Nero Claudius Caesar Augustus Germanicus
ታሪክ እንደሚያትተው የግሪክ ፣ የሮማና የአቢሲኒያ/የኢትዮጵያ/ ስልጣኔ ለዓለም ያበረከተው አስተዋፅኦ የትየለሌ እንደሆነ መድበለ መዛግብት ቁልጭ አድርገው ያለማወላወል ዘግበውታል።
ከላይ በተጠቀሱት የስልጣኔ ፈርጥ ቀዳጅ ሃገራት ጥንታዊ የአገዛዝ ዘመናት አንቱ የተባሉ ነገሥታትና መሪዎች እንደነበሩ ሁሉ ጨካኞች ፣ የአዕምሮ ችግር ያለባቸው ፣ ግፈኞች፣ ለሃገርና ለህዝብ ደንታ የማይሰጣቸው ነገሥታትና መሪዎች ተፈጥረው ነበር።
በዘመናት መካከል በሸረኛነት ፣ ባለመብሰል ፣ በጭቃኔ ፣ ሃገርን በቅጡ ከማስተዳደር ይልቅ በብልጭልጭ ነገሮች ጊዜ ሲያጠፉ፣ ቅንጡ ቤተ-መንግስቶችን ፣ መናፈሻ ፣ መዝናኛ መዕከላትን በማነፅ ተጠምደው የንግሥና ዘመናቸውን ካሳለፉት ፣ ገናናነታችንን አቆለጳጵፁ ከሚሉና የዐይን እርካታ አቅላቸውን ከሚያሳጣቸውም ዓለም ካፈራቻቸው ንጉሦችና መሪዎች መካከል አንድ ኔሮ /Nero / የሚባል የሮም ንጉስ ነበር ።
ከላይ የተዘረዘረው ዓይነት የዘቀጠ ፣ የወረደ፣ ጨቅላ አስተሳሰብ ያላቸው ፣ በበታችነት ስሜት የተወጣጡሩ ጋጠ ወጥ የሮም ዓይነት ንጉሦችና መሪዎች በአሁን ሰዓት ታላቅዋን አገረ ኢትዮጵያን እየመሩ ይገኛሉ።
የኛዎቹን ስንኩል ፣ በትንሹ በትልቁ “ ከረሚላውን እደተቀማ ሕፃን” አኩራፊና አነፍራቂ ፣ እራሳቸውን በቅጡ ሳይመሩ በግርግር ለሃገር መሪነት የበቁትን መሪዎቻችንን እንደ ኔሮ /Nero/ ካሉ በዓለማችን ለንገሥና ከበቁት የሕፃን አስተሳሰብ ካላቸውና አዕምሯቸው ከታወከ መሪዎች ከነበሩት ጋር እያነፃፀርና እያመሳሰልን የጋራ የሚያደርጋቸውን ባህሪያቸውን እየመዘዝን እናብጠለጥላቸዋለን።
ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ54ኛው ምህተ ዓመት በ16 አመቱ ለንግሥና በቅቶ በ30 ዓመቱ እራሱን ያጠፋው የሮም አምስተኛ ንጉስ ኔሮ /Nero/ አሁን ኢትዮጵያን እየመሩ ካሉት የሃገርና የፈረደበት የክልል መሪ ተብየዎች ጋር የሚመሳሰል ባህሪያት እንዳላቸው አምሳያ ተግባራቸው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ።
የሮም ከተማ በጭንክ ተሞልታ ፣ ተወጥራ ፣ በፈተና ታምሳና በለውጥ ጎዳና ትሄዳለች ተብሎ ታስቦ በነበረበት ከክርስቶስ ልደት በ54ኛው ምዕተ ዓመት የነገሠው ፣ እንደ ሕፃን የሚያደርገውንና ግራ ተጋብቶ ግራ ያጋባ የነበር የንጉስ ኔሮ /Nero/ ታሪክን የእንግሊዙ የምርምር ዶሴ / The British Encyclopedia/ እንደሚከተለው ዘግቦ ለታሪክ አስቀምጦታል።
“Nero was the 5th emperor of Rome and Nero is known as one of Rome’s most infamous rulers, notorious for his cruelty and debauchery. He ascended to power in AD 54 aged just 16 and died at 30. He ruled at a time of great social and political change, overseeing momentous events such as the Great Fire of Rome and Boudica’s rebellion in Britain. He allegedly killed his mother and two of his wives, only cared about his art and had very little interest in ruling the empire”
ኔሮ /Nero/ ከአባቱ ንግሥናን የወረሰ በጣም ክፉ ፣ ረብሻ የሚወድ /Notorious /፣ በታሪክ በጥዮፍ ስራው ስሙ የሚነሳ ፣ ገብጋባ /Debauchery / ፣ እናቱንና ሁለት ሚስቶችን የገደለ ፣ በየግድግዳው የተለጠፉት አማላይ ስዕሎችና አሽብረቅራቂ ነገሮች በማየት ከመርካት በቀር ለሕዝብ ሰላምና የተሰላሰለ ህይወት ፍላጎትና ደንታ ቢስ የሆነ ንጉስ ነበር።
ይህን ከላይ የሰፈረ የንጉስ ኔሮን /Nero/ ታሪክ ከኛዎቹ መሪዎች ጋር መሳ መሳ አድርገን ስንመረምራቸው የሚያመሳስላቸው ምልክቶች ይታያሉ። የአሁኖቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ያልተረጋጉ ፣ ግብረ ገብ የሌላቸው ፣ ልመስገን ባዮች ፣ በሕዝብ ገንዘብ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ፣ ንብሮቶችና ሃብቶች “የግላችን ብቻ ናቸው” ብለው የሚያስቡ የግለኝነት ባህሪ የሚያጠቃቸው ከመሆኑ ባሻገር ጎልቶ የወጣ የአረመኔነት ፣ ጭካኔ ፣ እረብሸኛነት የሚናፍቁ እና ንቀትን የሚያበዙ በመሆኑ ይህም ባህሪያቸው ከንጉስ ኔሮ/Nero/ ጋር ያመሳስላቸዋል።
አሁን በየ ሥልጣን እርከኑ የተሰየሙ ባለሥልጣኔች ሕዝብ የሚቀመስ እጥቶ መናፈሻ ፣ ቤተመንግስት ፣ ህንፃ ወዘተ ይገነባሉ። በግል የሚታሙበት ነፍስ የማጥፋት ታሪክ ባይታየንም የሕዝብን ደህንነትና ሰላም እንደመንግስት አስከብሮ ለማኖር ደንታ ቢስነት መግለጫቸው እየሆነ በመምጣቱ ይህም ባህሪያቸው የሮማ ንጉስ ከነበረው ኔሮ /Nero/ ጋር በአንድ ረድፍ የሚያስቀምጣቸው ባህሪያቸው ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ጨቅላው ንጉስ ኔሮ ክርስቲያኖችንና ቅዱሳንን “ቅዱስ ጳውሎስንና ቅዱስ ጼጥሮስን “ሳይቀር በማሰቃየት የጭካኔውን ጥግ አሳይቷል። ከዚህ ባሻገር የተንጣለለ ቅንጡ ቤተመንግስቴን ልገነባ ነው በሚል ህሳቤ ሮም ከተማን በእሳት ረመጥ አቃጥሏታል። ይህም የጭካኔ ታሪኩ እንደሚከተለው በታሪክ መዝገብ ተሰንዷል።
Nero, one of the most notorious Roman emperors ruthlessly persecuted early Christians, including Saint Peter and Saint Paul, and even set fire to Rome itself – famously fiddling amid the flames – to make room to build himself a vast, luxurious palace.
የዚህ ታሪክ ግጥምጥሞሽ የሚያሳየው “ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” እንዲሉ የአሁኖቹ የኢትዮጵያ ሹማምንት የበቁ ክርስቲያን ጻጻሳትን ፣ መነኮሳትን ፣ ክርስቲያኖችንና ምእመናንን ከማሳደድ አልፎ ቤተክርስቲያናት በአረማውያን ሲቃጠሉ ዝም ማለትን መርጠዋል። በአዲስ አበባ ያሉ ንዋሪዎችን መኖሪያ እያፈረሱና እያፈናቀሉ ፣ ደንና መልክአ ምድርን እያቃጠሉ ለራሳቸውና በራሳቸው የተሰየመ ከተማና ቤተመንግስት በብዙ ቢሊዮን መዋለ ንዋይ አፍስሰው የግል ስሜታቸውን ብቻ ለማርካት እየተውተረተሩ ይገኛሉ። ይህ ባህሪያቸው ከላይ እንደሰፈረው ከሮሙ ጨካኙ ፣ ረብሸኛውና ለሕዝብ ደንታ ቢስ ከነበረው ንጉስ ኔሮ /Nero/ ጋር የሚያመሳስላቸው በግልፅ ገቢር እየታየ ያለ ባህሪያቸው ነው።
መቸም አንዳንድ መሪዎች ከአረመኔነታቸው ፣ ከጭካኔያቸውና ከአስመሳይነታቸው በተቃራኖ የሚሰሯቸው የማዘነጊያ እብላጭላጭ ፣ አማላይና ህዝብን የሚያምታቱበት መልካም መሰል ተግባራትን ይከውናሉ። ይህን ተመርኩዞ አረመኔው ኔሮ /Nero/ ቅንጡ ቤተመንግስቶችን ፣ በወርቅ ቅብ የተገነቡ ቤቶችንና የመዝናኛ ቦታዎችን ገንብቷል። ወታደሮቹ የሚቃወሙትን መውጫ መግቢያ እያሳጣ ቀስ በቀስ በቁጥጥሩ ፣ በእግሩ ስር እንዲወድቁና የንግሥናው አገልጋይ ያደርጋቸው ነበር። ለስነጥበብ ያለው ቀናይነት አጃይብ የሚያሰኝ ነው። ንጉስ ኔሮ /Nero/ ለጠላቶቹ ደግሞ ደግና ሩሩህ እየመሰለ ከማጥቃት ወደ ኋላ የማይል “ የእርግብና የእባብ” ባህሪያት የተላበሰ እንደነበር ታሪኩ በመፅሃፍት እንደሚከተለው ተከትቦ ይገኛል።
Nero built a palace, the Golden House, which was apparently magnificent, but it was so resented by the public and by his successors that it was almost completely dismantled. His armies put down rebellions in Britain and Judaea, he was an enthusiastic patron of the arts, and he was lenient toward his enemies.
የሚያሳዝነው ለአፍሪካና ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነት የተጉ መሪዎች ታላቅዋ ሃገረ ኢትዮጵያ እንዳላፈራች ከላይ በተዘረዘረው የቀደመ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ54ኛው ምዕተ አመት ከነገሱት ነገሥታት አስተሳሰብ የሚመጠን አስተሳሰብ ይዘው ፣ የአዕምሮ መሰራስራቸው ወደ ኋላ ተጓቶ ፣ ደንዘዝዘው፣ ደደበውና የዘገጠ ባህሪ ተላብሰው ታላቅዋን ኢትዮጵያ ለመምራት መብቃታቸው የሚያሳዝና ሲሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከነዚህ ሰው መሰል እንስሶች ነፃ ይወጣ ዘንድ አምላክን ሊማፀን የግድ ይለዋል።
በመጨረሻም እንደ በሬ ቀንበር ከሕዝብ አንገት ላይ ተጭነው ሃገረ ኢትዮጵያን እያመሱ ፣ ሕዝቡን ግራ እያጋቡና እያምታቱ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዓለም በስልጣኔ ፣ በቴክኖሎጂ ፣ በዲሞክራሲና መሰል ኩነቶች እየነጎደ ባለበት ጊዜ በቀደም ዘመን አስተሳሰብና መርህ “ ሰውን ፣ ከሰው ፣ ሰውን ከአራዊት ጋር እያታገሉ ፣ ሰው ሲሞትና ደም ሲፈስ እየተሳለቁ ፣ ወይን እየተጎነጩ ፣ አያሌ ዕቁባቶቻቸውን ከጎናቸው ሽጠውና የግል ፍላጎታቸው በመርካት ተጠምደው እየተለፋደዱ ሮምን ፣ ግሪክን ፣ ራሻንና መሰል ሃገሮችን ሲመሩ እንደ ነበሩ እንደ ኔሮ ፣ ቲቶ ስታሊን ፣ ኢትለርና መሰል ሃገራትን ይገዙ እንደነበሩት ንጉሶችና መሪዎች የሥልጣኔ ፈርጥ የሆነችውን ኢትዮጵያን ለመምራት መሞከራቸው የሚያሳዝን ሲሆን መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጋር አንድ ሆኖ በመቆም መላ ሊያበጅላቸው ፣ በቃችሁ ሊላቸው ይገባል እንላለን።
“ኦ እግዚኦ አድኅን ሕዝብከ ወባርክ ርስትከ”
“ አምላኬ ሆይ
አቤቱ ሕዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ”
ተዘራ አሰጉ
ከምድረ እንግሊዝ።
ይሄ ሰውዬ ዲያቆን ነው። እምነቱን እንጂ ብሄሩን ወክሎ አይደለም የሚያናግርህ የሱን ፀያፍ ንግግር ይዘህ ድፍን አማራን‼በዘር መነሻ አትጥላ‼ይልቁንም ይህንን ጋጠ ወጥነት ቀኖና ካደረገው እምነቱ ገለል በል።
ibnu munewor pic.twitter.com/acYuVz3vfo— ???????????????????????? ???????????????? ???????????????????????? (@Peace4Ethiopiaa) February 11, 2023