May 16, 2023
34 mins read

አማራ ኦሮማይ!!! ኦሮማይ ህገ-አራዊት!!! ፌዴራል መከላከያ የኦነግ ሠራዊት በአስቸኳይ ከአማራ ክልል ይውጣ!!!

አማራ ባህር ዳር፣ የኦነግ ህገ-መንግሥት እሳት ዳር!!!

 ክፍል  አራት      

ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

መግቢያ  

5666665y 2 1

የጦርነት ኢኮኖሚና የነፍስ ገበያ በኢትዮጵያ!!!

በኢትዮጵያ የተፈራረቁ መንግሥታት ባለፈው ግማሽ ክፍለ ዘመን ሽምቅ ተዋጊዎች ከሻብያ፣ ጀብሃ፣ ወያኔ/ህወኃት፣ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ወዘተ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር መሣሪያ ገፈው በመታጠቅና በወታደራዊ ሥልጠና     ክህሎት ራሳቸውን  ሲያጠናክሩ ኖረዋል፡፡ ዛሬ የምናየው የእርስበእርስ የወንድማማቾች ጦርነት  (civil war) የመንግሥትን በጀት ሃምሳ በመቶ ለጦርነት ወጪ እንደዳረገው ይገመታል፣ አመዛኙ ገንዘብ ከባህር ማዶ የጦር መሣሪያ በዶላር መሸመቻና ሌላ ዘመናዊ የጦርነት ቴክኖሎጂ (modern war technologies) መግዣ አገልግሎል፡፡  በኮነሬል አብይ የብልጽግና መንግሥት የተዛባ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሃያ ሚሊዮን  ኢትዮጵያዊያን በርሃብ ቸነፈርና ድርቅ ተመተዋል፡፡  በእርስበእርስ ጦርነት  ከቀያቸው የተፈናቀሉ ከሦስት እስከ አምስት ሚሊዮን ህዝብ የእለት ጉርሱን ከረድኤት ድርጅቶች እንደሚሠፈርለት ይታወቃል፡፡ በሰሜኑ የትግራይ ጦርነት አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሽህ ወጣቶች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ሁለት መቶ ሽህ ወጣቶች አካላቸው ጎድሎል፣ በጦርነቱ የሃገሪቱ አምራች ኃይል የሆኑትን ወጣቶች አሳጥቶናል፡፡ በዚህ የጦርነት ማሽን (war machine) ምርቱ ሞትና የአካል መጉደል  ብቻ ነው፡፡ እነዚህ ወጣቶች አገር ለመገንባትና በግብርና የተትረፈረፈ ምርቶች አምርተው ርሃብና ድርቅን ለማስወገድ የተሸለ የኢኮኖሚ ሁኔታን መፍጠር ይችሉ ነበር፡፡ በአጠቃላይ በሰሜኑ ጦርነት ሃያ ስምንት ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ መሠረተ-ልማቶች ውድመት አስከትሎ አልፎል ትምህርት ቤት፣ የጤና ተቆማት፣ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች፣ የመብራትና ውኃ ወዘተ መሠረተ-ልማቶች ወድመዋል፡፡  ለጦርነቱ የወጣው ወጪና በጀት ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለንጹህ ውኃ አቅርቦት፣ ለኤሌትሪክ ኃይል ማስፋፋት፣ ለቴሌኮሙኒኬሽን ስልክ አገልግሎት፣ ለመስኖ ልማት፣ ለመንገድ ግንባታ ሥራ፣መዋል ይቻል ነበር፡፡ የጦርነቱን ማሽን የሚዘውሩት ተጠቃሚ የበለጸጉ አገሮች የጦር መሣሪያዎች በማቅረብ ትርፍ አግበስብሰዋል፡፡ ኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት በ2022 እኤአ የአንድ ቢሊዮን ደላር ወይም የሃምሳ አራት ቢሊዮን ብር ልዩ ልዩ የጦር መሣሪያዎችና  ጥቁር ክላሸንኮቨ ኤኬ-47 ሸምቷል፡፡………….(2)

የበለጸጉ አገሮች ልማታዊ ቴክኖሎጅዎች ከማቅረብ ይልቅ  የጦር መሳሪያዎች በማቅረብ ለሚሊዮን ወጣቶች ሞትና አከል መጉደል አስተዋፅዖ አድርገዋል፡፡  የሠለጠነው ዓለም በጦርነት የህዝብ ቅነሳ አንዱ ዘረኛ ፖሊሲቸው  ነው፡፡ አሁንም የትግራዩ ጦርነት ባለቀ ማግስት የአማራውን ጦርነት በመቆስቆስ ሚሊዮን ወጣቶችን በጦርነት ማሽን ውስጥ ለመፍጨት የአሜሪካና የአውሮፓ መንግሥቶች አሰፍስፈዋል፡፡ የኢራቅ፣ የሶሪያ፣ የአፍጋኒስታ፣ የሶማሊያ፣ የሊቢያ፣ የየመን፣ ወዘተ የእርስበእርስ ጦርነት  (civil war) ሚሊዮኖች እልቂት፣ የሠለጠነው ዓለም አቀፍ ህብረተሰብ ቁብም አይሰጠው ስብአዊነት፣ ማራሊቲ፣ ወዘተ ፋሽናቸው አልፎል፡፡ ዴሞክራሲ፣ እኩልነት፣ ወንድማማችነት ወዘተ ፋሽናቸው አልፎል፡፡  ዛሬም በኢትዮጵያ ምድር ከአስር እስከ ሠላሣ ሚሊዮን ወጣቶች ልዩ ልዩ የጦር መሣሪያዎች  ጥቁር ክላሸንኮቨ ኤኬ-47፣ ኤም ፎርቲን፣ ኡዚ፣ ቶምሶን፣ ቢኤም፣ ሞርታል፣ ዲሽቃ፣ ዙ23 ወዘተ ታጥቀው በዱር በገደሉ ዱር ቤቴ ያሉ ወጣቶች ከትምህርት ገበታቸው ተነጥለው የሸፈቱበት ዋና ምክንያት የማንነት ጥያቄና በህይወት የመኖር የህልውና ጥያቄን በማንገብ ነው፡፡ የኮነሬል አብይ የኦነግ/ኦህዴድ ብልጽግና የኦሮሙማ አንባገነናዊ አገዛዝ ጦርነት ጠማቂነት፣ ዴሞክራሲ አፋኝነት፣ ዘረኛነትና ተረኛነት የአስራአምስተኛው ክፍለ ዘመን ገዳ ሥርዓት፣ በሌሎች ብሄሮች ላይ ለመጫንና ለዝንተ ዓለም የመግዛት ቅዥት ሆኖባቸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ  በዓለም አቀፍ ደረጃ   በፕሬስ ነጻነት፣ በፖለቲካ ነጻነት፣ በኢኮኖሚ ነጻነት፣ በሕግ አውጪ ነፃነት፣ በማህበራዊ ጉዳይ ነጻነት፣ በፀጥታና ደህንነት ነፃነት መለኪያዎች ሃገራችን የመጨረሻ ደረጃ በመውረድ ወደ አዘቅት  ጉድጎድ ውስጥ በመግባት ላይ ትገኛለች፡፡ Ethiopia | RSF ሪፖርተር ዊዝአውት ቦርደር ድረ-ገጽ መረጃውን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

  • ኢትዮጵያ በ2022 እኤአ በፕሬስ ነፃነት መለኪያ (Press Freedom index) ከ180 (ከመቶ ሰማንያ) አገሮች 114 (መቶ አስራአራተኛ) የነበረች ሲሆን በ2023 እኤአ ወደ 130 (መቶ ሠላሣኛ) ደረጃ አቆልቁላለች፡፡  The 2022 Press Freedom index ranked Ethiopia 114thout of 180 countries. In 2023 the country was demoted to the rank of 130th out of 180 countries, according to the Index.
  • ኢትዮጵያ በ2022 እኤአ በፖለቲካ ነፃነት መለኪያ (POLITICAL INDICATOR) ከ180 (ከመቶሰማንያ) አገሮች 112 (መቶ አስራሁለተኛ) የነበረች ሲሆን በ2023 እኤአ ወደ 111 (መቶ አስራአንደኛ) ደረጃ ወርዳለች፡፡
  • ኢትዮጵያ በ2022 እኤአ በኢኮኖሚ  ነፃነት መለኪያ (ECONOMIC INDICATOR) ከ180 (መቶሰማንያ) አገሮች 176 (መቶ ሰባ ስድስተኛ)  የነበረች ሲሆን በ2023 እኤአ ወደ 113 (መቶ አስራሦስተኛ)  ደረጃ ወርዳለች፡፡
  • ኢትዮጵያ በ2022 እኤአ በሕግ አውጭ ነፃነት መለኪያ (LEGISLATIVE INDICATOR) ከ180 (መቶሰማንያ) አገሮች 99 (ዘጠናዘጠነኛ) የነበረች ሲሆን በ2023 እኤአ ወደ 89 (ሰማንያ ዘጠነኛ) ደረጃ ከፍ ብላለቸ፡፡
  • ኢትዮጵያ በ2022 እኤአ በማህበራዊ  ጉዳይ ነፃነት መለኪያ (SOCIAL INDICATOR) ከ180 (ከመቶሰማንያ) አገሮች 126 (መቶ ሃያ ስድስተኛ)   የነበረች ሲሆን በ2023 እኤአ ወደ 146 (መቶ አርባ ስድስተኛ)  ደረጃ ዝቅ  ብላለቸ፡፡
  • ኢትዮጵያ በ2022 እኤአ በጸጥታና ደህንነት ነፃነት መለኪያ (SECURITY INDICATOR) ከ180 (ከመቶሰማንያ) አገሮች 144 (መቶ አርባ አራተኛ)  የነበረች ሲሆን በ2023 እኤአ ወደ 146 (መቶ አርባ ስድስተኛ)  ደረጃ ዝቅ  ብላለቸ፡፡ ………() ()Ethiopia | RSF

 

የጦርነት ኢኮኖሚና የነፍስ ገበያ በኢትዮጵያ የእርስበእርስ የወንድማማቾች ጦርነት ተሳታፊዎች

በአሜሪካና በአውሮፓ ሃገራት ድጋፍ፣ የህወሓትና ኦነግ የጦር አበጋዞች ሠራዊት ከሰባት አማፂያን ጋር በማበር ‹የሽግግር መንግሥት› ለመመስረት እየተዋጉ ወደ  አዲስ አበባ  የገሠገሱበት ወቅት የተገለፀ ወታደራዊ መረጃን ከሠንጠረዡ ላይ እንደተገለጸው  ነበር፡፡ በህወሓት የጦር አበጋዞች  የሚመራው የተቃዋሚው ህብረት ኃይል አሰላለፍ ተዋጊ ኃይል ብዛት ከላይ በሠንጠረዡ በተገለፁት  መሠረት፤ የትግራይ መከላከያ ኃይል ሦስት መቶ ሽህ (300,000) ተዋጊ ኃይል ፣ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሠራዊት ሃያ ሽህ (20,000)፣ የአገው   ነጻ አውጪ ሠራዊት አምስት ሽህ (5,000)፣ አፋር ሦስት ሽህ (3,000)፣ ጉሙዝ ነጻ አውጪ ሠራዊት አስር ሽህ (10,000)፣ ጋምቤላ ነጻ አውጪ ሠራዊት አምስት ሽህ (5,000)፣ ቅማንት ነጻ አውጪ ሠራዊት አምስት ሽህ (5,000)፣ ሲዳማ ብሔራዊ የነፃነት ግንባር አምስት ሽህ (5,000) እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራና የሌሎች ኃይሎች  አሰላለፍ ተዋጊ ኃይል ብዛት በተመለከተ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት ሃምሳ ሽህ (50,000) እስከ ሰባ ሽህ ይገመታል፣ የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት ሦስት መቶ ሽህ  (300,000)፣ የአማራ ልዩ ኃይል  ሃምሳ ሽህ (50,000)፣ የአማራ መከላከያ ኃይል ፋኖና አማራ ሚሊሽያ ሁለት መቶ ሽህ (200,000)፣ ኦሮሞ ልዩ ኃይል (30,000)፣ የአፋር ልዩ ኃይል (10,000)፣ ሱማሌ ልዩ ኃይል (5,000)፣ ሪፓብሊክ ጋርድ ሦስት ሽህ (3,000)፣ የአየር ኃይል ኮማንዶ ሦስት ሽህ (3,000)  ተዋጊ ኃይል  እንዳላቸው ምንጩ ያልታወቀው መረጃ ከላይ ከሠንጠረዡ ላይ ያመለክታል፡፡ የዶክተር አብይ የኦዴፓ ብልፅግና ዘረኛና ተረኛ መንግሥት፣  የኦሮሞ ልዩ ኃይል ሠላሳ ሽህ (30,000) ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ልዩ የፖሊስ ኃይል ለአርባ ሁለተኛ ጊዜት ሲሰለጥን በአንድ ዙር ሥልጠና  አስር ሽህ መልምሎች ሲኖሩ በትንሹ  (400,000) አራት መቶ ሽህ ሠራዊት ይገመታል፡፡ በዚህ በሰሜኑ የወንድማማቾች የእርስ በእርስ ጦርነት በመሳተፍ   የሚሊዮን ወጣቶች ህይወት ተገብሮል፣ በመቶ ሽህዎች አካላቸው ጎድሎል፡፡ ለወጣቶቹ ሀገራቸው   ያበረከተችላቸው  ገጸ በረከት ይሄን ነበር፡፡

አሁን ደግሞ የኮነሬል አብይ መንግሥት የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት የጦርነት ዘመቻ ከፍቶል፡፡ አዲስ የጦርነት ማሽን በአማራ ምድር ተክለዋል፣ በዚህ ውጊያ የኦሮሞና አማራ ወጣቶችን ህይወት ይቀጠፋል ፡፡ በብልፅግና አስተዳደር ክልላዊ መንግሥትነት የጠየቁ የጉራጌ፣ የወላይታ ወዘተ ህዝብ ለሞትና እስራት ተዳርገዋል፡፡ የኮነሬል አብይ መንግሥት በነቢብም በግብርም በህገመንግሥት ስም ህገመንግስቱን የማይከተል የጋንግስተሮች ፖለቲካ የሚያራምድ መንግሥት ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉን አሳታፊ ሰላማዊ ትግል (peacefull and all inclusive) የትግል ስልት ወይም ህዝባዊ አመጽና እንቢተኛነት የትግል ሥልት የሚመርጥልን  አንባገነኑ ኦነግ/ ኦህዴድ የብልፅግና መንግሥት መሆኑ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ህዝባዊው ትግል ሁሉን አሳታፊ ሰላማዊ ትግልና ህዝባዊ እንቢተኛነትና ህዝባዊ አመፅን ያካተተ አማራው  የኦሮሞ ደም ደማችነው!!! እንዳለው አማራውም ሲጠቃ ጉራጌው የአማራ ደም ደማችን ነው!!! እንዳለው ዓይነት አስራአንዱ የክልል መንግሥት ህዝብ በቀጣዩ ትግል እንደተሳትፎቸው ልክ እንደሚያገኙ ከአሁኑ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡

 

መደምደሚያ

(I) አንባገነኑ ኦነግ/ ኦህዴድ የብልፅግና መንግሥት የኦሮሙማ የመሥፋፋት አባዜና ግጭት በሁሉም ክልሎች ላይ እየተፈጸመ በመሆኑ በኦሮሙማ ላይ ‹‹የፀረ-መሥፋፋት የክልሎች ግንባር›› (United Front against Oromuma Expanssion) መመሥረት

(II) አንባገነኑ ኦነግ/ ኦህዴድ የብልፅግና መንግሥት ‹‹የሃገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔር ብሔረሰቦች እና የህዝቦችን ሚዛናዊ ተዋዕዖ ያካተተ ይሆናል)  የሚለው አንቀፅ ሰውየው ኮነሬል አብይ የጦርኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣ ገብርዬው ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጆላ ገላልቻ ኤታማዦር ሹም በኦነግና ኦነግ ሸኔ ሠራዊት ከላይ እስከታች በኦሮሙማ የተሸሙ  ‹‹ከላይ ሰውዬው፣ ከታች ገብርዬው፣መኃል ያለው ንሳ ዝምብዬው!!!›› በኦሮሙማ ዘር ላይ ያማከለ መከላከያ ሠራዊት በመሆኑ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ ይልሆነ በበኦነግ ኦሮሙማና በኦነግ ሸኔ ፖለቲካ የተጠመቀ አራጅ ቡድን አሸባሪነት የተፈረጀ በመሆኑ፤  በኢትዮጵያ የሚገኙ የክልሎች ልዩ ኃይል ትጥቅ ያለመፍታት ግንባር መፍጠርና መተባበር ግድ ይላቸዋል የአዲሲቷን ኢትዮጵያ ዜጎች መከላከያ ሠራዊት በጋራ  በእኩልነት መመሥረት፡፡ በዘር ላይ የተመሠረተ የክልሎች ሠራዊት በጋራ በስምምነት በማፍረስ ኢትዮጵያ ዜጎች መከላከያ ሠራዊት በወታደራዊ ሳይንስና ክህሎት በሜሪት መገንባት፡፡

 

(III) ትግላችን ‹‹ማንኛውም ሰው ስብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር የአካል ደህንነትና የነጻነት መብት አለው›› በሚለው የህገመንግሥቱ አንቀጽ በህይወት የመኖር መብታችንን መጀመሪያ ለማስከበር እንታገላለን፡፡ የኮነሬል አብይ መንግሥት የዜጎችን በህይወት የመኖር መብት ያላከበረ፣ ሰው የሚታረድበት፣ ሴቶች የሚደፈሩበት፣ ሰዎች በገፍ የሚፈናቀሉበት፣ ከክልላችን ውጡ የነገሰበት በኦነግ/ኦህዴድ ስውር የፖለቲካ ሴራ የሚመራ በመሆኑ ዜጎች ትጥቃቸውን ሳይፈቱ በህይወት የመኖር መብታቸውን ማስከበር ያስፈልጋል፡፡

 

(IV) ከ2010 እስከ 2015 ዓ/ም የኮነሬል አብይ የብልጽግና መንግሥት የግፍ አገዛዝ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ሞተዋል፣መቶ ሽዎች የአካል ጉዳተኘች ሆነዋል፣ ሚሊዮኖች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፣ ብዙ ሽዎች  ሴቶችና እናቶች ተደፍረዋል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፈው አምስት አመታት ተጠያቂነት  እንዲመጣ፤ ገለልተኛ የስብዓዊ መብቶች አጣሪ ኮሚሽን ገብተው የተፈፀመውን የዘር ፍጅት፣ የጦር ወንጀልና የስብዓዊ መብቶች ጥስቶችን አጣርተው ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ የሚታገል የኢትዮጵያዊ ኃይል በየክልሎቹ ማደራጀት፣ ወቅታዊ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ናቸው እንላለን፡፡

 

(V) የኮነሬል አብይ የብልፅግና መንግሥት ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ምሁራኖች፣ ፖለቲከኞችን፣አስተማሪዎችን፣ ተማሪዎችን፣ ፋኖዎችን፣ ማናነት ተኮር እስራት በትግራይነት፣ በአማራነት፣ በጉራጌነት፣ በወላይታነት፣ በኤርትራዊነት    ወዘተ ዘር ተኮር እስራት በማድረግ ሃገሪቱን የህዝቦች እስርቤት አድርገዋታል፡፡ የህሊና እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡

 

(VI) የኢትዮጵያ የኮነሬል አብይ ብልጽግና ፊዴራል መንግሥት መከላከያ ሠራዊት በአስቸኳይ ከአማራ ብሔራዊ ክልል እንዲወጣና ጦርነት እንዲቆም እንጠይቃለን፡፡ ምላስ አደሩ ኮነሬል አብይ ‹‹ጦርነት ይብቃ፣ሰላም እናጽና!!!››  መፈክር  በተግባር  ይተርጎም፡፡

 

(VII)  የኢትዮጵያ የኮነሬል አብይ ብልጽግና መንግሥት በሽብርተኛነት ከተከሰሰው ህወሓት/ወያኔ ጋር በደቡብ አፍሪካ የሠላም ስምምነት አድርጎል፡፡እንዲሁም በሽብርተኛነት ከተከሰሰው ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር በታንዛኒያ የሠላም ስምምነት አድርጎል፡፡ የኮነሬል አብይ መንግሥት በሽብርተኛነት ካልተከሰሰው ከፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል ጋር የሠላም ስምምነት እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል የሽምቅ ውጊያ፣ የደፈጣ ውጊያ፣ የጎሬላ ታክቲክና ስትራቴጂ  ብቻ በመጠቀም የፊዴራል መከላከያ ሠራዊቱን አፈሙዙን በብልጽግና መንግሥት ላይ እንዲያዞር ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ የአንድ ፋኖ ህይወትን መጠበቅና መስዋት እንዳይሆን መከላከል ዋና ዓላማ በማድረግ አንዱን ለአሥር፣ አስሩን ለአንደ  የመዋጋት የጦርነት ስልት ማከናወን፡፡ ወያኔ በሰው ማዕበል (Human wave tactics)፣ ያረጀ ያፈጀ የውትድርና ታክቲክና ስትራቴጂ በመጠቀም የትግራይ ወጣቶችን በጦርነት በመማገድ አስፈጅቶል፡፡  ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል ይህን የውጊያ ሥልት በፍፅም መጠቀም አይኖርበትም በረዥም ጊዜ ህዝባዊ ጦርነት (Protracted people’s war strategy) በማድረግ ማሸነፍ እንደሚቻል መተማመን ያስፈልጋል እንላለን፡፡ ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል የሽምቅ ውጊያ፣ የደፈጣ ውጊያ፣ የጎሬላ ታክቲክና ስትራቴጂ  ብቻ እያጠቁ በመሸሽ የመፋለም ስልት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በወታደራዊ ሳይንስ የመጠቁ ዜጎች አስፈላጊውን የውጊያ ስልት ታክቲክና ስትራቴጂ እንዲነድፉ ማድረግ ያሻል እንላለን፡፡

 

(VIII) የወልቃይትና የራያ ጥያቄ በትግራይና አማራ ሽማግሌዎችና ህዝብ በሠላማዊ መንገድ እንዲፈታ የውይይት መድረክ ማዘጋጀት፡፡ በኢትዮጵያ የመሬት ጥያቄ፣ በዘር ላይ የተዋቀረና በክልል በዘር የተሸነሸነ ኃላ ቀር  ሥርዓት ማስወገድ  ግድ ይላል፡፡ ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች ልምድ በመውስድ የመሬት ኃብት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሃብት እንዲሆን፣ የክልሎች የመሬት ድንበር ማፍረስና፣ በዘር ታርጋና ካፔላ የሚሠየም መሬት  እንደሚጠፋ በህገመንግሥት መደንገግ፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ መስራትና ኃብት ማፍራት መብቱና ነጻነቱ እንዲረጋገጥ ማድረግ፡፡ የአዲስ አበባ፣ የድሬዳዋ፣ መቀሌ፣ አዳማ፣ ጂማ፣ የባህር ዳር፣ የጎንደር፣ ሃዋሳ፣ ጋምቤላ፣  ከተሞች የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ኃብትና ንብረት መሆናቸውን በህግ በማረጋገጥ የተለኮሰውን የዘር ጥላቻና የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማጽዳት፣ ወንጀል ማስቀረት ይቻላል፡፡

 

(IX) ኮነሬል አብይ አህመድ ቤተ-መንግስት አንድ ትሪሊየን ብር የግንባታ ወጪና  በአዲስ አበባ ዙሪያ አዲስ የሸገር ከተማ ለመመሥረት የሚወጣ  ሌላ ትሪሊዮን ብር በአስቸኳይ እንዲቆም በማስደረግ ለሚሊዮን ተፈናቃዬች ህይወትን መታደግ፣ በትግራይ በአማራና አፋር ክልሎች የወደሙ መሠረተ-ልማቶች በተለይ የጤና፣የትምህርት፣ የመብራት፣የውኃ፣ የስልክ አገልግሎቶች ቅድሚያ እንዲሠጣቸው ማድረግና በህዝቡ ላይ የደረሰውን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ መንግሥታዊ ድጎማዎች ማድረግ፣ ግብርና ታክስ መቀነስ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ማፍረስ ማስቆም አንገብጋቢ የህዝብ ጥያቄዎች ናቸው፡፡  የአዲስ አበባ መስተዳደር በአንድ በኩል ቤቶችን በማፍረስ በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ የከተማ ተፈናቃዬችን ሲኖሩባት፣ መሬቱን የተቀማው ደሃ ህዝብ መሬት የተመቻቸለት የሰው ጅብ ሪል እስቴት ዲቨሎፐር ተብዬዎች የደኃው ሰው መሬት እየተሸጠላቸው የአዲሰአበባ ከተማ መሬት በማግበስበስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ፣ አዳነች አቤቤና ሽመልስ አብዲሳ ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት ለመዐት ብለን ለማስቆም መታገል ግድ ይለናል እንላለን፡፡

 

የኢትዮጵያ አጠቃላይ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳዬች ሁኔታ

የኮነሬል አብይ የብልፅግና መንግሥት የሚቆጣጠረው ግዛት አንፃር ሲሦ መንግሥት ብቻ ነው፣የሃገሪቱ 70 (ሰባ) በመቶ ግዛትን አይቆጣጠርም፡፡ የትግራይ ክልልን ህወሓት/ወያኔ ከሠላም ስምምነቱ በኃላ ሙሉ በሙሉ በትግራይ መከላከያ ሃይል ይቆጣጠራል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል ወጥቷል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ግዛት በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) ተቀራምተውታል፡፡ የሽመልስ አብዲሳ የሚመራ ኦነግ ሸኔ በወለጋ የአማራ ጭፍጨፋ እጃቸው እንዳለበትና እንዲጣራ ኦነሠ በድርድሩ ላይ አንስቷል፡፡ የአማራ ክልልን በህዝባዊ አማፅ እየታመሰ ይገኛል፡፡  በጎንደር፣ በሸዋ፣ በወሎና ጎጃም ህዝባዊ እንቢተኞነት በአማራ ህዝባዊ ኃይል አማፅያን ስር ለማድረግ ፍልሚያው ቀጥሎል፡፡ የአማራ ህዝባዊ ኃይል በአንድ አመራር እዝ እንዲመራ ማድረግ አስፈላጊና አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡

 

የእንግሊዙ ኤም አይ ስድስት የስለላ ድርጅት የኢትዮጵያን ሁኔታ በመረጃ ካርታ ኤሪያል ፎቶ ለተጎዦች እንደዘከረው!!! የብልፅግና መንግሥት  የትግራይን፣ አማራንና አፋርን ክልላዊ መንግሥቶች አይቆጣጠርም፣ ግብርም አይሠበስብም፡፡   በዋና ከተማዎ በአዲስ አበባ ከተማ ዝርፍያ ሁኔታ መጨመርና በኑሮ ውደነት ሳቢያ ድንገተኛ ሰላማዊ ሠልፍ ወደ አመጽ ሊለወጥ ይችላል፡፡ በሃገሪቱ ውስጥ በተዛመተው የታጣቂዎች ፍልሚያና ህዝባዊ እንቢተኛነት ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሊዛመት ይችላል፡፡ በሃገሪቱ የሰሜን ክልል አቅጣጫ የትጥቅ ትግል ፍልሚያ፣ ህዝባዊ እንቢተኛነትና አመፅ በመኖሩ የፀጥታና ደህንነት ስጋቶች ይስተዋላሉ፡፡ በትግራይ ክልል ዞን 1 ዞን 2 ዞን 4 እና  በአፋር ክልል የደንከል በረሃ አካባቢ፣ በአማራ ክልል፣ ቤኒሻንጉል ክልል በተለይም በክልሉ  ጠረፍማ አካባቢና ዞኖች በ30 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የደህንነት ስጋት ስላለ ጥንቃቄ ያሻል፡፡ በመአከላዊ ክልል የፀጥታ ሁኔታ ህዝባዊ አመፅ፣ በሃይል የሚፈፀም ወንጀል፣ አፈና፣ የታጣቂዎች ፍልሚያ፣ የዓየር ድብደባ የመሳሰሉት ስጋቶች ስላሉ ጉዞችሁን አስወግዱ፡፡ በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ዞኖች፣ በምስራቅ ሸዋ ዞን፣ በምስርቅ አርሲ ዞን፣ ሃረርጌ ዞን፣ ጉጂ ዞን፣ ኤ 7 ሃይዌይ በሞጆና ሃዋሳ ዋና መንገድ አንዲሁም ኤ 1 ሃይዌይ ሰሜናዊ ምዕራብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከወለኝጪተ በስተቀር፣ ሰሜን ሸዋ ዞን እንዲሁም ደቡብ ምስራቅ ሸዋ ዞን በሙሉ ይካተታሉ፡፡ በጋምቤላ ክልል ሠላሳ ኪሎሜትር ርቀት ዞኖቹንና ክልሉን ዙሪያ፣ ሱማሌ ክልል የታጣቂዎች ጥቃትና ሽብርተኛነት ጥቃት እንዲሁም የሰው እገታ ይከሰታሉ፣ ይህም ጥቃት ከድሬዳዋ ከተማ ኦሮሚያ ክልል  እንዲሁም አፋር ክልል ከ30 ኪሎሜትር ርቀት የአደጋ ስጋት ይስተዋላል፡፡     ከሚከተሉት አገሮች  ከኤርትራ፣  ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሳውዝ ሱዳን እና ሱዳን ጠረፍማ አካባቢ  ባለ አለመረጋጋት፣አፈና፣ አመጽና የተቀበረ ፀረ ሰው ፈንጅ  አደጋ ምክንያት በጉዞ ጊዜ ሃምሳ ኪሎሜትር ከጠረፍ አካባቢ በመራቅ አደጋ ማስወገድ ይገባል፡፡

የኢትዮጵያና የጎረቤት ሃገሮች   ኤርትራ፣  ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሳውዝ ሱዳን፣ ሱዳንና፣ ጅቡቲ  ወቅታዊ ሁኔታ በማገናዘብ ትጥቅ ማጥበቅ እንጂ ትጥቅ ማውረድ አይሆንም እንላለን፡፡ ኮነሬል አብይ ትጥቅ ማስፈታት በሠላም እንጂ በኃይል እንደማይሆን መገንዘብና ከጦርነት የወጣቶች እልቂት፣ የአካል መጉደል፣ የህዝብ መፈናቀል፣ የመሠረተ-ልማቶች ውድመት፣  በትግራይ ጦርነት ገሃድ ምስክር ነው፡፡   በአማራ ልዩ ኃይል የተከፈተው ጦርነት ነገ በሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎች እንደሚሆን በማወቅ የእራሳችን ህልውና በክንዳችን እናስከብር እንላለን፡፡ tactics

የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ!!!

የኦነግ ፌዴራል መከላከያ ሠራዊት በአስቸኳይ ከአማራ ክልል ይውጣ!!!

አማራን ትጥቃቸውን ብቻ ሳይሆን ቀበቶቸውን እናስፈታለን ያለ ባንዳ ምርኮኛ ለፍርድ ይቅረብ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop