ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር የሚከተለውን መልስ ሰጥቷል።

ኦህዴድ መራሹ የዐቢይ አህመድ መንግሥት “የአማራ ሕዝብን እንደ ሕዝብ የምናደርስበትን መከራ ለምን ድምፅ ሆናችሁት” በሚል በርካቶችን እያሳደደ እና እያሰረ ይገኛል።
በዛሬው ዕለትም እኔን እና ወንድሞቼን “ሕገ – መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስ” በሚል በሽብር ወንጀል እፈልጋቸዋለሁ እያለ ነው።
ወንድማችን ግርማ የሺጥላን የገደለው ኃይል ከያዛቸው ከወራት በላይ የሆናቸውን እንዲሁም ፍርድ ቤት የዋስ መብት የሰጣቸውን ግለሰቦች የዋስ መብታቸውን ነፈጎ በአዲስ ክስ ለመመሥረት አመቺ መንገድ መፍጠሩ ነው። የዐቢይ አህመድ ‘መንግሥት’ የጡት አባታቸውን ሕውሓትን ከምኒልክ ቤተ መንግሥት ከመባረር እንዳላዳናቸው ማወቅ ተሥኗቸዋል።
በወንድሜ ሻለቃ ምሬ ወዳጆ እና በፋኖ በለጠ ጋሻው የተቀነባበረው የድምፅ ልውውጥም በማን እንደተቀነባበረ እንኳን እንደ እኔ አይነቱ ጋዜጠኛ እና የሳይበር ደህንነት ስልጠና ለወሰደ ሰው ለተራ ግለሰብም ሀሰተኛ የድምፅ ቅንብር መሆኑ የሚሰወር አይደለም።
እኔ አንድ አማራ ነኝ፤ በአማራነቴ የመጣብኝን መከራ እቀበለዋለሁ። ነገር ግን ስንቱን ገድሎ እና አፈናቅሎ እንደሚጨርሰው አብረን የምናየው ይሆናል። እኔና ሌሎች ጓዶቼ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ከፈጣሪ የተሰጠውን የመኖር መብት ቀምተን ከባሪያ ያነሰ አኗኗር እናኑራችሁ ለሚለን አካል እሺ እንደማንል ያደግንበት ሥሪትም ሆነ ሥነ – ልቦናዊ ውቅር እንደሌለ ልታውቁት ይገባል። ስለዚህ እንኳን የእስር ማደኛ አግኝታችሁ ብትሰቅሉኝም ከባሪያ ያነሰ ሕይወት ከምገፋ ለነጻነቴ እየታገልሁ ብሰቀል አይቆጨኝም።
የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ሁሉም ፋኖ መሆኑ እየታወቀ “ኢ – መደበኛ” ማቃለያ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ፈርጆ ለማጥፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ መላው የአማራ ሕዝብም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊያን ብሎም ለሰብዓዊ መብት መከበር የቆሙ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጉዳዩን በልዩ ትኩረት እንዲከታተሉት እና እየተፈፀመ ያለውን የዘር ጭፍጨፋ እና የዘር ማጽዳት እንዲያስቆሙ ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ።
በመጨረሻም፦
አማራ ግን የታወጀብትን የዘር ጭፍጨፋ እና የዘር ማጽዳት ግን ቀልብሶ እንደሚወጣ እርግጠኛ ነኝ!

ተጨማሪ ያንብቡ:  መኢአድ የሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄዎች መንግሥት በአስቸኳይ እና በተገቢው ሁኔታ መልስ እንዲሰጣቸው ጠየቀ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share