ዐምሐራ ይግደለኝ!!!
“”””””””””””””””””””””””””’ ‘
ማተቡን አጥባቂ፣በሃይማኖቱ የጸና
የሰው የማይፈልግ፣ኩሩና ቆፍጣና
ዐምሐራ ይግደለኝ፣የሀገር ዋልታ ካስማ::
ተዋርዶ ተራቁቶ፣ግፍም ተሰርቶበት
እየተሳደደ፣እየተዘረፈ፣እየተገደለም
ጠላቱን መርጦ እንጂ፣ንጹሐን አይነካም::
መሠልጠን እንዲህ ነው፣ክፉ ደግ መለየት
መሸሽና መራቅ፣ከቅጥፈት ከጥፋት::
ዐምሐራ እንዲ ነው፣ፈጣሪን ሚፈራ!!
በቂም ተነሳስቶ፣በጅምላ ተንጋግቶ
በከብት እንስሳቱ፣በሳር ቅጠሉ ላይ
ሴጣናዊ ተግባር፣ወንጀል የማይሠራ::
~***•°•***•°•***~
ዐም:- ሕዝብ ሐራ:- ሐርነት፣ነፃነት
ዐም ሐራ:- በፈጣሪው የሚያን፣በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ለማንም የማይገዛ “ነፃ ሕዝብ” ማለት ነው::
ለዐምሐራ ሃይማኖታዊ
ሥነ ምግባራዊ ጨዋነት
መዘከርያ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,,,,,,
ጥቅምት ፳፯/፳፻፲፬ ዓ.ም
November 06/2021
ቅዳሜ )4:46(ዋናው ፓስታ ቤት/አ.አ
©ያመጌዕ