January 16, 2023
6 mins read

በሚድን በሽታ ተይዛ ግን በሽታው እየገደላት ያለች ሀገር ኢትዮጵያ – ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

powerደወል 1 ዘኢትዮጵያ

ይቅርታ፥ እርቅ፥ ምክክር፥ መግባባት። የማንለው የለም። ግን የሚደረግ ነገር የለም። ለምን? አንድ ነገር ለማድረግ ቀርቶ፥ ለመነጋገርም የማይቻልበት ደረጃ ላይ ነን። ማስረጃ ቢባል በሦስት ረድፍ ላስረዳ። አንደኛ ንግግር መጀመር አይቻልም። ሁለተኛ ንግግር ቢጀመር እንኳን መቀጠል አይቻልም። ሦስተኛ ንግግር መቀጠል እንኳን ቢቻል፥ መጨረስ አይቻልም። በዚህ ዓይነት የመፍትኤ ሀሳብ እንዳይወለድ (እንዳይሰማ) በሦስት ደረጃዎች መላን የሚያጨናግፍ ብዙ ጩኸቶች አሉ።

 

1ኛ/ ንግግር እንዳይጀመር ፈንጂ ተጠመደ

የተቀበረ ፈንጂ ስለማይታይ ሰላም ነው ብሎ በመሬት ላይ የሚራመድ ሰው ሁሉ ላይ አደጋ ያደርስበታል።  ዛሬ ላይ የፈውስ ሀሳብን ማንሳት እጅግ የሚያስቸግርበት ሁኔታ እየሆነ ነው።  የተናጋሪው ስም እንደ ታፔላ (ፈንጂ) ይሆናል።  የሰው አስተሳሰቡ በራሱ እንዳይመዘን በማድረግ፥ የተናጋሪውን አስተሳሰብ እንዲመክን ይደረጋል።  አንዱ የሚናገረው ነገር ጆሮ ለመክፈት እንዳይችል ፈንጅ እንቅፋት ነው። ገና ከመነሻው ሥር እንዳይዝ የሀሳብ ፍሰት ማጥለያ (filter) ይደነቀርበታል።  ደግሞ የተወሰኑ ኮድ ቃላቶች እንደ ፈንጂ ያገለግላሉ።  በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ተናጋሪው ሀሳቡን ሊያብራራ ይቅርና የሀሳቡን ርዕስ እንኳን ለመግለፅ እንዳይችል ያደርጋሉ። አንዳንዶቻችን ከነገሩ ጦም እደሩ ብለን በግል ሕይወታችን ላይ ብቻ እንድናተኩር ተገደናል።

 

2ኛ/ ንግግር እንዳይቀጥል ቋንቋ ተደበላለቀ

በባቢሎን ከተማ ሰዎች ሰማይ የሚደርስ ሐውልት ሊሰሩ ተነሱ።  ፈጣሪ ከዓላማው ጋር የሚሄድ ራዕይ ስላልሆነ ቋንቋቸውን ደባለቀ።  አንድ ልብ ሆነው እንዳይሰሩ፥ ቋንቋ ተደበላልቆ መግባባት እንዳይችሉ አደረጋቸው።  ከዚያ ሁሉን ትተው በዓለም ዙሪያ ተበተኑ። ይህ ታሪክ በእኛ ተደገመ፥ በፈጣሪ ሳይሆን በክፉው።

ኢትዮጵያ በአብሮነት እንድንትገነባ በጎ ፍቃደኝነት እና ቅን ልቦና በኢትዮጵያ ልጆች ላይ አለ።  ሁሉም የሀገሩ ነገር እንቅልፍ አሳጥቶት የሚታትርና የሚጥር እንደሆነ ይታወቃል።  ግን ሁሉም የሚያውቀው ብዙ ዘርቶ ትንሽ ማጨዱን፥ ብዙ እየለፋ የሚታፈስ ነገር ግን ማጣቱን ነው። ኢትዮጵያን ለማዳን ላይ ታች በማለት በተስፋ ብንጠመድም፥ ትርፍ ሳይሆን ከዕለት ዕለት ኪሳራ ሆነብን።  በዚህ ውስጥ አንዱ ንግግር መጀመር ከቻለ፥ የሚቀጥለው ፈተናው ደግሞ ንግግሩን መቀጠል ነው።  ምክንያቱም ቋንቋ ስለተደበላለቀ ንግግሩን ያቆመዋል።  አማርኛ እየተናገርን የምንለው ግን የተለያየ ሲሆን ቋንቋችን ይደበላለቃል።  አፋን ኦሮሞ እየተናገርን የምንለው ግን የተለያየ ሲሆን ቋንቋችን ይደበላለቃል። ሌላውም እንደዚሁ።  ቃላቶች ትርጉማቸውን ከደበላለቁብን፥ እንደ ባቢሎን ዘመን አልሆንምን?

3ኛ/ ንግግር እንዳይጨረስ በሰበር ዜና ፋታ ጠፋ

የቁም ነገር ንግግርና ሚዛን የሚደፋ ሀሳብ የሚሰማ ጆሮ ብቻ ሳይሆን የሚያስተውል አዕምሮ ይፈልጋል።  ለማስተዋል ሰከን ብሎ ማዳመጥና አውጥቶ አውርዶ ውሳኔ ለመወሰን ጊዜ መውሰድን ይጠይቃል።  ታዲይ ሰብር ዜና ለዚህ ፋታ አይሰጥም።  ከአንዱ ሰበር ዜና ወደ ሌላኛው እየተቀባበለ ለማሰብ ፋታ እንዳይኖረን ያደርጋል።  እንደ ጉም በየጊዜው እየተነነ በማይጨበጥ ነገር እያደናገረን ጊዜያችንን ብቻ ሳይሆን እኛን ራሳችንን እየመዘመዘ ይበላናል።  ሁልጊዜ እሳት ላይ እንደተጣድን ነው።  እፎይታ የለም፥ ለማሰብ ፋታ የለም።  ሰብር ዜና እኛን የሚሰባብር ዜና ቢባል ጥሩ ነበር።

 

የነገሩ ፍፃሜ ምንድነው?

የሁሉንም ጆሮ ቀልብ ይዞ አንድን አሳብ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ማድረስ ካልተቻለ፥ እየተነጋገርን አይደለም ማለት ነው።  እስካልተነጋገርን ድረስ ደግሞ መግባባት ፈፅሞ አንችልም ማለት ነው። ካልተግባባን ደግሞ የሚድን በሽታችንን ማከም ስለማንችል፥ በሽታችን የምንኖር እስኪመስለን እያታለለን፥ ወደ ሞት ይወስደናል ማለት ነው። ታዲያ ምን ይሻላል? በተከታታይ እንመለከታለን፥ በደወል 2 ዘኢትዮጵያ እንገናኝ።

ፀሐፊውን ለማግኘት: www.myETHIOPIA.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop