March 11, 2023
14 mins read

አቶ ልደቱ አያሌው፤ ፖለቲከኛ ወይስ ፖለቲካ ተንታኝ?

ፖለቲከኛ ማለት የስልጣን ወይም ሌላ ግብ ያለው፣ ይህን ግቡን ለመምታት እስካስቻለው ድረስ ደግሞ ማናቸውንም ፖለቲካዊ ዘዴ ለመጠቀም የማያቅማማ የፖለቲካ ሰው ማለት ነው፡፡  በሌላ አባባል ፖለቲከኛ ማለት ለዱቄቱ እንጅ ላፈጫጨቱ የማይጨነቅ፣ ፖለቲካዊ መርሑ የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጨው (the end justifies the means) የሆነ የፖለቲካ ሰው ማለት ነው፡፡

ለምሳሌ ያህል ጭራቅ አሕመድ የተዋጣለት ኦነጋዊ ፖለቲከኛ ነው፡፡  የጭራቅ አሕመድ ኦነጋዊ ግብ ደግሞ የአማራን ሕዝብ እና አማራዊ ናት የሚላትን ጦቢያን ድምጥማጧን አጥፍቶ ባማራ ሕዝብና በጦቢያ መቃብር ላይ የኦሮሞን አጼጌ (empire) መገንባት ነው፡፡  ወደ ግቡ ማምራት የሚችለው ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆነ ነው፡፡  ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን የሚችለው ደግሞ ጦቢያን የሚወደው ያማራ ሕዝብ በነቂስ ከደገፈው ብቻ ነው፡፡  ስለዚህም ያማራን ሕዝብ በማታለል ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ሲል ብቻ፣ የሆዱን በሆዱ ይዞ፣ አምረሮ የሚጠላትን ጦቢያን አበክሮ አወደሳት፡፡  የሚጠላውን በማድረግ የሚወደውን አገኘ፡፡  የሚወደውን ከያዘ በኋላ ደግሞ የያዘውን በመጠቀም የሚጠላውን ለማጥፋት ቆርጦ ተነሳ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ፖለቲካ ተንታኝ ማለት ሊተገበሩ መቻል አለመቻላቸው ላይ ሳይጨነቅ የተለያዩ የፖለቲካ ሐሳቦችን በስፋት የሚተነትንና ባማራጭነት የሚያቀርብ የፖለቲካ ሰው ነው፡፡  በሌላ አነጋገር የፖለቲካ ተንታኝ ሲባል የፖለቲካ ተዋሪ (theorist) እንጅ የፖለቲካ ተግባረኛ (practicalist) አይደለም፡፡  የፖለቲካ ተዋሪ በመሆኑ ደግሞ ይበልጥ የሚያተኩረው ለሰሚው በሚያስደሰቱ፣ ነባራዊ ሁኔታወችን ያላገናዘቡ በመሆናቸው ግን ሊተገበሩ በማይችሉ ተምኔታዊ (utopian, idealist) የፖለቲካ አማራጮች ላይ ነው፡፡  ስለዚህም የፖለቲካ ተንታኝ ሥራ በየሚዲያው እየቀረበ ስለ ፖለቲካና ፖለቲከኞች መተንተን እንጅ፣ ፖለቲካዊ ተከታዮችን አፍርቶ የፖለቲካ ትግል በማደረግ ከፖለቲካዊ ግብ መድረስ አይደለም፡፡

በዚህ ረገድ ስናየው አቶ ልደቱ አያሌው የፖለቲካ ተንታኝ እንጅ ፖለቲከኛ አይደለም፡፡  አንድም ፖለቲካዊ ተከታይ ሊያፈራ ያልቻለውም ፖለቲካዊ ሐሳቦቹ ነባራዊ ሁኔታወችን ያላገናዘቡ በመሆናቸው ምክኒያት ወደ ምድር ወርደው ተግባራዊ በመሆን ሕዝብን በነቂስ ማነሳሳት የማይችሉ ባዶ ሐሳቦቸ በመሆናቸው ነው፡፡

አቶ ልደቱ አንድም ፖለቲካዊ ተከታይ ስለሌለው ምንም ፖለቲካዊ አቅም የሌለው የፖለቲካ ተንታኝ ነው፡፡  ጭራቅ አሕመድ ደግሞ አያሌ ፖለቲካዊ ተከታዮች ስላሉት ከፍተኛ ፖለቲካዊ አቅም ያለው ፖለቲከኛ ነው፡፡  ስለዚህም አቶ ልደቱ አያሌው ጭራቅ አሕመድን “ግልጽ ደብዳቤ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር” እያለ በሚያሳፍር ሁኔታ ከመለማመጥ በስተቀር በምንም መንገድ ሊገዳደረው አይችልም፡፡

አቶ ልደቱ የፖለቲካ ተንታኝ እንጅ ፖለቲከኛ ላለመሆኑ ከቅንጅት አብዮት በላይ ምስክር የለም፡፡  የቅንጅት አብዮት የመጀመርያው ዋና ግብ የጦቢያን ነቀርሳ (ወያኔን) መንቀል ነበር፡፡  ስለዚህም አቶ ልደቱ ፖለቲከኛ ቢሆን ኖሮ፣ ከግቡ ላይ ብቻ አተኩሮ፣ የነ ዲባቶ (doctor) ብርሃኑን ሸፍጥ ለጊዜው ችላ ብሎ፣ ወያኔን ለመንቀል ማድረግ የነበረበትን ሁሉ አድርጎ፣ መፈረም የነበረበትን ሁሉ ፈርሞ ግቡን ይመታ ነበር፡፡  ወያኔን ከነቀለ በኋላ ደግሞ እነ ዲባቶ ብርሃኑን ቀስ በቀስ በማራገፍ ቅንጅትን ከኢሕአፓ ሸፍጠኞች ሙሉ በሙሉ አጽድቶ፣ በራሱ እጅ አስገብቶ፣ በራሱ መንገድ ሊቀርጸው ይችል ነበር፡፡  ይህን ማድረግ ባይችልም እንኳን፣ ወያኔን ለመንቀል ያንበሳውን ሚና በመጫወቱ ብቻ የጦቢያና የጦቢያውያን ዘላለማዊ ጀግና ይሆን ነበር፡፡  አቶ ልደቱ ግን ግብ ያለው ፖለቲከኛ ሳይሆን ግብ የሌለው የፖለቲካ ተንታኝ ስለሆነ፣ ዓይኑን በወያኔን ላይ ከማድረግ ይልቅ እነ ብርሃኑ በሚፈጽሙበት ተራ ሤራ ላይ አድርጎ፣ እነ ብርሃኑን የጎዳ መስሎት የቅንጅትን አብዮት በማክሸፍ የኢትዮጵያን ሕዝብ በእጅጉ ጎዳ፣ የጦቢያ ሕዝብ ደግሞ ዓይንህን ላፈር አለው፡፡

በሌላ በኩል ግን ጭራቅ አሕመድ እንደ አቶ ልደቱ ግብ የሌለው የፖለቲካ ተንታኝ ሳይሆን ግብ ያለው ፖለቲከኛ ነው፡፡  ግቡ ደግሞ ወያኔን ጥሎ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ኦነጋዊ አጀንዳውን ማስፈጸም ነው፡፡  ስለዚህም ሙሉ ትኩረቱ በግቡ ላይ ስለሆነ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር እስከሚሆን ድረስ ኦነጋዊ አጀንዳውን በጽኑ ከሚቃረኑት ከነ ዶክተር አምባቸው ጋር በመተባበር በነሱ ወሳኝ ደጋፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ፡፡  ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆነ በኋላ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱ የሰጠውን ከፍተኛ ኃይል ተጠቅሞ እነዲባቶ አምባቸውን ረሽኖ አስወገዳቸው፡፡

በመድገም አጽንኦት ለመስጠት ያህል፣ አቶ ልደቱ ግብ ያለው ፖለቲከኛ ሳይሆን ግብ የሌለው የፖለቲካ ተንታኝ ነው፡፡  ባለመታደል ግን አቶ ልደቱ ራሱን የሚያየው እንደ ፖለቲካ ተንታኝ ሳይሆን እንደ ፖለቲከኛ አድርጎ ነው፡፡  አቶ ልደቱ ራሱን እንደ ፖለቲካ ተንታኝ ሳይሆን እንደ ፖለቲከኛ ማየቱ የሱ የራሱ ጉዳይ ስለሆነ እኔን አያስጨንቀኝም፡፡  እኔን የሚያስጨንቁኝ አቶ ልደቱን እንደ ፖለቲካ ተንታኝ ሳይሆን እንደ ፖለቲከኛ እየተመለከቱ፣ ያቶ ልደቱን ሊተገበሩ የማይቸሉ ፍሬከርስኪ ሐሳቦች እንደ ዋና ፖለቲካዊ አማራጭ የሚወስዱ የዋህ አማሮች ናቸው፡፡  እነዚህ የዋህ አማሮቸ ሙሉ ትኩርታቸውን የሚያደርጉት ሊተገበሩ በማይችሉት ያቶ ልደቱ ተምኔታዊ ሐሳቦች ላይ ብቻ ስለሆነ፣ ከወሬ በቀር ምንም መተግበር አይችሉም፡፡  ስለዚህም አቶ ልደቱ ራሱን እንደ ፖለቲካ ተንታኝ ሳይሆን እንደ ፖለቲከኛ አድርጎ በማቅረብ፣ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ የዋህ አማሮች ወያኔንና ኦነግን በወሬ ብቻ እንጅ በተግባር እንዳይታገሉ እያደረጋቸው ነው፡፡

በዚህ ረገድ ሲታይ፣ አቶ ልደቱ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላቶች የሆኑትን ወያኔንና ኦነግን በቀጥታም ባይሆን በተዛዋሪ የሚያግዝ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት ነው፡፡  በተለይም ደግሞ አቶ ልደቱ ከተደበቀበት እየወጣ በወያኔና በኦነግ ሚዲያወች ላይ በመቅረብ ትንታኔውን የሚተነትነው ያማራ ሕዝብ ትግል በተግባራዊ መንገድ ተቀጣጥሎ ወያኔንና ኦነግን ሊያቃጥላቸው ሲል ነው፡፡  ይህን ስታዝብ ደግሞ ያቶ ልደቱ ሙሉ ጥረት የአማራን ሕዝብ ውጤታማ ትግል አቅጣጫ በማስቀየር፣ ምንም ውጤት ወደሌለው ወደ ወሬ ትግል መለወጥ ይመስልኛል፡፡  አቶ ልደቱ እነ ጃዋርና ደብረጽዮንን ለመሰሉት ፀራማራ ጽንፈኞች የሚሰጠውን ከፍተኛ ክብር፣ እነ ፕሮፌሰር አሥራትን ጨምሮ ያማራ ብሔርተኞች ናቸው ለሚላቸው ሰወች የሚያሳየውን ግልጽ ንቀትና ጥላቻ ሳስተውል ደግሞ፣ የግለሰቡን ማንነት በተመለከተ ወደማልፈልገው ድምዳሜ ሳልወድ በግዴ አመራለሁ፡፡  ያማራ የሕልውና ጠላቶች የሆኑትን ወያኔንና ኦነግን በበጎ ዓይን እየተመለከተ፣ በእከክልኝ ልከክልህ መንፈስ ያማራን የሕልውና ትግል ሊያግዝ የሚችለውን የኤርትራን መንግሥት ነክሶ መያዙ ደግሞ ድምዳሜየን ያጠናክርልኛል፡፡  ባጠቃላይ ደግሞ ግለሰቡ ከወያኔና ከኦነግ በላይ አማራን የሚጠላ፣ ስምንቱን አስቀምጦ አንዱን የሚያጫውት ዘጠኝ ልበኛ ጽንፈኛ ይሆን እንዴ የሚለው ሐሳብ ውልብ እያለብኝ ይከነክነኛል፡፡

ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ አቶ ልደቱ ማለት ያማራ ሕዝብ ወያኔንና ኦነግን ዐመድ ለማድረግ በትግሉ በሚያቅጣጥለው እሳት ላይ ውሃ እየጨመረ፣ አውቆም ሆነ ባለማውቅ ወያኔንና ኦነግን የሚያግዝ፣ በሐሳቡ ባይሆንም በምግባሩ ፀራማራ የሆነ ግለሰብ ነው፡፡  ስለዚህም ያማራ ሕዝብ ሕልውናውን መታደግ የሚችለው ላቶ ልደቱ ኢተግባራዊ እንቶ ፍንቶ ጆሮውን ባለመስጠት፣ እንዲሁም አቶ ልደቱ አውቆ የተኛውን ጭራቅ አሕመድን ለመቀስቀስ የሚጽፋቸውን ግልጽ ድብዳቤወች ንቆ በመተው፣ ወያኔንና ኦነግን \በሚገባቸውና\ /በሚገባቸው/ ቋንቋ እያናገረ በተግባር ሲታገላቸው ብቻ ነው፡፡

ላማራ ስለሆነም ለጦቢያ ሕልውና እንታገላለን የሚሉ ሚዲያወች ደግሞ፣ ባሁኑ ነባራዊ ሁኔታ ጦቢያን ለማዳን ያንበሳውን ድርሻ መጫወት የሚችለውና ያለበት ያማራ ሕዝብ መሆኑን መረዳት አለባቸው፡፡  በዚህ መረዳታቸው መሠረት ደግሞ ሙሉ ትኩረታቸውን ያማራ ሕዝብ በሚያደርጋቸውና ሊያደርጋቸው በሚገባ ተግባራዊ የትግል ፈርጆች ላይ ብቻ ማዋል አለባቸው፡፡  ስለዚህም አቶ ልደቱን በየጊዜው እየጋበዙ ያማራን ሕዝብ ከውጤታማ ትግሉ እንዲያናጥብ መድረክ መስጠት፣ የትግላቸውን ዓላማ በፅኑ የሚፃረር መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]


 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop