በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከስም ግጥጥሞሽ በዘለለ እነዚህ ሁለት ሰወች በኢትዮጵያና በህዝቦቹዋ ላይ ባደረሷቸው ጉዳቶች፣ ባሳረፏቸው የታሪክ ጠባሳወችና በአፍራሽ ስራወቻቸው በስፋት ይታወቃሉ፡፤ በመካከላቸው ሰፊ የዘመን ልዩነት ቢኖርም ሁለቱም ለስልጣናቸው ሲሉ ሀይማኖትንና ዘርን ዋና ታሳቢወቻቸው አድርገው በአገርና ህዝብ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ግፍ፣ በደል፣ እልቂትና የህዝብ ፍልሰትን በስፋት አክሂደዋል፡፤ በታሪክ ፊት ወደርለሽ የአፍራሽነት ስራዎቻቸውን ከዚህ እንደሚከተለው አጠር አድርገን እንቃኘው፡፡
ግራኝ አህመድ፦
ግራኝ አህመድ እ.ኤ.አ ከ1507 እስክ 1543 የኖረ ሰው ሲሆን ትክክለኛ ሙሉ ስሙ ‘አህመድ ኢብራሂም አል-ጋዚ’ነው፡፤ ግራኝ አህመድ የባሪያ ፍንገላና ክርስቲያኖችን አስገድዶ የእስልምና ሀይማኖትን እንዲቀበሉ በማድረግ ሂደቱ ውስጥ የፈጸማቸው አረመኔያዊ ጭፍጨፋወችና የማስገደድ ስራወቹ ይታወቃል፡፡
ግራኝ አህመድ ከምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል ጀምሮ ወደ ሰሜን ብዙ ዘመቻወችን አካሂዷል፤፡ በዚህም ክርስቲያኖችን በማጥፋት የጭካኔ ስራወቹ ስፍር ቁጥር የሌላችቸው ባሪያወችን በመፈንገል በደቡብ አረቢያ፣ ለዘቢድ አስተዳዳሪ በስጦታ መልክ በመላክ በተራው የብዙ ጠመንጃወች ባለቤት ሊሆን ችሏል፡፡ ያ የመከራ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ “የግራኝ አህመድ ወረራ” ተብሎ ይጠቀሳል፡፤
ግራኝ አህመድወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ባደረጋቸው መስፋፋቶች በ1529 የአጼ ልብነ ድንግል ሰራዊት ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የያኔዋ ‘ሽምብራ ቁሬ’ የአሁኗ ‘ሞጆ’ ከተማ ላይ ተዋግቶ ድል በማድረጉ ግስጋሴዉን ወደ ሰሜን አስፋፋ፡፡ ከዚያም በየደረሰባቸው ስፍራወች ሁሉ ክርስትያኖችን በግደታ እያሰለመና እያሰቃየ የባሪያ ፍንገላን እያጧጧፈ በህዝቡ ላይ ብዙ ስቃይና መከራ ካደረሰ በኋላ ለ15 አመት ወደ ሰሜን ያደረገው መስፋፋት እ.ኤ.አ በ1543 ጎንደር ወይና ደጋ በተባለች ቦታ ላይ በአፄ ልብነ ድንግል ልጅ በአፄ ገላውዴዎስ ጦር ተሸነፈ፡፡ በዚህም የባሪያ ፍንገላ ስራው፣ የግዛት ማስፋፋት ወረራውና የእስልምና ሀይማኖትን በክርስቲያን ኢትዮጵያዊያን ላይ በማስገደድ ለማስፋፋት ያካሄዳቸው ሰቅጣጭ እልቂቶችና ጦርነቶች ቆሙ፡፡ መቃብሩ የሚገኘው ሀረር ከተማ ውስጥ ጀጎል በሚገኘው የጁማ መስጊድ ውስጥ ነው፡
አብይ አህመድ፦
አብይ አህመድ የተወለደው በሻሻ ተብላ በምትጠራ ትንሽ የጅማ ከተማ ውስጥ እ.ኤ.አ በ1976 ነው፡፡ አብይ የወያኔ አደረጃጀትንና፣ የኦነግን የዘር ፖለቲካን ተግቶ ያደገ ሰው ነው፡፡ በወያኔ ስር ከተራ ወታደርነት እስከ ኮሎኔልነት ማእረግ ደርሷል፡፡ ከሬድዮ መገናኛ ሰራተኛነት እስከ የኢህአደግ የስለላ ሚኒስቴርነት ደረጃ ደርሷል፡፡ ወያኔ ለስልጣኔ መወጣጫ በማናጆነት ይጠቅሙኛል ብሎ ከአማራው ከኦሮሞውና ከደቡቡ ያደራጃቸው ሶስት አሻንጉሊት ድርጅቶችና ራሱ ወያኔ አራተኛ ድርጅት ሆኖ ግንባር በሚል ድራማ ኢህአደግን ሲመሰረት አብይ በውስጡ ነበረ፡፤
ከወያኔ ውድቀት በኋላ አብይ አህመድ ራሳቸውን “የለውጥ መሪወች” ነን ይሉ የነበሩ 4 ቁልፍ የኢህአደግ ሰወች አንዱ ስለነበረ በተካነው ሴራ ሶስቱን ፈነጋግሎ ስልጣኑን በእጁ አስገባ፡፡ ከዚያም ህዝቡን ቀስ በቀስ አታልሎ ብልጽግና የሚል የማፊያ ድርጅት መሰረተና ራሱ መሪ ሆኖ አሁን የወጣለት ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን በቃ፡፡
አብይ የሚያምነው በአንድ ነገር ብቻ ነው፡፤ ምንም ይሁን ምንም፣ ማንም ይለቅ ስንትም ይለቅ፣ ማንም ይጨፍጭፍ ማንም ምንም ይዝረፍ ….ወዘተ << ስልጣኑ እንዳይነካ ብቻ ነው አብይ የሚፈልገው፡፡” አገር ትዋረድ፣ ህዝብ ይጨፍጨፍ ይሰደድ፣ ታሪክ ይጥፋ፣ ቅርስ ይውደም ለእርሱ ምኑም አይደለም፡፤ ሲጀመር አብይ አቅምም፣ ፍላጎትም ችሎታም ስለሌለው ውድመትንና እልቂትን ማስቆም የሚለውን ነገር አያስበውም፡፡ እንዲያውም ለስልጣኑ ማቆያ ሲጠቀምበት ነው የሚታየው፡፡ ይህ ነው የዘመናችን ግራኝ አህመድ ማለት፡፤ ለእነዚህ ሁሉ ወደርየለሽ አፍራሽ ስራወቹ ከበቂ በላይ ማሳያወች አሉ፡፤
ሚሊዮኖች ይለቁ፣ ሚሊዮኖች ይራቡ ፣ሚሊዮኖች ይሰደዱ አብይ ጉዳዩ አይደለም፡፤ የእርሱ ትኩረት ራሱ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ እንዴት አድርጎ በመዋሸት፣ በመቅጠፍ፣ በማስመሰልና፣ በማታለል ስልጣኑን ማስቀጠል እንዳለበት ብቻና ብቻ ነው፡፤ ይህንኑ እምነቱንና አስተሳሰቡን ስልጣን ከመያዙ በፊት “እርካብና መንበር” በሚል መጽሀፉ ላይ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጦልናል፡፡
አብይ በህዝብና በአገር ላይ ያደረሳቸው ጉዳቶችንና ቅጥፈቶችን እንደ ‘ሰው’ ማስቡ ይክብዳል፡፡ አብይ አህመድ ከአፉ እውነት ይወጣል፣ ህሊናው ቀና ያስባል፣ ስላልቻለ ነው እንጅ ልቡ በክፋት ያልተሞላ ነው ብሎ የሚያስብና የሚያምን ካለ ራሱ አብይ አህመድ ይስቅበታል፡፡ ሻጥር፣ ጩልሌነት፣ ውሸት፣ ክህደት፣ ዘረኝነት፣ ተረኝነት አስመሳይነት ከመገለጫወቹ ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፤ በዚህ ሁሉ ላይ “አጠቃቀስኩ’’ ከማለት በዘለለ እዚህ ግባ የሚባል እውቀትና ችሎታ የለውም፡፡ ከአማኑእል ካንት እስከ ሀይሌ ፊዳ ድረስ ስሞችን ይጠቃቅሳል፡፡ የግራና ቀኝ የሰው አአምሮ ክፍሎች ላይ ሊፈላሰፍ ሲጋጋጥ ይታያል፡፡ ግን በባዶው ነው፡፡ዜሮ እውቀትና ብቃት፡፡ ሰውየው አሁንም ያው “7ኛ ጬ” ላይ ነው፡፡ ፈቀቅ አላለም፡፡ ግን ዶክተር ነው፡፡፡ የ126 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባት አገር ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ላይ ሆኖ “እኛ ኦሮሞወች ዝሆን ነን ሌላው ሚዳቆ ነው እያለ” በወንጀል የተጨመላለቀ የኦሮሙማ አስተሳሰቡንና ስራወቹን በመርዝነት ይረጫል፡፡ ህዝቡ ይህንኑ የኦሮሙማ እሳቤውን ሲነቅፈው ሮጦ ኦሮሞ ህዝብ ጉያ ውስጥ ይወሸቃል፡፡ ‘እነዚህ ኦሮሞ ጠል ናቸው”’ይላል፡፡ የፈጠራ ዜናን በማሰራጨት ግጭት እየጠመቀ ህዝብን ባደራጃቸው የኦሮሙማ ሀይሎች ያሳጭዳል፡፡ እዚህ ላይ ሁለት ቃሎችን ማለትም “ኦሮሙማ” እና “ኦሮሞ” የተሰኙትን የሁለት ቃላቶች ልዩነት ለሁሉም ግልጽ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ኦሮሙማ ኦሮሞ ማለት አይደለም፡፤ ኦሮሞ ብሄር ነው፡፤ ኦሮሙማ ደግሞ በሁሉም ነገር የኦሮሞ በላይነትን የሚያጠነጥን አስተሳሰብ ነው፡፤ አይዶሎጅ ነው፡፤ የእሳቤው ማጠንጠኛም በሁሉም ረገድ ኦሮሞ የበላይነት አለው የሚል ነው፡፡ሁሉ ኬኛ !!ይህ እሳቤ ነው ወፍ ዘራሹ ህዝቄል ጋቢሳ በይፋ እንደሚለው “እየሱስ ክርስቶስ መጀመሪያ ዋቃ ነበር” ከሚለው እሳቤ ጋር የማይተናነሰው፡፡
በኦሮሙማው መንጋወች እሳቤ/አይዲኦሎጅ ኦሮሙማ የሚገነባው በኢትዮጵያዊነት መቃብር ላይ ነው፡፡ እሳቤው እውን የሚሆነውም የኦሮሞ የበላይነት የነገሰባትና ንግስናውም የተረጋገጠባት አገርን በመመስረት ነው፡፡ ያቺ የኦሮሙማ መንጋወች የሚቃዡላት አገር ታላቋ ኦሮሚያ ወይንም የኦሮሞ ሪፐብሊክ ወይንም ኦሮሞነትን ከሁሉም የበላይ ያደረገች የእነርሱ በህልምና ቅዠታቸው “የኦሮሙማ ኢትዮጵያ” የሚሏት አገር ነች፡፡
ስለኦሮሙማ አይዶሎጅ ምጡቆች ነን የሚሉት ኦሮሙማወች የሚሸሽጉት ነገር የለም፡፤ ይህንኑ በግልጽ ይናገሩታል፡፡ ከአቶ አሰፋ ጃለታ ጀምሮ እስከ ኦቦ ሌንጮ ባቲም ሆነ ኦቦ ሌንጮ ለታና ሌሎችም የዚህ አይዶሎጅ አራማጆች ይህንኑ አልደበቁም፡፡ ከዚያም የወቅቱ 7ኛ ንጉሳቸው አብይ አህመድና በእሳቤው ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ክፍልፋዮች በዚሁ የኦሮሞ የበላይነት እሳቤ አንድ ናቸው፡፡ ከ80 በላይ በሆኑ በብሄር ብሄረሰቦች የተሞላውን 126 ሚሊዮኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ወደጎን እናቆየዉና ኦሮሙማወች በውሸትና በሸፍጥ የኦሮሞን ህዝብ ቁጥር ብዛት ለጥጠውና ቁጥሩን አሳድገው 36 ሚሊዮን ወይንም 40 ሚሊዮን ቢያደርሱትም ከዚሁ የኦሮሞ ህዝብ ብዛት ውስጥ ስንት ፐርሰንቱ ወይንም መቶኛው ይህንን እብደት የተሞላበት እሳቤና አይዶሎጅ ይቀበለናል ብለው እንድሚያስቡ ከእብደታቸው ሲነቁ ይረዱታል፡፡
ለወደርየለሽ ወራዳ ስብእና ቁጥር አንድ ምሳሌ የሆነው አብይ አህመድ ልቆ ከሚታወስባቸው ጉዳዮች ውስጥ መቋጫ የሌላቸው ዉሸቶቹና የማጭበርበያ ቅጥፈቶቹ በተግባር ሲታዩ እርስ በርስ የሚጋጩ ብቻ ሳይሆን መጨረሻ የሌላቸው መሆናቸው ሰውየውን አደገኛ ትዝብት ውስጥ ጥለዉታል፡፤ ስለግለሰቡ ማንነት በአጭሩ አንድ ነገርን ማለት ይቻላል፡፤ የአብይ አህመድን ማለቂያ የሌላቸውን ውሸቶችና ቅጥፈቶች ለመዘርዘር ከመሞከር ይልቅ አብይ አህመድ የተናገራቸውን እውነቶች ካሉ እነዚሁኑ መጥቀሱ ይመረጣል፡፤ ነገሩ ግን ወዲህ ነው፡፤ አብይ አህመድ አንዲም ወቅት አንዲትም እውነት አልተናገረም፡፡ ሁሌ ውሸት፣ ሁሌ ቅጥፈትና ሁሌ ማጭበርበር ብቸኛ መገለጫወቹ ሆነዋል፡፡በዚህ ማንነቱ ላይ ተረኝነቱንና ዘረኝነቱን ስትጨምሩበት ስብእናው ምን ያህል የገማና የገለማ እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ትችላላችሁ፡፡
ለማሳያ ያክልም የሚከተሉትን ሶስት ጉዳዮች ብቻ ነቅሰን አውጥተን የሰውየውን ማንነት እንመልከት፡፡፦
1ኛ) አብይ አህመድ “መቀሌን በሻሻ ማድረግን በሚመለከት እንዲህ ብሏል፡፡ “ሀወሀት አየር ላይ ተበትኗል” ይህንን ተናግሮ ካቀረሼ በኋላ አሁን የስሜኑን ህዝብ ችግር እንዳስወገደና ለህዝብ ጥቅምና ሰላማዊ መፍትሄ እንዳመጣ በማስመሰል ይህ ባልሆነበት አግባብ እንደ ዉሻ አሁን ወደ ቅርሻቱ/ ወደትፋቱ ተመልሷል፡፡ ይህ አይነቱ አሳፋሪ መገለባበጥ ለምን ይመስላችኋል? የሰውየውን የ7ኛ ንጉስነት ህልም እንዳትረሱ፡፤ ለስልጣኑ ነው፡፡ አብይ አሁን ላይ ይህንን መሰሉን ከውያኔ ጋር ጋብቻ የፈጸመው ወያኔ ጋር ተጣምሮና አማራን ደፍቆ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ነው፡፡
አገርን በማፍረስ ደረጃ እዚህ ላይ የሚያሳዝነው የቡከኑ አብይ አህመድ ከንቱነት ብቻ አይደለም፡፤ የጣሊያን ምርኮኞች ሲሸኙ “የአገሬን አፈር በጫማቸው ይዘው እንዳይሄዱ ድንበር ላይ ጫማቸውን አውልቀው አፈሩን እያራገፉ እንዲሄዱ አድርጓቸው” ብለው ያዘዙት የጀግናው አሉላ አባነጋ የልጅ ልጆች የሆኑት የጥቂት ከሀዲ የትግራይ ልጆች ክህደት ጭምር ነው፡፡የጀግናውን አሉላ አባነጋን ታሪክ ካነሳን ዘንድ ስንቶቻችን ነን ደርግ ለአሉላ አባ ባነጋ ክብር በስማቸው ያሰራውን ትምህርት ቤት ወያኔ ስሙን ቀይሮ “ወደ መለስ ዜናዊ ትምህርት ቤት”መቀየሩን የምናውቅ??
2ኛ) አብይ አህመድ በአገር መሪነት ቦታ ላይ ተቀምጦ እርሱ በእጅ አዙር ባደራጃቸው ቡድኖች በአማራነታቸው ተለይተው በብዙ መቶ ሽህወች አማራወች እንደከብት ታርደው የተወሰኑት አስክሬናቸውን እንዳይነሳ ተከልክሎ ጅብ እንዲበላቸው ስለመደረጉ፤ ብዙወቹ ደግሞ በአንድ ጉድጓድ እንዳቀበሩ ስለመደረጉ ሲናገር “”መቃብራቸው ጥላ ያገኝ ዘንድ አትክልት መትከል”” ብሎ የተመጻደቀበት ሁኔታ መቼም ቢሆን የሚረሳ አይደለም፡፡ በሌላ ወቅትም መሰል የንጹሀንን ጭፍጨፋ አጋጣሚን አስመልክቶ ቴሌቭዥን ላይ ቀርቦ አስክሬናቸውን በዘር እየለየ ከየዘሩ የተጨፈጨፉትን ብዛት በቁጥር የጠቀሰበት ሁኔታ የሚያሳየው ሰውየው ጭፍጨፋዎቹን አለማወገዙን ብቻ ሳይሆን ጭፍጨፋወቹን ከላይ ሆኖ በስልት እየመራ ያለው ራሱና ራሱ ያደራጃቸው የኦሮሙማ መንጋ አባላት መሆናቸውን ነው፡፡
3ኛ) አብይ አህመድ እጅግ ፈሪ ከመሆኑ የተነሳ እጅግ ጨካኝ ሰው ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተፈጥሯዊ የጀግና ሰውና የፈሪ ሰው ዋናው መለያ ባህሪይ ነው፡፡ ነገሮችን አጠማዝዞና ሴራወችን ጎንጉኖ፣ ሰወችን በመናኛ ጥቅምና ስልጣን ደልሎና እነዚሁኑ ጥቅመኞችና ተደላዮች በማይጠረጥሩት መንገድ ማኖ አስነክቶ በደካማ ጎናቸው በመግባት ብዙ ይጠበቁ የነበሩትን ሰወች ወደ ስልጣን ማማው ላይ ለመወጣጫነት ሲጠቀምባቸው አስተውለናል፡፡ ለአብነት ለመጥቀስም ያህል ምሳሌ፣ ዶር ብርሀኑ ነጋ፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ ዶ/ር በለጠ ሞላ፣አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ አቶ ክርስቲያን ታደለ ወዘተ የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እኔ እነዚህንስሞች የጠቃቀስኩት “የመጠቁ’ ፖለተከኞች ነበሩ ለማለት ሳይሆን ተስፋ ከተጣለባቸው ጥቂቶች መካከል በእኔ እሳቢ ሊጠቀሱ የሚችሉ ነበሩ ለማለት መሆኑ ይታወቅልኝ፡፡ እነ ደመቀ መኮንን፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ አገኘሁ ተሻገር ወዘተ አይነቶቹ የአማራ ሆዳም ሹመኞች ዱሮም የወያኔ አሁንም የኦሮሙማ የጭነት አህያወች ስለሆኑ ስለእነርሱ ምንም ማለት አይቻልም፡፡
በታሪክ እንደምናውቀው እየሱስ ክርስቶስ ራሱ በአምላክነቱ በፈጠራት በአህያ ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ እየሩሳሌም ተጉዟል፡፡ አብይ አህመድ ደግሞ በሰው አምሳል በተፈጠሩት በእነ ደመቀ መኮንን አይነቶቹ አህያወች ጀርባ ላይ ሆኖ በፊት ወደስልጣን ማማው ለመውጣጫነት ተጠቀመበቸው፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮና አሁንም እነዚያዉኑ የአማራ አህዮች ተጠቅሞ ሚሊዮን ንጹሀን አማራወችን እያረደና እያሳረደ ወደ መቃብር የሚያጓጉዝበት አህዮቹ አድርጓቸዋል፡፡
ይሄዉና ግርማ የሽጥላንም በህይወት እያለ በአማራ ህዝብ ፍጅትና ሰቆቃ ላይ እንደ አህያ ሲጠቀምበት ከቆየ በኋላ አብይ ፋኖንና የአማራ ልዩ ሀይልን የማስወገድ ሙከራው እንዳቀደውና እንዳሰበው ሆኖ ሳይሄድለት ሲቀር ዘዴ ቀይሶ አማራን ለመምታት ግርማን የጦስ ዶሮ አድርጎ ገደለው፡፡ ይህንን በማድረጉም የአማራ ልዩ ሀይልንና የመከላከያን ዩኒፎርም የለበሱ የኦሮሙማ ወታደሮችን በማሰማራት አማራን የመጨፍጨፍ ድርጊቱን በሁሉም የአማራ ክፍሎች ውስጥ አሁን ጀምሮታል፡፤ አልፎ ተርፎም አብይ ለስልጣኔ ያሰጉኛል ብሎ የጠረጠራቸውን አማራ የሆኑ የንግዱ ህብረተሰብ አባላትንና ፖለቲከኞችን በውጭ አገራት የሚኖሩ ጋዜተኞችንና የሜድያ ሰወችን ጭምር በአማራነታቸው ብቻ ለይቶ የእስርና ወንጀል ክስ ፋይል በይፋ ከፍቶባቸዋል፡፡ እዚህ ላይ ፈገግ ያሚያደርገን ጉዳይ አለ፡፡ይህም በአስር አለቃ ብርሀኑ ጁላ ትእዛዝ በአገር ውስጥ እንደሚታሰሩት ምስኪን አማራወች በውጭ ያሉትንም አማራወች አብይ አህመድ አስራለሁ ብሎ መፎከሩ ነው፡፡ገገማ!!
ስለወቅቱ ሁኔታ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፤ ሰውየው የመጨረሻዋ ሰአት ላይ ስለደረሰ እየተወራጬ ነው፡፤ እንደ አብይ አህመድ የነበሩ ፋሽሽቶችን ታሪክ ወደኋላ ስንቃኝ በቀዳሚነት ጀርመናዊዉን ድክታተር ሂትለርን እናገኛለን፡፡ ሂትለር ድክታተርና ፋሽሽት የነበረ ቢሆንም እንደ አብይ አህመድ አገሩንና ህዝቡን አላዋረደም፡፡ ታሪክ እንደሚያረጋግጠው የመጨረሻዋ ሰአት ስትደርስ ሂትለር ራሱን በጀግንነት አጠፋ እንጅ እጁን አልሰጠም፡፡ የእኛው ፋሽሽትና ድክታተር አብይ አህመድ መጨረሻ ታሪክ ግን ከዚህ ፈጽሞ የተለየ ነው የሚሆነው፡፡ አብይ አገሩንም ህዝቡንም አዋርዷል፡፤አለቆቹ “አለም አቀፍ ፍርድ ቤት በወንጀልህ እንዳትጠየቅ እናደግልሀለን፣ አንተ ብቻ የምናዝህን ፈጽም ስላሉት”” አገሩን አዋርዶ ለምእራባዊያ አሽከር ሆኗል፡፡ የአገር መሪ ሆኖ የእነርሱ ተቀጣሪምሆሟል፡፡ በዚያ ላይ አብይ ቦቅቧቃም ስለሆነ የመጨረሻዋ ሰአት እየደረሰች መሆኑን ተረድቶ ጽዋዋ ስትሞላ የጀግና ሰው ምላሽ የመስጠት ብቃቱም ወኔውም የለውም፡፡ ያች ሰአት ስትደርስ አብይ የሚሆነው አንድም እንዴ ላይቤሪያው ሳሟኤል ዶ በውጭ ቀጣሪወቹ ተክዶ እንደተደረገው በራሱ ሰወች ጥፍሩና ጆሮው እየተነቀለና እየተቆራረጠ ተሰቃይቶ ይሞታል፡፡ አለበለዚያም ቀጣሪወቹ በሰራላቸው ውለታ የረኩበት ከሆነ በጎ ታስቦለት ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ሲሆኑ ወደ እነርሱ ወይንም እስነርሱ ወዳዘጋጁለት አገር ይፈረጥጣል፡፡
ይህ ሁሉ ሆነም አልሆነም አንድ ነግር ግን እርግጥ ነው፡፡ በኢትዮጵያ መቃብር ላይ የምትመሰረት ኦሮሚያ ምንጊዜም አትኖርም፡፤ የሚሆነው ከሚከተሉት ሁለት ታሳቢወች ውስጥ ከሁለቱ አንዱ ብቻ ነው፡፤
ታሳቢ ቁጥር አንድ፦አሁን ያለው በዘር የተማከለ ህገመንግስትና ፍትህ አልባ ስርአተ ታግዶና አገር ተረጋግታ ሁሉንም ተቃዋሚወች በሙሉ ያካተተ ሀቀኛ አገራዊ ውይይትን በማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሶ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለ አድሎ በእኩልነትና በነጻነት የሚኖርባት ፊደራላዊት ኢትዮጵያ ትመሰረታለች፡፡ አለበለዚያም፦
ታሳቢ ቁጥር ሁለት፦ አገር ፈርሳ ሁሉም ወዳልታሰበ እልቂትና ውድቀት ይገባል፡፤
ታሳቢ ቁጥር አንድ ጥሩና የሚመረጥ ታሳቢ ሲሆን ታሳቢ ቁጥር ሁለት ግን እጅግ መራር ቢሆንብንም እውን ሊሆን የሚችል መጥፎ ታሳቢ ነው፡፡ በታሳቢ ሁለት ዉጤት ለጊዜው ሁለቱ ማለትም ለወያኔና ኦህዴድ የሚጠቅማቸው አማራጭ ቢመስላቸውም ይህ አማራጭ ግን ለማንም የተሻለ አማራጭ አይሆንም፡፡ ይህ አማራጭ እውነት የሚሆን ከሆነ ሁሉም ሲደማና ሲዳማ ለአመታት ይኖራል እንጅ አንዱ ለብቻው ደልቶትና ሰላሙ ተጠብቆለት ሌላው ሰላሙን አጥቶ የሚኖርበት ሁኔታ ፈጽሞ አይኖርም፡፡ አሁን የኦሮሙማ ተረኞችና የወያኔ ርዝራዦች እንደሚያስቡት አማራው ተበታትኖና ጠፍቶ ወይንም እነርሱ እንደፈለጉት ሸንሽነዉት በተገዥነት እንዲኖር ቢደረግ እነርሱ ግን ደልቷቸው አይኖሩም፡ የሌላውም የኢትዮጵያ ክፍል ህዝብ እንዲሁ በኦሮሙማ የይተኮረኮመና ማንነቱ እየተዋጠና ርስቶቹ እየተሰለቀጡ የሚኖርበት ሁኔታ ፈጽሞ አይኖርም”፤ በጥቅሉ ይህ አማራጭ ፈጽሞ አይሰራም፡፤ወይ ለሁሉም የምትመች ኢትዮጵያ ወይንም ለሁሉም የማትመች ፍርስራሽ አገር ነው እውን የሚሆነው፡፡
ለሁለተኛው አማራጭ እውን መሆን ተግተው የሚሰሩት የተወሰኑ ምእራብዊያን አገሮች እንዳሉ አይካድም፡፤ ገሀድ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ጸረ ኮሎኒያሊዝም ትግሉ ወቅት ለሌሎች አገሮች መልሳ ጠንካራ ምሳሌ እንዳትሆን በጣት የሚቆጠሩ ምእራባዊያን አገሮች የኢትዮጵያ የቅርብ ጠላቶችን በመሳሪያነት በመጠቀም ተባብረው እየሰሩ ነው፡፡ ይህንን እውነታ ከሊቅ እስከደቂቅ ኢትዮጵያዊያን እናውቃለን፡፡ የሚያሳዝነው ግን ከውስጣችን እጅግ በጣም ጥቂት ሆዳሞችና ባንዳወች አሉ፡፡ የአገሪቱ ሩቅና የቅርብ ጠላቶቿ ይህንኑ ሁለተኛ አማራጭ እውን ለማድረግ በዋናን አስፈጻሚነት የመረጡት የውስጥ ተቀጣሪያቸውን አብይ አህመድ አሊን ነው፡፡ አብይም ይህንኑ እውን ለማድረግ እየሰራ ስለሆነ አገራችችንን የምንወድ ኢትዮጵያዊያን ይህ እንዳይሆን የቻልነውን ሁሉ ማድረግ አለብን፡፡ እናደርገዋለንም፡፡
በመጨረሻም ወደ ርእሳችን እንመለስና አሁን አገራችን ምን ያህል አደገኛ የውድቀት አፋፍ ላይ እንደቆመች ከገባን ዘንድ ታዲያ አገሪቱን ወደ ፍርስራሽነት በመቀየር ይበልጥ የጎዳት አብይ አህመድ ወይንስ ግራኝ አህመድ?? መልሱን ለእናንተ እተወዋለሁ፡፡