ኢትዮጵያ የፖለቲካ ወልቅ ውስጥ ናት … ሲና ዘ ሙሴ

ከመስከረም ወር 2015 ዓ/ም  ጀምሮ እንኳ በኢትዮጵያ  የተከሰቱ ፖለቲካ ሠራሽ እኩይ ድርጊቶችን እና በኦሮሚያ በተባለ ዘራዊ ክልል ( ያው ሁሉም የማይረቡና ሰውነትን በመካድ የዜጎችን ህልውና ለማሳጣት በወያኔ ዘ መለሥ እና በቅኝ ገዢዎች ምሥጢራዊ ዕቅድ የተጠፈጠፉ ከዓለም ጭራ በሆነ እጅግ ኋላ ቀር በሆነ የብረት ዘመን ሰዎች የድኩማን አስተሳሰብ የሚመሩ ክልሎች ናቸው ። ይህንንም ለመረዳት የኩንታኩንቲን ፊልም ተመልከት ። እንዴት  ነጮች ጥቁሮችን እንደሚንቁ እና ጥቁር የሚያስብ ጭንቅላት እንደሌለው በፊልሙ ውስጥ በአያሌ ትዕይንት  ሊያስረዱን እንደሞከሩ ትገነዘባለህ ። ደግሞም ጃኪ ቻን ከጥቁር ጋር በሰራበትም በራሽ ሀወር ፊልም ፣ እንደነጭ ጥቁሩ አክተር እንደማያስብ ለመግለፅ ብዙ ርቀት መሄዳቸውን አስተውል ። ) እየተፈፀመ ያለውን የሽፍትነትና የውንብደና ተግባር  ፣ በቅንፉ ከተገለፀው ጋር ደምረህ ፣  እነዚህን የታሪክ ሃቆች ፣ ከዛሬው የልጆች ጫወታ ከሚመስለው የአገራችን እጅ እግር ከሌለው  ፣  ፖለቲካ   አኳያ በቅጡ ስትመረምረው  ደግሞ አገራችን ምን ያህል የፖለቲካ ወልቅ ውስጥ እንደሰጠመች   ፍንተው ብሎ ይታይሐል ።

ነሐሴ 18/12/14 ዓ/ም ወያኔ ዳግም ቆቦን ወረረ ። መሰከረም 1/01/15 ዓ/ም የተኩስ አቁም ሥምምነት አደረገ ። ከወር በኋላ ፣ በ07/02/2015 ዓ/ም  ለደርድር ቁርጠኛ መሆኑንን አሳወቀ ። በጥቅምት 15/02/2015 ዓ/ም  በደቡብ አፍሪካ በፕሪቶሪያ ከተማ ለድርድር ተቀመጠ    ። …

እናም ፣  የቀደመው ወያኔ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር  በሰጥቶ መቀበል እርቅ አወረደ ። የህወሓት አመራሮች ምን ተቀብለው ምን እንደሰጡ ፤ መንግስት ምን ወስዶ ምን እንደሰጠ ግን ለማወቅ አልተቻለም ። በህቡ ምን እንደተስማሙ አይታወቅም ።የምናውቀው   የፖለቲካ  ወልቅ “ሀ” ብሎ እንደ ጀመረ ነው ።

በፖለቲካ ወልቁ የተነሳ ወያኔ / ህወሃት  ደግም ነፍስ ዘራች ። “ ትንሣኤ ዘ_ ወያኔ “ በፕሪቶሪያ ታወጀ ። ለእናት አገር ሲሉ የተሰው ጓዶች  መሰዋትነታቸው ከንቱ ሆነ ። ነፍሰ ገዳዮችን ፣ እጅግ ጨካኞችን ፣ በሃሺሽ የሰከሩ  አንገት ቀይ ግብረ ኃይል ያላቸውን እነ ደብረፂዮንን ማወደሰ ተጀመረ ።

እንሆ ዛሬ ፣በቀደመው  የጭቆና ታጋይ  በህወሓት ሥም  ፣ ምድረ ሌባ ሁሉ   እየነገደ    ” የትግራይ ተወላጅ  ሰው የፈጣሪ የእጅ ሥራ ሳይሆን የእኔ እጅ ሥራ ነው ። ” በማለቱ ፣ የቤተክርስቲያን መሪዎች ፣ አንዳንድ አገልጋዮችና መሄጃ ቢስ የሆኑ ምእመናንን ሁሉ ፈሩ ። የወያኔ / ህውሓት ነፍሰ በላነቱን አይተው ተንቀጠቀጡ ።   እናም  “ እንደ ፈቃድህ ሁለ ነገራችን ይሙላ ። ፈቃድህ ይፈፀም ። “  በማለት ፀጥ ፣ ለጥ ብለው የታዘዙትን እየፈፀሙ ሙሉ ለሙሉ ሰብእናቸውን ሸጠው መኖር ጀመሩ ።

ይሄ እንዲህ የተፈራው ና ሰው ስብእናውን የትላንትእንዲሸጥ ያስገደደው  ” ህወሃት ነኝ ፤ ” ባዩ  ይቅር የማይባል ሀጥያትን ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ደጋግሞ  በመሥራት ይታወቃል ።  ትላንት ኤርትራን  ከእናት አገሯ ገምሶ በወርቅ ሰሐን ለሻቢያ መስጠቱ ግን ከሐጢያቱ ሁሉ የከፋ እርኩስ ድርጊቱ ነው   ። ከዚህ ሐጢያቱ ተፀፅቶ አርፎ አልተቀመጠም ። ሥልጣንን ፣ ዳግም በትግራይ ልጆች ደም አገኛለሁ በማለት ፣ አያሌ ሀብት ካፈራበትና ካከማቸበት ከተማ ፣ ከጠ/ሚ እና ከምጠ/ሚ ጋር ባለመግባቱ መቀሌ መሸገ ። በህቡ ለጦርነቱ ሲዘጋጅ ከረመና አቶ ሰሴኮቱሬ እንዳለው መብረቃዊ ጥቃት በአገር መከላከያ ላይ ከፈተ ። እጅግ አፀያፊና ልብ ሰባሪ ድርጊት በኢትዮጵያውያን እና በኢትዮጵያ ላይ ፈፀመ ። በዚህ ሰበብም እስከ ጥቅምት 15 /02/2015 ዓ/ም ድረሰ አያሌ ንብረት ወደመ ደ ክቡሩ የኢትዮጵያዊያን ህይወት ተቀጠፈ ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአባይ ወንዝ ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ - ኪዳኔ ዓለማየሁ

ህውሃት / ወያኔ  የትግራይ አስተዋየሸ እና ኃይማኖተኛ   እናት ያልፈጠረችው ነፍሰ በላ ፣ አረመኔ ፣ ደቢሎሰ የማይወዳደረው እንደሆነ በተግባር ያሳየ ነው ። ከ1000000 በላይ ኢትዮጵያዊያን   ሙት ና ፣ቁስለኛ የሆኑበትን የእርስ በእርስ ጦርነት የጀመረው ይኸው የእነ ደብረፂዮንና የእነ ታደሠ ወረደ   ጥቂት ቡድን ነው ።  በታዋቂው ህውሓት  በተሰኘ ሥም ግን እየተሞካሸ እልፍ አእላፎችን ፣ ከበሮ እያስደለቀ ለሞት ዳርጓል ።

ይኽ በሥም የቸሞካሸው ቡድን የሚመራው በውሥጥም በውጪም ያለሆድ በሥተቀር  ህሊና በሌላቸው ግለሰቦች ነው ። የሚታገዘውም ከሰው ይልቅ ለገንዘብ በሚንሰፈሰፉ ቱጃሮች ነው ። በፕሮፖጋንዳውም የሚረዷቸው ህሊና የሌላቸው በልተው ብቻ ለመሞት በወሰኑ ጅቦች ነው ።

የፈለገውን ጊዝ እና ዘመን ኑር ፣ የቱንም ያህል እንደ ጅብ ብላ ፣ መሞትህ ግን እርግጥ ነው  ።  አብይ፣ ሽመልስ ደብረፂዮን ጌታቸው፣ ታደሰ ወዘተ እንደማንኛውም ፍጡር  ነገ ይሞታሉ ። ይኽ እርግጥ ነው ። ዛሬ ለነጩ ዓለም  ልጆች ሲሉ ዜጋን በዘርና በቋንቋ እየከፋፈሉ ፤ ሰዉ አብሮ በመኖር የተነሳ የማይለያየውን ፣ ሰውን በቋንቋ በማስፈር  ብቻ   ሊቀይሩት የማይችሉትን ዲሞግራፊ ለመቀየር ፣ እዚህ ሸገር ከተማ እዛ የወልቃይትና የራያን  ፓለቲካዊ ከበሮ ይመታሉ ።   ሰው ዕቃ ይመሥላቸዋል ። ወይም የቤት እንሰሳ ። ግን አይደለም ። አንድ ቀን ፣ የህዝብ ብሶት ሲገነፍል ፤ በቃኝ ሲል  ፤ ነፍሳቸው ሳትወጣ በአደባባይ ተሰቃይተው ሊሞቱ ይችላሉ …ለማናችንም ሞት አትቀርም ። “ አዳዲሶቹ  ባንዶች “ የሚዋረዱበት ቀን ይመጣል ።

ለመሆኑ ፤ በንዳ ፣  ከሃዲና የእናት ጡት ነካሽ ማን ነበር  ?  ”  ሻቢያ ? አዎ ፤ ዛሬ   ህውሓት   ፣ ትላንት ደግሞ  ሻቢያ ነበሩ ።

ሻቢያ  ” እኔ  የምታገለው ፣ ኦሮሞን ለሥልጣን ለማብቃት ፤ አማራን ነፃ ለማውጣት ፤  ትግራይን ለመቅጣት  ነው ። ”  ብሎ ነበር ፤ በ1991 ዓ/ም ። ከባድሜ ጦርነት በኋላ ። እናሳ አልተሳካለትም ?   ያቻ ባለግርማ ሞገሷ ለአፍሪካዊያን የነፃነት ተምሳሌት የሆነች አገር ዛሬ በቀደመ ክብሮ  አለች እንዴ ? ። ክብሯን በትግራይ ጭቁን ህዝብ ሥም ምድረ ባንዳ አላሳጣትም ወይ ? አልተዋረድንም ወይ ?  እንዴት በዚህ በሠለጠነ ክ/ዘ እርስ ፣ በእርሳችን እንተራረድ ?

በነገራችን ላይ  ይህ ፀሐፊ የዘርና የነገድ ፣ የባንዳ ፖለቲካን ነፍሱ እጅግ ትጠየፋለች ። ይኽ ኢትዮጵያን ለመበዝበዝ በመሰሪዎቹ ቱጃር ነጮች የተወጠነ የአገዛዝ ሥልት ነው ። ሥልቱ  እውነት መሆኑንን የምትረዱት መንግሥታችን ባልሰለጠነ ፖለታካ ፣ ከእነሱ ርዕዮት ባፈነገጠ የህሊና ቢስ አስተሳሰብ ፣ እና ፍፁም ጅልነት    አገርን ያለርዕዮት ሲያስተዳድርና በሃሺሽ፣በሥጋ እና በአልኳል የናወዙ ግለሰቦች ፤ ከፍተኛ የመንግሥት እና የክልል እንዲሁም የህግ ባለወንበር ሆነው ፤ ዜጎች በየቀኑ እንደ ቅጠል ሲረግፉ  እያዩ ፣ ጭራሽ መከፋፈሉ እንዲጦዝ ማድረጋቸውን ስታስተውሉ ነው ። እንጂ እንዴ በአንድ አረፍተነገር  የእኛን የሰለጠነ  ርዕዮት በማንበር ዜጎችን በህግ፣በሥርዓት፣በዴሞክራሲ አሥተዳድሩ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ይሰጡ ነበር ። “ምዕራቡ  ፣ምሥራቁ “  ፤  እንዲሁም”  አሜሪካ ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንድ ሀገር ከብዙ አመታት በፊት እቆመበት ቦታ ላይ አሁንም እንዴት ሊቆም ይችላል?

እርግጥ ነው ፤ ኢትዮጵያ የኩሩ ህዝብች አገር ነች ። ኢትዮጵያ ባርነትን የሚጠየፉ እልፍ አእላፍ ጀግኖች ትላንት ነበሮት ።  ዛሬም የጀግኖች ጀግና የሆኑ ፤ በሰውነታችው እንጂ ፣ በዜግነታቸው እንጂ በነገዳቸው ወይም በዘራቸው የማይመፃደቁ ፣ ከፍ ሲልም የማይጃጃሉ ፣ ከመሞታቸው በፊት ፣ ለአገራቸው ፣ ለቀጣዩ ትውልድ ታላቅነትን ለማጎናፀፍ የሚታትሩ  እንቁ ልጆች አሏት ። ኢትዮጵያ ፣  ሚሊዮኖች   ለክብራቸው ሲሉ በጠኔ ቢያዙ እንኳን ለሚንቃቸው ሸብረክ የማይሉባት  ፤ በፀጋ ሞትን የሚያስተናግዱ የእምነት ጠንካሪያቸው እጅግ ፣ እጅግ የሚያስደንቅ  ህዝቦች የሞሉባት አገር ናት ።

ኢትዮጵያ ሰው መሆናቸውን በተገቢው ልክ የተረዱ ፤ ቆዳው ለነጣ ሁሉ ፣ ጭራቸውን የማይቆሉ ፣ ከሆዳቸው ይልቅ ክብራቸውን የሚያስቀድሙ ህዝቦች ያሉባት አገር ነች ።

ኢትዮጵያ ለፈጣሪ ( እግዛብሔር / አላህ ) እጅግ የቀረቡ ብቻ ሳይሆን ፣ ዕለት ፣ በዕለት የሚነጋገሩ ፃድቃኖች ያሉባት አገር ነች ።

ኢትዮጵያ በገፀ ምድሯም ውብ ናት ። እጅግ ማራኪ ናት ።  አለም ከተፈጠረ ጀምሮ ያልተዳሰሰ መሬት ያላት ናት ።

ኢትዮጵያ ምድሯም ዜጋዋም ውብ ና ድንቅ ነው ።  ይሁን እንጂ መሪዎቿ ፈተና የበዛባቸውና የኃያላን ቁጣ ፣ ግልምጫ ና ዱላ እያየለባቸው ፣ ለዜጎች ውሳኔውን ከማቅረብ ይልቅ ዜጎቹ በማያውቁትና ባልተረዱት ጉዳይ የአገሪቷን የነገ ዕጣ ፈንታ ሲወስኑ ይስተዋላሉ ።  የራሳቸው ውሳኔ ከህዝባቸው ጋር አይንና ናጫ  ሲያደርጋቸው  ደግሞ ፣ ዛሬም ለወንበራቸው በመሳሳት ብቻ ፣ በዓለም ላይ በሌለ የፖለቲካ ርዕዮት ተጠምደው ህዝባቸውን ለመከራና ለስቃይ  ሲዳርጉ እየተስተዋለ ነው ።

ኢትዮጵያ በተለይ  ዛሬና አሁን ያጋጠማትን ችግር በፅሞና በማጤን ወደቀደመው የፍቅርና የመተሳሰብ አገራዊ የነፃነት ና የክብር መንገድ ገዢው ፓርቲ እስካልተመለሰ ጊዜ ድረስ ፣ ኃያላኑ በቀደዱለት የውድቀት መንገድ ና በቁማር ጫዎታው የመጣው ይምጣ ብሎ   ከተጓዘ ፣ ለህዝብና ለአገር የሚያተርፈው ውድመትና የታሪክ ጠባሳን ነው ።

ገዢው ፓርቲ ብልፅግና ኢህአዴጋዊ ቁማር ጫዋታውን ትቶ ( ይኽ … ጥቂቶችን አበልፃጊ መላ ዜጎችን አማቃቂ እና አሳቃቂነቱ  ከአምስት አመት በፊት የተረጋገጠ ሥርዓት መሆኑ ይታወቃል ። )   በትግራይ ክልል የሚስተዋለውን ህዝቡን ብቻ ሳይሆን  ኃይማኖትን ጨፍልቆ የመግዛት መንገድ ልብ ካላለው ነገ  ሌላ “ ኒኩለራዊ ጥቃት “ ይገጥመዋል ።

ኢትዮጵያዊያን እርስ በእራሳችን ቂቤ የተቀባባን ይመስል ፤ አንዱን ” አንገት ቀይ ” ፃድቅ ። አንዱን ” አንገት ተቀይ ” ኃጢያተኛ አድርጎ መሳልና ፣ የዘር ማጥፋት የደረሰበትን ፣ ይባስ ብሎ በቁስሉ ላይ እንጨት መስደድ ፤ ፈጣሪ ወይም እግዚአብሔር አለቃው ከሆነ ክርስቲያን ሆነ ሙስሊም ፈፅሞ አይጠበቅም ።

በፈጣሪ የሚያምኑ ተራ ሰዎች እንኳ በአምሳያቸው ላይ ግፍ ይቅርና ልምጭ እንዲያርፍበት አይፈልጉም ። በእነሱ ሊደረግባቸው የማይፈልጉትን በሌሎች ሰዎች ላይ እንዲደረግ ፈፅሞ አይፈቅዱም ። እነሱም አያደርጉትም ። ይሁን እንጂ በትግራይ ያሉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ፣ የህወሓትን ዘግናኝ የቁም ሥቃይ በመፍራት በልብስና በአንደበት ብቻ በመቅረት በፈጣሪ ላይ እያላገጡ እንደሆነ ተግባራቸው ይመስክራል ። ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን ሰብከዋልና እንደ ጠፉ በጎች እንቆጥራቸዋለን ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ተዉ እነ ጅብ አስፈጂ ! -  ማላጂ

እነሱን እንደ ጠፉ በጎች ብንቆጥርም የኢትዮጵያን ፖትርያርክን እና ብፁአን አባቶችን እንደ አንድ ትልቅ የመዳናችን ተሥፋ በአክብሮት ክብር እንሰጣቸዋለን ። ከእኛ ከምእመናኑ በፊት እንደ አባትነታቸው ሊሞቱልን ከፊት ለፊታችን በመሆን ሥለ ጥንታዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን  ሲሉ መንፈሳዊ ውጊያ በማድረግ ለድል አብቀተውናልና !!

ይኽ ድላችን  ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ  በቤተክርስቲያኗ የመሸጉ ሌቦችና ወንበዴዎች ሊመነጠሩ ይገባቸዋል ።  የክርስቶስ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የጋለሞታዎች መፈንጫ መሆን የለባትም ። አብሶ ካህናቱ በተግባር ከሐጢያት የፀዱ ሊሆኑ ይገባቸዋል ። በእነሱ ሰበብ ብዙዎች መሰናከል የለባቸውም ።

ኢትዮጵያ በፖለቲካው ተምሳሌትነት ባይኖራትና ለሌሎች የአፍሪካ አገራት  መሰናከያ የዘር ና የቋንቋ ፊደራሊዝም በዓለም የሌለ የፖለቲካ መንገድን ብትከተልም ፣ ከኃይማኖት አንፃረ ተከባብረውና ተፋቅረው ለመኖር የቻሉ  ፣ ሙሥሊም ና ክርስቲያን ያሉባት አገር ናት ። በዚህ ኢትዮጵያዊያን ደስ ይለናል ።

ዛሬ ና አሁን  ደስታችንን ለመቀማት ያሰፈሰፉ 800 ሺ ህዝብ እርስ በእርሱ ተዋግቶ ማለቁ ፍፁም የማይፀፅታቸው ፣ ዛሬም ሚሊዮኖች እንዲያልቁ የጦርነት ነጋሪት የሚጎስሙ  እዛና እዚህ አሉ ።

በተለይም በትግራይ ያሉት ፀረ _ ክርስቶስ በመሆናቸው ፣ የሰው እልቂት ቅጣት ያህል አይሰማቸውም ። በማህል አገር ያሉ በሰው ቁማር የሚጫወቱትም ፣ በየቀኑ ሰውን እያስበሉ ማትረፋቸውን እና ሁሌም አሮስቶ ቀለባቸው መሆኑንን ከማረጋገጥ ውጪ በደቂቃዎች ውስጥ እነሱም ሊሞቱ እንደሚችሉ አያስተውሉም ።

በነገራችን ላይ ማንም ሰው ፣ ነገን ይቅርና በሰከንዶች ውስጥ በእርሱ ባዮሎጂ ውስጥ ሥለሚከሰተው ፤ በምድሪቱ እና በከባቢዋ ስለሚሆነው ድንገቴ  ማወቅ አይችልም ።

ኢትዮጵያን ዛሬ ከገባችበት ማጥ ( ወልቅ ) ማውጣት የሚችለው እምነታችን ብቻ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ። የሚያስተሳስረን ፣ሰውችች የተገመዱበት አንዳአይነት ገመድ ኃይማኖት  ነው ።  በኃይማንት አይን ነገድ ፣ ዘር ና ቋንቋ ሥፍራ የላቸውም ። በተለይም በክርስትና እና በእስልምና ኃይማኖት ሰዎች  በሰውነታቸውና በእምነታቸው ብቻ ነው የሚተሳሰሩት ። የሚፋቀሩት ። ቤተሰብ የሚመሰርቱት ። አንድነታቸው በኃይማኖታቸው ብቻ ነው ። ኃይማኖተኝች በህብረታቸው ሁሉ ቋንቋን እንደመስፈርት አይቆጥሩም ።  …

ወዳጄ እግዛብሔር በቋንቋ ኮታ  ካህናትን አይሾምም ። ከክርስትና ኃይማኖት  አንፃር እውነቱን ማስረዳት ቀላል ነው ። የትኛውንም ቋንቋ ይናገር ለእግዛብሔር መንግሥት መመሪያ የተገዛ እና ለአገልግሎት የተዘጋጀ ና ብቁ የሆነ ሁሉ ፤ በሰገነት ላይ ቆሞ የክርስቶስ ኢየሱስን ምድራዊ ድንቅ የአገልግልት ጊዜ፣ ሥቃይ ፣ ሞትና ትንሣኤውን በራሱ ቋንቋ ለሚሰሙት ሁሉ በመስበክ ሰዎችን ወደ  ዘላለማዊ ህይወት እንዲያመጣ አንድን ሰው ከትቢያ ያስነሳዋል ። ይህን እውነት ከነ ፖስተር ቸሬ መረዳት ትችላለህ ።

እውነትን እየሸሸን ሥጋችንን በጥጋብ እየደለለን  እስከመቼ በጠማማ መንገድ ” በወልቅ ” ውስጥ እንደምንዳክር ፈጣሪ ነው የሚያውቀው ። ይኽንን መነሻና መድረሻው የማይታወቅ  የጭለማ  ጉዞችን ያበቃ ዘንድ በብርቱ ልንፀልይ ይገባል ። በፆም ፀሎታችን መልስ ከፈጣሪያችን ከክርስቶስ ኢየሱስ መልስ እንደምናገኝ እና ከተዘፈቅንበት የፖለቲካ ማጥ  እንደምንወጣ እናምናለን ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share