መፀለይ አሁን ነው ! – አሸናፊ ዋቅቶላ፣ ሕ/ዶ -የውስጥ ሕክምና ባለሙያ March 18, 2023 ግጥም Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ቋንቋው በረከተ ፣ መግባቢያው ቀነሰ፣ አንባጓሮ በዛ፣ ማዳመጥ አነሰ፣ ወጣት ጯሂ ሆነ፣ ባዛውንቱም ባሰ፣ አማኝ ነኝ የሚለው፣ እዚያም ያልደረሰ፣ ሁሉም ዓለም ይላል፣ዓለም ዓለም ዓለም! ከራሱ በስተቀር፣የሚያስብ ግን የለም። ~ዘመኑ ጨለመ ፣ ተስፋ መነመነ፣ መፀለይ አሁን ነው፣ ያመነ ያላመነ! መነጋገር ቢኖር፣ ባለከፋ ነበረ፣ በመጯጯህ ብዛት፣ ሁሉም ደነቆረ፣ ያጓራል ለብቻው ፣ ያጓራል በጋራ፣ ቁልቁል እየሮጠ፣ ትውልድ ሆኖ ተራ፣ ያራዳ ጎርምሳ ቤተ-እምነት ዘለቀ፣ ቀዳሽ አስቀዳሹም፣ ማዋከብ አወቀ፣ ~ ዘመኑ ጨለመ ፣ ተስፋ መነመነ፣ መፀለይ አሁን ነው፣ ያመነ ያላመነ! ሕዝብን ሜዳ ጥሎ፣ ብር እያሳደደ፣ ተው ባዩ ጠፋና፣ ባንድላይ አበደ፣ ወርቅ ሰላም ሞልቶ፣ በሁሉ ሰው ቤት፣ የብር ግርግር፣ ከተተው አዘቅት፣ ሞላጫው ዘራፊ፣ ምኑንም ሳያውቅ፣ ፈላስፋ ሆነብን፣በጊዜ መድርቅ። ~ ዘመኑ ጨለመ ፣ ተስፋ መነመነ፣ መፀለይ አሁን ነው፣ ያመነ ያላመነ! አሸናፊ ዋቅቶላ፣ ሕ/ዶ -የውስጥ ሕክምና ባለሙያ ሲልቨርስፕሪንግ ሜሪላንድ- ዩ ኤስ ኤ ማርች 18፣ 2023 Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በህወሓት ተመረጡ Next Story ከግርማ የሺጥላ ጋር የተሰዳደቡት ባለስልጣን ተባረሩ | በደሴ ተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ