ዳልቻ እና መጋላ – ያሬድ መኩሪያ

ሀገር ሙሉ እንክርዳድ፣ቅጥ ያጣ ቆሻሻ
እንዴት ብሎ ይለያል፣እንዴትስ ይጸዳል
ቢለቀም ቢንጓለል፣ቢበጠር ቢነፋ::
ቅርፊት ብቻ አይቶ፣ቡጡ ሳይነካ
በሰለ ይባላል ወይ፣ውስጥ ውስጡን የቦካ::
መልሰው መላልሰው፣የስህተትን መንገድ እየደጋገሙ
ማበድ ጨርቅ መጣልን ነው፣ለውጥን ማለሙ::
ዝም አይነቅዝም ብሎ፣አዋቂው ሲለጎም
ደፋርና ዐይን አውጣው፣መሪው ሆነ መቅድም::
ዳልቻ መጋላ፣መጋላ ዳልቻ የተደባለቀ
ግልጽና ቀጥታ፣አንዱን መንገድ ሳይዝ
እስከሚነቃበት፣ያው በተለመደ፣በቀየሰው ፍኖት
እያወናገረ እያወናበደ፣ትንሽ ጋት ዘለቀ::
       ~***°•***°•***~
የመሪነት የርዕዮት መንገዳቸው
ለዳመነ ለተዥጎረጎረ ቡሬ ለሆነ
ከፊት ተሰላፊዎች
መዘከርያ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ጥር ፲፮ /፳፻፲፬ ዓ.ም
January 24/2022
ሰኞ)02:44(ዊንጌት/አ.አ
©ያመጌዕ
ተጨማሪ ያንብቡ:  ያልደረሱትን እረሳን! - በላይነህ አባተ

1 Comment

  1. ምድረ አራጅ አመዱ ቡን አለ ቀጥሎ ጁዋር መሃመድ እጁ እግረ ሙቅ ሳይገባ ወደ አገሩ አሜሪካ ይገባል አቶ መራራ ጉዲናና በቀለ ገርባም አብሮ የኖረ ህዝብ ነው የሚለውን ነጠላ ዜማ ይለቃሉ፡፡ እነ አቶ ዳንኤል ክብረት የት ይገቡ ይሆን?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share