብቁ ስለ እነርሱ ሁላችንም እናስባለን ፡፡

ለምን ሲሉ የእነርሱ የዋህነት እና ገርነት ከጠላት ጥርስ የሚገፋቸዉ እንጂ የሚታደጋቸዉ አለመሆኑን ባለመረዳት ለህዝብ እና አገር የጀመሩትን ጉዞ በጂምር እንዲቋረጥ በማድረግ በሚከተላቸዉ እና በሚያማናቸዉ መሪዎች መዘናጋት ተስፋ የሚያስቆርጥ ዉሃ ስለሚቸልሳ ነዉ ፡፡

ከዚህ ጋር መታየት ያለበት ፍትህን እና ነፃነትን በተግባር ለባለቤቱ አስከሚሆኑ ጊዜ ድረስ በፅናት እና በአንድነት ከመታገል ዉጭ ከነጣቂ እና ከአሳባቂ መጠበቅ  ልክ ጉድጓድ ዙሪያ ሆኖ ገዳዩን እንደሚጠብቅ ቀበሮ ነዉ ፡፡

ብዙዎች ለአገር እና ለወገን አለኝታ የሆኑ ወንድ ልጆች (ጅግኖች) ይዘዉ የተነሱለትን ዓላማ ሃሳብ እና ተግባር ከዚህ በተቃራኒ ከቆሙት እና ባላጋራ ከሆኑት በዕርቅ እና በይሁንታ የሚዘልቁ መሆናቸዉን በመቀበል በአጭሩ የተበሉትን በተለይ ባለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት  ታሪክ እና ትዉልድ ይቁጠረዉ ፡፡

እናም ዕዉነተኛ የህዝብ እና የአገር ወዳድ ዜጎች ለነፃነት እና ለፍትህ በምታደርጉት ፍልሚያ አገር እና ህዝብ ወድቀዉ ከሚገኙበት  አረንቋ አዉጥቶ ለማሻገር የሚጥሩ የሚናገርትን እና የሚያደርጉትን በጎ ተግባር ከፍሬ ለማድረስ የታረቁትን ጠላት ማመን ይቅር ፡፡

እንደሚባለዉ “የታረቅከዉን ጠላት እና ዳግም የተቀቀለ ስጋ አትመን ” የሚለዉን ኢትዮጵያዉያን ጀግኖች የመኖር ጉዳይ የሁሉም የኢትዮጵያ አንድነት እና ህልዉና በተጨባጭ አስኪረጋገጥ የሑሉም ኢትዮጵያዉያን ፍላጎት እና ምኞት ነዉ ፡፡ ስለዚህ በህይወት እና በዓላመ ፅናት ለምትገኙ ነገረት ግን ስማችሁን ለመጥቀስ አንዱን ካንዱ ማቀዳድም ስለሚሆን ስራችሁ እና ታሪክ የሚያዉቀችሁ እና የሚመሰክራላችሁ መሆኑን ስታዉቁ በምንም በማንም ጊዜያዊ ነገር ላለመዘናጋት በፅናት መኖርን ማስቀጠል ነዉ፡፡

“ጠላት አይተኛም ፤ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ሞቶም ከመግደል አይቆምም !”

“ለነፃነት፣ፍትህ እና ህልዉና የሚደረገዉ ጥያቄ እና ትግል በተጨባጭ አስኪረጋገጥ ድረስ መቀጠል አለበት ፡፡ ”

“ሻሽ የጠመጠመዉ ሁሉ ቄስ አይደለም ፤  በቃ አንታለልም  ፡፡ ”

አንድነት ኃይል ነዉ !

 

Allen !

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

Go toTop