በአገራችን ምድር የሚካሄደው ሁለ-ገብ ጦርነት የውክልና ጦርነት ነው!!   ጦርነቱ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና የግብረ-አበሮቹ ነው!

ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)
ሚያዚያ  25፣ 2023

መግቢያ

ህወሃት ወይም ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ የመኖርና ያለመኖር ዕድል 27 ዓመታት ያህል ስልጣን ላይ በቆየበት ጊዜ ሲወስን፣ ቀጥሎ ስልጣንን የጨበጠው የኦርሞን የበላይነት አሰፍናለሁ ብሎ አገርን የሚያተረማምሰው የአቢይ አህመድና የሺመልስ አብዲሳ አገዛዝ አገራችን እንድትንኮንታኮት፣ ህዝባችን ደግሞ በጎሳና በሃይማኖት ተሳቦ በሚካሄድ ጦርነት የእርስ በርስ ጦርነት በማካሄድ አቅጣጫው እንዲጠፋበትና ኃይሉም ተሟጥቶ እንዲቀር የማይሰሩት ተንኮልና ወንጀል ይህ ነው አይባልም። ከአንድ ብሄረሰብ የተውጣጣው ወያኔ የሚባለው የወንበዴ ድርጅት እራሱን “የነፃ አውጭ” ድርጅት ብሎ በመጥራት አገራችንን በጎሳ በመከለልና በመከፋፈል ዘረፋ ሲያካሂድና አገርን ሲያተረማምስ እንደነበር ይታወቃል። ሀወሃት በነፃነት ስም ጦርነትን ሲያካሂድና ስልጣንን ከጨበጠ በኋላም የትግሬን ብሄረሰብ ጥቅም አስጠብቃለሁ ቢልም በመሰረቱ የአሜሪካንና የግብረአበሮቹን አገርን የመበታተንና ህዝብን የማዳከም ጥቅም ብቻ ነበር ያስጠብቅ የነበረው። ስለሆነም በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም፣ በአውሮፓ አንድነትና በወያኔ መሀከል በነበረው የጥቅም ግኑኘት የተነሳ  አገራችን ከውስጥ እንድትቦረቦር በማድረግ ከውጭ ለሚመጣ ወራሪ ኃይል እንድትጋለጥ ለማድረግ በቃ። በተለይም ተግባራዊ ባደረገው የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊሲ አማካይነት ከፍተኛ የባህል ውድመት በማድረስ፣ በዶላር የሚታለልና በቀላሉ ለአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ለመንበርከክ ዝግጁ የሆነ አዲስ የህብረተሰብ ክፍል ብቅ እንዲል አደረገ።  ወያኔ ስልጣን ላይ በቆየበት ጊዜ የአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ፖለቲካን እከተላለሁ ቢልም በመሰረቱ ከዚህ አስተሳሰብ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር አልነበረም። በመለስ ዜናዊ ይመራ የነበረው የህወሃት አገዛዝ የተሰማራው የአገሪቱን ሀብት በመዝረፍ እንጂ በኢንዱስትሪ ተከላና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ ሊሰማራ የሚችል ኃይል ለመፍጠር አልነበረም ዋና ዓላማው።  ስለሆነም ህወሃት ተግባራዊ ባደረገው የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊስ አማካይነት በዘረፋ የተሰማሩ የናጠጡ ቱጃሮች ብቅ ከማለታቸው በስተቀር ወደ ውስጥ ያተኮረ፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተና ለሰፊው ህዝብ የስራ መስክ ሊከፍት የሚችል ሰፋ ያለ የአገር ውስጥ ገበያ ሊገነባ አልቻለም።

ካለፉት አምስት ዓመታት ጀምሮ ደግሞ ስልጣንን የተቆናጠጠው በአቢይ አህመድ የሚመራው የኦሮሙማ አገዛዝ በመሰረቱ በሌላ ሽፋን ስም የወያኔን ፈለግ በመከተል ነው ብዝበዛና ዘረፋ የሚያካሄደውና በህዝባችንም ላይ ሁለ-ገብ የሆነ ጦርነትን የከፈተው። ይህም ማለት አቢይና አገዛዙም ልክ እንደወያኔው የዘረፋና የከፋፍለህ ግዛው አገዛዝ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምንና የግብረአበሮቹን ጥቅም የሚያስጠብቁ ናቸው ማለት ይቻላል። ይህም ማለት ወያኔ የሰፊውን የትግሬን ብሄረሰብ ጥቅም ያላስጠበቀውን ያህልንና ከድህነትም እንዲላቀቅ ያላደረገውን ያህል፣ የአቢይ አህመድና የሺመልስ አብዲሳ ቡድንም ከድህነትና ከኋላ-ቀርነት ለመላቀቅ የሚፈልገውን ሰፊውን የኦሮሞ ብሄረሰብ ጥቅም የሚያስጠብቅ አይደለም።  ስለሆነም በተለይም አቢይ አህመድ በዓለም አቀፍ የአገዛዝ ሂራርኪ ውስጥ በመካተትና የአሜሪካንን ኢምፔሪያሊዝምን የአገር አፍራሽነት ሴራንና ህዝብን የመበታተን ፍላጎት በማስጠበቅ አገራችንን ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ከቷታል ማለት ይቻላል። ወያኔ ነፃ አውጭ ነን ባዮች ሌሎች የብሄረሰብ ኢሊቶችን በስሩ በማሰባሰብና የእርስ በርስ ጦርነት በመቀስቀስና በመዝረፍ የአገራችንን ታሪክ፣ ባህሉን፣ ማህበረሰብአዊ ግኑኝነቱንና ስነ-ልቦናውን በመበወዝ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ሰርቷል፤ ወይንም የአገራችን ታሪክ በአዲስ መልክ እንዲጻፍ ለማድረግ ሞክሯል። የኦሮሙማው የአቢይ አገዛዝ ደግሞ ሁሉንም በመሰልቀጥና ግዛትን በማስፋፋት የኦሮሞን የበላይነት አሰፍናለሁ በማለት እዚህና እዚያ ሲንቀጀቀጅ ይታያል፤ በሁሉም አቅጣጫ ጦርነት በመክፈት ህዝባችንን መቆሚያና መቀመጫ አሳጥቶታል። ይሁንና ግን አቢይ አህመድና ግብረ-አበሮቹ የኦሮሙማን የበላይነት ለማስፈን ሳይሆን የሚሰሩት በቀጥታ የአሜሪካንን ትዕዛዝ በመቀበል ኢትዮጵያ ከውስጥ እንድትዳከምና እንድትከፋፈል ማድረግ ነው። የተከፋፈለና የተዳከመ ህዝብ ደግሞ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ስለማይችል በተለያዩ ኢሌቶች መሀከል በሚፈጠር የስልጣንና የሀብት ሽኩቻ በጦርነት ውስጥ በመዝፈቅ ልጆቹን ሲገብር ይኖራል። ባጭሩ በጋራ በመነሳት አገሩን እንዳይገነባ ይደረጋል ማለት ነው። በዚህ መልክ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የውጭ ኃይሎችን ጥቅም ለማስጠበቅ በሚካሄድ ዘረፋና የእርስ በርስ ጦርነት ሰፊው ህዝባችን እፎይ ብሎ እንዳይኖር ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ አገራችንና ህዝባችን ቆርቁዘውና ደሃ ሆነው ለብዙ ዓመታት እየተሰቃዩ ይኖራሉ። የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምም ዋናው ዓላማ እንደ ኢትዮጵያ የመሰለች የብዙ ሺህ ዓመታት ታሪክና ሰፊውን ህዝብ የሚያስተሳስር ባህል ያላትን አገር አዳክሞና በታትኖ ሰፊው ህዝብ አቅጣጫው ጠፍቶበት ተበታትኖ እንዲቀር ማድረግ ነው። በሌላ አነጋገር፣ የሃይቲው ዐይነት ሁኔታም በአገራችንም ምድር መፈጠር አለበት። ምናልባትም ማፊያዊ የሚመስሉ ቡዱኖች በመፈጠር አገራችንን ሲያምሱና ምስኪኑን ህዝባችንን ደግሞ  በሰላም እንዳይኖር ያደርጉታል። ይህ ዐይነቱ ነው የታላቁ አሜሪካ የውጭ ፖለቲካ ስልትና ስትራቴጂ።

ቀደም ብሎ የህውሃትን አገዛዝ አነሳስ፣ ምንነትና ተግባር በሚመለከት ከተለያዩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ተዋንያንና ጋዜጠኞች የሚቀርቡትን ገለፃዎች በምንመረምርበት ጊዜ በሳይንስ አነጋገር፣ ገለፃ(Descriptive) እየተባለ የሚጠራው አቀራረብ እንጂ፣ ሳይንሳዊ ትንተና እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ገለፃ ነው የሚያሰኘው ማንኛውም ሰው የሚያውቀውን በጽሁፍ ወይም በዜና መልክ ማቅረቡ ሲሆን፣ ውስጣዊ ይዘቱን፣ የርዕዮተ-ዓለም መሰረቱንና ከዓለም አቀፍ የብዝበዛ፣ የፀረ-ዕድገትና የጭቆና አገዛዝ አወቃቀር ተዋረድ( World governance or military industrial complex hierarchy)ጋር የተያያዘ መሆኑን በመመርመር ስለማይጻፍ ነው። የፖለቲካውን ሜዳ እንደዚህ ዐይነቱን ፊዩዳላዊ አቀራረቦች ወጥረው ስለያዙት 27 ዓመት ያህልም ሆነ ከዚያ በፊት በተለይም በአብዮቱ ወቅት የተካሄደውን የፖለቲካ ቲያትር በሳይንስ፣ በፍልስፍናና በቲዎሪ መልክ በማገናዘብና ተጨባጭ ድርጊቶችን በመተርጎም ለመተንተንና ለማሳመን እጅግ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። አቢይ አህመድና ግብረ-አበሮቹ ስልጣን ላይ ሲወጡም የውጭ ኃይሎች በስተጀርባው እንዳሉበት ስለማይታወቅ፣ ቢታወቅም እንኳን ደፍሮ ለመናገር የሚችል ሰው ወይም ድርጅት ባለመኖሩ አቢይ አህመድና ጓደኞቹ በህዝባችን ላይ የሚሰሯቸው ወንጀሎች፣ የሚከተሉት የኢኮኖሚ ፖሊሲ በእነሱ እንደተቀነባበረ ተደርጎ ነው የሚቀርበው። ስለሆነም የአቢይ አህመድን አገዛዝ የሚወነጅሉ ግለሰቦችም ሆነ ይህንን ወይም ያኛውን ድርጅት እንወክላለን የሚሉ ግለሰቦች የሚሰሩት የታሪክ  ወንጀል የአሜሪካንንን ኢምፔሪያሊዝምና ግብረ-አበሮቹን ከደሙ ንጹህ በማድረግ እነሱን በመለማመጥ ታዳጊውን ወጣት ማሳሳት ነው። በተለይም ሰሞኑን በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን የጦር መኮንኖች የሚሰጠው የተዘበራረቀ ገለጻ በኢትዮጵያ ውስጥ በተንሰራፋው የውንብድና ፖለቲካ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና ግብረ-አበሮቹ እጃቸው እንደሌለበት ነው።  በነዚህ የፖለቲካ ተዋንያን ዕምነትም አሜሪካ የኢትዮጵያ ህልውና በጥያቄ ውስጥ እንዲገባ፣ አገሪቱም እንድትፈራርስ አይፈልግም የሚል ነው። በጭንቅላቱ የቆመ አዲስ ቲዎሪ እያስተማሩነ ነው መለት ነው። ቀድሞ ህወሃት፣ አሁን ደግሞ አቢይ አህመድና ግብረ-አበሮች በራሳቸው ስሜትና አስተሳሰብ በመነሳት ብቻ ነው አገራችንን እያፈራርሱና በህዝባችን ላይ ጦርነት በማወጅ ህዝባችንን ፍዳውን የሚያሳዩት ብለው ነው  የሚነግሩን። በአቋራጭ ስልጣን ለመውጣት የሚፈልጉ እነዚህን የመሳሰሉ ኃይሎች ከሚታዩና ከተጨባች ሁኔታዎች በመነሳት ሳይሆን ነገሮችን ሸፋፍነው በማቅረብና የአሜሪካንን ኢምፔሪያሊዝም ከደሙ ንጹህ አድርጎ በማቅረብ ለዕውነተኛ ነፃነትና ዲሞክራሲ፣ እንዲሁም ለተሟላ ዕድገት  ለሚደረገው በዕውቀት ላይ ለተደገፈ ትግል እንቅፋት በመሆን ላይ ናቸው።

እንደሚታወቀው እንደኛ ባለው አገር ውስጥ የሚከሰቱና የሚያድጉ የፖለቲካ ሁኔታዎች ከሰማይ ዱብ የሚሉ ሳይሆኑ፣ በተለይም በዛሬው ዓለም የዚያው አገር ህብረተሰብአዊ አወቃቀርና ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ አገዛዝና ሁኔታ ውጤቶች ናቸው ማለት ይቻላል። ከ1940ዎች መጨረሻ ጀምሮ በአገራችን ምድር የተዋቀረውን የመንግስት መኪናና አገዛዝ፣ የፖለቲካ ግንዛቤ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ግኑኝነት፣ እንዲሁም የባህልና የስነ-ልቦና አቀራረጽ በምንመረምርበት ጊዜ በአገራችን የታሪክ ሂደት ውስጥ፣ የመዘበራረቅ ሁኔታና ራስን በራስ ያለማግኘት ጉዳይ የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ አወቃቀር፣ የፖለቲካ፣ የሚሊታሪና የፀጥታ ጉዳይ ወሳኝ ሚናን እንደተጫወቱና እንደሚጫወቱ መገንዘብ እንችላለን። በሌላ አነጋገር፣ ከ1940ዎቹ ዓመታት መጨረሻ ጀምሮ በተለያየ መልክ የሚገለጸው የአገራችን ሁኔታ በውስጣዊ ኃይል ንቃተ-ህሊና የሚወሰንና የሚታቀድ ሳይሆን በውጭው ዓለም እንደተወሰነና እንደሚወሰን በሳይንስና በቲዎሪ ማረጋገጥ ይቻላል።  ካፒታሊዝም በተንጠባጠበ መልክ ሲገባና በተለይም የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል የፍጆታ አጠቃቀምና ባህላዊ ሁኔታ ሲለውጥ በፖለቲካው መስክም ላይ የበኩሉን አስተዋጽዖ ለማድረግ ችሏል። እንደዚሁም የሚሊታሪው፣ የጸጥታው፣ የፖሊሲና የሲቪል ቢሮክራሲው፣ እነዚህ ሁሉ ከረጅም ጊዜ አንስቶ ሲወርድ ሲዋርድ በመጣና በዳበረ ዕውቀት የታነፁ ሳይሆን አነሰም በዛም የግሎባል ካፒታሊዝምና የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ውጤቶች በመሆናቸው ይሰሩ የነበረው አገራችንን በጸና መሰረት ላይ ለመገንባትና ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ ሳይሆን አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ይሰሩ የነበረው ለአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ነበር ማለት ይቻላል። እነዚህ ደግሞ የግዴታ በመንግስት ፖሊሲና የአስራር ሁኔታና የዕድገት ጉዳይ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ነበራቸው። በአፄ ኃይለስላሴ የአገዛዝ ዘመን ተግባራዊ የሆነውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በምንመረምርበት ጊዜ በቀጥታ ከውጭ ረቆ የመጣ ሲሆን፣ በማኑፋክቸሪንግ ላይ የተመሰረተና ሰፋ ላለ  የገበያ ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያመች አልነበረም። ይህ ዐይነቱ ሳይንሳዊና ሁለ-ገብ ባህርይ የሌለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በአገራችን ምድር ውስጥ ዝብርቅርቅ ሁኔታንና የተሙለጨለጨ የህብረተሰብ ክፍል  በመፍጠር፣ በዚያው መጠንም ለተገንጣይ ኃይሎች አመቺን ሁኔታ ሊፈጥር ቻለ። በሌላ አነጋገር፣ የብሄረሰብ እንቅስቃሴ ቀስ በቀስ እያለ እያደገ የመጣው በአገራችን ምድር ብሄራዊ ባህርይ ያለውና የተስተካከለ ዕድገት ተግባራዊ ለመሆን ባለመቻሉ ነው። በሌላ ወገን ግን በጊዜው ተግባራዊ የሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ አንድን ብሄረሰብ ብቻ ለመጥቀም ተብሎ ተግባራዊ የሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንዳልነበር ሁኔታውን የመረመረ ሊገነዘበው ይችላል።

ከዚህ ሀቅ ስንነሳ የአገራችን ህልውና መዳከም መሰረቱ የተጣለው በአፄ ኃይለስላሴ ዘመን ነበር ማለት ይቻላል። ለዚህ ምሳሌ የሚሆነን የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ኤምባሲ ህንፃ እንዲስራ አንድ ጋሻ ያህል መሬት የተሰጠው ሲሆን፣ በአስመራ ደግሞ የቃኘው የጦር ካምፕ እንዲገነባ የተሰጠው ሰፊ መሬት የአገራችንን ህልውና አደጋ ላይ የጣለና ስትራቴጂያዊ በሆነ መልክ ሳይታሰብ አሜሪካንን እንደ አጋር አገር አድርጎ በማየት የተነሳ ነው። ይህ ዐይነቱ ከፊዩዳላዊ አስተሳሰበ የመነጨ የየዋህነት ፖለቲካ በቀላሉ ልንላቀቀው  የማንችለው ውስብስብ ሁኔታ ውስጥ ሲከተን፣ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ደካማ ጎናችንን በመጠቀም ከዚኸኛውና ከዚያኛው የተውጣጡ የየብሄረሰቡን ኤሊቶች በመመልመል አጠቃላይ ጦርነት እንዲያውጁብን አመቺ ሁኒታን ፈጥሮላቸዋል። በአፄው ዘመን ይካሄድ የነበረው ፖለቲካ ከሳይንስ አንፃር ፖለቲካ ተብሎ ሊጠራ የሚያስችለው አንዳችም ነገር ስላልነበር በአገራችን ምድር መንፈሱ የጠነከረና ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ ሊያስብ የሚችል የህብረተሰብ ክፍል ለመፈጠር አልተቻለም። የጠለቀ አስተሳስብ ያለውና አገር ወዳድ የሆነ ምሁራዊ ኃይል ለመፈጠር ባለመቻሉ አገራችን ከውስጥም ሆነ ከውጭ በተቀነባበረ መልክ የምትቦረቦርበትና የምትዳከምበት ሁኔታ ሊፈጠር ቻለ። ይህም ማለት ኢትዮጵያ የዛሬው አጅግ አደገኛ የሆነ የህልውና አደጋ ውስጥ ለመውደቅ የቻለችው የተለያዩ ኃይሎች በማወቅም ሆን ባለማወቅ የአሜሪካንን ኢምፔሪያሊዝም እንደ ነፍሰ-አባታቸው በማየታቸውና ሰፊውን ህዝብ ከድህነትና ከኋላ-ቀርነት ሁኔታ ውስጥ ሊያላቅቀው የሚችል ሁለ-ገብ የሆነ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲ ባለመከተላቸው ነው። በተጨማሪም አንድ አገር ከታች ወደ ላይ ቀስ በቀስ እንዴት እንደሚገነባና ህብረተሰቡ ርስ በርሱ እንዲተሳሰር የባህል ጥገናዊ ለውጥ ተግባራዊ ለማድረግ ባለመቻላቸውና ልዩ ልዩ ተቋማትን ለመገንባት የወሰዱት እርምጃ ባለመኖሩ ነው።

ስለሆነም ባለፉት ስድሳ ዓመታት በንቃተ-ህሊና ጉድለት ወይም በአዕምሮ አለመብሰል ምክንያት የተነሳ ተማርኩኝ የሚለውና በተለያዩ ጊዜያት በመንግስት መኪና ላይ ቁጥጥ ያሉ አገዛዞች አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ፀረ-ዕድገትና ፀረ ህዝብ ፖሊሲና ፖለቲካ በመከተላቸው የአስተሳሰብ መዘበራረቅና የእርስ በእርስ ሽኩቻ ተፈጥሯል። ሃሳብን የሚሰበስብና ለጋራ ዓላማ እንድንታገል የሚያደርግ ፍልስፍና ወይም ርዕይ ለመዳበር ባለመቻሉ፣ በተለይም የቢሮክራሲው፣ የተወሰነው የሚሊታሪና የፀጥታው ኃይል የዚህ ወይም የዚያኛው የውጭ የስለላ ድርጅት ሰለባ በመሆን አገራችንን ወደ ጦር አውድማነት ሊለውጣት የሚያስችሉ ሁኔታን አመቻችተዋል።  ይህ እየተደራረበና እየተወሳሰበ የመጣ ጉዳይ ዛሬ አገራችን ለምትገኝበት ሁኔታ ዋናው ምክንያት ነው ማለት ይቻላል። በሌላ ወገን የወጭው ኃይል ሰለባ ያልሆኑ  ቀድሞ እንደሶብየት ህብረት፣ ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ፣ እንዲሁም ቻይና ጠንካራ ኢኮኖሚና ባህል በመገንባት ራሳቸውን ነፃ ማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን መፈራትና መከበር ችለዋል። ህዝባቸውም በሄዱበት ሁሉ የሚከበሩ ለመሆን በቅተዋል። ቻይና ደግሞ አሜሪካንን ለመተካት የምትችል ኃያል መንግስት ለመሆን በመገስገስ ላይ ናት። በአንፃሩ ግን የሶስት ሺህ ዘመን ታሪክ አላት የምትባል አገር እጅግ የደቀቀና በሁሉም አቅጣጫ  ለማሰብ በማይችል ጭንቅላት አገዛዞች እየተረበሽችና፣  በተለይም ደሃው ህዝብና ወጣቱ የጦርነት ሰለባ ለመሆን በቅተዋል።

ከዚህ ስንነሳ የወያኔን አነሳስና የኋላ ኋላ ስልጣን ላይ ወጥቶ የአገራችንን ዕድል 27 ዓመታት ያህል መደንገጉና ታሪክን ማበላሸቱ፣ ወይም ታሪካችን በአዲስ መልክ እንዲጻፍ ማድረጉ የተለያዩ የኢትዮጵያ ኃይሎችም ከውጭው ዓለም በተለይም ከአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ጋር ባላቸው የቀረበና የተቆላለፈ ግኑኝነት አማካይነት ነው። ከዚህ ውጭ ማሰብና እስከዛሬ ድረስ በአገራችን ምድርና በህዝባችን ላይ የደረሰውንና የሚደርሰውን ሰቆቃና መሰደድ የወያኔ ድርጊት ብቻ አድርጎ ማቅረብ አላዋቂነት ብቻ ሳይሆን ከፖለቲካ ሳይንስ የአቀራረብና የአተናተን ዘዴ አንፃር ስንመረምረው የተሳሳተ አመለካከትና አቀራረብ ነው። በተጨማሪም በተለይም ከ1945 ዓ.ም በኋላ በዓለም አቀፍ ላይ ብቅ ያለው የኃይል አሰላለፍ  እንደኛ ባለው አገር ላይ ሊኖረው የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመረዳት አለመቻል ነው። ስለሆነም ካለብዙ ምርምር ከውጭ የኮረጅነው ትምህርት በዲሲፕሊንና በጥሩ ርዕይ የሚመራና የሃሳብ ጥራትነት የሚኖረው አዲስ ትውልድ እንዲፈጠር ለማድረግ አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን፣ በተለይም ደግሞ ከአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ጋር የነበረን የጠበቀ ግኑኘነትና በፖሊሲ አውጭው በቢሮክራሲው ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ አገራችንና ህዝባችን የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት እንዳይሆኑ ለማድረግ በቅቷል። አንድ አገር ከታች ወደ ላይ የሚያድግ በሳይንስና በቴክኖሎጂ የሚደገፍ ኢኮኖሚ ከሌላት ደግሞ ህዝቧን ከድህነትና ከረሃብ ለማላቀቅ በፍጹም አትችልም ማለት ነው።

አቢይ አህመድና አገዛዙ፣ በተጨማሪም የአማራን ክልል እንወክላለን ብለው አገራችንን የሚያተረማምሱት ኃይሎች በሙሉ በዚህ ዐይነቱ የተበላሽ ሁኔታ ውስጥ  የተፈጠሩና ያደጉ  ህሊና ቢሶች ለመሆን የበቁ ናቸው። ጭንቅላታቸውን ለማዳበርና በሁሉም አቅጣጫ ለማየት እንዲችሉ ጠለቅ ያለና ሁለ-ገብ ዕውቀት ያልቀሰሙ በመሆናቸው የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ታዛዥ በመሆን አገራችንን ለመሰነጣጠቅ ሽር ጉድ ሲሉ ይታያሉ። አቢይ አህመድም ሆነ የአማራ ክልል መሪዎች ነን የሚሉት የወያኔን ጡት ሲጠቡ ያደጉ በመሆናቸው የሚያካሂዱት ፖለቲካ በሙሉ በአጠቃላይ ሲታይ ክልሉንና አገራችንን ያዳከመና ሊበታትንም የሚችል ነው። አቢይ አህመድም ሆነ እነዚህና ሌሎች የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ አቀንቃኞች ስለማህበረሰብና ስለህብረተሰብ ዕድገት የሚያውቁት ነገር ስለሌለ በቀላሉ ለውጭ ኃይሎች የሚያጎበድዱ ናቸው። በዝቅተኛ ስሜት በመመራትና ትዕዛዝ በመቀበል ለብሄራዊ ነፃነት በሚታገሉ ኃይሎች ላይ ጦርነትን  ያወጁ ናቸው። ባጭሩ ወያኔም ሆነ የአቢይ አህመድ አገዛዝ በህዝባችንና በአገራችን ላይ፣ በተለይም ደግሞ በአማራው ወገናችን ላይ የከፈቱት ጦርነት በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የሚደገፍ ነው። ይህም ማለት፣ ሁለቱም ኃይሎች፣ ህወሃትም ሆነ አቢይ አህመድና አጋሮቹ የሰፊውን የትግሬና የኦሮሞ ብሄረሰብ ጥቅም የሚያስጠብቁ አይደሉም። የሚያካሂዱትም ጦርነት የውክልና ጦርነት ስለሆነ በአገራችንና በህዝባችን ላይ ብቻ የታወጀ ሳይሆን በጠቅላላው የጥቁር አፍሪካ ህዝብም ላይ ነው። የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ከቻይና ጋር በገባው የጥሬ-ሀብት መቀራመት ፉክክርና የበላይነቴን አጣለሁ በማለት በሚያካሂደው ድብቅና የይፋ ጦርነት ወያኔንና አቢይ አህመድን በመጠቀም ጠቅላላውን አገራችንን ወደ ጦር አውድማነት በመለወጥ ላይ ይገኛል። ከዚህ ሀቅ ስንነሳ በተለይም ወጣቱ የትግሬና የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጆች ቆም ብለው በማሰብ ከእንደዚህ ዐይነቱ የወያኔና የአቢይ አህመድና የግብረ-አበሮቹ ሴራ በመቆጠብ ከጠቅላላው ህዝባችን ጎን በመቆም ለዕውነተኛ ነፃነትና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መታገል አለባቸው። ዕውነተኛ ነፃነታቸውንም ለመጎናጸፍ የሚችሉት እኔ ትግሬ ወይም ኦሮሞ ነኝ ብለው የመለየት አስተሳሰብን ሲያራምዱ ሳይሆን ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ወጣት ጋር በመሰለፍ ብቻ ነው። ይህንን ለማድረግ የሚፈልጉ ከሆነ ደግሞ ራሳቸውን ማወቅ አለባቸው። ራሳቸውን ለማወቅ ደግሞ ከዕውነተኛ ዕውቀትና ጭንቅላትን በጥሩ መልክ ከሚኮተኩት ዕውቀት ጋር መተዋወቅ አለባቸው። አንድ ሰው ሰው መሆኑን የሚገነዘበው ጭንቅላቱ በትክክለኛ ዕውቀት ሲኮተኮት ብቻ ነው። ስለሆነም አገራችንን ከውድመት አድኖ ጠንካራና የምትከበር አገር እንድትሆን የሚፈልግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሁሉ የግዴታ መንፈሱን በትክክለኛ ዕውቀት ማነጽ አለበት። ይህ ሲሆን ብቻ ነው ራስን በራስ አግኝቶና ታሪክን ሰርቶ ለተከታታዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሚቻለው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አካላዊና መንፈሳዊ ጎኗ ክፉኛ የተጎዳውን ኢትዮጵያን ለመጠገን የሚታገለውን ፋኖ የማይደግፍ ኢትዮጵያዊ በምን ቀን የተፈጠረ ነው?

ይህንን የአሰራር ስልት ወይም ሳይንሳዊ አቀራረብ መሰረት በማድረግ ነው የወያኔ አገዛዝንም ሆነ አሁን ደግሞ ህዝባችንን የሚያተረማምሰውንና ፋሺሽታዊ የሆነውን የአቢይ አህመድን አገዛዝ ምንነት ለመመርመር የምንችለው። ወያኔ በዓለም አቀፍ የአገዛዝ ሂራርኪ ውስጥ በመካተት ሀብትን ሲዘርፍና አገርን ሲያውድም የህወሃትን ጡት ሲጠቡ ያደጉት እነ አቢይ አህመድና ሺመልስ አብዲሳ የመሳሳሉት ባህለ-ቢስ ኃይሎች ከወያኔ የተሻለ ፖለቲካና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሊያካሂዱ በፍጹም አይችሉም።  እንዲሁም ባህልን ከስካሽና ስነ-ልቦናን አድክሞ አንድን ህዝብ አቅመ-ቢስ እንዲሆን ከሚያደርገው ከአጠቃላዩ የህወሃት አሰራር ለመላቀቅ ያልቻሉት ከወጣትነታቸው ጀምረው በተበላሸ አስተሳሰብ መንፈሳቸው በመታነጹ ነው። ለዚህ ደግሞ የወያኔ አገዛዝ በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና ዓለም አቀፋዊ በሚባሉ ተቋማት ተገዶ ተግባራዊ ያደረገው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ወሳኝ ሚናን እንደተጨዋተ ማረጋገጥ ይቻላል።  የኒዎ-ሊበራልን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረጉ፣ ከውጭው ዓለም ዕርዳታ ማግኘቱ፣ በዓለም አቀፍ የጦርነት ስልት ስትራቴጂ ውስጥ በመግባት በአካባቢው ጦርነት በማካሄድና፣ ወደ ውስጥ ደግሞ ግድያን፣  በተለያዩ የማሰቃያ ዘዴዎች ህዝባችንን ማሰቃየትና ወጣቱ እንዲሰደድ ማድረግ፣ ጎሳንና ሃይማኖትን አሳቦ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲነሳ ማድረግና፣ አገራችንን ዘለዓለማዊ የጦር አውድማ ማድረግ፣ ህዝባችንም የራሱን ታሪክ እንዳይሰራ መሰናክል መፍጠር፣ እነዚህ ሁሉ ከአሜሪካን ኢምፔርያሊዝምና ግብረአበሮቹ የውዝግብና የማተረማመስ፣ የህዝብን ቁጥር ከመቀነስ ስትራቴጂና ፓለቲካ ጋር በጥብቅ የተያያዙ ናቸው። ስለሆነም ወያኔ ወደ ዘራፊነት የተቀየረውና ሀብትን በከፍተኛ ደረጃ ማውደም የቻለው በግሎባል ካፒታሊዝምና በተቋማቱ በመደገፉ ብቻ ነው። የአቢይ አህመድ አገዛዝም ከጆርጅ ሶሮን ከመሳሰለው በሄጅ ፈንድ ከደለበው ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ሊኖረው የቻለው የአሜሪካንን የነጭ ኦሊጋርኪ ጥቅም ስለሚያስጠብቅ ብቻ ነው። ይህንን የማይቀበል የፖለቲካ ታጋይ ነኝ ባይ ኢትዮጵያዊ ስለ ዲሞክራሲና ነፃነት፣ እንዲሁም ስለ ሁለ-ገብ ዕድገት በፍጹም ሊያወራ አይችልም። በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባትና የተከበረች አገርም ለመፍጠር አይችልም። እንደዚህ ዐይነቱ ሰው ደግሞ ሰው ነኝ ሊል አይችልም። ስለሆነም ኢትዮጵያዊም ነኝ እያለ ሊዘባነን በፍጹም አይችልም።

 

የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊነት ለወያኔ አገዛዝ

ሀብትን መዝረፍ አመቺ ሁኔታን ፈጥሮለታል !

ወደ ፖሊሲው ተግባራዊነትና አሉታዊ ተጽዕኖ ከመግባቴ በፊት ኒዎ-ሊበራሊዝም ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳቱ በጣም አስፈላጊ ነው። ጽንሰ-ሃሳቡንና ውጤቱን በሚመለከት በሁላችንም ዘንድ የመረዳት ችግር አለ። አብዛኛዎቻችን የአንድን ጽንሰ-ሃሳብ ወይም ፖሊሲ አፀናነስ፣ ማደግና ወደ ተግባር ተመንዝሮ ዓለም አቀፋዊ ባህርይ እንዴት ለመያዝ እንደቻለና፣ የጽንሰ-ሃሳቡን ይዘት ለመመርመርና ከህብረተሰብ ዕድገት ጋር ለማገናኘት ገቱ ስለሌለን ዝም ብለን እንናገራለን። አንዳንድ የፖለቲካ ታጋይ ነን የሚሉ ድርጅቶች ደግሞ በአገራችን ምድር ምን ዐይነት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ እንደተደረገ ሳይመረምሩ የፖለቲካውን ሜዳ በመያዝ የባሰ ውዥንብር ይነዛሉ። አንድን አገር ለመገንባትና እንደማህበረሰብ በፀና መሰረት ላይ ለማቆም ደግሞ የግዴታ  አንድን ጽንሰ-ሃሳብ በሚመለከት የአስተሳሰብ ጥራት መኖር አለበት። አንድ አገር እንደ ህብረተሰብ እንዲገነባ ከተፈለገ ግብዝነትና ፉከራ ወይም ቀረርቶ ቦታ የላቸውም። ለአንድ አገር ግንባታ ዋናው ቁልፍ የሆንኑ ነገሮች ሳይንሳዊ አስተሳሰብና አርቆ-አሳቢነት ብቻ ናቸው  በመሆኑም የያንዳንዱን የፖለቲካ ድርጅት ወይም አክቲቪስት አቋምና ሀቀኝነት ለማወቅ እንደዚሁ የሃሳብ ጥራት ያስፈልጋል። አንድ አገር ሊገነባና ህዝቡም የተሟላ ነፃነት ማግኘት የሚችለው በሳይንስና በፍልስፍና እየተመራ ንቃተ-ህሊናውን ሲያዳብርና ማንነቱን ሲያውቅ ብቻ ነው። በቁጥር እየጨመረ ለሚሄድ ህዝብ ሰፋ ያለ የስራ መስክ ለመክፈት ትናንሽና ማዕከለኛ ኢንዱስትሪዎች ያስፈልጋሉ። እነዚህ ደግሞ በሳይንስና በቴክኖሎጂ መደገፍ አለባቸው። ከተማዎችን በተሟላ መልክ ለመገንባት እንደዚሁ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በጣም አስፈላጊ ናችው።  ለዚህ ሁሉ ደግሞ የተፈጥሮ ሳይንስን ውስጣዊ ምስጢርና የፖለቲካ ኢኮኖሚ ህግን መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው። ካለበለዚያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያሉ መጮህ፣ ወይንም የጊዜው ጥያቄ ኢትዮጵያዊነት ነው እያሉ መናገር ትርጉም የላቸውም። ለሚራብና ለሚጠማ፣ እንዲሁም ነፃነቱ በተቀነባበረ መልክ በውጭና በውጭ ኃይሎች ለተረገጠበት ህዝብ፣  የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚባለውን ነገር የዓለም አቀፍ ኮሙኒቲው በሚባለው የሚወጣና የሚደነገግ ከሆነ ስለኢትዮጵያዊነት ማውራት ምንም ትርጉም አይሰጥም።

በመሰረቱ ኒዎ-ሊበራሊዝም የሚባለው ጽንሰ-ሃሳብ እ.አ በ 1938 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረ ሲሆን፣ ዋናው መሰረቱም የተጣለው በ1880 ዓ.ም ገደማ ነው። ጽንሰ-ሃሳቡን ባፈለቁት ምሁራን አስተሳሰብና ዕምነት መንግስት በኢኮኖሚ ፖሊሲ አማካይነት የገበያውን ተዋንያን ማደናቀፍ የለበትም። ማንኛውም ኢኮኖሚያዊ ክንዋኔና አንድን ህብረተሰብ የሚመለከቱ ጉዳዮች በሙሉ በገበያ ህግ መሰረት መደንገግ አለባቸው። እያንዳንዱ ግለሰብ እንደ ህብረተሰብ አካል የሚታይ ሳይሆን የራሱን ጥቅም ለማሳደግ የሚሯሯጥ ነው። በዚህ ዐይነቱ ግለሰብአዊ ሩጫ የመጨረሻ መጨረሻ ሁሉም ተጠቃሚ ይሆናሉ ይለናል። በአንድ አገር ውስጥ የሚገኝን የተፈጥሮ ሀብት ቁጥጥር ጉዳይና መሬትንም ጨምሮ በኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ አውጭዎች ዘንድ ሁሉም ነገር በገበያ ህግ የሚደነገግ ወይም እንደ ተሰጠ(as given)ተደርጎ ነው የሚታየው። የቤት ወይም የመኖሪያና እንዲሁም የህክምናና የትምህርት ጉዳይ በገበያ ህግ የሚወሰኑ ናቸው። በኒዎ-ሊበራል አስተሳሰብ አንድ አገር እንደ ገበያ መድረክ ስለሚታይ፣ ባህል፣ ግብረ-ገብነትና ስነ-ምግባር ቦታ የላቸውም። የሚያማምሩ ከተማዎችና ጋርደኖች፣ እንዲሁም የባህል መንደሮች በኒዎ-ሊበራል አስተሳሰብ  በግምት ውስጥ የሚገቡ አይደሉም። በመሆኑም ገንዘብ ያለው ብቻ ሁሉን ነገር የሚደነግግበት፣ አንድን ህብረተሰብ እሱ በመሰለው የሚያሽከረክርበት ነው። ደሀና አካለ-ስንኩላት እንዲሁም የደከሙ ሽማግሌዎች  ቦታ የላቸውም። ይህም ማለት የፖሊሲው አውጭዎችና አራማጆች አስተሳሰባቸው ሶሻል ዳርዊኒዝም ወይም አረመኔያዊ አስተሳሰብን(Barbarian Ethos) ያዘለና የፋሺዝም መሰረት ነው። ይህ ዐይነቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው በተለይም ባለፉት አርባ ዐመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ቫይረስ በመስፋፋት አገሮችን የሚያተራምሰውና ለዘራፊ መንግስታት መሰረት በመሆን አንዱ ሌላውን እየፈራ እንዲኖር የተደረገበት ሁኔታ ሊፈጠር የቻለው። በዚህ ዐይነት ህብረተሰብ ውስጥ የመንግስት መኪናዎች፣ ማለትም የሚሊታሪው፣ የፀጥታውና የፖሊሱ የጥቂት ሀብታሞችን ጥቅም ማስጠበቂያ በመሆን በህዝብ ላይ ጦርነት እንዲያካሂዱ ለማድረግ በቅተዋል። ስለሆነም በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ከዘጠና በመቶ በላይ የሚሆን ህዝብ እንደ እንግዳ ወይም እንደ አላስፈላጊና ትርፍ(Redundant) ነገር በመታየት በውጭ ኃይሎች በተቀነባበረና በተቀመጠ አገዛዝ ህልውናውን እንዲያጣ ለመደረግ በቅቷል ማለት ይቻላል። በማዕከለኛውና በላቲን አሜሪካ አገሮች ያለውን አደገኛ ሁኔታና የህዝብ ፍልሰት መመልከቱ በቂ ምሳሌ ነው። ከዚህ በመነሳት ነው በአገራችን ምድር ተግባራዊ የሆነውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ መረዳት የሚቻለው።

የሚያሳዝነው ጉዳይ 27 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ምድር ተግባራዊ በሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይ አንዳችም የፖለቲካ ታጋይ ነኝ የሚልም ሆነ የኢኮኖሚ ምሁር አመርቂ ጥናት ለማቅረብ አልቻለም። እንዲያውም በአብዛኛዎቹ ግንዛቤ የወያኔ አገዛዝ እስከዛሬ ድረስ ተግባራዊ ያደረገው የኢኮኖሚ ፖሊሲ የመንግስት ልማታዊ ፖሊሲና አብዮታዊ ዲሞክራሲ እንጂ ሌላ ነገር አይደለም  እያሉ  ነው ይነግሩን የነበረው። በአገራችን ምድር አፍጦ አግጦ ለታየው ቀውስና አገዛዙን እንዲወድቅ ያደረገው ይኸው በመንግስት የተደገፈ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ በመሆኑ ብቻ ነው ይሉናል። የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲን በሚመለከት ከአስር ጊዜ በላይ በሳይንስና በተነፃፃሪ ትንተና(Comparative studies) ለማረጋገጥና ለማሳመን ቢሞከርም ታጋይ ነኝ ባዩና የኢኮኖሚ ተንታኝ ባዩ አሻፈረኝ በማለት አሁንም ድርቅ በማለት „ወያኔ ሲያራምድ የነበረው በመንግስት የተደገፈ ልማታዊ ፖሊሲ ነው“ እያለ ከሳይንስና ከተጨባጭ ሁኔታዎች ባሻገር ልባችንን ሲያደርቀው ከርሟል። ይህ ዐይነቱ ችኮነትና ፀረ-ሳይንስ አመለካከት ትርጉሙ ሊገባኝ በፍጹም አይችልም።

ያም ሆነ ይህ በካፒታሊስት አገሮች የህብረተሰብ ዕድገት ታሪክ ውስጥ የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንደ ዕድገት መመሪያ ተግባራዊ የሆነበት ጊዜ የለም። ከ14ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ካፒታሊዝም ስር መስደድና መቆናጠጥ እስከጀመረበት እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ ተግባራዊ የሆነውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስንመለከት በመንግስት የተደገፈ ፖሊሲ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል። በተለያየ ዘመናት ወይም ኤፖኮች እንደ ኃይል አሰላለፍ የተለያዩ የአውሮፓ መንግስታት ጣልቃ-ገብ ፖሊሲዎችን በማካሄድ ለካፒታሊዝም ዕድገት፣ ማበጥና ዓለም አቀፋዊ ባህርይን ለመያዝ ዕምርታን ሰጥተውታል። ይህንን በሚመለከት በሺህ የሚቆጠሩ የኢምፔሪካልና የቲዎሪ ጥናቶች አሉ። የኒዎ-ሊበራሊዝምን ፖሊሲ በሚመለከት አሁን በቅርቡ የወጡ ሁለት መጽሀፎችና የቀድሞው የግሪክ የገንዘብ ሚኒስተር የነበሩት ፕሮፌሰር ፋሮፋኪስ እንደሚያረጋግጡት ኒዎ-ሊበራሊዝም የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንዳልሆነና አገርንም ለመገንባት የሚያመች እንዳይደለ ነው። እንደ ሃይማኖት ከመያዙና ከመሰበኩ በስተቀር ሳይንስ እንዳልሆነ ይነግሩናል። ስለሆነም በአውሮፓው የህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ ካፒታሊዝም ሊያድግ የቻለው የተለያዩ ዕውቀቶች፣ ማለትም ፍልስፍና፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የሶስይሎጂና የስነ-ልቦና ዕውቀቶች አንድ ላይ በመጣመራቸውና አንድ ህብረተሰብም እንደ ሁለንታዊ ነገርና እርስ በእርሱ እንደተያያዘ በመታየቱና ግንዛቤ ውስጥ በመግባቱ ነው። አልፎ አልፎ ካፒታሊዝም ፈሩን ሲለቅና ህብረተሰብአዊ ኖርሞች ወደ መላላት ሲያመሩ፣ በተለይም የማህበራዊ ጥያቄዎችና(The Social Question)ባህላዊ ጉዳዮች አትኩሮ እንዲሰጣቸው ከፍተኛና የማያቋርጥ ትግል ይደረግ ነበር። በዚህ መልክ በአውሮፓ ምድር ውስጥ ምሁራዊ ዕድገት፣ በጥልቀትና በሰፊው ማሰብ፣ እንዲሁም አንድ ህብረተሰብ ተከታታይነት እንዲኖረው የማያቋርጥ ትግል ማድረግ እንደባህል የተወሰዱ ናቸው። በሌላ አነጋገር፣ አንድ ህብረተሰብ ወደ ገበያነትና መገባያያነት ብቻ ተቀንሶ መታየት እንደሌለበት በተገለጸላቸው የአውሮፓ ምሁራን ዘንድ ከፍተኛ ግንዛቤ ነበር። ይህ ዐይነቱ ግልጽና ፍልስፍናዊ አስተሳሰብ ግን በኒዎ-ሊበራሊዝም አይሎ መውጣትና በየተቋማቱ ውስጥ በመሰግሰጉና ፓርቲዎችንም በቁጥጥሩ ስር በማድረጉ ካፒታሊዝም ፈሩን ለቆ በመውጣት ብዙ  አገሮችን በማተራመስ ላይ ይገኛል። በተለይም የፋይናንስ ካፒታል የበላይነትን መቀዳጀት ሁሉንም የተፈጥሮ ሀብቶችና ሰውንም ጨምሮ ወደ ተራ ሸቀጣ ሸቀጥነት በመለወጡ የኑሮ ትርጉም ሊበላሽ ችሏል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ጦርነቶች መስፋፋትና መንግስታት ህግን እየጣሱ የሌላውን አገር ህዝብ ማፈናቀልና መበታተን፣ ሌላውን ደግሞ አመጸኛ እንዲሆን ማድረግ ከግሎባል ካፒታሊዝም ጋር በጥብቅ የተያያዘ ነው። ይህ ግልጽ ሲሆን ብቻ ነው በአገራችን ምድር ተግባራዊ የሆነውን የኢኮኖሚ ፖሊሲና ውጤቱን መረዳት የሚቻለው።

ለማንኛውም ወያኔ ስልጣን በያዘ በዓመቱ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው የኒዎ-ሊበራልን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው። በፖሊሲው መሰረትም፣ 1ኛ) የኢትዮጵያን ብር ከዶላር ጋር ሲወዳደር ዝቅ እንዲል ማድረግ(Devaluation)፣ 2ኛ) በመንግስት ቁጥጥር ስር የነበሩትን ወይም የህዝብ ሀብት የሆኑትን ፋብሪካዎችና የንግድ መደብሮችን በሺያጭ ወደ ግል ይዞታ(Privatization) ማዘዋወር፣ 3ኛ) የውጭውን ንግድ ልቅ ወይም ሊበራላይዝ ማድረግ፣ 4ኛ) የመንግስት በጀት ድጎማ በሚደረግላቸው ነግሮች ላይ፣ ምግብ፣ ትምህርትቤትና ጤንነት የመሳሰሉት ላይ በጀቱን መቀነስ፣ 5ኛ) የውስጡን ገበያ በገበያ ህግ  (Demand and Supply)እንዲተዳደር ማድረግ ናቸው የፖሊሲው ይዘቶች። ይህንን ዐይነቱን ፖሊሲ ዴሬጉሌሽን(Deregulation) ብለው ይጠሩታል። በሌላ አነጋገር፣ ኢኮኖሚው እንዳለ ከመንግስት ማነቆ መላቀቅና በገበያ ህግ መሰረት መተዳደር አለበት። ይህ ሲሆን ብቻ ኢኮኖሚው ያድጋል፤ የስራ መስክም ይከፈታል፤ ሰራተኛውም ገቢ ስለሚያገኝ በመግዛት ኃይሉ ለኢኮኖሚው ዕድገት ዕምርታን ይሰጠዋል። በዚያውም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳለ ይፈነጥዛል፣ ወይም በደስታ ዓለም ውስጥ ይኖራል ይሉናል።

የዚህን ፖሊሲ ውጤት ስንመለከት፣ በተለይም የመንግስት ሀብትን ወደ ግል በማዘዋወሩ ላይ ተጠቃሚ መሆን የቻሉት የወያኔ ሰዎችና ከሱ ጋር በጥቅም የተቆላለፉና ትልቁ ኩባንያው ኢፈርት የሚባለው ነበሩ። ስለሆነም የወያኔ ሰዎች ከባንክ በቀጥታ ብድር በማግኘት ካለምንም ነፃ ውድድር የመንግስትን ሀብት በመቀራመትና ስትራቴጂ የኢኮኖሚ ንዑስ-መስኮችን፣ እንደ እጣን፣ ቡናና ሻይ እንዲሁም ሰሊጥና ኑግን የመሳሰሉትን በመቆጣጠር በአጭር ጊዜ ውስጥ የናጠጡ ሀብታሞች ሊሆኑ በቅተዋል። ከዚያም አልፈው የወርቅና ሌሎች በጣም ጠቃሚ የሆኑ ማዕድኖችን በመቆጣጠርና ቆፍሮ እንዲወጣ በማድረግ በከፍተኛ ደረጃ የሀብት ዘረፋ ማካሄድ ችለው ነበር። ከዚህ በተጨማሪ መሬትን በከተማም ሆነ በገጠር ውስጥ በመቀራመትና ህዝቡን በማፈናቀል የኢትዮጵያን ህዝብ ዕድል በእጃቸው ስር ማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን እንደፈለጋቸው ማሽከርከር ችለው ነበር። ይህ በራሱ ልዩ የሆነና በህይወታቸው ያላለሙትን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ስታተስ እንዲያገኙና የተንደላቀቀ ኑሮ እንዲኖሩ አስችሏቸው ነበር። ትላልቅ ቪላ ቤቶችንና መዝናኛ ቦታዎችን በመገንባት ከሌላው የተሻሉ እንደሆኑ ለማሳየት ሞክረዋል። ይሁንና ግን በምሁርም ሆነ በባህል ደረጃ የአስተሳሰብ ለውጥ ማድረግ እንዳልቻሉ፣ እንዲያውም እየናጠጡ በመጡ ቁጥር ጭንቅላታቸው እየታወረና የነገሮችን ሂደት ለመገንዘብ ያልቻሉበት ሁኔታ እንደተፈጠረ ከድርጊታቸው መገንዘብ እንችላለን። በዚህ ዐይነቱ ዐይን ያወጣና ህገ-መንግስቱን፣ የተፈጥሮንና የህብረተሰብን ህግ በሚፃረር የሀብት ዝርፊያ ውስጥ እንደነ አላሙዲን የመሳሰሉት በስለላ ድርጅት ውስጥ የታቀፉ ቱጃሮች በመካተት፣ በአንድ በኩል በሀብት ዘረፋነት ሲሰማሩ፣ በሌላ ወገን ደግሞ ሰፊውን ህዝብ ወደ ድህነትና አቅመ-ቢስነት ገፍትረውት እንደነበር ይታወቃል። በዚያው መጠንም የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል በማባለግ የባህል ውድመት እንዲፈጠር ለማድረግ በቅተዋል።  በዚህ መልክ ለወያኔ ያደሩ ግለሰቦችን በሀብት ዘረፋ ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ አገዛዙ የተወሰነ ደጋፊ ኃይል(Social Base) ለማፍራትና ጭቆናውንና ዘረፋውን ለማስፋፋትና ጥልቀት እንዲያገኝ አመቺ ሁኔታ ፈጥሮለታል። ይህም ማለት በዚህ ዐይነቱ የዘረፋና የአገር አውዳሚነት ሂደት ውስጥ ከተለያዩ ብሄረሰብ የተውጣጡ ግለሰቦችም እንደተካተቱበትና፣ ከውጭ የጥፋት ኃይሎች ጋር በመመሰጣጠርና በመተባበር የአገራችን ሀብት እንዲዘረፍና ህዝባችንም እንዲደኸይ ለመደረግ እንደበቁ ማረጋገጥ ይቻላል።

ይህ ዐይነቱ የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ የተቋም መሰተካከል ዕቅድ(Structural Adjustment Programms) በመባል ሲታወቅ፣ በፕሬዚደንት ሬገንና በወይዘሮ ቴቸር አገዛዝ ዘመን በ1980ዎቹ ዓመታት መጀመሪያ ላይ በታወቀው የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚክስ አራማጅ በሚልተን ፍሪድማንና ጓደኞቹ የረቀቀና የሶስተኛው ዓለም አገሮች ተግባራዊ እንዲያደርጉት የተደነገገ ነው። በአርቃቂዎቹና ኃላፊነትን በተሰጣቸው መሪዎች ዕምነትና ፍላጎት ጠቅላላውን የዓለም ህዝብ በገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ስር በማካተት የአሜሪካንን የበላይነት ማስፈን ነው። ስለሆነም በየአገሮች ውስጥ የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍልና አገዛዞች በዚህ ዐይነቱ ዕቅድ ስር በመካተት፣ በአንድ በኩል ወደ ውስጥ የሀብት ሽግሽግና ዘረፋ በማካሄድ ያልተስተካከለ ዕድገት(Unequal Development) ተግባራዊ ማድረግ ሲሆን፣ ወደ ውጭ ደግሞ ሀብት የሚሸሽበትን ዘዴ ማመቻቸት ነው። ብድርና የተዛባ የውጭ ንግድ ዋናው የሀብት ማዘዋወሪያ መሳሪያዎች ናቸው። በዚህ መልክ ፖሊሲው ከጋና እስከናይጄሪያና ዚምባብዌ ድረስ፣ እንዲሁም በራሺያ ከ1989 ዓ.ም በኋላ ተግባራዊ በማድረግ ለኦሊጋርኪዎች መነሳትና የሀብት መዝረፍ ምክንያት ለመሆን በቅቷል። በእነ ዓለም ባንክና በዓለም የገንዘብ ድርጅት ዕምነት አንድ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከጠቅላላው ህዝብና ከየአገሩ የማቴሪያል ሁኔታ በመነሳት መነደፍ ያለበት ሳይሆን፣ የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል ብቻ መነሻ በማድረግና በዓለም አቀፍ አገዛዝ ሂራርኪ ውስጥ በማስገባት ነው መነደፍና መዋቀር ያለበት። ስለሆነም በየአገሩ ውስጥ ያለ ሰፊ ህዝብ እንደትርፍና(Redundant) ጠቃሚ ያልሆነ ሆኖ ነው መታየት ያለበት። ማንኛውም አገር ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላ ትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ታሪክና ባህል፣ ህብረተሰብአዊ እሴቶችና መተሳሰሮች፣ እንዲሁም ራሱን ወደ ውስጥ የሚመለከትበት ሃይማኖትና ፍልስፍናዊ አመለካከት የለውም። ካለውም ይህንን በሳይንሳዊ ዘዴ መንከባከብና ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ የለበትም። በኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊሲ አራማጆች ዕምነት፣ በአንድ አገር ውስጥ ያሉና በጭንቅላት ውስጥ የተቀመጡ እሴቶችና ሞራላዊ ነገሮች ለገበያ ኢኮኖሚ እንቅፋት ስለሚሆኑ ከጭንቅላት ውስጥ መደምሰስ አለባቸው። የእያንዳንዱ ግለሰብ ጭንቅላት ምንም ነገር እንዳልተጸፈበት ወረቀት(Tabula rasa) በመሆን የገበያ ኢኮኖሚ መርህን በጭንቅላቱ ውስጥ መትከል አለበት። ከዚህ በኋላ እያንዳንዱ ግለሰብ የገበያ ኢኮኖሚ እያለ መጮህና መዝፈን ይጀምራል። ሰራተኛው ጥቅሙን ለማሳደግ ቀና ደፋ እያለ ሲሰራ፣ አሰሪው ደግሞ ትርፉን ለማሳደግ የተለያዩ ዘዴዎች ይፈጥራል። ለዚህ ደግሞ ገንዘብ ማግኘት ዋናው ዓላማ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በባህር ዳርና አዲስ አበባ በተከሰቱ ቀውሶችና በሌሎችም አካባቢዎች በሚታዩ ውጥረቶች ተሸንፈን አገራችንን አንድነት በሚፈታትን ቀውስ ውስጥ እንዳንገባ ሰከን ባለ መንፈስ  እናት ኢትዬጵያን በጋራ እንታደግ!!

በዚህ መልክ ተግባራዊ የሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንደምንመለከተውና እንደምንረዳው የንግድና ሌሎች የአገልግሎት መስኮችን ከማስፋፋትና ዋናው የኢኮኖሚ ዘርፍ ከማድረግ በስተቀር በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ፣ ስርዓት ያለው የኢንዱስትሪ ፖለቲካ(Systematic Industrialization) ተግባራዊ እንዲሆን ያገዘ አይደለም። ስለሆነም አድጓል እየተባለ ብዙ ይወራለት የነበረው ኢኮኖሚ ስራ ለሚፈልገው ሰፊ ህዝብ የስራ መስክ ለመክፈት የቻለ አልነበረም። የአገልግሎት መስኩ ከመንዛዛቱም የተነሳ በአገራችን ምድር የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል ከአዳዲስ የፍጆታ ዕቃዎች ጋር በመለማመድ ልዩ ዐይነት የተዛባ ሞራል ሲከሰት፣ በሌላ ወገን ደግሞ ለቅንጦት ዕቃዎች የሚወጣው የውጭ ምንዛሪ በአገሪቱ የውጭ ንግድ ሚዛን ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደር ችሏል። የውጭው ንግድ ሚዛን በከፍተኛ ደረጃ መዛባትና ብድሩ መቆለልና በተከታታይ ዕዳ ከፋይ መሆን የዚህ ዐይነቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ውጤቶች ናቸው ማለት ይቻላል።

ከዚህ በመነሳት ነው የወያኔን የሀብት ዘረፋና፣ በሀብት ደልቦ በከፍተኛ ደረጃ በአገራችን ምድር ውስጥ የእስራት ዘመቻ ማካሄድ፣ ህዝብን ማሰርና መግደል፣ እስርቤቶች ውስጥ በተለያዩ የማሰቃያ ዘዴዎች ማሰቃየትና አካለ ስንኩላን እንዲሆኑ ማድረግን መረዳት የሚቻለው። የሀብት ዘረፋን ጥልቀትና ስፋት ለመስጠት ደግሞ የግዴታ የመጨቆኛ መሳሪያውንና የስለላ ድርጅቱን በረቀቀ መልከ ማዘጋጀት ነበረበት። ለዚህ ደግሞ ጠቅላላው ሰለጠንኩኝ የሚለው፣ የህግ የበላይነትና የሰብአዊ መብት መከበርን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ እንዲሆን ነው ጥረቴና ትግሌ የሚለው የምዕራቡ ካፒታሊስት ዓለም በስተጀርባው እንደቆመና ማንኛውንም የጭቆናና የስለላ መሳሪያ ያቀርብለት እንደነበር ግልጽ ነው። 27 ዓመታት ያህል የምዕራቡ ዓለም በተለይም የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የወያኔ አገዛዝ የሚያደርገውን የሀብት ዘረፋና ጭቆና እንዲሁም ግድያ የሚያውቀው ነገር የለም ብሎ መናገር በህዝባችንና በታሪኩ ላይ መሳለቅና መቀለድ ነው። ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉና በኮንግረስ አማካይነት እርምጃ እዲወሰድ ቅስቀሳ ማድረግና መለማመጥ የዚህ ዐይነቱ ዐይን ያወጣ ዘረፋና አገር አውዳሚ፣ እንዲሁም ህዝብ ገዳይ ድርጊት ተባባሪ እንደመሆን ነው የሚቆጠረው።

አቢይ አሀመድም ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ከአምስት ዓመት በፊት እስከዛሬ ድረስ ከዚህ ዐይነቱ አገርንና ህዝብን ለመዝረፍ ከሚያመቸው የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ በፍጹም ሊላቀቅ አልቻለም። የዛሬ ሁለት ዐመት ገደማ በአገር ውስጥ በሚያድግ ኢኮኖሚ(Home Grown Economy) አማካይነት ጠቅላላውን ኢኮኖሚ መልክ ማሲያዝ አለብን ተብሎ ዕቅድ ቢነደፍም የዚህ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመሰረቱ አሁንም ቢሆን ኒዎ-ሊበራሊዝም በመሆኑ ይኸው እንደምናየው ህዝባችን በዋጋ ግሽበት፣ በድህነትና በስራ-አጥነት በመሰቃየት ላይ ይገኛል። የአቢይ አህመድና የሺመልስ አብዲሳ አገዛዞች ዐይን ባወጣ መንገድ አዳዲስ የኦሮሞ ወጣቶችን ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ በማድረግና ገንዘብ እየተበተነላቸው ሀብታም እንዲሆኑ በማድረግ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚታየው የሀብት ዘረፋና በአካባቢው የቤቶች መፍረስና ህዝቡ ከቤቱ ተፈናቅሎ መንገድ ላይ እንዲተኛ መደረግ ዋናው ምክንያት ለመሆን በቅተዋል። አንዳንዶቹ በጸጥታው ውስጥ እንዲመለመሉ በመደረግ ነቃ የሚባለውን የህብረተሰብ ክፍል እየተከታተሉ እንዲደበድቡና የማጅራት መቺነት ሚና እንዲጫወቱ ለመደረግ በቅተዋል። በተለይም ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት የአቢይ አህመድ አገዛዝ ወደ ተራ ዘራፊነትና ውንብድና በመሸጋገር የህግ የበላይነትን በመጣስ ኢትዮጵያን እንደፈለገው የሚያሽከረክር ግለስብ ለመሆን በቅቷል። አቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆኖ የተመረጠ ቢሆንም ሶስቱንም የአገዛዝ መዋቅሮች በራሱ ቁጥጥር ስር በማድረግና በመንግስት ላይ መንግስት(Deep State) በመፍጠር በተለይም በአማራው ላይና፣ በአጠቃላይ ደግሞ በጠቅላላው ህዝባችን ላይ አጠቃላይ ጦርነት በማወጅ ህዝባችንን በፍርሃት እንዲዋጥ አድርጎታል። በሰላም እንዳይወጣና እዳይገባ በማድረግ ከስራ እንዲስተጓጎል አድርጎታል። ለማንኛውም ዐይነት ኢኮኖሚያው እንቅስቃሴ እንቅፋት በመሆን ህዝባችንን በተደበቀና በግልጽ በሚታይ ረሃብ እንዲሰቃይ በማድረግ ላይ ነው። ለማለት የሚቻለው በዛሬው ምድር በአገራችን ምድር ፋሺሽታዊ አገዛዝ ሰፍኗል። እንደዚህ ዐይነቱ ህሊና-ቢስ የሆነና ታሪክና ባህል ምን እንደሆኑ የማይገባው ግለሰብ ደግሞ አገርን በማፈራረስና ሀዝብን በመበተን በቀጥታ ለአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና ለግብረአበሮች ነው የሚሰራው ማለት ይቻላል። ህሊና-ቢስ የሆነው የኦሮሞ ኤሊት የሚባለው በመሰረቱ ኢሊት ያልሆነ የወያኔ ካድሬዎችን ቦታ በመተካት ልዩና የተንደላቀቀ ኑሮ በመኖር አገራችንን ምስቅልቅሏን እያወጣት ይገኛል።

የምዕራብ አውሮፓ ካፒታሊስት አገሮችና የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ለምድን ነው ታዲያ እንደዚህ የመሳሰሉ ዘራፊና ህዝብን ጨቋኝና ገዳይ አገዛዞችን አቅፈው ደግፈው ግፉበት የሚሏቸው?  ለምንድ ነው በዕርዳታ ስም በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያፈሱላቸው? ነገሩ ቀላል ነው። ያልተገለጸላቸውና የታሪክ ግንዛቤ የሌላቸው አገዛዞች የዕውነተኛ ስልጣኔ ጠንቅ በመሆናቸው ብቻ ነው። የሳይንስና የቴክኖሎጂን ዕድገት ስለሚቀናቀኑና ዕንቅፋትም ስለሚሆኑ ነው። ሰፋ ያለ በሳይንስና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአገር ውስጥ ገበያ እንዳይገነባ ስለሚያደርጉ ብቻ ነው። በተጨማሪም በራሱ የሚተማመን ኢንደስትሪየስ የሆነ የከበርቴ መደብ ብቅ እንዳይልና ህዝቡ በራሱ ላይ አመኔታ እንዳይኖረው ለማድረግ ነው። ስለሆነም አንድን ህዝብ በዕርዳታ ስም አቅመ-ቢስ ማድረግና ሞራሉን አዳክሞ ለዘለዓለም ተገዢ ማድረግ ዋናው የኢምፔሪያሊስት አገሮች ስትራቴጂና ዓላማ ነው። በዚህ መልክ በአፍሪካ ምድር ውስጥ እንደ ጃፓንና ቻይና፣ እንዲሁም ደቡብ ኮሪያ የመሳሰሉ በራሳቸው የሚተማመኑ አገሮች ብቅ እንዳይሉና ተቀናቃኝ እንዳይሆኑ ጨቋኝና ዘራፊ አገዛዞችን መደገፍና አንድ ህዝብ እንዲበወዝ ማድረግ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና የግብረ-አበሮቹ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው።

በመሰረቱ ይህ ዐይነቱ ሰይጣናዊ አካሂድ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጠበቃ ቆሚያለሁ ለሚለውና እዚህና እዚያ ባንዲራ ለሚያውለበልበው፣ እንዲሁም በየሚዲያው እየተጋበዘ ለጥያቄዎች መልስ የሚሰጥና ለራሳቸውም ጋዜጠኛ ነን ባዮችና የሚዲያ ሰዎች ግልጽ መሆን ነበረበት፡፡ እንደማየው ከሆነ በከፍተኛ ደረጃ የጭንቅላት መደንዘዝ ተስፋፍቷል። በምድር ላይ የሚካሄዱ ነገሮችን የማየት፣ የመመርመርና የመተንተን ችግር አለ። የግሪክ ፈላስፎች እንደሚሉት ጭንቅላት ማየት የማይችል ከሆነ ዐይንም ማየት አይችልም እንደሚሉት፣ በተለይም ምሁር ነኝ የሚባለው የሚሰጠውን ትንተና የሚባል ነገርና ገለፃ ስመለከትና ስሰማ የምረዳው ነገር የቱን ያህል የምሁር ክፍተት እንዳለ ነው የምገነዘበው። ነገሩ በግራና በቀኝ አመለካከት በሚሉት የአወናባጆችና የፋሺሽቶች ስም ማጥፊያ ዘዴ የሚገለጽ ሳይሆን፣ በሳይንስ፣ በቲዎሪና በፍልስፍና መነፅር ብቻ ነው። ችግሩም እዚህ ላይ ነው እንጂ የግራ ናፍቆት ጉዳይ አይደለም። በመሰረቱ የሰው ልጅ የግራና የቀኝ አስተሳሰብ ሊኖረው በፍጹም አይችልም፤ ወይም ደግሞ የግራ ወይም የቀኝ አስተሳሰብ የሚባል ነገር የለም። ሊኖር የሚችለው ሳይንሳዊ ወይም ኢ-ሳይንሳዊ፣ ፍልስፍናዊ ወይም ኢ-ፍልስፍናዊ አመለካከት ብቻ ነው። ሊኖር የሚችለው ልዩነት በራሺናሊዝም ላይ የተመሰረተ ፍልስፍናዊና ሰብአዊ አመለካከት፣ ወይም ደግሞ አርቆ-አሳቢነት የጎደለው፣ አንድን ነገር ነጣጥሎ የሚያይና በነገሮች መሀከል መተሳሰር የሚሉት ነገር የለም ብሎ በሚያምን  መሀከል ብቻ ነው። ባጭሩ በዓለምም ሆነ በአገራችን ምድር የሚካሄደው ትግልና ያለው ልዩነት፣ በአንድ በኩል ሰብአዊነትን በሚሰብኩና በሚያራምዱ፣ እንዲሁም ለኢኮኖሚያዊና ለማህበራዊ እኩልነት(Economic and political justice) በሚታገሉ፣ በሌላ ወገን ደግሞ ባልተገለጸላቸውና ኢ-ሰብአዊነትን በሚያራምዱና በስለላ መረብ ውስጥ በመግባት ህዝባዊ ኃይል እንዲበታተን በማድረግ የድህነቱንና የመፈናቀሉ ዘመን እንዲራዘም ለማድረግ በሚጥሩ ሰይጣናዊ ኃይሎች መሀከል ነው። ከዚህ ስንነሳ ለአንድ ህዝብና ለአንድ አገር ችግር መመርመሪያው ዘዴ ሳይንሳዊ ቲዎሪ እንጂ የግራና የቀኝ አመለካከት አይደለም። ዋናው ቁም ነገር በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ በተለያየ የታሪክ ኤፖክ የሚከሰቱ ህብረተሰብአዊ ግኑኝነቶች፣ ማህበራዊ ችግሮችና የርስ በርስ ግጭቶችን በሳይንስ የመመርመሪያ ዘዴ በመመርመር ብቻ ነው አነሰም በዛም መፍትሄ ለመስጠትና ታሪካዊ አስተዋፅዖ ለማድረግ የሚቻለው። የአንድን ህብረተሰብ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ በጎሳና በሃይማኖት ተሳቦ የሚነሳን ግጭት መረዳት የሚቻለው በሳይንስና በፍልስፍና አማካይነት ብቻ ነው። እንደዚሁም መፍትሄ መስጠት የሚቻለው በሳይንስና በፍልስፍና መሳሪያዎች ብቻ ነው። ስለሆነም በአንድ አገር የሚኖር ግለሰብም ሆነ እንደ ማህበረሰብ የሚቆጠር የሚሆነውን የማይሆነውን ነገር በሚያወሩ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች በመወናበድ ፈሩን እንዳይለቅ መጣር እንጂ ማስፈራሪያ ነገር ጣል እያደረጉ መጠራጠርን በማስፋፋት የባሰውን በህዝብ ዘንድ አለመተማመን እንዲኖር ማድረግ አይደለም የአንድ ምሁር ሚናና ታሪካዊ ተልዕኮ።

ከዚህ በመነሳት በአገራችን ምድር ብቻ ሳይሆን በብዙ የአፍሪካ አገሮችና፣ የማዕከለኛውና የላቲን አሜሪካ አገሮች ያለውን የተዘበራረቀና የጭቆና እንዲሁም የዘረፋ ሁኔታ ስንመለከት በቅርጽ ይለያዩ እንጂ በይዘት አንድ ናቸው። በአገራችንም ሆነ በተለያዩ የሶስተኛው ዓለም አገሮች የተዋቀሩት አገዛዞች በሙሉና፣ የመንግስት የጭቆና መኪናዎች ጭምር ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረው የኃይል አሰላለፍ ውጤቶች ናቸው ማለት ይቻላል። ማንኛውም አገር ቢሆን ከአገሩ ሁኔታ በመነሳትና የአገሩን ህዝብ ፍላጎት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት መንግስታዊ መኪናን ያዋቀረበትና የኢኮኖሚ ፖሊሲን አርቅቆ ተግባራዊ ያደረገበት ጊዜ የለም። በመሆኑም ነው  በአገራችንም ሆነ በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ከውስጥ አለመረጋጋት የሚኖረው፤ ህዝብ የሚጨቆነውና ሌላው ደግሞ የሚሰደደው። ይህንን ነው የምዕራቡ ዓለም የሚያራምደውና በራሳቸው የሚተማመኑ አገዛዞች ካሉ ደግሞ በኩዴታ መልክ እንዲገለበጡ የሚያደርገው። ነገሩ ግልጽ ነው፤

ይህች ዓለም በነጩ የኦሊጋርኪ መደብ መዳፍ ስር መዳሽቅ አለባት፤ በዓለም ላይ ያሉ የጥሬ-ሀብቶች በሙሉ በምዕራቡ  የካፒታሊስት አገሮችና በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ቁጥጥር ስር መዋል ያለባቸው ናቸው። እያንዳንዱ አገርና መንግስት ራሳቸው በመሰላቸው መንገድ ኢኮኖሚ ፖሊሲያቸውን መቀየስ የለባቸውም። በመጀመሪያ ደረጃ የህዝባቸውን መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት የለባቸውም። ከዚያም በኋላ ቀሰ በቀስ ጠቅላላውን ኢኮኖሚያቸውን በሳይንስና በቴክኖሎጂ አማካይነት በመገንባት ጠንካራ ህብረተሰብ መመስረት የለባቸውም።  ጉዳዩ በዚህ መልክ ነው መታየት ያለበት። በዚህ መልክ ማየት የማይችል ወይንም የማይፈልግ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ስለነፃነትና ስለዲሞክራሲ፣ ስለተሟላ ዕድገትና እንዲሁም ስለኢትዮጵያ አንድነት ማውራት በፍጹም አይችልም።

የዕፅ ጦርነትና(Opium War) ጠንቁ በአገራችን ምድር !

የዕፅ ጦርነት(Opium War) በመባል የታወቀው ጦርነት የተካሄደው በ19ኛው ክፍለ-ዘመን ሲሆን መነሾውም እስከዚያ ጊዜ ድረስ በጊዜው የነበረው የቻይና መንግስት የውጭ ገበያውን ለምዕራቡ ዓለም፣ በተለም ለእንግሊዝ ክፍት ባለማድረጉ ነበር። ከ18ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የውጭ ንግድ አስፈላጊ እየሆነ መምጣቱ ሲታወቅ እንግሊዝና ሆላንድ በተለይም የጥሬ-ሀብት ያላቸውን አገሮች ማሰስ ይጀምራሉ። እንደቻይና የመሳሰሉት አገሮች እንደ ሀር፣ ከፖርሴላን የተሰሩ ልዩ ልዩ የቤት ዕቃዎችንና ሻይ ወደ አውሮፓ በመላክና ወደ ውስጥ ደግሞ ገበያቸውን በመቆጣጠራቸው ወይም ክፍት ባለማድረጋቸው የእንግሊዝንና የተቀሩትን የምዕራብ አውሮፓ የውጭ ንግድ ሚዛን ማዛባት ቻሉ። ምክንያቱም እንግሊዝም ሆነ ሌሎች የምዕራብ አውሮፓ አገሮች ከቻይና የሚመጡ ዕቃዎችን ስለሚፈልጉ፣ በሌላ ወገን ደግሞ ቻይና በራሴ ምርት ብቻ መወሰንና ፍላጎቴንም ማሟላት እችላለሁ በማለቷና በሯን በመዝጋቷ  በጊዜው እንደገንዘብ የሚያገለግለው ከብር የተሰራ ገንዘብ ወደ ቻይና በመፍሰስ የእንግሊዝንና የተቀሩትን አገሮች የንግድ ሚዛን ያዛባል። በዚህ የተናደደችው እንግሊዝ የነበራት አማራጭ በአካባቢው አገር ኦፒየምን በማምረትና በተለያየ መልክ በማስገባት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ መፍጠር ነው። ስለሆነም በተለይም በንግድና በጉምሩክ መስሪያ ቤት ተቀጥረው የሚሰሩ ቻይናዎች ኦፒየምን በማጨስ ጥገኛ በመሆናቸው ይህ ጉዳይ ማህበራዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን መፍጠር ቻለ። በዚህ መልክ ቻይና ገበያዋን እንድትከፍት ተገደደች። ይህ ዐይነቱ የኦፒየም ጦርነት በሙዚየም መልክ ቻይና ውስጥ ይታያል።

ወደ አገራችን ስንመጣ ጦርነቱ በዚህ መልክ የተካሄደ ሳይሆን ዘራፊ መንግስትን ስልጣን ላይ በማስቀመጥ በዚያ አማካይነት በተለይም ወጣቱን የዕፅ ሰለባ በማድረግ ለስራ፣ ለፈጠራና ለህብረተሰብ ዕድገት ያለውን ውስጣዊ ፍላጎት ማኮላሸት ነው። በዚህም መሰረት ቀስ በቀስ ህብረተሰቡን በማደንዘዝ አገርን በተለያዩ የኢኮኖሚ መሳሪያዎች መቆጣጠርና የባሰ ማሽመድመድ ነው። ተጨባጩን ሁኔታ ስንመለከት ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በጣም ፈጣን በሆነ መልክ ዕፅ ማጨስና ጥገኛ መሆን፣ ጨአት መቃምና የጨአት መቃሚያ ቤቶች መስፋፋት፣ ለአቅመ-አዳም ያልደረሱ ሴት ልጆች በየመንገዱ እየቆሙ ሰውነታቸውን እንዲሸጡና በተለያዩ የአባለ-ዘር በሽታዎች እንዲለከፉ ማድረግ፣ የአስረሽ ምችው ቦታዎች መስፋፋትና የአልክሆል ሱሰኛ መሆን፣ የተለያዩ ሃይማኖት የሚመስሉ ነገሮች በመግባት ህብረተሰቡን ግራ ማጋባት… ወዘተ፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የተስፋፉትና ህበረተሰብአዊ እሴቶች ሊበጣጠሱ የቻሉት በአገዛዙና በውጭ ኃይሎች በተቀነባበረ ሴራና ጦርነት በሚመስል በሚካሄድ ሂደት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ የዕርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ነን የሚሉና የአረብ ነጋዴዎች የተከፈተላቸውን አመቺ ሁኔታ በመጠቀም በአገራችን ብዙም የማይታወቅ በወንዶች መሀከል የሚካሄድ የወሲብ ግኑኝነት እንዲስፋፋ በማድረግ የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል እንዳለ ሊበላሽ ችሏል። በዚህም ምክንያት የደርግ አገዛዝ ስልጣን ላይ እስከቆየበት ጊዜ ድረስ በኤይድስ ቫይረስ የተለከፈው የህብረተሰብ ቁጥር ከአንድ በመቶ በታች ሲሆን፣ ወያኔ ስልጣን ከያዘ በኋላ በኤይድስ ቫይረስ የተለከፈው ህዝብ ቁጥር ወደ 5% በመቶና ወደ 7% ሊያድግ ችሎ እንደነበር ስታትስቲክሶች ያሳያሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ቀደም ብለው በብዛት ያልተስፋፉ በሽታዎች፣ እንደ ልብ በሽታ፣ ስኳርና የጉበት በሽታዎች በመስፋፋት ህብረተሰብአዊ ቀውስ ሊፈጠር ችሏል። በተለይም ቆሻሻ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በመግባታቸውና በየቦታው በመጠላቸውና ስለሚጣሉም ገንዝብ ለማግኘት የሚፈልገው ወጣት ለጤንነት አደገኛ የሆኑ የማዕድን ውጤቶችን በሚፈልግበት ጊዜ ወዲያውኑ ለአደጋ ይጋለጣል። እንደምንከታተለው ከሆነ በተለይም ወጣቱ በዚህም ሆነ በሌላ ምክንያት ካለ ዕድሜው በልብ በሽታ እንዲጠቃ ተደርጓል። ከዚህም ባሻገር የወጣቶችን ኦርጋን መሸጥ እየተለመደ መጦ እንደነበር ይታወቃል።

ይህ ማለት ምን ማለት ነው? አንድ ህብረተሰብ በዚህ መልክ ሲወጠር የማሰብ ኃይሉ እንዳለ ይደመሰሳል። ዕውነትን ከውሸት ለመለየት የማይችልበት ሁኔታ ስለሚፈጠር አገሩን ለወጭ ኃይሎች ክፍት በማድረግ ራሱንና አገሩን ይሸጣል። ዶላርና ኦይሮ እንደብርቅ በሚታዩብት አገር ውስጥ ደግሞ አንዳንዱ ልጆቹንም እስከመሸጥ ይደርሳል። ዋናው ነገር ሆድ መሙላቱ ላይ ስለሆነ አብዛኛው ህዝብ በዚህ መልክ ህብረተሰብአዊ እሴቱ እንደሚበጣጠስበት አይረዳም። በተለይም የነቃ ምሁራዊ ኃይል በሌለበትና ሁሉም በየፊናው በሚሯሯጥበት አገር ውስጥ ያልተማረው ሰፊ ህዝብ የሚደረገውንና ሌላው የሚያደርገውን ነገር በቅጡ ለማገናዘብ አይችልም። በዶላርና በዕፅ ናላው የዞረው የህብረተሰብ ክፍል የሀፍረት ገበና የሚባለው ነገር ከጭንቅላቱ ተሟጦ ስለጠፋ ማንኛውንም እሴትንና ባህልን የሚጥሱ ነገሮች ሁሉ ከማድረግ አይቆጠብም። በአጭሩ ጭንቅላቱ ስለደነዘዘ ሞትንም እንደቁም ነገር ስለማይወስድ ዛሬ የተደረገውን ነገር ወዲያውኑ ይረሳል። ጭቆናንና መሰደድን፣ ሴት ልጆችን ወደ አረብ አገር በመላክ ገንዘብ ማግኘት እንደተራ ነገር ስለሚታዩ አንድ ሰው ማድረግ ባለበትና  በሌለበት መሀከል ያለውን ልዩነት ስለማይገነዘብ አንድ ህብረተሰብ መጨፈሪያና ቀስ በቀስ ደግሞ ወደ ጦር አውድማነት ሲለወጥ ዝም ብሎ ይመለከታል። በዚህ መልክ የአንድ ህብረተሰብ የሞራል ኮምፓስ የሚሉት ነገር እንዳለ ይደመሰሳል። ህብረተሰቡ ወዴት እንደሚጓዝ፣ ከየት እንደመጣና ለምንስ በዚህች ዓለም ላይ እንደሚኖር ስለማይገነዘብና ታሪካዊ ሚናውንም ስለማይረዳ ጮሌዎችና አገር አከረባባቾች እየመጡ ሲበውዙት ዝም ብሎ ይመለከታል። በራሱ የሚተማመንም ዜጋ ስለሌለና እንደዚህ የመሳሰሉትን ህብረተሰብን ጎጂ የሆኑ ነገሮች ለጥያቄ ስለማይቀርቡና ስለማይጠኑም ሁኔታው ስር እየሰደደና በቀላል የህክምና ዘዴ ለማከም የማይቻልበት ሁኔታ ይፈጠራል። አቢይ አህመድና ግብረ-አበሮቹ ስልጣንን ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ይህንን ሁኔታ ለማረምም ሆነ ለማስወገድ የወሰዱት እርምጃ በፍጹም የለም። እንዲያውም ሁኔታው እንዲባባስ አመቺ ሁኔታዎችን እየፈጠሩ ነው። እነ አቢይ አህመድ ከአማራው ጋር እልክ ስለተጋቡና አገራችንንም ለመበታተን ቀና ደፋ ስለሚሉ እንደዚህ ዐይነት መንፈስን የሚያዳክምና የሚያደነዝዝ ነገር ሊያስከትል የሚችለውን ህብረተሰብአዊ ጠንቅ የመከታተል ፍላጎትና ዕውቀትም የላቸውም። ምሁራዊ ብቃትነትም ስሌላቸው ስለአገርና ስለመጭው ትውልድ ዕጣ ደንታ የላቸውም። ሰው መሆናቸውንም ስለማይገነዘቡ አገርና ህዝብ፣ እንዲሁም ታሪክ መስራት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስለማያውቁ አዕምሮን የሚያደነዝዝ ዕፅ ተስፋፋ አልተስፋፋ፣ ብልግና ተስፋፋ አልተስፋፋ፣ ወጣት ልጆች አካላቸውን ሸጡ ወይም አልሸጡ ለእነሱ ደንታ የሚሰጣቸው ጉዳይ አይደለም። በጭንቅላታቸው ውስጥ ማንኛውም የስው ልጅ ሊኖረው የሚገባው ባህርዮች በሙሉ ተሟጠው ያለቁ ወይም አብሮአቸው ያልተፈጠሩ በመሆናቸው የሚሰሩትን የሚያውቁም አይመስሉም። ስለሆነም ከእነዚህ ዐይነት ሰዎች ቁም ነገር መጠበቅ አይቻልም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ምን አገባኝ!” እና “ምን አሳጣኝ ብዬ!” ያሳጡን ዕድሎች - ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ከዚህ ስንነሳ በግልጽ ከሚታየው ጦርነት ይልቅ የአገራችንን ህልውና የበጣጠሰውና ለማስተካከልም የሚችግረው ይህ ዐይነቱ በረቀቀ መልክ የሚካሄድ የኢምፔሪያሊስቶች የዕፅ ጦርነትና፣ የወያኔ፣ አሁን ደግሞ የአቢይ አህመድና  አንዳንድ ለአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ያደሩ ኃይሎች መንገድ አመቻችነት ነው። ይህንን ጦርነት ለመዋጋትና ህብረተሰቡን በአዲስ አስተሳሰብ አንጾ ጠንካራ አገር ለመገንባት የግዴታ ጠንካራና በራሱ የሚተማመን መንግስት መመስረት ያስፈልጋል። ዛሬ በአገራችን ምድር የመንግስትን መኪና በመቆጣጠር ህዝባችንን ፍዳውን የሚያሳየውን፣ ግልጽ የሆነና ግልጽ ያልሆነ ጦርነት የሚያካሂደውን አገዛዝ አስወግዶ በሌላና ለአገር ተቆርቋሪና በተገለጸለት ኃይል መተካት የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው። በመቀጠልም የመንግስቱን መኪና ከዳተኞች፣ ከተንኮል ሰሪዎችና በህዝብ ላይ አሿፊዎች ከሆኑ ኃይሎች በማጽዳት በአዳዲስና በነቁና ለህዝብ ታዛዥና ለአገር ተቆርቋሪ በሆኑ ኃይሎች መተካት ያስፈልጋል።  ከዚህም ባሻገር ለህብረተሰቡ አለኝታ የሚሆን የተገለጸለትና ነገሮችን በግልጽ የሚናገር ደፋርና የታሪክን አደራ ለመቀበል የተዘጋጀ ምሁራዊ ኃይል መፍጠር እጅግ አስፈላጊ ነው። በህብረተሰብ የግንባታ ታሪክ ውስጥ እንደተረጋገጠው በአንድ አገር ውስጥ በልዩ ልዩ ዕውቀት የታነፀና የዳበረ ምሁር ብቻ ነው መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው። አብዛኛውን ጊዜ ስልጣን ላይ ቁጥጥ የሚሉ ኃይሎች በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የሚካሄዱ ነገሮች ስለማይታያቸውና፣ በተለይም በአሁኑ ዘመን በውጭ ኃይሎች ስለሚታለሉ ወይም በእነሱ መረብ ውስጥ ስለሚገቡ አንድን ህብረተሰብ ወደ ውስጥ ጠጋ ብሎ የመመልከት ኃይል የላቸውም። በመሆኑም በሶስዮሎጂ፣ በፍልስፍና፣ በህሊና ሳይንስና በተፈጥሮ ሳይንስ የሰለጠኑ ምሁራን ተከታታይ ጥናት በማድረግ ህብረተሰቡ በቀናና ዕድገት አጋዥ በሆነ መስመር ላይ እንዲጓዝ የማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነት አለባቸው።

አገራችንን ከረቀቀ ጦርነት ወደ ግልጽ ጦርነት ውስጥ የመክተት ስትራቴጂ!

ህወሃት የዛሬ አምስት ዓመት ገደማ ወዶ ሳይሆን ተገዶ ስልጣኑን እንዲለቅ ከተደረገ በኋላ፣ እንደገና ስልጣን ላይ ለመመለስ ባለው ፍላጎት የተነሳ በአሜሪካኖች በመመከርና በመታገዝ በሰሜኑ ዕዝ ጦር ላይ በተኙበት ጦርነት በመክፈት ወደ ስምንት መቶ የሚጠጉ፣ በተለይም ከአማራውና ከደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል የመጡ አገር ወዳድ መኮንኖች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ እንዲገደሉ ለመደረግ በቅተዋል። በተለይም በአማራው ክልል የተደራጀው የአማራው ልዩ ኃይልና ፋኖዎች በወሰዱት የመከላከልና የማጥቃት እርምጃ በፌዴራሉ ወታደር በመታገዝ የወያኔን ኃይል ሶሶት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሊያዳክሙትና ሊበታትኑት ችለዋል። ይሁንና ግን በዚያ በመቀጠልና ወያኔ እንዳያንሰራራ አስፈላጊውን የማጠናቀቅ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የአቢይ ወታደር መቀሌንና አካባቢውን ጥሎ በመውጣት ለወያኔ እንደገና እንዲያንሰራራ አመቺ ሁኔታን ሊፈጥረልት ችሏል። ወታደሩም ትግሬ ውስጥ የሚቆጣጠራቸውን ቦታ ለቆ ሲወጣና ሲያፈገፍግ ለወያኔ በብዙ ሺሆች የሚቆጠሩ ቀላልና ከባድ መሳሪያዎች ትቶለት እንደሄደ ግልጽ ነው። በዚህም ምክንያት የተነሳ ወያኔ ራሱን እንደገና ለማደራጀትና ለማስታጠቅ በመቻሉ ወረራ ከፍቶ በወሎ፣ በአፋር፣ እንዲሁም በተወሰነው የጎንደር መሬት ላይ ጦርነት በመክፈት በሰዎች ላይ ከፍተኛ እልቂት ሲፈጽም፣ እንዲሁም ከብቶችን በመዝረፍና ሀብት በማውደም፣ ወደ ትግሬ ሊወስድ የሚችለውን በመዝረፍ፣ በዘመተባቸው ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ አሮጊቶችንና ህፃናትን በመድፈር ለከፍተኛ የህሊና ቀውስ ዳርጓቸዋል። ይሁንና የኢትዮጵያ ወታደር፣ ፈኖዎችና የክልሉ ኃይል በሚያጠቁበት ጊዜ ከአራት ኪሎ በሚተላለፍ ቀጭን ትዕዛዝ እንዲያፈገፍጉ በመደረግ ወያኔ እየዳገገመ በአካባቢው ኗሪ፣ በተለይም፣ በወሎና በአፋር ህዝብ ላይ መጠነ-ሰፊ የሆነ ጭፍጨፋና የሀብት ውድመት አድርሷል። ይህ ዐይነቱ ወንጀል የተፈጸመው ሆን ተብሎ በአቢይ አህመድ በራሱና በሚሊታሪው ውስጥ በተሰገሰጉ፣ እንዲሁም ደግሞ ወያኔን ናፋቂ በሆኑ አንዳንድ የአማራ ካድሬዎች አማካይነት ነው። ወያኔ እየደጋገመ በህዝባችን ላይ በከፈተው ጦርነትና ባደረሰው ዕልቂት አሜሪካን በሱዳን በኩል የጦር መሳሪያ በማስገባት የጭፍጨፋውና የውድመቱ ተባባሪ ለመሆን በቅቷል። የሚሰጠውም ድጋፍና ጦርነቱም እንዲቀጥል የተፈለገበት ዋናው ምክንያት ሌላ ሳይሆን ወያኔን እንደገና ስልጣን ላይ መልሶ በማምጣት የኢትዮጵያ ህዝብ ስነ-ልቦናው ተዳክሞ እንደገና እንዳያንሰራራና የኢትዮጵያንም የተትረፈረፈ ሀብት ለመዝረፍ ነው። ባጭሩ ወያኔ ያካሂድ የነበረውና ዛሬም የሚያካሄደው ጦርነት የውክልናና የቅጥረኝነት ጦርነት በመሆኑ በጠቅላላው አገራችንና ህዝባችን ላይ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው የአፍሪካ ህዝብም ላይ ያነጣጠረ ለመሆኑ የማይካድ ሀቅ ነው።

ከዚህ ሀቅ ስንነሳ በአሜሪካኖችና በሳውዲ ድጋፍ የወያኔን ቦታ እንዲተካ የተደረገው በአቢይ አህመድ የሚመራው ኦነግ የተባለ የወንበዴዎች ስብስብ መሪ ዋና ዓላማውም የህዝቡንና በተለይም የወጣቱን ስነ-ልቦና በመሰረሰር ቀስ በቀስ የተወሰነውን የኢትዮጵያን ግዛት በራሱ ስር በመጠቅለል፣ እንደ ወልቃይት ጠገዴ የመሳሰሉትን በሀብት የተትረፈርፉ ቦታዎች  ደግሞ ለወያኔ በመተው ኢትዮጵያን ለመበታተንና የማይሸርበው ተንኮል ይህ ነው አይባልም። የአቢይ አህመዱ የኦነግ አገዛዝ ይህን ዓላማውን ለማሳካት በተደጋጋሚ በፋኖዎች ላይ ጦርነት በመክፈት በብዙ ሺሆች የሚቆጠሩትን እስር ቤት በመክተት ሲያሰቃይ ከርሟል። ለዚህ እርኩስ ድርጊቱ ተባባሪ የሆኑት ደግሞ የአማራን ህዝብ እንወክለዋለን የሚሉት የክልሉ መሪዎች ናቸው። በሌላ ወገን ደግሞ ሺመልስ አብዲሳ ኦነግ ሸኔ የሚባለውን ፋሺሽታዊ ቡድን በማስታጠቅና ተባባሪ በመሆን በወለጋ ውስጥ በሚኖ´ሩ የአማራ ተወላጆች ላይ እጅግ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች አካሂዷል፤ እያካሄደም ነው። ዋና ዓላማቸውም ኦሮሚያ ብለው በሚጠሩት በወረራ ከያዙት ቦታ እንዳለ አማራውን ለማጥፋትና በራሳቸው ቁጥጥር ስር ለማድረግ ነው። እነ ሺመልስ አብዲሳ የተፈጥሮንና የህብረተሰብን ህግ በመጣስ ቢያንስ ክልላችን ነው ብለው በሚጠሩት ቦታ ሰፋ ያለ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴና ዕድገት እንዳይኖር ለማድረግ በቅተዋል። በዚህ ዐይነቱ አካሄዳቸውም የፖለቲካ ኢኮኖሚን መሰረተ-ሃሳብ ጥሰዋል ማለት ይቻላል። ምክንያቱም በአንድ አካባቢም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሊመጣ የሚችለው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሲሳተፉበትና የስራ-ክፍፍል ሲዳብር ብቻ ነው። በአንድ ወጥ ብሄረሰብ ሁለ-ገብ የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት ሊፈጠር በፍጹም አይችልም። በታሪክና በአገሮች የኢኮኖሚ ግንባታ ሂደትም ውስጥ ታይቶ በፍጹም አይታወቅም። የየአገሮችን የሁለ-ገብ የኢኮኖሚ ግንባታ ታሪክ በምንመረምርበት ጊዜ አንድ አገር በተሟላ መልክ ሊገነባ የሚችለው ከተለያየ አካባቢ በፈለሱና ዕውቀታቸውን ባጋሩና ባስተባበሩ ግለሰቦች አማካይነት ብቻ ነው። ከአንድ ብሄረሰብ ብቻ በተውጣጣ አንድ አካባቢም ሆነ አገር ያደጉበትና የህዝቦቻቸውን ችግሮች የቀረፉበት ጊዜ  በታሪክ ውስጥ አልታየም።  የእነ አቢይ አህመድና የሺመልስ አብዲሳ አካሄድ የሚያመቸው ለጥሬ-ሀብት ዘረፋ ብቻ ነው። ሳይሰሩ በቀላሉ መደለብም የሚያመቸው ይኸኛው መንገድ ብቻ ነው የሚታያቸው። ይህ ሁሉ የሚያረጋግጠው አቢይ አህመድና ሺመልስ አብዲሳ፣ እንዲሁም የተቀረው የኦሮሞ ኤሊት ደንቆሮዎችና ከዕውቀት የራቁ መሆናቸውን ነው። በዚህም አስተሳሰባቸውና ድርጊታቸውም እንወክለዋለን የሚሉት የኦሮሞ ተወላጅ አደንቁረውና አድኸይተው ብቻ ነው የሚያልፉት።

አቢይ አህመድና ሺመልስ አቢዲሳ እንዲሁም ያረጀ አስተሳሰብ ያላቸው የኦነግ ሰዎች ይህ ሁሉ አልበቃ ሲላቸው እንደተከታተልነው ቀደም ብለው የጀመሩትን የእርቶዶክስ ሃይማኖትን የማዳከም ስትራቴጂ እንደገና በልዩ መልክ በማፋፋም ሃይማኖትን ለመስንጠቅ ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ። በዚህም የተነሳ ከፍተኛ ቁጣን በመቀስቀስ ውዝግብና አለመረጋጋት እንዲፈጠሩ አደረጉ። ዋና ዓላማቸውም የኦርቶዶክስን ሃይማኖት ከማዳከም ባሻገር አማኙን ህዝብና ጠቅላላውን አገራችንን እረፍት መንሳትና በጭንቀት ዓለም ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ ነው።  ይህ ጉዳይ ሙሉ በሙሉ አልሳካ ሲላቸው ደግሞ የአማራውን ክልል ለማዳከም ሲባል በተለይም የክልሉ ልዩ ኃይል መፍረስና በፌዴራሉ ውስጥ መካተት አለበት የሚል እጅግ አደገኛን መንገድ መከተል ጀመሩ። አቢይ አህመድ በክልሉ ባሰማራው ጦርና በተከፈተው ጦርነት የተነሳ በአንዳንድ ቦታዎች እየተመከተ ቢመለስም ቀላል ነው የማይባል ጉዳት አድርሷል። የክልሉንም ህዝብ ለሌላ ጭንቀት በመዳረግ በሰላም አርፎ እንዳይሰራና እንዳይኖር አድርጎታል። በሌላ ወገን ደግሞ ወያኔ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ እየተዘጋጀ ነው። ጌታቸው ረዳ መሬታችንን ማስመለስ አለብን እያለ እየፎከረ ነው። በአሜሪካን አቀነባባሪነትና አማካሪነት አቢይ አህመድ በገባው ቃል ቂዳን አማካይነት ወልቃይትና ጠገዴን ለወያኔ መልሶ ለመስጥት ያለው አማራጭ የአማራውን ህዝብ ጭንቅት ውስጥ በመክተት ኃይሉን ማዳከም ነው። ለዚህ ደግሞ የክልሉን ልዩ ኃይልና ፋኖዎችን መበተን አለበት፤ ትጥቃቸውን መፍታት አለባቸው። ይህም የሚያረጋግጠው አቢይ አህመድና ወያኔ የሚያካሄዱት ጦርነት የአሜሪካና የግብረ አበሮቹ ጦርነት ለመሆኑ የማይታበል ሀቅ ነው። ለዚህ ሁሉ ያለው አማራጭ በተባበረ ክንድ እነዚህን ቅጥረኛ ኃይሎች ማስወገድና ለፍርድ ማቅረብ ብቻ ነው። ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለባቸው። ዋናው ዓላማቸው አገርን መበታተን ስለሆነ ከእነሱ ጋር በመቀመጥ ሰላም ይመጣል ብሎ ማሰብ አላዋቂነትን ብቻ  የሚያረጋግጠው።

 

መደምደሚያ !

አገራችንና ህዝባችን ዛሬ ከገቡበት ጭንቀት፣ መፈናቀልና መገደል ለማላቀቅ ከተፈለገ በአገራችን ምድር በማንኛውም መልክ የሚገለጽ ጦርነት በውስጥና በውጭ ኃይሎች የተቀነባበረ መሆኑን መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው። ባለፉት አርባ ዐመታት በህዝባችን ላይ የተከፈተው ጦርነት የተለያየ ስምን በመያዝ የሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያውያን የአሜሪካንና የተቀረው የኢምፔሪያሊስት ኃይሎች ቅጥረኛ በሆኑ ኃይሎች አማካይነት ነው። ለማሳየት እንደሞከሩት ጦረነቱ በድብቅና በግልጽ የሚካሄድ ሲሆን፣ የውስጥ ኃይሎች የጦርነቱ አራማጅ በመሆን  ለአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ተባባባሪ ለመሆን የበቁት የታሪክና የባህል ንቃተ-ህሊና ስሌላቸው ነው። አንድ አገር በስንትና ስንት ልፋት እንደተገነባና፣ ስንት መስዋዕትነት እንደተከፈለበት ለመገንዘብ ባለመቻላቸው  ይቅርታ ሊደረግለት የማይችል የታሪክ ወንጀል ሰርተው አልፈዋል፤ ዛሬም እየሰሩ የሚገኙ ጥቂት የማይባሉ ኃይሎች አሉ። በተለይም እናቶቻችንና አባቶቻችን የአደረጉትን ተጋድሎና አገርን ለመገንባት ያበረከቱትን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ለመረዳት ባለመቻላቸውና፣ የኢትዮጵያን ታሪክ በአስከፊ መልክ ብቻ በመጻፍ፣ ወይም ደግሞ በተጨቋኞችና በጨቋኞች መሀከል የነበረ ትግል አድርጎ በመቀነስ በተለይም ወጣቱን ትውልድ ለማሳሳት በቅተዋል። በህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ የሰው ልጅ ንቃተ-ህሊናው በየጊዜው እንዲሻሻል ከተፈለገ የግዴታ በዕውቀት መደገፍ እንዳለበት ያልተገነዘቡ ኃይሎች እናቶቻችንና አባቶቻችን በሰሯቸው ታሪካዊ ነገሮች ላይ በመዝመት ይኸው እንደምናየው አገራችን በዛሬው እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ ውስጥ እንድትገኝ ለማድረግ በቅተዋል። የተለያየ ስምን ይዘው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችም ሆነ ለአገራችን እንቆጫለን የሚሉ  በሙሉ ራሳቸውን እየደጋገሙ ለመጠየቅና ስራቸውን ለማገናዝብ የሚያስችል በቂ ዕውቀት ስለሌላቸው እየደጋገሙ የታሪክ ወንጀል ሲሰሩ ይታያሉ። ከዚህ ዐይነቱ መደናበርና የግንዛቤ እጦት ለመላቀቅ ከተፈለገ በየጊዜው አስተሳሰብን ማደስ ያስፈልጋል። ከአዳዲስ ዕውቀቶች ጋር መተዋቅ ያስፈልጋል። ሌላውን ብቻ ወንጀለኛ አድርጎ ከመቁጠርም መዳን የሚቻለው የራስንንም ሚና ወደ ኋላ ዞር ብሎ መመርመር ከተቻለ ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ ሳይንሳዊ ዕውቀት(Scientific Knowledge) እጅግ አስፈላጊ ነው።

ሌላው ለግንዛቤ እጦት፣ በአርቆ-አሳቢነትና በሳይንስ ላይ ለሚደረግ ውይይት እንቅፋት የሆነው ትልቁ መሰናክል አንዱ ሌላውን በጥርጣሬ ዐይን ስለሚያየውና፣ ከመጀመሪያውኑ እንደ ዋና ጠላቱ አድርጎ ስለሚገነዘብ ነው። ለዚህ ዋናው ምክንያት ደግሞ ጭንቅላትን ክፍት የሚያደርግ፣ ራሳችንን እንድንጠይቅና ሰው መሆናችንን እንድገነዘብ ከሚያስችል ዕውነተኛ ዕውቀት ጋር ባለመተዋወቃችን፣ ወይም ደግሞ በፍጹም ጥረት ለማድረግ ስለማንፈልግ ነው። እንደሚታወቀው በዛሬው ወቅት በየአገሮች ውስጥ  በተለይም ስልጣንን ለመያዝ በሚሽቀዳደሙ ኃይሎች ዘንድ ያለው አለመግባባትና በህዝብ ላይ በተለያየ መልክ የሚካሄድ ጦርነት ዋናው ምክንያት ጭንቅላት በተበላሸ ወይም ስንኩል በሆነ በተራ የአካዳሚክስ ዕውቀት ስለተቀረጸ ብቻ ነው። ታላቁ ፈላስፋ ፕሌቶ እንደሚለን በአንድ አገር ውስጥ በፖለቲካው መስክና በአንድ ህዝብ መሀከል ያለው አለመግባባትና ለጦርነትም ዋናው ምክንያት በተሳሳተ ዕውቀት ጭንቅላት ሰለሚቀረጽ ብቻ ነው። ስለዚህም የትግሬና የኦሮሞ ኤሊቶች አማራውንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን አምርረው የሚጠሉት እነዚህ ሁለቱ ኃይሎች በታሪክ ውስጥ ለአገራችን ያደረጉትን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ለመረዳት በፍጹም ባለመቻላቸው የተነሳ ነው። አማራውንም ሆነ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ጠልቶ፣ ወይም እንደዋና ጠላት አድርጎ የሚቆጥር ኃይል ደግሞ በእነዚህ ኃይሎች ትብብር የተፈጠረውን ባህላዊ ክንዋኔዎች በሙሉ  መጥላትም አለበት።  ሂትለር ካለበቂ ምክንያትና ምርምር በይሁዲዎች ላይ እንደዘመተውና፣ በተለያየ መልክ የሚገለጸውን ህብረተሰብአዊ ቀውስና እንደተስቦ በሽታ የመሳሰሉትን፣ የኋላ ኋላ ደግሞ ለሶሻሊስት አብዮት መቀስቀስ ይሁዲዎችን ተጠያዊ አድርጎ እንደዘመተባቸውና ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉትን እንደጨረሰ ሁሉ፣ የተግሬና የኦሮሞ ፋሺሽታዊ ኃይሎች በአማራው ወገናችንና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ በመዝመት ቁጥራቸው የማይታወቁ ሰዎችን ጨርሰዋል። በጊዜው ሂትለር ያልገባውና ያልተገነዘበው ነገር የጀርመን ዕድገት፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ መመንጠቅ፣ በሊትሬቸር ማበብ፣ ለክላሲካል ሙዚቃ መስፋፋትና፣ ከዚያም በኋላ የባንክና የንግድ እንቅስቃሴ በጥብቅ ከይሁዲዎች ከፍተኛ አስተዋፅዖ ጋር የተያያዘ መሆኑን ነው። በሌላ አነጋገር፣ ጀርመን በ19ኛው ክፍለ-ዘመንና በ20ኛው ክፍለ-ዘመን እንግሊዝን ቀድማ ለመሄድ የቻለችው እንደ አነስታይን የመሳሰሉ አዋቂ ሰዎች በመፈጠራቸው ነው። ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ደግሞ፣ በተለያየ ምክንያት የተነሳ የኢትዮጵያ ዕድገት ባለበት እንዲቀር ቢደረግም፣ ከባህል አንፃር ስንነሳ በፊዩዳሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰሩት ክንዋኔዎች በሙሉ በአማራው ብሄረሰብ አማናካይነት ነው። የኋላ ኋላ የሌሎች ብሄረሰቦች አስተዋፅዖ ሲታከልበት ዕምርታን ለማግኘት የቻለውም ዋናው መነሾ በሰሜኑ የፊዩዳሉ ኢትዮጵያ ግዛት ነው። የአማርኛ ቋንቋ በጥራትም ሆነ በስፋት ማበብና የሰፊው ህዝብ መነጋገሪያ ቁንቋ መሆን፣ የእርሻ ሙያ መስፋፋት፣ የተለያዩ የምግብ ዐይነድቶችና እንደጠላና ጠጅ፣ እንዲሁም ካቲካላ የመሳሰሉ የባህል መጠጦች በሙሉ ወደድንም ጠላንም ከአማራው፣ ከኦርቶዶክስ ሃይማኖትና ከፊዩዳሊቱ ኢትዮጵያ ጋር በጥብቅ የተያያዙና ቀስ በቀስ እያሉ በማደግ የሌላውም ብሄረሰብ መጠቀሚያ ለመሆን የቻሉት የሚያረጋግጠው የባህልን ውስጣዊ.-ኃያልነት ነው።

ከዚህ ሃቅ ስንነሳ የኦሮሞና የትግሬ ኤሊቶች አማራውን እንደዋና ጠላትና እንደ ጭራቅ የሚያዩበት ምክንያት ግልጽ የሆነላቸው አይመስልም። የድንቁርናቸው ሰለባ በመሆን በተለይም በአማራው ወገናችን ላይ የሚያካሂዱት ጦርነት ዋናው ምክንያት በዝቅተኛ ስሜት በመወጠራቸው እንደሆነ መረዳት ያለባቸው ጉዳይ ነው። የዝቅተኝነት ስሜት የሚሰማው ሰው ወይም ቡድን ደግሞ ፍቱን መፍትሄ ስለማይገኝለት ያለው አማራጭ ጦርነትን እያካሄደና ህዝብን እየጨፈጨፈ በዚያው መቀጠል ብቻ ነው። በዝቅተኛ ስሜት የተለከፈ ኃይል ደግሞ የውጭ ኃይሎች መሳሪያ በመሆን የጦርነቱንና የስቃይን ዘመን ያራዝመዋል ማለት ነው። ስለሆነም ይህንን ጉዳይ በግልጽ መወያየትና በጋራ ለመታገል መነሳት የጊዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። መልካም ግንዛቤ!!

 

fekadubekele@gmx.de

www.fekadubekele.com

 

https://www.youtube.com/watch?v=hmu3qdtH7LE

https://www.youtube.com/watch?v=09maaUaRT4M&t=362s

 

 

1 Comment

  1. ለዘመናት የአፍሪቃ ችግር በተለይም የምሥራቅ አፍሪቃ ግጭትና ረሃብ በአሜሪካ መሪነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚፈጸሙ በደሎች ናቸው ያልነው ያለ መረጃ አልነበረም። ሰሚ ግን የለም። በቅርብ ካመለጠው የፔንታጎን ሚስጥርም የምንረዳው በይፋ የሚናገሩትና በውስጥ የሚያምኑበትና የሚከተሉት የውጭ ፓሊሲዎች ጭራሽ አብረው እንደማይሄድ ነው። ለዓለም ዪክሬን እያሸነፈች ነው በማለት ምድሪቱ አመድ እንድትሆን እያስደረጉ በሚስጢር ደግሞ ውጊያው የጅሎች እንደሆነ አምነው ተቀብለዋል። ይህ ግጭት የተነሳውም በአሜሪካ መሰሪ ፓሊሲ ነው። ዪክሬን ከራሽያ ስትለይ ያኔ የታጠቀችውን የኑክሌርና የረጅምና የቅርብ የአውሮፕላን ሃይሎች በዘይት ለራሺያ እንድትለውጥ ያደርጉት አሜሪካኖች ናቸው። ያ ትጥቅ ዛሬ ከዪክሬን ጋር ቢሆን ኑሮ ረጅም ድላ ባይመቱበት ያስፈራሩበት እንዲሉ ጦርነቱ እዚህ ደረጃ ላይ ባልደረሰም ነበር። የአሜሪካ አላማ አንድ ነው። በዪክሬንና በራሺያ ጦርነት ራሺያን አዳክሞ ከቻይና ጋር ለመፋለም ነው። ሌላው የማታለያ ብልሃት ነው።
    ወደ እኛዋ መከረኛ ሃገር ስንመለስ ደግሞ ለ 27 ዓመት ወያኔ እልፍ ግፍ ሲሰራ እንዳላዪ ሆነው የኖሩት ወያኔ የእነርሱ ተላላኪና ጉዳይ አስፈጻሚ ስለሆነ ነው። አሜሪካኖች ወያኔ በክፋቱ ከጀርመኑ ናዚ እንደማይተናነስ ገና በረሃ እያለ ጭምር ያውቃሉ። ለዚህም በየጊዜው በዘመናት መካከል በግል ያነጋገርኳቸው የድሮና የዛሬ ባለስልጣኖች እማኝ ናቸው። ይህ የማይፈታ እንቆቅልሽ የሆነው የሃበሻው ህዝብ ገመና አሜሪካኖች ለራሳቸው ጥቅም ያኔም ዛሬም የሚያነድት እሳት እንደሆነ አሁን ላይ ዓለም ሁሉ የገባው ይመስለኛል። በቅርቡ አቶ ጌታቸው ረዳና ሌሎች በሰላም ጎን ቆመው ሲሸለሙ ማየት ምን ያህል አፍሪቃውያን በሰላም ስም ግፍ እንደምንሰራ ያመላክታል። ከአንድ ሚሊዪን በላይ ህዝብ እንዲያልቅና ይህ ነው የማይባል መፈናቀልና ውድመት እንዲሁም ዘረፋ የፈጸሙ ሃይሎችን መድረክ ላይ አስቁሞ መሸለም አሳፋሪ ነው። የጠ/ሚሩ መንግስትም ሆነ የኦሮሞ ክልል መሪዎች አሁን ከወያኔ ጋር ቂጥ መግጠማቸው ጊዜአዊ ግርግር እንጂ ዘለቄታዊነት የለውም። የአሜሪካ የአፍሪቃ ዲፕሎማቶችና ባለስልጣኖች ወደ አዲስ አበባና ወደ መቀሌ የሚሯሯጡትም ለራሳቸው እቅድና ፕላን እንጂ ለትግራይ ህዝብ ጨንቋቸው አይደለም። ዓለምን በአበዳሪ ባንኮች ወጥረው የያዙት እነዚህ ሾተላዪች ለጥቁር ህዝብ በጭራሽ የማይገዳቸው ጭራቆች ናቸው። ያለፈም ሆነ የአሁን ታሪካቸው የሚያሳየው ይህኑ እውነት ነው። እንዳትሞትም እንዳትድንም የነቀዘ ስንዴአቸውን በልዪ ልዪ የተራዶ ስም እያፈሰሱ ሰውን የዝንተ ዓለም ተመጽዋች ማድረጋቸው ከቅዳቸው አንድ ነው። የትላንቱንና የዛሬውን ረስተው ዛሬን ብቻ ደስ ብሎዋቸው ለመኖር ደፋ ቀና የሚሉ ሁሉ የቀን አልቃሽ እንደሚሆኑ ከአሁኑ መተንበይ ጠንቋላ አይሆንም። እልፍ እያለቀሰ ዳንኪራ ጊዜአዊ ነውና። እነዚህ የቁም ሙታኖች የተጋቱት የዘርና የቋንቋ ፓለቲካ ጢምቢራቸውን ስላዞረው ተማሩ አልተማሩ ልዪነት የላቸውም። ልክ እንደ እንቁራሪት አንድ ሲጮህ አብሮ መጮህና ቀን በጎደለባቸው ላይ ሰቆቃና መከራን ማዝነብ ሙሉ ስራቸው ሆኗል።
    ባጭሩ በአረብና በነጭ እሳት አቀባዪች እየተገፋን ያኔም እናረግ እንደነበረው አሁንም በከፋ ሁኔታ በአፓርታይዷ ኢትዮጵያ መገዳደላችን ቀጣይና የማያባራ ነው። በሁለት ኮፊያ ለባሾች በሱዳን የተቀሰቀሰውም ጦርነት በዚህም በዚያም ነዳጅ እየተርከፈከፈት ምሥራቅ አፍሪቃን ሳያቋርጥ ያናውጣታል፡፡ ችግራችን የዘርና የቋንቋ ፓለቲካ ነው። የውጭ እጅም የሚገባው ይህኑ ቀዳዳና ሃይማኖትን ተገን አርጎ ነው። ተመድ ስለ አፍሪቃ ያወጣውን የገመና ዘመን ግምገማ ለተመለከተ ከ 50 በላይ ከሚጠጉት ሃገሮች 45 አስቸኳይ ድጋፍ ያሻቸዋል ይልና ከዚህም የሃበሻዋ ምድር፤ ኤርትራ፤ ሱማሊያና ሱዳን በደረጃ ተቀምጠዋል። የጠራ ጭንቅላት ላለው ይህ ጉዳይ ያንገፈግፋል። መቼ ነው ህዝባችን በልቶና እፎይ ብሎ የሚኖረው? እስከ መቼ ነው በውጭ እርዳታ ድጋፍ የሚኖረው? ይህ ለምን ለድህነቱ መንግስት ግልጽ እንዳልሆነለት አይገባኝም። የጠ/ሚሩ መንግስት የቱንም ያህል ለወያኔ ቢያጎበድድም በምንም መንገድ እነርሱን ሰላማዊ አድርጎ የትግራይ ህዝብ ደህንነትና ሰላም ይጠበቃል ብሎ ማሰብ ቀበሮን የበጎች እረኛ እንደማድረግ ይቆጠራል። ወያኔ ከጸጉር እስከ እግራቸው ጥፍር በተንኮል የተዋቀሩ፤ በደም የተነከሩ ናቸው። ለዚህም ነው ከኦሮሞ አፍራሽ ሃይሎችም ዛሬ ላይ ቂጥ የገጠሙት፡፡ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል ሂሳብ። ግን ተመልሰው መፋለማቸው አይቀሬ ነው። ፓለቲካና ፓለቲከኞች እንደሚያልፍ ጥላ ናቸውና። የጊዜን መምሽት አይመለከቱም። የራሳቸውን ድሎትና ተድላ እንጂ። ሳያስቡት ይናዳሉ/ይገዳደላሉ። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share