ከቶ ማን ነው ህገ ወጡ? – ገለታው ዘለቀ

የኦሮምያ ክልል መንግስት አዲስ አበባ ላይ ቤተ መንግሥት እሰራለሁ ብሎ ቢሊዮን ብሮች መድቧል። በአንድ በኩል የኦሮሞ ህዝብ ስንት ፈጥኖ ደራሸ እርዳታ በሚፈልግበት በዚህ ሰአት የክልሉ መሪ ቅንጡ ቤተመንግስት ለመገንባት መነሳቱ አንድ አሳዛኝ ታሪክ ነው።

በጣም የሚገርመው ነገር ግን ይህ የቤተመንግስት ግንባታ ህገ ወጥ መሆኑ ነው።  የኦሮምያ መንግስት አዲስ አበባ ላይ ቤተ መንግሰት ለመስራትም ሆነ መቀመጫውን ለማድረግ የሚያስችለው አንድም ድንጋጌ የለም። በፌደራሉ ህገ መንግስትም ይሁን በኦሮምያ ህገመንግስት ውስጥ አዲስ አበባ የኦሮምያ ክልል መቀመጫ ናት የሚል ድንጋጌ የለም። የተሻሻለው የኦሮምያ ህገ መንግስትም አዲስ አበባ ዋና ከተማዬ ናት አይልም። ለነገሩ የኦሮምያ ክልል ህገ መንግስት ይህንን ለማለት ቢነሳም ከዋናው ህገ መንግስት የሚቀዳ ስለማይሆን ውድቅ ይሆናል። የሆነ ሆኖ ግን አንድም ሰነድ አዲስ አበባ የኦሮምያ ዋና ከተማ ናት የሚል የለም።
 በዚህ ሰአት ፌደራል መንግስት አዲስ አበባን መቀመጫው ሲያደርግ ድንጋጌዎች አሉት። በፌደራል መንግሥት እና በአዲስ አበባ አስተዳደር መካከል ህጋዊ መተሳሰር አለ። ትስስሩ መሻሻል እንዳለበት የሚታወቅ ቢሆንም።
#image_title
 ነገር ግን በኦሮምያና በአዲስ አበባ አስተዳደር መካከል ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ አንድም ትሰሰር የለም። በዚህ መሰረት የኦሮምያ መንግስት አዲስ አበባ ላይ የተቀመጠው ህገ ወጥ ሆኖ ነው። ግንባታዎቹ ህገ ወጦች ናቸው። ይልቅ እነዚህ ህገ ወጥ ቤት ሰርታችኋል የሚባሉት እና ቤታቸው የሚፈርስባቸው ወገኖች ይልቅ እነሱ ከገበሬው መሬት ያዛወሩበት ሰነድ አላቸው። ደግሞም መንግስት የቤት ፍላጎቶችን ማሟላት ስላልቻለ ጎጆ ቀልሰው የሚኖሩ ዜጎች ናቸውና ልንታገሳቸው የሚገባቸው ነበሩ።
አዲስ አበባ ላይ የኦሮምያ መንግስት ያለ ምንም ድንጋጌ ዋና ከተማዩ እያለ ሲኖር፣ ግንባታ ሲያካሂድ፣ ወይዘሮ አዳነች አበቤ ሽፋን ይሰጣሉ። ለነገሩ እኚህ ሴት ከንቲባ የሆኑትም ለዚህም ነው። ወይዘሮ አዳነች በአንድ ወቅት ህገ መንግስታችን አዲስ አበባ የኦሮምያ መቀመጫ ናት ይላል ብለው የሃሰት መረጃ ሰጥተው አልተጠየቁም። አዲስ አበባ የኦሮምያ ዋና ከተማ ናት የሚል በሀገራችን ሰማይ ስር አንድም ህግ የለም ጎበዝ።
ከሁሉም ከሁሉም የልየሚያሳዝነው ግን ፓርላማውም ይሁን የአዲስ አበባ ምክር ቤት የኦሮምያን ክልል መንግሰት ለመሆኑ በየትኛው ድንጋጌ ነው አዲስ አበባ መቀመጫዬ ናት የምትለው? ድንጋጌ አምጣ፣ ስነድ አምጣ፣ ብሎ አለመጠየቁ ነው። የጉድ ሀገር……ከማለት ሌላ ምን ይሏል?
አዲስ አበባ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ቤት መሆኗ ተከብሮ ደግሞ የኦሮምያ ክልል መቀመጫ አዲስ አበባ ይሁን ከተባለ ስምምነትና ድንጋጌ ያስፈልጋል እኮ። የአዲስ አበባ አስተዳደር እና የኦሮምያ ክልል የሚተሳሰሩበት ግልጽ ዶክመንት ያስፈልጋል እኮ። አገርን የሚያስተዳድር ሰው እንዴት ህገ ወጥ ስራ በዚህ ደረጃ ይሰራል?
ወገኖቼ ሆይ በዚህ ሰአት የኦሮምያ መንግስት እንቅስቃሴ አዲስ የአበባ ላይ ህገ ወጥ ነው። ሁላችንም ተባብረን ህግ ይከበር እንበል። አሰራርና ህግ ይኑር። እባካችሁ ህግ ይከበር!
ተጨማሪ ያንብቡ:  ፋሽስቶች ሁልጊዜም በእነሱ አሸናፊነት እንጂ በድርድር አምነው አያውቁም፤ አያምኑምም

1 Comment

  1. ባነሱት ህጋዊነት ጉዳይ እኔም እስማማለሁ። እሺ ህግም ተጥሶ ይሰራ ብዬ ልቀጥል። በመንግስት ሚዲያዎች ሳይቀር “ቤተ መንግስት” ተብሎ መጠራቱ ግር ያሰኛል። የፕሬዚደንት/የመስተዳድር ጽህፈት ቤት ለማለት ይሆን? ብዬም ጠየኩ። ወይስ ቤተ መንግስት in its classical sense ነው?
    ቤተ፟መንግስት የሚለው ቃል እኔ እንደሚገባኝ በነገስታቱ ዘመን በእንግሊዝኛ “Palace” የሚለው ትርጉም መሰለኝ፣ ለምሳሌ Buckingham palace። ታዲያ የእንግሊዙ ጠ/ሚ Rishi Sunak [smart guy!] የት ነው የሚኖረው/የሚሰራው? 10 Downing Street! እንደው እግረ መንገድ ከሂንዲ ዝርያ ወላጆች የተወለደን ሰው “my Prime Minister” ብለው መቀበላቸው ብቻ ሳይሆን ሥርዓታቸው ሥልጣንን ለማንም ክፍት ማድረጉ እንግሊዞችን እንድታደንቋቸው አላደረጋችሁም? እኔን አድርጎኛል!
    ስንቀጥል ከደርግ ጊዜ ጀምሮ “ንጉስ” የሚባል ስለቀረ በአሁኑ ወቅት ያለው የፕረዚደንት [Head of State] and የጠቅላይ ሚኒስቴር [Head of Government] ጽህፈት ቤት ነው። ከንጉሱ ዘመን በዘልማድ በቀጠለው ነው “ቤተመንግስት” የምንለው። የቀድሞ እንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች [common wealth countries] የመሪዎች የመኖሪያ/የስራ ቦታዎች “State House” ተብለው ይጠራሉ። በአሜሪካ “Whitehouse” ነው፣ የኛ ጋዜጠኞች ዜና ያሳመሩ መስሏቸው ሲተረጉሙት “ነጩ ቤት” እንደማለት “ነጩ ቤተመንግስት” ይላሉ። በቃ የሃገር መሪ ያለበት ሁሉ በአማርኛ “ቤተ መንግስት” ነው። አሁን የክልል መሪንም ሊጨምር ነው ማለት ነው? የፍሎሪዳው ገዥ Ron DeSantis ጽ/ቤት ነው ቤተመንግስት ነው ያለው? የማንቸስተር ገዢ ወይም አስተዳዳሪስ? በርግጠኘት ቤተ መንግስት [ፓላስ] የለውም!

    ሰላማችን ይብዛ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share