February 24, 2023
16 mins read

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ወቅታዊ የኢትዮጵያን ሁኔታ አስመልክቶ ላወጣው መግለጫ የተሰጠ ድጋፍ 

የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. (February 23, 2023)

የአማራ ክልል መንግሥት በየካቲት 13 2015 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ያለችበትን የህልውና አደጋ አመላክቶ አደጋው የመነጨውም የታሪክ እስረኛ በሆነ በሐሰት ትርክት የሰከረና ህዝብን ከህዝብ እያጋጨ የግልና የቡድን ጥቅምና ስልጣን ይዞ ለመቆየት ከሚጥር ኃይል መሆኑን በማያሻማ መልኩ አስቀምጧል። ይህ የትኛውንም ህዝብ የማይወክል ቡድን ኢትዮጵያን  እንደ አገር ህዝቡንም እንደ ዜጋ ከፍተኛ አደጋ ላይ እንደጣለ መግለጫው አመላክቷል። ይህ ቡድን አገርንና ህዝብን ለህልውና አደጋ ሲዳርግ ዝም ተብሎ መታየት እንደሌለበትና ይልቁንስ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ሊታገሉትና ለለውጥ በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አድርጓል።

እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተዘረዘርን የሲቪክ ድርጅቶች የአማራ ክልላዊ መንግሥት ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ወቅቱን የዋጀና ሁሉንም  ኢትዮጵያዊ በጋራ ለለውጥና ለተባበረ ትግል ስለሚጠራ አዎንታዊ ድጋፍ እንሰጠዋለን። ሌሎች የክልል መንግስታትም ተመሳሳይ መግለጫ እንደሚሰጡም እንጠብቃለን።  በእውነትም በአሁኑ ውቅት ኢትዮጵያ እንደ አገር ለመቀጠል እጅግ ፈታኝ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ህዝቡም በማንነቱ እየተለየ በተለይ አማራው የሚጨፈጨፍበት በገፍ የሚፈናቀልበት እንደዚሁም ለበርካታ አመታት ጥሮ ግሮ የሰራውን ቤት ህግን በማያውቁ ጊዜው የእኛ ነው በሚሉ አምባገነኖች በገፍ እየፈረሰበት በአስር ሺህ የሚቆጠር የከተማ ህዝብ ተፈናቃይ እየሆነ ይገኛል።  አገሬ ነው ብሎ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተዘዋዉሮ ለመስራት፣ ለመማር እንዲሁም ህክምና ለማግኘት የማይችልበት ደረጃ ላይ ነው። ለሁለት አመት የተካሄደው የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ስምምነት ተደመደመ በተባለ ማግስት ሆን ብለው ከመጥፋት የታደጉት ህወሓት ኢትዮጵያን በተለይም አማራውን ለአራተኛ ጊዜ ጦርነት ሊከፍትበት ጫፍ ላይ ደርሷል።

ባለ ጊዜ ነኝ የሚለው የኦሮሞ ብልፅግና አመራር ግዛት ለማስፋፋት አጎራባች ክልሎች ላይ ጦርነት ከፍቷል።  በተለይም አማራው በወለጋ ከሚደርስበት የዘር ማጥፋት እና ጭፍጨፋ  በተጨማሪ  በሰሜን ሸዋና በደራ እየደረሰበት ያለው ተደጋጋሚ ወረራ የዚህ ስግብግብ ቡድን የመስፋፋት ስትራቴጂ እንዱ አካል ነው። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ በጣም ከባድ የሆነ የህልውና አደጋ ላይ ናት። ከዚህ የህልውና አደጋ ለመዳንና ሰላምን አስፍኖ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደ ዜጋ እኩልነትና ፍትህ ሰፍኖ እንዲኖርና ልማትንና እድገትን ለመፋጠን ሁሉም በተጠናከረ ህብረት ይህን  የጨነገፈ ለውጥ ተሻግሮ ለአዲስና እውነተኛ ለውጥ መታገል የግድ ይላል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሁን ያወጣው መግለጫ ተግባራዊ እንዲሆንና  ለትግል የጠራው ህዝብም አመኔታ አድሮበት ለአፋጣኝ አገር አድን ትግል እንዲነሳሳ በአስቸኳይ ከዚህ በታች የሚከተሉትን ጥያቄዎች  እንዲተገብሩ እንጠይቃለን፦

ለአገርመከታ የሆነውና በተግባርም ያስመሰከረው ፋኖ ለአገር ህልውና የከፈለውን  መስዋዕትነት በማሰብ በህግ  ማስከበር ሽፋን የታሰሩበት ወደ 20 ሺ  የሚጠጉ አርበኞች፣ አርበኛ  ዘመነ ካሴን ጨምሮ የልዩ  ኃይልና የሚሊሺያ አባላት በአስቸኳይ ተፈትተው የትግሉ አካል እንዲሆኑ እንዲሁም ከእስር ለማምለጥ በዱር በገደል የሚገኙት ፋኖወች ዋስትና አግኝተው እንዲመለሱ እንዲደርግ፣

አማራውክሌሎች ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ለፍቶ በመሰረታት የኢትዮጵያ መዲና ወደ  ሆነችው  አዲስ አበባ እንዳይገባ በእብሪተኞች ተከልክሎ ማየት እጅግ የሚያም ነገር ነው። ለመሆኑ ኢትዮጵያ እንደ አገር አለች ወይ ብሎ ለመጠየቅ ያስደፍራል። ይህንን ጉዳይ ሳይውል ሳያድር ከፌደራል መንግሥት ጋር ተነጋግሮ የማያዳግም መፍትሄ እንዲሰጥ፣

በቅርቡየኦሮሚያ ክልል መንግሥትና የአዲስ አበባ መስተዳደር የወሰን ማካላል ስምምነት ደረሱ  የሚለውን መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ  አካል ከነበሩት ስድስት ትናንሽ ከተሞች ሸገር የሚል በከንቲባ የሚመራ ህገ  ወጥ ከተማ በመመስረት ማንነትን መሰረት ያደረገ የቤት ማፍረስና በተለይ አማራው ላይ ያነጣጠረ እንዲሁም የጉራጌ ጋሞ ወላይታ በሺህ የሚቆጠሩ ቤቶችን ጨለማን ተገን  በማድረግ በላያቸው ላይ ያለምንም ሃይ ባይ እያፈረሰ ይገኛል። እነዚህ ዜጎች ለአስርና ሃያ አመታት የኖሩበት ቤት ሲሆን ማፍረሱ ህጋዊ ካርታ ያላቸውን ሁሉ እንደሚያካትት ይነገራል። የሚገርመው የኦሮሞ  ተወላጅ ቤቶች ህጋዊ ባልሆነ ሁኔታ ተሰርቶም ቢሆንም እንደማይፈርስባቸው ተረጋግጧል።  ይህ መቸም ህግ ማስከበር ሳይሆን ከወለጋ አማራውን ለማፅዳት እንደሚደረገው ጭፍጨፋ እዚህ አዲስ አበባ ደግሞ ቤቱን በማፍረስና በማፈናቀል የማፅዳት ስትራቴጂ ነው።  ይህ ፍፁም ኢሰብዓዊ የሆነ እብደት በአስቸኳይ እንዲቆም የድርሻችሁን እንድትወጡ፣

ባለፉትአምስት አመታት ጫካ ከገባው ሸኔ መባል በሚታወቀው የኦነግ ሰራዊት በክልሉ  መንግሥት ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ እገዛ  በአማራው ላይ መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ እንደደረሰ  የአደባባይ ሚስጢር ነው።  በቅርቡ ደግሞ የተፈናቀሉትን ከኦሮሚያ ለቀው ወደ አማራ ክልል  እንዲሰደዱ እያደረገ ይገኛል።   አሁን ከወለጋ ወደ አማራ ክልል እንዲሰደዱ ለተገደዱት ተፈናቃዮች የሚሆን በጀት የኦሮሚያ ክልል እንዲሁም የፌደራል መንግስት ተፈናቃዮችን የማገዝ ግዴታቸውን እንዲያከብሩ፣

የፌደራልመንግሥት ህገ መንግሥቱን በመተላለፍ በኃይማኖቶች ውስጥ የፓለቱካ ጣልቃ ገብነት በመፈፀም የእምነት ቤቶችንም ሆነ ምዕመኑን እያመሰ ይገኛል። ከጥቂት ወራት በፊት የመጅሊሱን ህጋዊ አመራሮች በማውረድ ከህግ አግባብ እና ከአብዛኛው የእስልምና ተከታዮች ፍላጎት  ውጭ በራሱ ብሄረሰብ በሚወክሉ ግለሰቦች በማስያዙ ጠንካራ ተቃውሞ  እያስተናገደ ይገኛል። በእብዛኛው ኢትዮጵያውያን ዘንድ እውነትን ሰላምንና ፍትህን በማራመድ ተወዳጅ የሆኑትን ሃጂ ሙፍቲ ኡመርንም ከስልጣናቸው ያወረዳቸው በዚህ መልኩ ነበር። በቅርቡ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመከፋፈልና ለመቆጣጠር ያደረገው ዘመቻ ለብዙ ምዕመናንና ካህናት መገደል፣ በመቶወች ለሚቆጠሩ መቁሰልና መታሰር፣ አብያተ ክርስቲያናት መሰበር ምክንያት ሆኗል። ዞሮ ደግሞ አስታራቂ በመምሰል ጉዳዩ በትክክል መልስ እንዳያገኝ እንቅፋት ሆኖ ይገኛል።  በዚህ ሰበብ የታሰሩት በሙሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንዲሁም ቅዱስ ሲኖዶሱ ለነነዌ ፆም ጊዜ ጥቁር በመልበስ በማዘን ፀሎተ ምህላ እንዲያደርስ ምዕመኑን ባዘዘው መሰረት ይህን የፈፀሙ ምዕመናን ለምን ጥቁር ለበሳችሁ ተብለው ከስራ የታገዱ ስላሉ ይህ ፍፁም ህገ ወጥ ድርጊት በፍጥነት እንዲታረም፣ መንግሥትም በህዝቡ በግልፅ እንደተጠየቀው አሁንም እጁን ከኃይማኖት ላይ ማንሳት አለበት።

በህወሓትከህግ አሰራር ውጭ በጉልበት ወደ ትግራይ ተከልለው የነበሩት ወልቃይትና ራያ ህዝቡ ልዩ ኃይሉ ፋኖው ሚሊሻውና መከላከያው በከፈለው መስዋዕትነት ወደ ማንንታቸው  ተመልሰዋል። ነገር ግን ህጋዊ እውቅና እና የበጀት ምደባ ከሁለት አመት በላይ ስላላገኙ ጊዜ ሳይወሰድ ወደ አማራ ክልል መመለሳቸው ህጋዊ እውቅና እንዲሰጠውና  በጀት እንዲያገኙ ለማድረግ ጠንካራና ለህዝብ ግልፅ የሆነ ጥያቄ ለፌደራል መንግሥት እንድታቀርቡ እንጠይቃለን። በሪፍረንደም ይፈታል የሚለው ፈፅሞ ተቀባይነት  የሌለው በመሆኑ የነበረው ጦርነት በቅጡ ሳይጠናቀቅ ወደ ሌላ የከፋ ጦርነት እንዳይገባ የፌደራል መንግሥቱን እንድታስጠነቅቁ እናሳስባለን።

ከስምንትጊዜ በላይ ተደጋጋሚ ጥቃት የደረሰባት አጣየ በጠቅላላው በሰሜን ሸዋ ላይ  እየተፈፀመ ያለው ወረራ  ሚስጢሩ በደንብ ግልጥልጥ ብሎ እየወጣ ነው። በተለይም በአማራ ክልል ውስጥ የኦሮሞ  ብሄረሰብ ዞን ለወረራው ስልጠና መውሰጃ ዝግጅት ማድረጊያና የሎጂስትክ ማዕከል መሆኑ በግልፅ ታውቋል። የአማራ ክልል መንግሥት ይህንን ልዩ ዞን በጥብቅ በመፈተሽ ተገቢውን መፍትሄ እንዲሰጥ፣ ለተወሰነ ጊዜ በክልሉ በቀጥታ እንዲተዳደር እንዲደረግ፣ ይህ የተፈለገውን መፍትሄ የማያስገኝ ከሆነ ይህንን ልዩ ዞን እስከ ማፍረስ የደረሰ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን።

ኢትዮጵያእንደ አገር የተጋረጠባትን የህልውና አደጋ በአዎንታዊነት ለመፍታት የአብዛኞች  ክልሎች  መንግሥታት ትብብር እንዲሁም  የድርጅቶችና የሁሉም ዜጋ ርብርብ በእጅጉ አስፈላጊ በመሆኑ የአማራ ክልል  መንግሥት የአስተባባሪ ሚናን በመውሰድ ተጨማሪ የትብብር ጥሪ ለክልሎችና ለተለያዩ አደረጃጀቶች እንዲያስተላልፍ እናሳስባለን። እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት የአማራ ክልል መንግሥት ይህን የመሰለ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ መግለጫ ከሰጠ በኋላ ወደ ፊት ለተጠናከረ እርምጃወች እንደመስራት ወደ ኋላ ለመመለስ ቢሞክር  የክልሉ አመራር በራሱ  ላይ የፓለቲካ ሞት እንደፈረደ እንደሚቆጠርና በአማራው የህልውና ትግል  ላይ ትልቅ ጠባሳ እንደሚጥል እንዲገነዘብ እናሳስባለን።

እኛ ይህንን መግለጫ የፈረምን ድርጅቶች ኢትዮጵያን  ከህልውና አደጋ ለመታደግና ዜጎች በዕኩልነት  የሚስተናገዱባት የህግ የበላይነትና ፍትህ  የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ለማምጣት  በሚደረገው ትግል  ሁሉ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።  ሌሎች መሰል አደረጃጀቶችም ይህንኑ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቹዋ  መስዋዕትነት ታፍራና ተከብራ ትኖራለች።

 

ፊራሚ ተቋሞች፤

  1. Adwa Great African Victory Association (AGAVA)
  2. All Shewa Ethiopian People Multipurpose International Association
  3. Amhara Dimtse Serechit
  4. Amhara Well-being and Development Association
  5. Communities of Ethiopians in Finland
  6. Concerned Amharas in the Diaspora
  7. Ethio-Canadian Human Rights Association
  8. Ethiopian Civic Development Council (ECDC)
  9. Freedom and Justice for Telemt Amhara
  10. Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause
  11. Global Amhara Coalition
  12. Gonder Hibret for Ethiopian Unity
  13. Major Lemma Woldetsadik Memorial Foundation
  14. Network of Ethiopian Scholars (NES)
  15. Radio Yenesew Ethiopia
  16. Selassie Stand Up, Inc.
  17. The Amhara Association in Queensland, Australia
  18. The Ethiopian Broadcast Group
  19. Vision Ethiopia
  20. Welkait, Tegede, Telemt, Setit Humera Global Amhara Unity Association
  21. Worldwide Ethiopian Civic Associations Network (WE-CAN)

 

http://amharic-zehabesha.com/archives/180004

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop