April 10, 2023
6 mins read

የፖለቲካ ትግልን ከግብ ለማድረስ የትግሉን አላማ የተረዳ፤ በራሱ የተማመነ፤ ህዝብን የሚያደራጅና የሚያታግልና ብሎም ለመስዋትነት የተዘጋጀ መሪ መኖር አለበት

Leader 1 1 1

እንደሚታወቀው ብአዴናውያን ወደ  ኢህአዴግ ፖለቲካ ከ1984 ዓም ጀምሮ አባል የሆኑት የራሳቸውን ጥቅም ብቻ በማስላት ነው፡፡ የፖለቲካ አላማ ገብቶአቸው አይደለም፡፡ በራሳቸው የተማመኑ አይደሉም፡፡ የአቅም ውስን ያለባቸው የወያኔዎችን ትዕዛዝ ብቻ የሚቀበሉ ነበሩ፡፡ ወያኔ መራሹ መንግስት ተወግዶ የኦሮሙማው መንግስት ስልጣል ላይ ሲወጣ አይናቸውን በጨው ታጥበው ኮታቸውን ገልበተው በልጽገናል ሲሉ ለህዝብ ሲባል እስከመሰዋዕተነት ሊታገሉ ሳይሆን ከርስ የመሙላት አላማቸውን ለማሳካት ነበር፡፡ ባለፉት አምስት አመታት በአማራ ላይ ግፍ ሲደርስ የፓረቲ ውስጣዊ ትግል በማድረግ ችግሮችን ሲያስተካክሉ አላየነም፡፡ ይልቁንስ ሎለነታቸውን አጸኑት እንጂ፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት ልዩ ሀይል እንዲፈርስ የብልግና ስራ አስፈጻሚ ከሚቴ ወሰነ የሚል መረጃ ከማህበራዊ ሚዲያዎች ሰማን፡፡ እንደመረጃዎቹ ከሆነ አንድም የስራ አስፈጻሚ አባል አልተቃወመም፡፡  ምክንያቱም ለይስሙላ ስራ አስፈጻሚ አባላት አሉ ይባል እንጂ ማንኛውም  ነገር በጭራቅ አህመድ እንደሚወሰን ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ውሳኔው ውሉ ሳይድር በመጣደፍ በቆማቸው የሞቱ በአዴናውያን ከላይ በወረደላቸው ትዕዛዝ ለማፍረስ ተንቀሳቀሱ፡፡ ለምን፤እንዴት፤መቼና ሌሎችም ጥያቄዎች እንዳላነሱ በስብሰባው ላይ ከነበሩ ሰዎች መረዳት ይቻላል፡፡ ልዩ ሀይሎች መፈረስ  በመርህ ደረጃ ተቀባይነት እንዳለው በበኩሌ እስማማለሁ፡፡ ምክንያቱም ከሌሎች አገሮች ተሞክሮ ሳይሆን ከትህነግና ኦሮሚያ ልዮ ሃይሎች ተሞከሮ የሰላም ጠንቆች መሆናቸው ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ትህነግ በ3 ዙር በአማራና በአፋር ክልል ህዝብ ላይ የማይረሳ  ዘግናኝ ግፍ ፈጽሞአል፡፡ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል የኦነግ ሰራዊት ብሎ ራሱን የሚጠራ አረመኔ ቡደን  የአማራን ህዝብ በጅምላ ሲጨፈጭፍ ለመከላከል ሳይሆን ዋና የጅምላ ግድያው ተዋናይ ነበር፡፡

339748900 160017223653443 5546421025620999721 n 2 1 1

ይሁንና የብልግና ስራ አስፈጻሚ ውሳኔ የሁሉንም ክልል ልዩ ሀይሎች ማስፈታት ሳይሆን ድብቅ አላማው የአማራ ክልል ልዩ ሀይልና ፋኖ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ጭራቅ አህመድ የኦሮሞን ጥቅም የምታስቀድም አገር ለመገንባት የሚያደርገውን ምናባዊ እንቅስቃሴ ተግባራዊ ለማድረግ ተግዳሮት ይሁኑብኛል ብሎ ከፈረጃቸው መካከል አማራ ስልሆነ ነው፡፡ በቂ ምክክር ሳይደረግበትና የልዩ ሀይል አባላት እንዲሁም ህዝብ  ሳያምንበት በመከላከያ ሰራዊት ከበባ አድርጎ ትጥቅ ማስፈታት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለሽፋን ብአዴን እንዲያስፈጸም ተደርጎአል፡፡ አበባው ታደሰ፤ ግርማ የጅብጥላ (ዋና የኦሀዴድ ተላላኪ) ና የመረጃና ደህንነት ዳሬክተር ተብየው (ትጉው )  በሃላፊነት እየመሩት እንደሆ በግልጽ እያየን ነው፡፡ እኒህ ሰዎች በስርዓቱ ሀብት ክፍፍል ውስጥ ገብተው የራሳቸውን ጥቅም እንጂ የህዝብ ደህንነት ጉዳያቸው አይደለም፡፡

339335692 1298744800989991 1883147134541045752 n 1 1

ሰሞኑን በልዩ ሀይሉ መፍረስ ምክንያት በክልሉ የህዝብ ቁጣ ሲገነፍል፤ በስራ ቦታቸው ላይ ሆነው የህዘብን ስሜት በማዳመጥ ማስተካከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ሲንቀሳቀሱ አይታዩም፡፡ የክልሉ ፕሬዜዳንት ተብየው እንቅልፋሙ ይዘቅጣል ዝቅአለ በፕሮፖጋንዳ ሚዲያው ከቀበሌ ቤት ውስጥ ይሁን ሌላ የተሰነጣጠቀ ቤት ውስጥ ተቀምጦ መግለጫ ሰጥቶአል፡፡ መግለጫው አለቃው ጭራቅ አህመድ ሥጥ ብሎ የጻፈለት ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ጭራቅ አህመድ በፌስቡኩ ላይ ከጻፈው ዝባዝንኬ መልክት ልዩነት የለውም፡፡ ለዚህም ነው ነው ብኤዴናውያን በየጊዜው ስያሚያቸውን እየቀየሩ የራሳቸውን ጥቅም እንጂ ህዝብን አስበው አያውቁም፡፡ ለሌሎች መሳሪያ በሆን የአማራን ሰቆቃ ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ አደርገዋል፡፡ ስለሆነም የአማራ ህዝብ በብአዴ የተሰበሰቡ ህሊና ቢሶች እስካሉ ድረስ  እየደረሰብህ ያለው ግፍ አይፈታም፡፡ ስለሆነም ወደሌሎች ጣትህን አትቀስር፡፡ ውስጣዊ ትግል ያስፈልጋል፡፡

ከበሐይሉ ምንይልክ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop