ከአንዱአለም በእውቀቱ ፌስቡክ ገፅ የተወሰደ።
አንዳንድ ሰዎች ስለትላንትናው የፍ/ቤት ትእዛዝ የሚያወሩትን አወዛጋቢ ጉዳይ በተመለከተ ለብጹአን አባቶች ዛሬ ጠዋት ገለጻ አቀረብን።
‘ህገወጡ ቡድን የያዛቸውን ቦታዎች ለምን ይዞ እንዲቀጥል ተባለ?!’ የሚለውን ጠየቁን።
እስከ አሁን የእግድ ፋይል እንጂ(ያውም ክስ ሳይጀመር በእግድ ጉዳይ ብቻ በቀጥታ የተከፈተ የመጀመሪያው የፍ/ቤት ፋይልም ነው) ዋናው ክስ እንዳልተከፈተ :ከጉዳዩ ውስብስብነት አንጻር ክስ ለመክፈት ጊዜ ለማግኘት ሰው እንዳይሞት ሲባል ለፍርድ ቤት እግድ ጠይቀን በዚህ ጉዳይ ያሉ አከራካሪ ነገሮች እስኪጠናቀቁ ብቻ የተሰጠ ጊዜያዊ የእግድ ትእዛዝ መሆኑን :የቤተክርስትያን ንብረቶችን የማስመለስ ክስ በቀጣይ የምንከፍት መሆኑን ነገርናቸው ።
…ለአንዳንዶች ‘ኒውክለር ሳይንስ’ የሆነባቸው የእግድ እና የውሳኔ ልዩነት ብጹአን አባቶች ለመረዳት 30 ሰከንድ ነው የፈጀባቸው!!
ያስገኘነውን ውጤት በተመለከተ በመላው ብጹአን አባቶች አጥንት ድረስ የሚደርስ ምርቃት እና መባረክ ተችሮናል!!
ከዛ በተረፈ ቅድም እንደሰማችሁት አንዳንዶች እኔን እና አንዳንድ የህግ ኮሚቴ አባላትን በተመለከተ እላፊ ሄደው የሚናገሩት ለቤተክርስትያን ካላቸው ቀናኢነት እና መንፈሳዊ ቅናት የመነጨ መሆኑን በብጹአን አባቶች ደስስ በሚል ሁኔታ ምክር ስለተለገሰኝ ማንም እኔን በተመለከተ በሰጠው ትንታኔ ቂም ላልይዝ ነገሩን ሁሉ እርግፍ አድርጌ ትቻለሁ!!
( ትንሽ የከበደኝ ለሰማይ ለምድር የከበዱ ብጹአን አባቶች በካሜራ ፊት ቆመው እባካችሁ ከእንደዚህ አይነት ነገር ተቆጠቡ ሲሉ እና ሲማጸኑ ሳይ ነው!!)
በነገራችን ላይ ይሄን ስራ የምሰራው ከበርካታ የህግ ባለሙያዎች ጋር ነው! በእውቀት በልምድና ቤተክርስትያንን በምንወክልበት ሁሉ የፈጣሪ እርዳታ እንዳይለየን ተባርከንም ጭምር ነው!!
ስራውን ስንሰራ አሁንም ወደፊትም ከበረከት በቀር የምንቀበለው አምስት ሳንቲም የለም!!
ለኔ እስከዛሬ ከያዝኳቸው ጉዳዮች ሁሉ የምንግዜም ከባዱ እና ወሳኙ ጉዳዬ ነው!
ያው በፌስቡክ እና በዩቲዩብ ጥቆማ አልተመረጥኩምና በፌስቡክ እና በዩቲዩብ የነቀፌታ ጋጋታ የተጣለብኝን ሃላፊነት አልለቅም!!
ገና ብዙ ስራ እንሰራለን!!
አብረውኝ ባሉት ባልደረቦቼ :እና በሁሉም ጉዳይ በሚመሩን የቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች እተማመናለሁ:እጸናለሁም!!
አንድ ነገር ግን ልለምናችሁ…
እኔን ተፋቱኝ እና ዋናው ጉዳይ ላይ (እንደዚህ ሰሞኑ ሁሉ) አተኩሩ!!
መልካም ቀን!!